SU|ኤስዩ
رفتن به کانال در Telegram
የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር [Scripture Union Ethiopia] #ኤስ.ዩ፣ ከ1957 ጀምሮ የኃይስኩል ተማሪዎችን እያገለገለ ይገኛል። #ራዕያችን "ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት" ነው በዚህ ቻናል:— በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ነክ መረጃዎች ይተላለፍበታል።
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
674
مشترکین
+324 ساعت
+57 روز
+330 روز
آرشیو پست ها
674
+7
የትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ጥናት
----- -------- ----- -----
በቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) #የደቡብ_ምስራቅ ክልላዊ ቢሮ (ሐዋሳ) የተዘጋጀው የሁለት ቀን ዎርክሾፕ ተጠናቋል።
ህዳር 6 እና 7 በሐዋሳ በተካሄደው #የትንቢተ_ዮናስ_መጽሐፍ ዎርክሾፕ በሐዋሳና አካባቢው የሚገኙ የኤስ.ዩ አሶሼት ስታፎች ተሣታፊ ሆነዋል።
የዮናስ መጽሐፍ ዎርክሾፕ፣ የተማሪ አገልጋዮች፣ ሕይወት ለዋጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ከማጥናት ባሻገር ታማኝ የቃሉ አገልጋዮች የመሆን ክህሎታቸውን ያሣድጋል። በቃሉ ላይ የተመሰረተ በራስ መተማመንናቸው እንዲጨምርም ያደርጋል።
ሰልጣኞቹ እንደመሰከሩት፣ የትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ዎርክሾፕ የእግዚአብሔር የተልዕኮ ልብ የተገለጠበት ሆኖ አግኝተውታል። ከጥናቱ በኋላ፣ ስለ መጽሐፍ አንኳር መልዕክት የነበራቸው የቀደመ አስተሳሰብ በእጅጉ እንደተለወጠም ተናግረዋል።
በዎርክሾፑ ተሳታፊ የነበሩ አሶሼትስ፣ ለተማሪ ሕብረቶች እና ለአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው በረከት እንደሚሆኑ እምነታችን ነው።
የዎርድ ፓርትነርስ ስልጠና፣ ሥነ አፈታት፤ሥነ አሰባበክና ገላጭ ስብከት አዘገጃጀትን አጣምሮ የያዘ ጠቃሚ ስልጠና ነው።
-----------------------
#ኤስ_ዩ
#ኢየሱስን_የሚከተሉ
#በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ
#ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ
674
+9
በዶዶላና አካባቢዉ የተማሪ ህብረት መሪዎች ስልጠና (ALS)
----- ----- ------- -------
በደቡብ ምስራቅ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ በዶዶላ እና አካባቢው የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረት የመሪዎች ስልጠና ተካሂዷል፡፡ ጥቅምት 29 እና 30 በተካሄደው በዚህ የመሪዎች ስልጠና ከአራት ከተሞች ፡- ዶዶላ፣ወርቃ፣አዳባ እና አሳሳ የተወጣጡ የተማሪ ህብረት መሪዎች ተሣታፊ ሆነዋል፡፡
በዕለቱ ከ#ዘፍጥረት መጽሐፍ መልዕክት ቀርቧል፡፡ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ ሕብረት ስለማድረግ ሴሚናር ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም የኤስ.ዩ የተማሪዎች አገልግሎትን በተመለከተ ቪዥን ዶክመንቱ በተብራራ መልኩ ቀርቧል፡፡
ከተማሪ ሕብረት መሪዎች ባሻገር፣ ከዶዶላ #አብያተክርስቲያናት_መሪዎች ጋር የምክክርና ራዕይ የማጋራት መርሐ ግብርም ተካሂዷል።
-----------------------
#ኤስ_ዩ
#ኢየሱስን_የሚከተሉ
#በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ
#ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ
#ተማሪዎችን_ማየት
674
+9
የአርባምንጭ እና አካባቢዉ ኤስዩ የተማሪ ህብረት መሪዎች ስልጠና
----- ----- ------- -------
በደቡብ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ አርባምንጭ እና አካባቢው የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረት የመሪዎች ስልጠና ተካሂዷል፡፡ ጥቅምት 29 በተካሄደው በዚህ የመሪዎች ስልጠና ሶስት ከተሞች ፡- ከአርባምንጭ፣ ከጨንቻና ሻራ የተወጣጡ የተማሪ ህብረት መሪዎች ተሣታፊ ሆነዋል፡፡
በዕለቱ የቤተሰብ ቡድን፣ አገልጋይ መሪነት የሚሉ ሴሚናሮች በተጨማሪም የኤስ.ዩ የተማሪዎች አገልግሎትን በተመለከተ ቪዥን ዶክመንቱ በተብራራ መልኩ ቀርቧል፡፡ በአገልግሎቱ ዙርያ ከተማሪ መሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
ከአርባምንጭ እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአብያተክርስቲያናት_ህብረት_መሪዎች ጋር የምክክርና ራዕይ የማጋራት መርሐ ግብርም ተካሂዷል። ከ #ኢቫሱ አገልጋዮች ጋር በአጋርነት በሚሰሩ ጉዳዮች ዙርያ ገንቢ ውይይት ተደርጓል።
በተጨማሪም ጥቅምት 30 ከኤስዩ አሶሼት አገልጋዮች ጋር የምክክር እና የስልጠና ጊዜ ነበረ።
-----------------------
#ኤስ_ዩ
#ኢየሱስን_የሚከተሉ
#በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ
#ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ
#ተማሪዎችን_ማየት
674
+8
ለቤተክርስቲያን የልጆች አገልጋዮች የተሰጠ ስልጠና
———————————————————-
ኤስዩ ከቤተክርስቲያን ጋር በአጋርነት ሲያገለግል የቆየ አገልግሎት ነው። የዚህ አካል የሆነ ለቤተክርስቲያን የልጆች አገልጋዮች አሻንጉሊትን በመጠቀም ልጆችን ማስተማር በሚል ርዕስ የተዘጋጅ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው በአዲስ አበባ ከሚገGኡ የተውሰኑ አጥብያዎች የተወጣቱ የልጆች አገልጋዮች ተሳትፈውበታል። ስልጠናው እጅግ አሳታፊና በቤተክርስቲያን የልጆች አገልግሎት እድሜያቸውን ያማከሉ ስልቶችን ለመጠቀም የሚረዳ መሆኑን ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የዕሴቶች ትምህርት በሚል በዩጋንዳ ኤስዩ ተዘጋጅቶ ለመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሰጥ ትምህርት የአሰልጣኝ መምሪያ በአዲስ አበባ እና ዙርያው ለተወጣጡ የኤስዩ አገልጋዮች ተሰጠቷል። ስልጠናው ከ ኤስዩ ዩጋንዳ እንዲሁም ከካናዳ እና አሜሪካ በመጡ አስልጣኞች ነው የተሰጠው።
———————————————————-
#ኤስ_ዩ
#ኢየሱስን_የሚከተሉ
#በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ
#ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ
#ተማሪዎችን_ማየት
674
Repost from የየዕለቱ ብርሃን
ኦሪት ዘዳግም 4:35
[35] እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቅ ዘንድ ይህ ለአንተ ተገለጠ፤ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም።
@yeyeletuberehan
