fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

የክብሩ ነፀብራቅ✨

የክብሩ ነፀብራቅ✨

رفتن به کانال در Telegram

ልጁም የእግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅና የአምላካዊ ባሕርዩ አምሳያ ነው፡፡ ወልድ አምላክ በመሆኑም ይህን ዓለም በሥልጣኑ ኃይል ይቆጣጠረዋል ፤ በሥርዓት እንዲመራም ያደርገዋል ። እኛን ከኃጢአት ለማንጻትና የተመዘገበብንን የበደል ደብዳቤ ለመደምሰስ ከሞተ በኋላ ፥ አሁን በአባቱ ጎን ባለው ከፍተኛ ሰማያዊ የክብር ቦታ ተቀምጧል ። [ሕያው ቃል ዕብራውያን 1:3]

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
358
مشترکین
+324 ساعت
+137 روز
+9030 روز
آرشیو پست ها
አቤቱ ጌታችን እግዚአብሔር ሆይ፥ለራስህ ክብርና ዓላማ ሰርተሄናልና ዛሬም አንተን እንፈልግሃለን፥ ለፈቃድህ መንገድ ህያው አድርገን: በሰው ፍጥረት በዕድሜው ማለዳ የህይወት እስትንፋስን እፍ ያልክብን
አቤቱ ጌታችን እግዚአብሔር ሆይ፥ለራስህ ክብርና ዓላማ ሰርተሄናልና ዛሬም አንተን እንፈልግሃለን፥ ለፈቃድህ መንገድ ህያው አድርገን: በሰው ፍጥረት በዕድሜው ማለዳ የህይወት እስትንፋስን እፍ ያልክብን ፈጣሪያችን ሆይ : ዛሬም በመንፈስህ ለራስህ ለክብርህ እና ለክቡር ዓላማ አንቃን :: @Kbr111

አባ... መገኘትህ አይለመደን! 🥺 በሰው ፊት ምንም ያህል ጠንካራ ብንመስልም፣ በአንተ ፊት ግን የጀግንነት ድራማ አንሰራም። ያለምንም መሸማቀቅ «ደክሞኛል፣ ብቻዬን አልችለውም» ብለን በእቅፍህ ውስጥ እንወድቃለን ። «ሁሉን ቻልኩ» ያልን ዕለት፣ የገዛ ብርታታችን እንዳይጥለን ሮጠን እግርህ ሥር እንደፋለን። እኛማ ያንተ የዕድሜ ልክ ጥገኞች ነን! 🤍
«እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።» — የዮሐንስ ወንጌል 15፥5
የተባረከ ሳምንት ይሁንላችሁ 🥰

የሞት አዋጅ የሕይወትን አምላክ ሊያቆመው አይችልም!
🔥🔥🔥

Repost from Christ-centered
እግዚአብሔር በሰው ልጅ ልብ ውስጥ በምንም ዓይነት ምድራዊ ነገር ሊሞላ የማይችል መለኮታዊ ክፍተት (God-shaped void) አስቀምጧል። ዓለምን ሁሉ ብታተርፍ፣ እውቀትን ሁሉ ብትጨብጥ፣ ነፍስህ ወደ ፈጣሪዋ ካልተመለሰች በቀር ዕረፍት አታገኝም። የነፍሳችን ጥማትና የዘላለምነት ፍላጎት፣ እግዚአብሔር ዘላላማዊ አምላክ ሆኖ መኖሩንና ለእርሱ እንደፈጠረን የሚያሳይ ታላቅ ማስረጃ ነው።

Fact!👌

ፈቃዶች..........? በመንፈሳችን ውስጥ በኃይል የሚጮኸው የእግዚአብሔር ፈቃድ እና የነፍሳችን ግራ መጋባት ሲላተሙ ከሚፈጠር የውስጥ ስብራት የበለጠ የሚያም ሕመም የለም። አንዳንዴ እግዚአብሔር የሚፈልገው ነገር ግልጽ ሆኖ እያለ፣ የገዛ ፍላጎታችንና ፍርሃታችን መላ ያሳጡናል። በሁለት ሐሳብ መካከል ተወጥረህ ስትቀር ደግሞ በምንም ዓይነት ምድራዊ ነገር መደሰት አትችልም፤ የውሳኔ አቅምህ ይዝላል።
ለእግዚአብሔር ፈቃድ እጅ ያልሰጠች ነፍስ በምንም ተአምር ዕረፍት አታገኝም!🙌
የፈለግከው የስኬት ጫፍ ላይ ብትደርስ፣ ምድር በሙሉ ብታጨበጭብልህ፣ ነፍስህ በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ እስካላረፈች ድረስ ያገኘኸውና የጨበጥከው ነገር ሁሉ ባዳ ይሆንብሃል። የያዝከው ሁሉ ትርጉም ያጣል፤ ውስጣዊ እርካታ ይናፍቅሃል። በተለይ ደግሞ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥሪ ላለበት ሰው፣ ከፈቃዱ ውጪ መኖር ማለት በየቀኑ በዝምታ እየባሰ የሚሄድ የማይድን የነፍስ ሕመም ነው። ይህን የነፍስህን ስቃይ ከተረዳህ፣ መፍትሔው.... መታገል ሳይሆን በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ጥለህ መጮህ ብቻ ነው።  ከበዛ የሰው ምክርና ንዝነዛ ርቀንወደ ቃሉ በትህትና ወደጌታ መምጣት አማራጭ የለለው ጉዳይ ነው፦ ራስህን ሙሉ በሙሉ ባዶ አድርገህ፦ «ጌታ ሆይ፣ ምን ትለኛለህ? እኔ አቅሜን ጨርሻለሁ... አንተ ምራኝ» በለው።
This is the only way your soul will find genuine rest and peace!
ካልሆነ ግን ምንም ያህል ብትሮጥ ነፍስህ እንደታመመችና እንደባከነች ትቀራለች። ለእግዚአብሔር ፈቃድ እጅ መስጠት መሸነፍ ሳይሆን፣ የነፍስህ ትልቁ ዕረፍት፣ ነጻነትና መዳን ነው! 🤍
" አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ። "     — መዝሙረ ዳዊት 143፥10
@Kbr111 #የክብሩ_ነጸብራቅ #የእግዚአብሔር_ፈቃድ #የነፍስ_ዕረፍት #የመንፈስ_ጥሪ #በእግዚአብሔር_ፊት #SoulRest #DivineWill #SurrenderToGod #Psalm143

ኔ ሳባይ ታው ጎንዳሌ 🛡️🛡️🛡️ ኔ ማሮታይ ታው ጣሌ 💊 ❤️‍🩹❤️‍🩹
ሞገስህ ጋሻዬ ነው ምህረትህ መድኃኒቴ ነው
🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌

Oooooow this is so insane ሰዎች ይህንን ስሙት! https://youtu.be/BE3ACAngZ54?si=DodZamU-n4Jn-Eg7

Repost from EvaSUE |ኢቫሱ
አብዛኛውን ጊዜ፣አንድን ሰው ስናጣ፣ ችግር ውስጥ ስንገባ፣ውጤት አልመጣ ሲለን፣ ብቸኝነት ሲሰማን እና ነገሮች እንዳሰብነው ሳይሆኑ ሲቀሩ፣ እግዚአብሔር እንደተወን እናስባለን፤ ተስፋ እንቆርጣለን። አም
አብዛኛውን ጊዜ፣አንድን ሰው ስናጣ፣ ችግር ውስጥ ስንገባ፣ውጤት አልመጣ ሲለን፣ ብቸኝነት ሲሰማን እና ነገሮች እንዳሰብነው ሳይሆኑ ሲቀሩ፣ እግዚአብሔር እንደተወን እናስባለን፤ ተስፋ እንቆርጣለን። አምላካችን ማን እንደሆነ እንረሳለን። ይህ በእኛ አልተጀመረም። በኢሳይያስ ምዕራፍ 40:27ን ብናይ፣ እስራኤላውያን መብታቸው በእግዚአብሔር እንደተዘነጋ፣ እንደተተዉ እና እንደተረሱ ስለተሰማቸው፣ በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ መቁረጣቸውን እናያለን። እኔም ብዙ ጊዜ ይህን አድርጌያለሁ። ዓለም በዙሪያዬ እየፈራረሰ እንደሆነ ፣ እግዚአብሔር ግን የትም እንደሌለ የተሰማኝ ወቅቶች ነበሩ። እግዚአብሔር ግን ለእስራኤላውያን የሰጠውን መልስ ቁጥር 28 ላይ እዩ። የእስራኤላውያን ትኩረት ሁኔታቸው ላይ ስለነበር፣ እግዚአብሔር ትኩረታቸውን ወደ እርሱ ማንነት መለሰ። ስለ ታላቅነቱ በማስታወስ፣ እርሱ የምድር ፈጣሪ መሆኑን፣ የማይደክም፣ የማይታክት፣ ብርታት ሰጪ አምላክ እንደሆነ ዘርዝሮ፣ ተስፋ የሚጣልበት አምላክ መሆኑን አሳያቸው። ቁጥር 31 ላይም፦ “እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፥ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፥ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፥ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።” በማለት መልእክቱን ደመደመው። እስራኤል በወቅቱ የእግዚአብሔርን ማንነት ማስታወስ እንደነበረባት ሁሉ፣ እኛም እንዲሁ ማድረግ አለብን ብዬ አስባለሁ። አዎ፣ ሁኔታዎቻችን እግዚአብሔር እንደረሳን ሊነግሩን ይችላሉ፤ ነገር ግን ባሕርዩ የሚነግረን ከዚህ በተቃራኒ ነው። ለዛም ነው እርሱ ማን እንደሆነ ራሳችንን ማስታወስና ተስፋችንን በእርሱ ላይ ማድረግ የሚገባን። ምክንያቱም እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ኃይላቸውን ያድሳሉና። እግዚአብሔር ይህን ዓመት ዕለት ተዕለት ማንነቱን እንድናስታውስ ይርዳን! አሜን። —ምሕረት

ክርስቶስ በምድር እስክንባል ድረስ ቃሉ ከእኛ ጋር መዋሓድ አለበት። ምክንያቱም፣ እኛ የክርስቶስ መዳረሻ እግሮች፣ መዳሰሻ እጆች፣ ማጽናኛ አንደበቶች፣ መመልከቻ ዐይኖች ነንና። ዲ. አ. መ.

ዕልፍ ሰው አጅቦት ልቤ ይፈራል ያላንቴ 🙌

ከኖርን ላይቀር.... 🔥😭 በዚህች ምድር ላይ እጅግ የምቀናባቸው ሰዎች ቢኖሩ… ሀብት ያከማቹ፣ ዝና ያተረፉ ወይም የዓለምን ስኬት የረገጡ አይደሉም። እኔ እስከ ጥግ የምቀናው በእግዚአብሔር መንፈስ ክፉኛ በተነኩ፣ ሕይወታቸው በአንድ መለኮታዊ ንክኪ (Encounter) ለዘላለም በተለወጠባቸው ሰዎች ነው። በቃ የእግዚአብሔር እጅ አሻራ በነፍሳቸው ላይ በግልጽ ያረፈባቸው ሰዎች ሁሌም ያስቀኑኛል! አንዳንዴ በጸሎቴ ጓዳ ሆኜ፦ «ምናለ በሕይወቴ አንዴ እንኳን ያቺ የያዕቆብ ሌሊት ለኔ በሆነች!» ብዬ አነባለሁ። «ምናለ እንደ ጳውሎስ የክርስቶስን የክብሩን ፊት አይቼ፣ በዚያ ሰማያዊ ብርሃን የምድሩ ዓይኖቼ በታወሩ!» እላለሁ። እኛ የምንፈልገው የተለመደውን ደረቅ የሃይማኖት ልምምድ አይደለም፤ ነፍሳችን የናፈቀችው ታሪክ የማይሽረውን ያንን እውነተኛ የእግዚአብሔር ንክኪ ነው።
We don’t just need religion; we are desperate for a real encounter. 🙌 🧎‍♀️🧎‍♀️🧎‍♂️🧎‍♂️
በቃ በሩቅ መስማት ሰልችቶናል፤ ስለ ሌሎች ሰዎች መንፈሳዊ ታሪክና ምስክርነት ብቻ ማጨብጨብ ደክሞናል። እኛም የራሳችን የሆነ «ጵኒኤል» ያሻናል! በእርግጥ መለኮታዊ መንነካት የራሱ የሆነ ትልቅ ዋጋ አለው፦    -ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር ታግሎ ሲያነጋው የሥጋው ብርታት ተሰብሮ አካሄዱ ተቀይሮ ነበር He walked with a physical limp, but with a spiritual authority.    -ጳውሎስ ኢየሱስን ሲያገኝ የዓለም ብርሃን ጠፍቶበት የሰማይ ብርሃን በራለት። የእግዚአብሔር መንፈስ ሲነካን ዝም ብሎ አስደስቶን ብቻ አይተወንም፤ ይልቁንም ከምድር ስበት ያላቅቀንና ለዘላለም የፍቅሩ እስረኛ ያደርገናል። God doesn’t encounter us just to give us goosebumps; He encounters us to transform our destiny permanently. ወዳጆቼ፣ ከኖራችሁ ላይቀር… ዕድሜ ልካችሁን የምትመሰክሩት፣ ትውልድን የሚቀይር አንድ ትልቅ እና ሕይወት ቀያሪ የሆነ Encounter በእግዚአብሔር ፊት ይሁንላችሁ! ጧት ማታ የምትጸልዩት፣ የምትዘምሩትና የምትሰበሰቡት ዝም ብሎ ለልማድ አይሁን። እግዚአብሔር ራሱን በሙላት ይግለጥላችሁ።🙌 ልባችሁን ሰንጥቆ የሚገባ፣ ታሪካችሁን ለሁለት የሚከፍል፣ «ከዚህች ቀን በኋላ እኔ ያ የቀድሞው ሰው አይደለሁም!» የሚያስብል መለኮታዊ ንክኪ ያግኛችሁ! 🔥
  «በጆሮ መስማት ስለ አንተ ሰምቼ ነበር፤ አሁን ግን ዓይኔ አየችህ።»
                  — ኢዮብ 42፥5 📍 @Kbr111 #የክብሩ_ነጸብራቅ #DivineEncounter #መለኮታዊ_ንክኪ #የመንፈስ_ንክኪ #እውነተኛ_ሕይወት #የእግዚአብሔር_ፊት #SpiritualAwakening #Job42

We need each other ! 💊 «አንተማ ብርቱ ነህ፤ አንተ ምን ጎደለህ?» ይህ አባባል አንዳንዴ አድናቆት ሳይሆን፣ የአገልጋዮችን እውነተኛ ጩኸት በዝምታ የሚያፍን ከባድ እስር ቤት ነው። በዚህ ጭፍን ግምት ጥላ ሥር ስንት የእግዚአብሔር አገልጋዮችና ታማኝ ሰዎች የልብ ቁስላቸውን በብቸኝነት ታቅፈው እየደሙ እንዳሉ እናውቃለን? መድረክ ላይ ቆመው እኛን ስለሚያጽናኑ ብቻ በጓዳቸው አያለቅሱም ማለት አይደለም። የሌላውን ሸክም ስላቀለሉ ብቻ የገዛ ትከሻቸው አልዛለም ማለት አይደለም። They bleed, they get tired, and they break. ገና አልከበሩም፤ ዛሬም በደካማ ሥጋ ውስጥ የሚኖሩ፣ እንደ ማንኛውም ሰው የሚዝሉ፣ ከእግዚአብሔር በታች የሰውን እውነተኛ ርኅራኄ፣ ማዳመጥና ይቅርታ የሚሹ ተራ የሰው ልጆች ናቸው። አይገርማችሁም? የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተክርስቲያን የተሰበረ የሚጠገንባት፣ የደከመው ነፍስ የሚዘረጋባት የጸጋ ሆስፒታል መሆን ነበረባት። ዛሬ ግን ብርቱ የመሰለን ሰው አንዲት ቀን ሲደክም ወይም ሲሰናከል ድንጋይ የምናቀብልባት፣ በወደቀው ላይ ያለ ርኅራኄ የምንፈርድባት መድረክ ሆነችብን። የሰውን ድካም enjoy አናድርግ፤ don’t advertise it! የወንድማችንን ውድቀት ርዕስ አድርገን «እኔ ከእርሱ እሻላለሁ» የሚል ራስን የማግነን ማስታወቂያ አንሥራ። እውነት የክርስቶስ ልብ ካለን—if we have a true heart—አደባባይ ወጥተን ከመስበር ይልቅ ጓዳችን ገብተን በጸሎት እናንሳቸው፤ በቅን ፍቅር እናክማቸው። ክርስቲያኖች ሆይ፣ take this seriously! This generation desperately needs genuine fellowship. ይህ ካልሆነ ግን ከጥቂት ዓመታት በኋላ ብዙ ወጣቶችን ቤተክርስቲያን ውስጥ ላናገኛቸው እንችላለን። ሳይቀደሙ እንቅደማቸው! Let’s make church a real healing place 🥺። በዚህ ዘመን እያንዳንዱ ሰው በውስጡ የራሱ የሆነ ከባድ ጦርነትና ትግል አለበት (everyone has their own strong struggles and silent war inside)። በቃ እውነተኞች እንሁንና እንነጋገር። ከልባችን የክርስቶስ ፍቅር በሞላበት መንፈስ፣ ለመውገር ሳይሆን ለመረዳዳት «እንዴት ነህ? እንዴት ነሽ?» እንባባል። የእኛ ዘመን ትውልድ ብቻውን survive የሚያደርግ አይመስለኝም—all of us need each other! እውነተኛ ሕብረት ያስፈልገናል። ድካማችንን፣ ብርታታችንን፣ መውደቃችንንና መዛላችንን ያለ ፍርሃት በጌታ ፊትና በእውነተኛ ሕብረት እንወያይ፤ እንጸልይበት። 🙌 We don’t need another staged performance; we desperately need authenticity. ስንደክም ሳንሸማቀቅ «ደክሞኛል» የምንልበት፣ በድካማችን ሳይፈረድብን በፍቅሩ ተደግፈን የምንነሳበት፣ ማስመሰል የሌለበት እውነተኛ መንፈሳዊ ቤተሰብ ካላችሁ፣ እንደ ዓይናችሁ ብሌን አጥብቃችሁ ጠብቁት—በዚህ ዘመን የትም የማይገኝ ውድ ሀብት ነው! 🤍
«ደካሞችን አበርቱ፥ በሁሉ ታገሡ።» — 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥14
— 📍 @Kbr111 #የክብሩ_ነጸብራቅ #የጸጋ_ሆስፒታል #እውነተኛ_ሕብረት #ሳይቀደሙ_እንቅደማቸው #በፍቅር_እናክማቸው #AuthenticCommunity #GraceAndMercy #1Thessalonians5

Repost from Anti World
ከማውቃቸው ሴት ዘማሪዎች በአለባበስ ሥርዓቷ ቅድሚያ የምሰጣት ናት። Look at her... her decency is extremely and absolutely beautiful! She is modest an
+4
ከማውቃቸው ሴት ዘማሪዎች በአለባበስ ሥርዓቷ ቅድሚያ የምሰጣት ናት። Look at her... her decency is extremely and absolutely beautiful! She is modest and at the same time ዘናጭ። እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉ ሴቶች እንደሚገባ መልበስ ማለት አለመዘነጥ እንደሆነ ለሚያስቡ ሁሉ Selu is a living example. አቤት elegance! የእግዚአብሔር መንገድ ሰላም አለው። How I love her dress style and her beautiful head covering (ሻሽ)! @ALDERADERIM ​Selam Desta, God bless you and your family! You honor God, you honor your husband, and you honor the saints (your brothers in Christ) by the way you dress!

this Worship ሕብረት ❤‍🔥❤‍🔥❤‍🔥🔥🔥🔥🔥🔥 https://youtu.be/R6-vuz3X8_8?si=6yxLj6fClr6eWP2W

ቀኔ ተባርኳል🙌🔥

የውስጤን አወራልኝ።

🙌🥺

አዲስ ክርስቲያን 👌 አሁን አሁን ፊቱን እለት እለት መፈለግ:ድምፁን ለይቶ ቶሎ መንበርከክ:የእውነት ማምለክ:ከልብ መሰጠት:ከመንፈስ መለየት :ሁሉን እንደ እግዚአብሔር ቃል መመዘን የአዲስ ክርስታያን ባህሪ ነው ብለን አብዛኞቻችን ሰይመነዋል!.....በድርቀት መያዛችን የመዘመን ምልክ መስሎን በኛ የበረታውን መድረቅ በሌሎች እንደ እግዚአብሔር ቃል በበረቱ እህትና ወንድሞቻችን ላይ ለማበርታት እየተዘጋጀን የውስጥ መሰጠታቸውን ልናደርቅ ለመጎበዛቸው ማዕረግ እንደሆነ ሳይገባን የነቀፍን መስሎን"አዲስ ክርስቲያን"ነህ/ነሽ እንዴ እያልን የመሰጠታቸውን ልክ እንሰብራለን🤦‍♀️ ስለ ቃልህ መናገር:እንደ ቃልህ መጓዝ:ለሃሳብህ መበርታት:ለፍቃድህም መገዛት:ለድሞፅህ መለየት:ለመንገድህ መከተል:ሁሉን እንደ ቃልህ መመዘን:ሀለዎትህን መፈለግ:ባለመፍቀድህ መቆጠብ:በመፍቀድህም መቀጠል አዲስ ክርስቲያን ካስባለኝ ofc እቀበለዋለሁ!የዚህ ማንነት መገለጫም ይህ ከሆነ"አዲስ ክርስቲያንነቴ'ማእረጌ ነውና ለዘመኔ ስንቅ ሆኖኝ እቀጥልበታለሁ!"አዲስ ክርስቲያን ነኝ‼️" ከTikTok መንደር 🖊️ ምፅላል_🌸