fa
Feedback
Purity Matters

Purity Matters

رفتن به کانال در Telegram

"ትቀደሱ ዘንድ ፈልጉ ...(ዕብ12፥14) ቅድስና እግዚአብሔርን የምናይበት መንፈሳዊ ዐይናችን ነው! 📖 የጸሐፊው የታተሙ መጻሕፍት፦ 1️⃣ ፖርኖርሽኝ (የፖርኖግራፊ መርዝ፣ መዘዝ እና መድኃኒት) 2️⃣ የኅሩያን ሕይወት (የወሲባዊ ቅድስና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሖዎች እና አተገባበራቸው) 📩 መጻሕፍቱን ለማዘዝና ለመግዛት፦ • በቴሌግራም፦ @minassieyirgu • በስልክ ቁጥር፦ 0986552076

نمایش بیشتر
1 317
مشترکین
+524 ساعت
+247 روز
+5130 روز

در حال بارگیری داده...

کانال‌های مشابه
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
سپتامبر '26
سپتامبر '26
+55
در 2 کانال‌ها
اوت '26
+96
در 2 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '26
+127
در 3 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '26
+114
در 2 کانال‌ها
Get PRO
مه '26
+156
در 2 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '26
+176
در 4 کانال‌ها
Get PRO
مارس '26
+148
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '26
+38
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '26
+47
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '25
+70
در 2 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '25
+137
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '25
+318
در 1 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
23 سپتامبر+2
22 سپتامبر+5
21 سپتامبر+1
20 سپتامبر+2
19 سپتامبر+7
18 سپتامبر+7
17 سپتامبر+1
16 سپتامبر+6
15 سپتامبر0
14 سپتامبر+6
13 سپتامبر+2
12 سپتامبر+2
11 سپتامبر0
10 سپتامبر+1
09 سپتامبر+5
08 سپتامبر+1
07 سپتامبر+1
06 سپتامبر0
05 سپتامبر0
04 سپتامبر+1
03 سپتامبر+3
02 سپتامبر+1
01 سپتامبر+1
پست‌های کانال
በምድራዊው ሥርዓትና በተፈጥሮ ሕግ እሳት በውኃ እንደሚጠፋ ቢታወቅም፣ በመንፈሳዊው ዓለም ስሌት ግን ነገሩ ፈጽሞ የተለየ ነው። በሰውኛ ድካምና በግልብልብ የፍትወት እሳት የሚናወጠውን የሰውን ማንነት በሰውኛ ጥረት፣ በሕግጋት መደርደር ወይም ስሜትን ዝም ብሎ በመጨቆን (በውኃ) ለማጥፋት መሞከር ዘላቂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ይህንን ፈታኝና የሚለበልብ የሥጋ ምኞት ማሸነፍ የሚቻለው፣ ከዚያ በሚበልጥና በሚበላ ሌላ መለኮታዊ እሳት ሲዋጥና ሲተካ ብቻ ነው። ስለዚህ ወሲባዊ ቅድስናን በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በተግባር ማረጋገጥ የሚቻለው ከፈተናዎች በመሸሽ ወይም ራስን በማታለል ሳይሆን፣ ያንን የፍትወት እሳት በመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ እሳት በመርታትና በመዋጥ ነው። 📚የኅሩያን ሕይወት (ገጽ 147)

2
https://t.me/Nazrawit38
169
3
መሸሽ ዐደጋ ሊያደርስ ከሚችል ከማንኛውም ነገር ለማምለጥ የምንወስደው የጥንቃቄ ርምጃ ነው። መሸሽ ልንጋፈጠው የማንችለው ነገር ሲመጣብን የምንሰጠው ደመ ነፍሳዊ ምላሽ ነው። መሸሽ በእጅ አልሰጥም ባይነት ከመዋጋት ይልቅ ከመሞት መሰንበት በሚል ድምፀት ራስን ለማዳን መፈትለክ ነው። መሸሽ በብዙኀኑ ዘንድ የፈሪዎች ድርጊት እንደኾነ ተደርጐ ይታሰባል። ታግለው የማያሸንፉትን ጠላት ሸሽተው የማያመልጡ አላዋቂዎች መጠሪያቸው ጀግኖች የሚል የመዓርግ ስም ሳይኾን ሞኞች የሚል የወል ስም ነው። መሸሽ አንዳንዴ ጥበብ ነው! መዳረሻ ያለው ፍርጠጣ፣ ዓላማ ያለው የእግሬ አውጪኝ ሩጫ ከኾነ ሽሽት መልካም ነው። ሽሽት ወይም ማፈግፈግ አንዱ የጦርነት ስልት ነው። ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ በጐ ወታደር መልካሙን ገድል እንዲጋደል እንደተጠራ ኹሉ፣ እንደ ሕያው ቤተ መቅደስ ከሚያረክሰው ከማንኛውም ነገር እንዲሸሽም ጭምር ታዝዟል። ክርስቲያን እንዲሸሽ ከታዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱና ዋነኛው ክፉ የጐልማሳነት ምኞት ነው። ይኽ ክፉ የጐልማሳነት ምኞት የዝሙት ወላጅ አባት ነው። ስለዚህ በተዘዋዋሪ ሽሹ እያለን ያለው ከዝሙትም ጭምር ነው። በርግጥ፣ ጳውሎስ በቀጥታ ለቈሮንቶስ አማኞች "ከዝሙት ሽሹ" በማለት ሐዋርያዊ የማስጠንቀቂያ ቃልን እንዳስተላለፈ ዕውቅ ነው። ዝሙት ኃይለኛውን መስፅን ሶምሶንን፣ ልበ እግዚአብሔር የተባለውን ንጒሥ ዳዊትን እና ስመ ገናናውን ጠቢብ ንጒሥ ሰሎሞንን የጣለ ዐደገኛ ጠላት ነው። ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ ሲል ይኼንንም የብሉይ ታሪክ እያሰበ ሳይኾን አይቀርም። ዝሙት መንፈስን የሚያረክስ፣ ነፍስን የሚያሳድፍ፣ ሥጋንም የሚያጐድፍ የአጋንንት መሥዋዕት ነው። ዝሙት እጅ በእጅ የማይፋለሙት ባላንጣ፣ በወንድነት ወኔ ተጋጥመው የማያሸንፉት አሳድዶ ገዳይ ጠላት ነው። 📚ፖርኖርሽኝ (ገጽ 226)
293
4
በዓመታት የተገነባን መንፈሳዊ ግርማ እና እግዚአብሔር የሰጠንን ታላቅ ዓላማ በጥቂት ቅጽበታት ስሜት መለወጥ ብኲርናንን ማቃለል በመሆኑ ዐደጋው የከፋ ነው። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰዉ የሰጠው ታላቅ እምቅ አቅም እና ሊደርስበት የሚገባ የሕይወት ግብ አለ። ወሲባዊ ርኲሰት ግን ይህንን ግብ የሚያጨናግፍ እና ከታየልን ክብር የሚያጐድል ሥውር ወጥመድ ነው። 📚የኅሩያን ሕይወት (ገጽ 146)
253
5
የሰው ልጅ ለማዳ ፍጡር ነው። በስሜት ሕዋሳቱ አማካኝነት በሚቃርመው መረጃ በዙሪያው ካሉ ሰዎችና ከአካባቢው ጋር በመላመድ፣ በፍጥነት ከሚለዋወጠው የኑሮ ሥርዐት ጋርም ዐብሮ በመለወጥ እና ራስን በማሠልጠን ሒደት ውስጥ ያለማቋረጥ የሚያልፍ የምንጊዜም የሕይወት ተማሪ ነው። የሰው ልጅ ከሕይወት ትምህርት ቤት የሚያገኛቸው ትምህርቶች ጭማቂ ደግሞ ልማደ ሕይወት (EXPERIENCE) በመባል ይጠራል። ልማድ በአንድ ጀንበር የማይገነባ፣ በአንድ ጀንበርም የማይፈርስ ነገር ነው፤ ልማድ የልምምድ ውጤት ነውና። ልማድ የየዕለት ድርጊቶች እና ክንውኖች ድምር ውጤት ነው። የሰው ልጅ የልማዱ እሥረኛ ነው ሲባል እንሰማለን፤ በርግጥም ነን። (ድመት መንኲሳ አመሏን አትረሳ እንዲሉ!)። አንድን ነገር ልማድ ካደረግን በኋላ እንዲኹ ለመላቀቅ የማይቻል ነው። ከምንወደው ጐጂ ልማድ ራሱ የምንላቀቀው በሌላ በማንወደው ገንቢ ልማድ ነው። የሰው ልጆች ስንባል ሊሰበር በማይችል የልማድ ቀለበት ቅርቃር ውስጥ የገባን ልማደኛ ፍጡሮች ነን። ልማድ መንታ ገጽታን የተላበሰ በመኾኑ እንደሚያደርሰው ተጽዕኖ ሠናይ (በጐ) ወይም እኲይ (ክፉ) ሊኾን ይችላል። የልማድ እስረኛነታችን አርነት የሚመስል ባርነት ያለበት ከኾነ (ልክ እንደ አደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት) ልማዱን ጐጂ (እኲይ) ልማድ ብለን ስንጠራው፥ በተቃራኒው ደግሞ ባርነት የሚመስል ግን አርነትን የሚያጐናጽፍ ከኾነ (ለምሳሌ በጠዋት ተነሥቶ ስፖርት መሥራት፣ ስኳር የበዛበትን ምግብ መቀነስ ወዘተ...) ልማዱን ጠቃሚ (ሠናይ) ልማድ ብለን እንጠራዋለን። በዚኹ የትርጒም ማሕቀፍ ውስጥ ኾነን የኀጢአት ልምምድን ከክፉ ልማድ ውስጥ መመደብ እንችላለን። የኀጢአት ልምምድ ግን ከክፉ ልማዶች ተርታ ብቻ የሚሰለፍ አይደለም፤ የክፉ ልማዶች ኹሉ መፍለቂያ ምንጭም ጭምር እንጂ! ኀጢአት ከምኞት ማኅፀን ተወልዶ እና አድጐ ሞትን እስከሚወልድበት ጊዜ ድረስ በመኻከል ያለውን ጒዞ ነው የኀጢአት ልምምድ እያልን የምንጠራው። ይኽ የኀጢአት ልምምድ መነሻው እዚህ ግባ የማይባል እና ቀላል የሚመስል ምኞት ዐዘል ዐሳብ ነው። ረቂቅ የነበረችው ምኞት ግዘፍ ነሥታ ደጋግማ በግብር የመገለጥ ዕድል ስታገኝ የኀጢአት ልምምድ ትኾናለች። የኀጢአት ልምምድ "ግማሽ መርዝ አይገድልም" (HALF POISON WON'T KILL) በሚል ዕብደት የተቀላቀለበት ጀብደኝነት በምኞት እሳት መጫወት ወይንም ለምለም ሳሩን ብቻ የማየት ዝንጒነት በተጠናወተው አኳኋን ወደ ጥፋት ገደል መንደርደር ማለት ነው። 📚ፖርኖርሽኝ (ገጽ 167-168)
300
6
በፖርኖግራፊ ሱስ ምክንያት የሚከሠት የበታችነት ስሜት ከሰው ኹሉ የተለየኹ ርኲስ ነኝ ያስብላል፤ ከራስ ጋር ያፋልማል። ልብን ለዐመፅ ያጀግናል፤ ለንስሓ ደግሞ ያደነድናል። ከማኅበራዊ ሕይወት ራስን ማግለልን ያስከትላል። ከደስታ አፋትቶ ከኀዘን ያጋባል። ርካታ የለሽነትን ያመጣል፤ ተስፋ መቊረጥ እና ጨለምተኝነት እንዲያንሰራራ ያደርጋል፤ ውሻ ወደ ትፋቱ እንዲመለስ እንዲኹ ወደ ፖርኖግራፊእና ወደሌሎች ጊዜያዊ ወደኾኑ የስሜት ማደዘንዣዎች እና የመደበቂያ ዋሻዎች ገብቶ መመሸግን ምርጫ አልባ አማራጭ አድርጐ ያቀርባል። አለፍ ሲልም ራስን በማጥፋት እስከ ወዲያኛው ይኽችን አታክቴ ዓለም መሰናበትን ያስመኛል። በማስመኘት ብቻ አያበቃም፣ ራስን ለማጥፋት ድፍረት ሰጥቶ ያስሞክራል፤ ከተሳካለትም ለአንዴና ለመጨረሻ ከአፈር ይቀላቅላል። 📚ፖርኖርሽኝ ገጽ 144
377
7
እግዚአብሔር በመዓቱ ከመጣ የሚተርፍ የለም። ዝም ካለንም የሚመለስ የለም። ለካ እግዚአብሔር የሚቀጣን ስለሚያዝንልን ነው። ዲ. አ. መ.
353
8
https://youtu.be/uPIWotzNMlY?si=xyl0BSr2LQKZHibZ
407
9
ገንዘቡ ተሟልቷል🎉🎉🎉🎉🎉
523
10
https://t.me/sexualpurity
424
11
ይቺን መጽሐፍ ከማተሚያ ለማውጣት የቀረን ብር 27,000 ብር ብቻ ነው። ማን ይሆን ይኼንን ገንዘብ በመሙላት የቅድስናን ወንጌል የማስፋትን ራዕይ የሚደግፍ? ማን ትሆን የእግዚአብሔርን የልብ ጩኸት ለ
ይቺን መጽሐፍ ከማተሚያ ለማውጣት የቀረን ብር 27,000 ብር ብቻ ነው። ማን ይሆን ይኼንን ገንዘብ በመሙላት የቅድስናን ወንጌል የማስፋትን ራዕይ የሚደግፍ? ማን ትሆን የእግዚአብሔርን የልብ ጩኸት ለማስተጋባት ቀኝ እጁን የሚዘረጋ?
542
12
https://ye-buna.com/minassie#7
1
13
በምድር ላይ ትልቁ ውድቀት ለክብር ተጠርቶ በውርደት መኖር ነው። ወሲባዊ ርኲሰት የሚያደርገው ይኽንን ነው። የሕይወት ዓላማንና ዐቅምን ነጥቆ፣ በትርጒም የለሽ ሕይወት እና በጥፋተኝነት ስሜት ውስጥ በመዝፈቅ፣ በማይቆም የውርደት አዙሪት ውስጥ እንድንዳክር ያደርጋል። 📚የኅሩያን ሕይወት (ምዕራፍ 8)
509
14
Psalm 119:101-104 AMPC [101] I have restrained my feet from every evil way, that I might keep Your word [hearing, receiving, loving, and obeying it]. [Prov. 1:15.] [102] I have not turned aside from Your ordinances, for You Yourself have taught me. [103] How sweet are Your words to my taste, sweeter than honey to my mouth! [Ps. 19:10; Prov. 8:11.] [104] Through Your precepts I get understanding; therefore I hate every false way.
556
15
ክርስቶስ በምድር እስክንባል ድረስ ቃሉ ከእኛ ጋር መዋሓድ አለበት። ምክንያቱም፣ እኛ የክርስቶስ መዳረሻ እግሮች፣ መዳሰሻ እጆች፣ ማጽናኛ አንደበቶች፣ መመልከቻ ዐይኖች ነንና። ዲ. አ. መ.
630
16
መንፈሳዊ ረኃብ የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው። ሥጋዊ ረኃብ የሚመጣው ባለ መብላት ነው። መንፈሳዊ ረኃብ ግን የሚመጣው በመብላት ነው። መንፈሳዊ ረኃብ የሚጨምረው ቃሉን በበላን ቁጥር ነው። እየበሉ መራብ፣ እየተራቡ መብላት የመንፈሳዊያን ሰዎች የየዕለት ተግባር ነው። እየበላችሁ ነው ወይ? በማይጠረቃ መንፈሳዊ ረኃብ እግዚአብሔር ይባርከን🙏🙏🙏
532
17
https://youtu.be/mCrB9zuPDDE?si=2Zqawh7ecdcZ314T
486
18
መጽሐፍ ቅዱስ ወኅኒ በሆነችው ዓለም ስንኖር ዘላለማዊነትን አጮልቀን የምናይበት መስኮት ነው።
620
19
https://youtu.be/cQMKZtU7-tU?si=zZmjfPKavoq2tdQc
490
20
https://youtu.be/f1tUflI1_QI?si=GZN6zjf8NRSesLyK
459