ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 589
Suscriptores
+524 horas
+5667 días
+97730 días
Archivo de publicaciones
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በንፁሀን ሰዎች ላይ እስርና እንግልት እየፈፀመ ይገኛል ።
ዛሬም ከትላንት ስህተቱ መማር ያልቻለው ለፖለቲካዊ ጥያቄዎች ፖለቲካዊ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ጦርነትን እና ንፁሀኖችን ማሰርና ማንገላታት ብቸኛው መፍተሄ አድርጎት የቀጠለው የብልግናው አገዛዝ እጅግ ኢ-ሰበዓዊ ድርጊቶችን እየፈፀመ እንደሚገኝ ተገለፀ ።
በወቅቱ ከፍተኛ እብሪት ዉሰጥ እና የተሳሳተ ግምገማ ዉስጥ የነበሩት የብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች እና የጦር አዛዦች በ15 ቀኑ ዉስጥ አማራን አይደለም ትጥቁን ቀበቶዉን እናስፈታዋለን ብለዉ ፎክረዉ ቢገቡም በተገላቢጦሽ አማራዉ አይቶት የማያዉቀዉን የዘመናዊ ትጥቅ ባለቤት አድርገዉት ማረፋቸዉ የአደባባይ ሀቅ መሆኑ ይታወቃል ።
በቡልጋ ቀጠና አገዛዙ በተደጋጋሚ ኔትወርክ በማጥፋትና በሌሊት ኦፕሬሽኖችን በማድረግ ከኪሳራ ዉጪ ምንም አይነት ለዉጥ ማምጣት ያልቻለዉ የአብይ አህመድ ሰራዊትና ካድሬ፤ ከመጋቢት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀጠለው፤ በበረኸት ወረዳ መተህብላ ከተማ ላይ የፋኖ ቤተሰቦች ናችሁ በማለት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ አቅመ ደካሞች ፥ ሴቶችና ህፃናት ለእስርና እንግልት እየዳረጉ እንደሚገኝ የውስጥ አርበኞቻችን መረጃውን አድርሰውናል ።
ንፁሀንን ማሰርና ማንገላታት የአምባገነኖች መገለጫ ቢሆንም ዉድቀትን ከማፋጠን በቀር የሚቀይረዉ አንዳች ለዉጥ እንደሌለ ታሪኮች ምስክሮች ናቸው ። በህዝባችን እየተፈፀመ ያለዉ ግፍና በደል ትግላችንን በከፍተኛ ወኔ እና ተነሳሽነት እንድናስቀጥለዉ ከማድረግ በቀር የሚያስቆመን እና አንገት የሚያስደፋን እንዳልሆነ በዚህ ሶሰት አመት ዉስጥ ያደረግነዉ ተጋድሎ ምስክር ነው ።
ለመላዉ የከተማችን ማህበረሰቦች በሙሉ ይሄን ፀረ አማራ እና ፋሽስታዊ ስርዓት ከስር መሰረቱ ነቅለን መጣል እስካልቻልን ድረስ የነፃነት አየር መተንፈስ እንደማይቻል እያያችሁት ስለሆነ ራሳችሁን ለዚህ ለተቀደሰና ለማይቀረዉ የህልዉና ትግል ታዘጋጁ ዘንድ ግድ ነው ። ይሄን ለማድረግ ዝግጁ ያልሆነ ህዝብ ትርፉ እንግልት ፥ እስርና ሞት መሆኑን የአማራ ህዝብ በዚህ ሶስት የጦርነት አመታቶች ዉስጥ ያየዉና የተረዳው ሃቅ ነው፤ በማለት ከሰም ፪ኛ ኮር የቡልጋ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት መረጃውን አድርሶናል ።
"ንፁሃኖችን በማሰርና በማሰቃየት የሚቀጣጠል እንጂ የሚቆም ትግል የለም "
- መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
- ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
- አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ።
ለምርጫ አስፈፃሚ ስልጠና ለመስጠት የተላከው የስርዓቱ አሽከር በቁጥጥር ስር ውሏል።
➾➾➾➾➾⛰➾➾➾➾➾⛰➾➾
መጋቢት 11/2018 ዓ.ም
ከሽንዲ ወንበርማ በመነሳት ባህርዳር ላይ በበይነ መረብ ስልጠና በመውሰድ በሽርፍራፊ ጥቅም የአማራን ህዝብ ለድጋሜ 5 ዓመት ቀንበር ለመጫን ቢቡኝ ወረዳ ወረዳ ምርጫ አስፈፃሚወችን ለማሰልጠን የመጣው ወጣት #_ቸኮለ_ሙላቱ በንስሮቹ 2ዐ1ኛ ኮር 54ክፍለ ጦር ኬላ ላይ በቁጥር ስር ውሏል ።
ሌሎች ወጣቶችም በጥቅም ተታላቹህ የአማራን ህዝብ ስቃይና መከራ ለማራዘም ከስርዓቱ ጎን በመሆን ምርጫ እናስተባብራለን በማለት የተሰማራቹህ ወጣቶች ከድርጊታቹህ እንድትቆጠቡ እያለን በዚህ ድርጊት ተባባሪ የሆኑን የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑን በመገነዘብ ከድርጊታቹህ ተቆጠቡ በማለት የማስጠንቀቂያ መልክታችን እናስተላልፋለን።
የአፋብን ቴወድርስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሰበር ዜና
ዳግማዊ ቴዎድሮስ (5ተኛ ) ኮር ሬሽን ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ጠላት ላይ እር*ምጃ ወሰደ ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ኮር ዛሬ መጋቢት 11/2018 ዓ/ም በጠዋት ከማክሰኝት ከተማ ወደ ደጎማ ከተማ ሬሽን ጭኖ በሁለት ዙ 23 እና በዲሽቃ ታጅቦ ለማለፍ ሲሞክር ልዩ ቦታው ደጎላና ድንዛዝ ቀበሌ ላይ በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቴውድሮስ እና ጎንደር ብርጌድ እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ክፍለ ጦር በኩል ደግሞ ድል በር ብርጌድ የተወጣጡ አባላት በተሳተፋበት አውደ ውጊያ የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት ከፍተኛ ምት ደርሶበታል ።
በአውደ ውጊያው ተጨማሪ ሶስተኛ ዙ 23 የተሳተፈ ቢሆንም ከሞት ሳይተርፋ 17 የአገዛዙ አባላት ላይመ*ለሱ ሲ*ሸኙ 12 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ክፍኛ ቆስለዋል ።
በተመሳሳይ ዜና
ያለ ስራው ክብሩን አውርዶ ምርጫ አስፈፅማለሁ ብሎ ከአምባጊወርጊስ ከተማ ወደ ኮሶየ ቀበሌ ምርጫ ለማስፈፀም የሞከረው የአገዛዙ ተላላኪ ጥምር ሀይል በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቴውድሮስ ብርጌድ አባላት ድንገተኛ ምት ገጥሞት 3 አባላቱን አስመ*ትቶ እንደ ምርጫ ቁሳቁስ ተሸክሞ ወደ መጣበት እየፈረጠጠ ተመልሷል ።
በአጠቃላይ የዛሬው እርምጃ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5 ተኛ ኮር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ህዝባችን በምርጫ ሰበብ
የሚያጭበረብሩና የሚያወናብዱ የአገዛዙ ተላላኪዎ ላይ የማያዳ*ግም እር*ምጃ እንደምንወስድ ማሳያ ነው ።
በቀጠናው ሌሎች አውደ ውጊያዎች እንየተካሄዱ ይገኛሉ ዝርዝር መረጃዎችን ወደ በኃላ እናደርሳለን ።
አንድነት ሀይልም መዳህኒትም ነው !!!
©አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከፍተኛ አመራሮችና ማህበረሰብ 147ኛውን የኢድ አል-አድሃ በዓል በአንድነት አከበሩ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደቡብ አማራ ቀጠና የአሳምነው ዕዝ፣ 1447ኛውን የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓልን በዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር በሚገኙ ቀጠናዎች ከነዋሪው ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር በደመቀ ሁኔታ አክብሯል። በበዓሉ ላይ የአሳምነው ዕዝ ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ (ሽዋ) እና ምክትል መሪው አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ ጨምሮ የኮርና የክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። በዓሉ የአማራ ህዝብ የቆየ የሃይማኖት መከባበርና የፅናት መገለጫ በሆነ መልኩ ተከናውኗል።
እምነታችን ውበታችን ነው የዕዙ አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክት የፋኖ ትግል የሁሉንም አማራ እኩልነትና ማንነት የሚያስከብር መሆኑን አጽንኦት በመስጠት የአብይ አህመድ አስተዳደርና ተላላኪው ብአዴን አንድነታችንን ለመሸርሸርና በሃይማኖት ለመከፋፈል ቢሞክሩም፣ እኛ ግን የንጹህ አማራ ማንነትና የኢትዮጵያዊነት ኩራት ያለን በመሆናችን ሴራቸው አይሳካም ብለዋል። አክለውም አርበኛ መሪዎቻችን እኛ ዘመን የወለደን የሚኒልክ የበላይ የአሳምነውና የቴዎድሮስ አጥንት በውስጣችን የታተመብን ጀግኖች ነን። ክንዳችን ለጠላት የማይበገር አስተሳሰባችን ንጹህ የጥቁር ህዝቦች መፍለቂያ የሆነችው ምድራችን ቅድስት መሆኗን በተግባር እናረጋግጣለን።
በመጨረሻም በበዓሉ ላይ የተገኙት የሃይማኖት አባቶችና እናቶች ፋኖዎች ሃይማኖታዊ በዓላት ላይ መገኘታቸው ትልቅ ክብር መሆኑን ገልጸዋል። የባዓሉ ባለቤት ሙስሊሙ ማህበርሰብም ባስተላለፉት የምስጋና መልዕክት ፋኖዎች የዛሬው የአማራ የመኖር ነፃነት ባለቤቶችና የነገዋ ኢትዮጵያ ባለአደራዎች መሆናችሁን ስንገልፅ ሁሌም ቤሆን እኛ ከጎናቸው ለመቆም በነብዩ መሐመድ ስም ቃል እንገባለን አላህ አንድነታቸውን አጽንቶ ለድል እንዲያበቃቸሁ ጸሎትና ምኞታችን ነው። ሆኖም በዓሉ ከታናናሾች እስከ አዋቂዎች ድረስ በታላቅ ደስታና ምስጋና የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ይህም በደቡብ አማራ ቀጠና ያለውን ጠንካራ የህዝብና የፋኖ ትስስር ዳግም ያሳየ ነው በማለት ተጠናቋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው!!!!!!
መጋቢት 11 /07/2018 ዓ.ም
የማይቀረው የኢትዮጵያ ትንሳኤና ዘመኑ ያበቃለት አምባገነን ስርዓት
ሰሞኑን በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን የሰላም እጦት ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያዊያን ከሁለት ጎራ ተከፋፍለው ሲከራከሩ እያየሁ በጣም እያስገረሙኝ ነበር። ከምንም በላይ ደግሞ አብይ አህመድ United Arab Emirates ከኢራን የሚሰነዘርበትን የሚሳይል ጥቃት አወገዘ የሚል ዜና ስሰማ በእጅጉ አስገርሞኛል። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች የሚለው አባባል ምንኛ እውነት ነው! ከጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ የኢትዮጵያ ሁኔታ አሁን አሳሳቢ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ሀገሪቱ በታሪክ እንደ አሁን አይነት ፈተና ገጥሟት አያውቅም። አስተዳደራዊ መዋቅሩ በመበላሸቱ ሃገሪቱ በጦርነት እየታመሰች ሲሆን የኑሮ ውድነቱም ህዝቡን እያማረረው ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብ በማንኛውም ሁኔታ ተስፋ ቆርጦ ይገኛል።
የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ለምን እንደተጀመረ አቅጣጫ ከማስቀመጤ በፊት ስለ ኢትዮጵያ መከራና ስለሚሆነው ነገር ልነግራችሁ እፈልጋለሁ። አመናችሁም አላመናችሁም ወደዳችሁም አልወደዳችሁም ሊሆን ያለው ይሆን ዘንድ ግድ ነው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ፈተና ላይ ትገኛለች። ከዘመናት በፊት እናት አባቶቻችን ሲጠብቁት የነበረው ዘመን እነሆ አሁን ነው (መጽሐፈ ኪዳን፣ፍካሬ ኢየሱስ፣ራዕዬ ሲኖዳ፣ፊቅጦር፣ድርሳነ ዑራኤል ፣ራዕዬ ሳቤላ፣ መጽሐፈ ምስጢርና ትርጓሜ ወንጌልን ተመልከቱ::)
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ላይ እየተካሄደ ያለው ውጊያ በጥልቁ መንፈስ በሚመሩ የሰውን ልጅ የመከራ ቀንበሩን ባከበዱ አምባገነኖችና የሰውን ልጅ ፍጹም ሰላም ወይንም ትንሳኤ ብለን የምንጠራውን ለማጎናጸፍ በሚጥሩ በእግዚአብሔር በተመረጡ መካከል ነው።
ኢትዮጵያ አሁን ልክ በእሳት ተፈትኖ ነጥሮ እንደሚወጣ ወርቅ ትልቅ ፈተና ውስጥ ናት። ከኮሮና ቫይረስ መምጣት በፊት ጀምሮ ይህ ህዝብ እንዲነቃ ለብዙ ዓመታት ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ:: ምን መልእክት ሳስተላልፍ እንደነበር የሰሜን ወሎ በተለይም ደግሞ የላስታና የግዳን ህዝብ ያውቃል። ነገር ግን ይህ ትውልድ አመጸኛ ነው ከመንቀፍና ስም ከመስጠት የዘለለ ምን ምን አያደርግም። በዚህ ሁኔታ ስለሚፈጸመውና ስለሚሆነው ነገር ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልገው በርካታ እውነተኛ አባቶች ሰማይ ስሚ ምድርም አድምጭ እያሉ ተናግረዋል። ግን የሚሰማ ትውልድ የለም ሁሉ ነቃፊ ሁሉም ተሳዳቢ ነው። እኛ ተናግረናል ስላልሰማችሁን እሳት እየበላችሁ ነው ወደፊትም ካልሰማችሁ የመከራችሁ ቀንበር ይከብዳል።
ከዚህ አምባገነን ስርዓት ጋር ሆናችሁ የሰው ልጅ መከራ የምታራዝሙ ሁሉ ዋጋ ትከፍላላችሁ። ከህዝብ ጀምሮ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችና የመንግስት ባለስልጣናት ሁላችሁም ነፍሳችሁን እና ስጋችሁን የምታድኑበት ሰዓት አሁን ነው። የብልጽግና ስርዓት ይዟችሁ ይጠፋል። በተለይ ደግሞ አገልጋይ አባቶች ንቁ! ጸልዩ፣ መጽሐፍትን አገላብጣችሁ መርምሩ ፣ ስለ ጊዜውም በደንብ ለመረዳት ልቦናችሁን ክፈቱ፣ ነቃፊዎች ብቻም አትሁኑ ለሆዳችሁም አትሙቱ፣ አድርባይም አትሁኑ! ከምድራዊ ንጉስ ይልቅ ሰማያዊውን ንጉስ ፍሩ። አባቶች ይህንን አምባገነን ስርዓት አንድ ሆናችሁ ማውገዝ አለባችሁ:: ቀደምት አባቶቻችን ነገስታትን የማይፈሩ ለእግዚአብሔር ቃልና ለሚጠብቋቸው ምዕመናን የሚኖሩ ነበሩ:: አሁን አሁን የምናያቸው አባቶች በጣም ያሳዝናሉ:: አባቶች ሆይ ህዝብን (ኢትዮጵያን) ወክላችሁ ይህንን አምባገነን ስርዓት መቃወም አለባችሁ:: ይህን ካላደርጋችሁ ዋጋ ትከፍላላችሁ::
ስለሆነም ከመንግስት ጎን ሆነው የሚጨፈጭፉ ማንኛቸውም ኃይላትና በማንኛውም መንገድ የሚተባበሩ ሁሉ ፍጻሜያቸው የከፋ ነው የሚሆነው። የእግዚአብሔር የፍትህ ሰይፍ ወርዳለች። ኢትዮጵያ እንደወደቀች አትቀርም ትነሳለች። ትንሣኤዋ ተረት ተረት አይደለም በእውነተኛ ልጆቿ በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅርብ እውን ይሆናል። ሁላችሁም ወደዳችሁም አልወደዳችሁም የማይቀር ነገር ነው። በዓለም ሁሉ የምትሰሙት የጦርነት ጉሰማ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ መቅረብ አመላካች ናቸው። ከኢትዮጵያ ትንሳኤ በኋላ የቀሩት ሃገራት ይናወጻሉ። ከዚያም ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል የሚባለው ትንቢት ይፈጸማል ማለት ነው። "መልእክተኞችን በባሕር ላይ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣኖች መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥ ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ወደ ሆነ ወገን፥ ወደሚሰፍርና ወደሚረግጥ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።በዓለም የምትኖሩ ሁሉና በምድር የምትቀመጡ ሆይ፥ ምልክት በተራሮች ላይ በተነሣ ጊዜ እዩ፤ መለከትም በተነፋ ጊዜ ስሙ።" ትንቢተ ኢሳይያስ ፲፰፥፪
ኢትዮጵያ ከጨለማ ወደ ብርሃን ስትሸጋገር ሌሎች ሀገራት መከራቸው ይከብዳል:: ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ጽኑ መናወጥ ምክንያት በርካታ ህዝቦች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ለመጠለል ይለምናሉ። ይህ ከመፈጸሙ በፊት ግን የኢትዮጵያ ትንሳኤ ይጀምራል። ኢትዮጵያ የመከራው ቀን መሸሸጊያ ናት የሚባለው ለዚህ ነው:: ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ተራ አድርጋችሁ የምታስቡ ይህ ምስጢር ሊሰወርባችሁ ተረትም ሊመስላችሁ እንደሚችል አውቃለሁ! ግን ሊሆን ግድ ነው::
ስለዚህ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማምጣት ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይኖርብናል። ከንሰሃ እንዲሁም ከጸሎት ጀምሮ ሀገርንና ሃይማኖትን ለማስጠበቅ ከሚደረጉ ማንኛውም መልካም የሆኑ እንቅስቃሴዎች ልንሳተፍ ግድ ይለናል። ኢትዮጵያውያን ንቁ ንቁ ንቁ!
ተንሳኤው አይቀርም ግድ ነው፤ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!
ቆሞስ አባ ጳውሊ ከግንባር
ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮችና በዱር በገደሉ አማራንና ኢትዮጵያን ነፃ ለማዉጣት እየታገላቹህ የምትገኙ ሙስሊም የፋኖ አመራሮችና አባለት እንዲም ቤተሰቦቻቹህ እንኳን ለ1447ኛዉ የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም የፍቅር የአንድነትና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
መጋቢት 10,2018ዓ.ም
ፍኖተ አማራ ሚዲያ እዚሁ ከግንባር ሁነን ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለመላው ህዝባችን ተደራሽ በማድርግ እየሰራን እንገኛለን የቴሌግራም ገፃችንን ይወዳጁ
👇
+1
4 (አራት) ወንድም አማቾች ዳግማዊ በላይ ዘለቀ ማሰልጠኛ ልዩ ኮማንዶ ስልጠና በልዩ ሁኔታ እና ብቃት ወስደው ተመረቁ።
መጋቢት 10/2018 ዓ.ም
1ኛ.አበባው አሰፋ
2ኛ. መኳንት አሰፋ
3ኛ.ይታያል አሰፋ
4ኛ.መልኩ አሰፋ የተባሉ የእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ ተወላጆች የአብይ አህመድ አገዛዙ ስረዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ዝርፊያ፣ ግፍ እና መከራ ያስቆጫቸው አራት ወንድም አማቾች አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ልዩ ኮማንዶ ለተከታታይ 6(ስድስት) ወራት ስልጠና በመውሰድ የአገዛዙስ ስረዓት ለመገርሰስ በደማቅ ሁኔታ ተመረቀው ወደ ትግሉ ተቀላቅለዋል።
የአብይ አህመድ አገዛዝ በጭካኔ ተግባሩ በሆዱ ያደር ምሊሻ፣ አድማ ብተና፣ የብልጽግና አመራርን መንገድ እንዲመሩ በማድርግ የአማራን ህዝብ ከምድር ገፅ ለማጥፋት በመስራቱ ምክንያት እኛ ወደዚህ ትግል ለመግባት ተገደናል ብለዋል።
የ64ኛ ክፍለ ጦር ልዩ ኮማንዶ አራት ወንድም አማቾች ተመራቂዎች ወደ ፋኖ ለመግባት የተነሳሱበት ተጨማሪ ምክንያታችን የአማራ ህዝብ በአማራነቱ ተለይቶ በአብይ አህመድ አገዛዝ በተለያዩ ቦታዎች በጅምላ መገደሉ እና አሁን ላይ ስረዓቱ በሰፈሬቸው፣ ቤታቸው ንፁሀን አማራን በጅምላ እየርሸነ መምጣቱ ወደዚህ የትጥቅ ትግል ለመቀላቀል ምክንያታችን ነው ብለዋል።
ጀግኖቹ ወንድም አማቾች የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳው የአብይ አህመድ አገዛዝ የጥፋት ቡድን ለመገርሰስ በታማኝነት እና በቅንነነት ድርጅቱ የሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት እንደሚወጡ ተናገሩ፡፡
መጋቢት 10/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ስራችንን እየሰራን ነው ስራችሁን ስሩ
💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
ይህ እውነተኛ የፍኖተ አማራ ሚዲያ፣ ፍኖተ አማራ ሚዲያ ግንባር ላይ ያሉ መረጃወችን ከግንባር ሁነን ከአፋብን ወንድሞቸና ጓዶቸ ጋር መረጃዎች በብርሃን ፍጥነት እንሰራለን እንገኛለን ከታች በአለው የቴሌግራም ሊንክ ይወዳጁን!!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች እንኳን ለኢድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል። በተለይም ስለ ሕዝባችሁ ነፃነት ስትሉ ለነፍሳችሁ ሳትሳሱ በዱር በገደሉ እየተዋደቃችሁ ከምትከፍሉት መራር ዋጋ ጎን ለጎን ይህን ታላቁን የረመዳን ወር በፆምና በጸሎት ያሳለፋችሁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራሮች እና አባላት እንዲሁም ደጋፊዎቻችን ከፈጣሪ ዘንድ እዝነትና በረከት ለሚታደልበት የኢድ አልፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ።
የአማራ ሕዝብ ላለፉት በርካታ አሥርት ዓመታት ከደረሰበትና አሁንም እየተፈጸመበት ካለው መንግሥት-መር የጅምላ እልቂትና ጭፍጨፋ እንዲሁም የሀብትና ንብረት ውድመት ውስጥ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዩ ወገናችን ከፊት ተሰላፊ ነው።
ወገኖቻችን በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጭ አማራ-ጠል እሳቤ ባነገቡ ቡድኖችና የጸረ-አማራነት ትርክትን ሥጋ አልብሶ በሚንቀሳቀሰው አገዛዝ በሚፈጸምባቸው ጭፍጨፋ በርካቶች ሕይወታቸው ተቀጥፏል፣ ሀብትና ንብረታቸው ወድሞ ለከባድ ማኅበራዊ ምስቅልቅል ተዳርገዋል። በዚህ ጸረ-አማራ እሳቤ በሚመራው ሥርዓት የሚፈጸመው ሁሉን አቀፍ ጥቃት ተባብሶ በመቀጠሉ ዛሬም በሞት አፋፍ የሚገኙ ወገኖቻችን እልፍ ናቸው።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ከተፈጸመባቸው ጭፍጨፋ እንደ እድል ተርፈው፡ ሀብትና ንብረታቸው ወድሞ ከቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ፡ ከሞት ያልተናነሰ ኑሮን እያሳለፉ ይገኛሉ። ወገናችን በዚህ መከራ ውስጥ ሆኖም ታላቁን የረመዳን ወር በፆምና በዱዓ በማሳለፍ የጽናት ተምሳሌትነቱን እያሳየ ነው።
በመከራ ውስጥ ሆኖም ለፈጣሪው መገዛትን፣ ጽናትን፣ አሸናፊነትን፣ ትዕግሥትንና ጥበበኝነትን ከወለደው ሕዝብ የወረሰው የአማራ ፋኖ፡ በአማራ ሕዝብ ላይ የተጫነውን የመከራ ቀንበር ይሰብር ዘንድ ሐቅን ከነፍጥ ጋር አንግቦ በድሉ ዋዜማ ላይ ይገኛል።
የአማራ ፋኖ እያደረገ ባለው ትግል ሞታቸውን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን ታድጎ ሕልውናቸውን ማስከበር፣ ለተፈፀመው እልቂትና በደል ፍትሕና ርትዕ ማስፈን፣ እንዲሁም ወገኖቻችን በገዛ አገራቸው በነፃነት ተንቀሳቅሰው ሀብትና ንብረት ማፍራት የሚችሉበትን ሥርዓት ማንበር፡ የትግላችን ቀዳሚ ዓላማና ከምንም በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ግባችን ነው።
ለዚህ ታላቅ ዓላማ ስኬት ሕዝባችን፡ በተለይም ሕዝበ ሙስሊሙ፡ ትግሉን በባለቤትነት ከመምራት፣ ከመታገል ጀምሮ ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ፣ የሐሳብና የመረጃ እገዛ በማድረግ እንዲሁም በዱዓ በመርዳት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ቅዱስ ቁርኣን "እናንተ ያመናችሁ ሆይ፡ በትዕግሥትና በሶላት ታገዙ፡ አላህ በእርግጥ ከታጋሾች ጋር ነውና" ("ያ አዩሀለዚነ አመኑ ስተዒኑ ቢሷብሪ ወሷላህ፣ ኢን-አላሀ መዐ-ሷቢሪን") ሲል ያስተምራል።
በእርግጥም ሐቅን ከነፍጥ ጋር ያነገበው የሕልውና ትግላችን፣ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ንቁ ተሳትፎ ዛሬ በድሉ አጥቢያ ላይ ደርሷል።
ነገ የህልውናን ትግላችን በነፃነታችን ሲረጋገጥ በዓሉን በሚመጥን ሁኔታ በአደባባዮቻችን እስከምናከብር በዚህ መከራ ውስጥ ሁናችሁ እያከበራችሁ ያላችሁ ህዝባችን እና ሰራዊታችን ድርጅታችን አፋብን መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
በድጋሚ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ኢድ-ሙባረክ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ!
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በሉማሜ ከተማ ከሌሊቱ 5:30 በሰራው ኦፕሬሽን ምርጫን ተከትሎ አፋብን ያወረደውን መመሪያ ጥሶ የተገኘው አቶ ደረጀ ያለው በቁጥጥር ስር ውሏል።
መጋቢት 10/2018ዓ.ም
=================================
አቶ ደረጀ ያለው የሉማሜ ከተማ መሰረተ ልማትና የከተማ አገልግሎ አሰጣጥ ቡድን መሪ ኃላፊ እንዲሁም የ02 ቀበሌ ም/ አፈ ጉባኤ ህዝብን አስገድዶ ቤት ለቤት ምርጫ ካርድ ሲያስወጣ የነበረው ታማኝ ካድሪ በ206 ኮር አዳኝ ቡድን በሉማሜ ከተማ ከሌሊቱ 5:30 ባደረገው ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውሏል።
በአማራ ህዝብ ላይ ጨቃኝ ሰራዊት በማሰማራትና ጅምላ ጨራሽ መሳሪያን በመጠቀም ግልፅ የዘር ፍጅት እየፈፀመ የሚገኘውን የብልፅግና ስርዓት እድሜ ለማራዘም በማቀድ በተያያዘው አመት ምርጫን አጀንዳ ያደረጉ ካድሬዎችንና የአጀንዳውን አጃቢዎች እርምጃ እንድንወስድ በድርጅታችን አፋብን በተሰጠ መመሪያ መሰረት 206ኛ ኮር ግዳጁን በመቀበል በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።
ከትናት በስተያ ሌሊት 5:30 በሉማሜ ከተማ በተወሰደ ኦፕሬሽን ከወረዳ ካድሬዎች ፊት በመሰለፍ በሉማሜ ከተማ 02 ቀበሌ ቤት ለቤት እየዞረ ህዝብ እያንገላታ በማስገደድ ካርድ ሲያስወጣ የነበረውና ካርድ አናወጣም ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሲያስር የነበረው አቶ ደረጀ ያለው በ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በቁጥጥር ስር ውሏል።
ይህን ተከትሎ የድርጅታችን መመሪያ ይፈፀም ዘንድ ኮሩ ግዳጁን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በዚህ እኩይ ተግባር የተሰለፋችሁ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ እናሳስባለን።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ዋሲል ክፍለ ጦር ጃማ ደጎሎ ከተማ በመግባት የተሳካ ግዳጅ በመፈፀም ድል አስመዘገበ‼️
ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር መጋቢት 8/2018 ዓ.ም ቀን 10:00 ወደ ጃማ ደጎሎ ከተማ በሁለት አቅጣጫ የጠላትን ሃይል ጥሶ በመግባት ከአስር በላይ ጠላት በመደምሰስና ከአስራ አንድ በላይ በማቁሰል የተሳካ ግዳጅ ፈፅሞ ድል አስመዝግቧል::
የፋሽስስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጥምር ጦር የዞንና የወረዳ ከተሞች ላይ ኮንክሪት ምሽግ ሰርቶ የተቀመጠ ሲሆን ጃማ ደጎሎ ከተማ የመሸገውን ግፈኛ ሃይል ንስሮቹ በሁለት አቅጣጫ ማጥቃት በማድረግና ጥሶ በመግባት ያሰቡትን የከተማ ግዳጅና ግብ አሳክተው ድል አስመዝግበዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 10/2018 ዓ.ም
10/ዐ7/2018 ዓ.ም
+2
ተጠናክሮ በቀጠለው የብልፅግናው ሰራዊት ፍልሰት ዛሬም በጠዋቱ ጀግናው የአማራ ፋኖ አፄ አምደ ፅዮን ኮርን መቀላቀላቸውን ኮሩ አስታወቀ።
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
መጋቢት 10/2018ዓ.ም
በውድቀት ዋዜማው ላይ ለሚገኘው ለፋሽስቱ ስርዓት ዕድሜ ማራዘሚያ መጠቀሚያ አንሆንም በሚል በርካታ የብልፅግናው ወታደሮች በየቀኑ ፋኖን እየተቀላቀሉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም መጋቢት 10 ቀን 2018ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በአፄ አምደ ፅዮን ኮር ስር የሚገኙ ክፍለጦሮችን ተቀላቅለዋል።
ከፊቼ ከተማ የተነሱ አራት (4) የ8ኛ ዕዝ የ12ኛ ክፍለጦር የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው የኮሩ አካል የሆነውን የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦርን ሲቀላቀሉ፣ መነሻየውን ከደራ ጉንዶመስቀል ከተማ ያደረገው የብልፅግናው 6ኛ ዕዝ 15ኛ ክፍለጦር የ5ኛ ሻለቃ መረጃና እና ደህንነት ክፍል ኃላፊው የመከላከያ ሰራዊት አመራሩ የተለያዩ የአገዛዙን ምስጥራዊ ሰነዶች እና ከነሙሉ ትጥቁ በመያዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦርን መቀላቀላቸውን ኮሩ በግንባር መረጃው አስተውቋል።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!
ድል ለአፋብን!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል
መጋቢት 10 / 2018 ዓ.ም
የብልፅግና ሰራዊት እየፈረሰ የፋኖን ትግል መቀላቀሉን ቀጥሏል‼️
ከመጋቢት01- 10/2018 ዓ/ም ብቻ ከአረመኔዉ ብልፅግና ስዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት በመክዳት የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮርን የተቀላቀሉ የሰራዊት አባላት:-
1ኛ.ወንድምሰዉ ብርሌዉ= ከጃዊ
2ኛ.ዘለቀ ገበየሁ= ከጃዊ
3ኛ.ወንድም በላይ ከደቅ
4ኛ.ግዛቸዉ ወርቄ ከደቅ
5ኛ.10 አለቃ ቢኒያም አስማማው ጋንታ መሪ
6ኛ.10 አለቃ ባንተጊዜ አለማየሁ ቲም መሪ
7ኛ.10 አለቃ እንዳልክ ጋንታ መሪ
8ኛ.እስራኤል እየሱስ አድማ ብ/አባል
29ኛ.ሞገስ እሸቱ አድማ ብ/አባል
10ኛ.አበበ መልካሙ አድማ ብ/አባል
11ኛ.ሞገስ ክንዱ አድማ ብ/አባል
12ኛ.ም/አስር ዓለቃ ሚካኤሉ
13ኛ. ጌታሰው ግዛ.
14ኛ.ምስጋናው በለጠ
15.ተፈሪ አለኸኝ ሚሊሻ
16ኛ.ሳጅን ሀይማኖት አቤ =ከመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ የሸፍት አዛዥ የነበረ
17ኛ. አምሳ አለቃ ሙሉቀን አማረ =የ95ኛ ክ/ጦር ሻ/መሪ
18ኛ.ዝግጁ አሸብር= ከ95ኛ ክ/ጦር ፐርሰኔል
19ኛ. አትንኩት ጌቱ =ከ95ኛ ክ/ጦር
20ኛ.አስቻለ ገድፍ= ከዳንጉር የፀጥታ ሀይል
ሁሉም የሠራዊቱ አባላት አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመው ያለውን ዘር ማጥፋት በቅጡ በመገንዘብ ሙሉ ትጥቃቸውንና አንዳንዶቹ ደግሞ ከ2-3 መሳሪያ ደርበው በመያዝ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል:: በገቡበት ቀጠና የክፍለ ጦር አመራሮችና የኮር አመራሮች እንዲሁም በአባላት አቀባበል ተድርጎላቸዋል።
አዲስ ተውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ሕ/ግንኙነት
