ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد3 606
المشتركون
+6624 ساعات
+5877 أيام
+1 04130 أيام
أرشيف المشاركات
🔴የማስጠንቀቂያ መልዕክት ለሚመለከተው ሁሉ!
እንደሚታወቀው ፋሽስታዊው የብልጽግና ሥርዓት መንበረ ሥልጣኑን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ ሥልጣኑን ለረከሰና ለግል ዓላማ ማስፈጸሚያ በማድረግ የተከበረውንና ሀገር ሰሪ የሆነውን የአማራን ሕዝብ ለማጥፋትና ስም አጠራሩን ከታሪክ መዝገብ ላይ ለመፋቅ እየተጠቀመበት ይገኛል። በዚህ እኩይ ተግባሩም የተከበረውን የሕዝብ ሥልጣን ለራሱ ለሕዝቡ መጥፊያ በማድረግ በዓለማችን ቀዳሚው ሥርዓት ሳያደርገው አይቀርም።
በዚህ ሰይጣናዊ ተግባሩ ክፉኛ ካማረረው ዘንድ ከብዙኃን ኢትዮጵያውያን ዜጎች ልቡና ውስጥ የተተፋው ይህ ሥርዓት "ምርጫ" በሚል የማጭበርበሪያ ካርድ በድጋሚ የሥልጣን ዘመኑን በማራዘም ወገቡን ታጥቆ ለያዘው አማራን በጅምላ የመፍጀት ተግባር ሕጋዊ ከለላና እውቅና ለማግኘት ከላይ ታች እያለ መሆኑን እየተመለከነው ነው።
ይህ ርካሽ ተግባሩ መሬት ድረስ ወርዶ ተግባራዊነቱ ይረጋገጥ ዘንድ ደግሞ "ክብራቸውን በነውራቸው ሆዳቸው አምላካቸው" የሆኑ ሁሉን ነገር በገንዘብ ማያ የሚያዩ ሆድ አደር አማራዎች የትወናውን ስራ ለመስራት በእጅጉ እየተዘጋጁ መሆኑን ሰምተን ታዝበናል።
ለአብነት ያህልም በደብረ ማርቆስና ደብረ ኤልያስ ከተሞች ውስጥ የተወሸቀው ሆዳም የብልጽግና ስብስብ መምሕራንን፣የመንግስት ሰራተኞችን፣ ወጣቶችንና አስቀድሞ በጥቃቅንና አነስተኛ ያደራጃቸውን ወጣቶች በመሰብሰብ የምርጫ ሂደቱን ያስፈጽሙለት ዘንድ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ደርሰንበታል። ይህ ተግባርም አገዛዙ የአማራን ለመጨፍጨፍ ተጨማሪ አምስት ዓመት እንዲኖረው የሚያስችለውን ሕጋዊ ማረጋገጫ ለመያዝ የሚያደርገው ሩጫ መሆኑን ልብ ይሏል።
በመሆኑም አሁን ላይ በምርጫም ሆነ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚመጣ የአማራ ነጻነት አለመኖሩ እየታወቀ ለዚህ አውዳሚ አገዛዝ ሎሌ በመሆን የዚህ ጨዋታ ተዋናይ ለመሆን አውቃችሁም ሆነ ባለማወቅ እየተረባረባችሁ የምትገኙ ከላይ የተጠቀሳችሁ አካላት ይህ ተግባር በድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ፈጽሞ የተወገዘና እርምጃ የሚያስወስድ መሆኑን አውቃችሁ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ስንል እያሳሰብን ይህን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ የምንወስድ መሆኑንና በዚህ ተግባር ስትሳተፉ ለሚደርስባችሁ የትኛውም ጥቃት ኃላፊነቱን የምትወስዱ መሆኑን እናሳስባለን።
ድል ለአማራ ፋኖ!
የአፋብን 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር
መጋቢት 12/2018 ዓ/ም
የፓራ ኮማንዶ አባላቱ የምረት ጥሪውን በመጠቀም ክላሽ ትጥቅ እና ተተኳሽ በመያዝ ወደ ፋኖ ተቀላቀሉ ።
➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽
መጋቢት 12/2018 ዓ.ም
በዛሬው እለትም ከሸበል በረንታ እና ሰዴ ወረዳ መሽጎ የነበረው ሀይል ስርዓቱ በአማራ ላይ እየፈፀመ ያለውን ድርጊት በመቃወም በርካቶቹ ወደ 201ኛ ኮር 64ኛ እና 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
1ኛ ታምሩ እማኝ.. 6ኛ ዕዝ 605ኛ ኮር ፐርሰኔል የነበረ
2ኛ.ይሁኔ ውዱ.. ሸበል በረንታ ወረጎ እና አካባቢው
3ኛ.እሸቱ አለማየሁ ...እናርጅ እናውጋ አብራራው
4ኛ.ሙክታር አህመድ..25ኛ ክ/ጦር ከሰዴ ወረዳ
5ኛ. ሁነኛው አጥናፉ ...ሰዴ ወረዳ ፓራ ኮማንዶ በመያዝ ከደብረወርቅ እና ሸበል በረንታ የአገዛዙን አፀያፊ ስራ በመቃወም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የተቀላቀሉ ሲሆን በአመሪሩም አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አሁንም አልረፈደም ሁሉም ከዚህ አረመኔያዊ ከስርአቱ ተቋም በመውጣት ወደ ቀድሞ ማንነታቹህ ተመለሱ
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+3
74ኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድራቸው ሶስት ወረዳወች ጊዜያዊ መንግስቱ ጥልቅ ግምገማወች ተከሄ።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
መጋቢት 11/2018 ዓ.ም
የ201ኛ ኮር እና የ74ኛ ክ/ጦር አመራሮች እንዲሁም የሶስቱ ወረዳወች የጎንቻ ሲሶ እነሴ፣እናርጅ እናውጋ እና እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር አካላት በተገኙበት ለተከታታይ 7 ቀናት ጥልቅ ግምገማና ውይይት ተካሂዷል።
ኮሩ እና ክ/ጦሩ ባካሄደው ጥልቅ የግምገማ ሃሳብ መሰረትም በሶሰቱም ወረዳዎች ባለፉት አራት ወራት ስለተከናወኑ አበይት ግባራት ውይይት በማካሄድ የአደረጃጀት ማሻሻያ በማድረግ የቀጠይ የስራ ተልኮወችን በመስጠት ውይይቱ ተፈፅሟል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+2
መብረቅ ክፍለ ጦር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ምልምል ፋኖዎች አስመረቀ!
ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ምልምል ፋኖዎች አስመረቀ::
ከአፋብን ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ በወረደላቸው አቅጣጫ መሰረት ኮርና ክፍለ ጦሮች ምልመላ በማካሄድና ስልጠና በመስጠት ራሳቸውን በሰው ሃይል በማደራጀትና በማጠናከር ላይ ይገኛሉ::
በዚህም ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር የመለመላቸውን ወጣቶች ለወራቶች ስልጠና በመስጠት አስመርቋል:: በቀጣይም ስልጠናው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አመራሮች ገልፀዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 11/2018 ዓ.ም
በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ፥ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ-አልፈጥር በአል አደረሳችሁ የሚል መልእክቴን እያስተላለፍኩ፥ በአሉ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።
ኢድ ሙባረክ!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር
ፍቅር ያሸንፋል!!!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
+3
ቀን 11/07/18
ከትግሉ ሜዳ
🌿🌿🌿◌◎🌿🌿🌿
ጎንደር ጠቅላይ ግዛት 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር በስሩ ካሉ ክፍለ ጦር አመራሮች ጋር ውይይት አድርገናል።
ኮሩ ሪፎርም ከሰራ በኃላ ከትግሉ ጎን ለጎን
● ያለፉትን የትግል እንቅስቃሲያችን መገምገም
● የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ማስቀመጥ
➸ ከተለመዷዊ የአተጋገል ስልት በመውጣት ተቋማዊ አተጋገልን ተግባራዊ ማድረግ ለትግሉ ትልቅ ሚና ይኖረዋል‼️
ድል ለአማራ ፋኖ
የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል
+3
የጠላት ኃይል መፍረሱን ቀጥሏል ! ኢድ ሙባረክ ብለናል!!
አቤ ጉበኛ ሻለቃ ማስከዳቱን ቀጥሏል ።
በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር አቤ ጉበኛ ሻለቃ ተቀላቀለዋል። ከተቀላቀሉት መካከለም ፦
1ኛ.10 አለቃ ቢኒያም አስማማው ጋንታ መሪ
2ኛ.10 አለቃ ባንተጊዜ አለማየሁ ቲም መሪ
3ኛ.10 አለቃ እንዳልክ ጋንታ መሪ
99ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ 1ኛ ሻምበል አባል ናቸው ። የክፍለ ጦሩ ም/ል ጦር አዛዥ ኮማንዶ አስፋው በክብር ተቀበሎታል ።
በርቱ እንበርታ !
+3
አፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ለተከታታይ 6 ወራት ያሰለጠናቸውን የልዩ ግዳጅ ኮማንዶዎችን አስመረቀ።
105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ሻለቃ ለተከታታይ 6 ወራት ያሰለጠናቸዉን ሰልጣኞች የቲዎድሮስ እዝ ም/ፓለቲካ ዘርፍ አርበኛ ግሩም ምሳሌ፣የቲዎድሮስ ዕዝ ኦርዲናንስ ሃላፊ 10 ዓለቃ ታደሰ ስመኝ እንዲሁም የ55ተኛ ክ/ጦር አመራሮች የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ሻለቃ አመራሮች የሰሜን አቸፈር ወረዳ የጊዜዊ መንግስት አሰተዳደር አመራሮች የአካባቢዉ ማህበረሰቦች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ በቀን 11/07/2018 ዓ/ም ተመርቀዋል።
+2
አፋብን ምንሊክ ዕዝ 101ኛ ኮር ፖለቲካ ዘርፋ ሀላፊ አርበኛ መሀመድ መጎስ እና የኮሩ ዘመቻ መሪ አርበኛ እንድሪስ ጉደሌ እንዲሁም ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግኑኝነት አርበኛ ሃብታሙ የሱፍ እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ መሪዎቻችን
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በንፁሀን ሰዎች ላይ እስርና እንግልት እየፈፀመ ይገኛል ።
ዛሬም ከትላንት ስህተቱ መማር ያልቻለው ለፖለቲካዊ ጥያቄዎች ፖለቲካዊ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ጦርነትን እና ንፁሀኖችን ማሰርና ማንገላታት ብቸኛው መፍተሄ አድርጎት የቀጠለው የብልግናው አገዛዝ እጅግ ኢ-ሰበዓዊ ድርጊቶችን እየፈፀመ እንደሚገኝ ተገለፀ ።
በወቅቱ ከፍተኛ እብሪት ዉሰጥ እና የተሳሳተ ግምገማ ዉስጥ የነበሩት የብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች እና የጦር አዛዦች በ15 ቀኑ ዉስጥ አማራን አይደለም ትጥቁን ቀበቶዉን እናስፈታዋለን ብለዉ ፎክረዉ ቢገቡም በተገላቢጦሽ አማራዉ አይቶት የማያዉቀዉን የዘመናዊ ትጥቅ ባለቤት አድርገዉት ማረፋቸዉ የአደባባይ ሀቅ መሆኑ ይታወቃል ።
በቡልጋ ቀጠና አገዛዙ በተደጋጋሚ ኔትወርክ በማጥፋትና በሌሊት ኦፕሬሽኖችን በማድረግ ከኪሳራ ዉጪ ምንም አይነት ለዉጥ ማምጣት ያልቻለዉ የአብይ አህመድ ሰራዊትና ካድሬ፤ ከመጋቢት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀጠለው፤ በበረኸት ወረዳ መተህብላ ከተማ ላይ የፋኖ ቤተሰቦች ናችሁ በማለት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ አቅመ ደካሞች ፥ ሴቶችና ህፃናት ለእስርና እንግልት እየዳረጉ እንደሚገኝ የውስጥ አርበኞቻችን መረጃውን አድርሰውናል ።
ንፁሀንን ማሰርና ማንገላታት የአምባገነኖች መገለጫ ቢሆንም ዉድቀትን ከማፋጠን በቀር የሚቀይረዉ አንዳች ለዉጥ እንደሌለ ታሪኮች ምስክሮች ናቸው ። በህዝባችን እየተፈፀመ ያለዉ ግፍና በደል ትግላችንን በከፍተኛ ወኔ እና ተነሳሽነት እንድናስቀጥለዉ ከማድረግ በቀር የሚያስቆመን እና አንገት የሚያስደፋን እንዳልሆነ በዚህ ሶሰት አመት ዉስጥ ያደረግነዉ ተጋድሎ ምስክር ነው ።
ለመላዉ የከተማችን ማህበረሰቦች በሙሉ ይሄን ፀረ አማራ እና ፋሽስታዊ ስርዓት ከስር መሰረቱ ነቅለን መጣል እስካልቻልን ድረስ የነፃነት አየር መተንፈስ እንደማይቻል እያያችሁት ስለሆነ ራሳችሁን ለዚህ ለተቀደሰና ለማይቀረዉ የህልዉና ትግል ታዘጋጁ ዘንድ ግድ ነው ። ይሄን ለማድረግ ዝግጁ ያልሆነ ህዝብ ትርፉ እንግልት ፥ እስርና ሞት መሆኑን የአማራ ህዝብ በዚህ ሶስት የጦርነት አመታቶች ዉስጥ ያየዉና የተረዳው ሃቅ ነው፤ በማለት ከሰም ፪ኛ ኮር የቡልጋ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት መረጃውን አድርሶናል ።
"ንፁሃኖችን በማሰርና በማሰቃየት የሚቀጣጠል እንጂ የሚቆም ትግል የለም "
- መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
- ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
- አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ።
ለምርጫ አስፈፃሚ ስልጠና ለመስጠት የተላከው የስርዓቱ አሽከር በቁጥጥር ስር ውሏል።
➾➾➾➾➾⛰➾➾➾➾➾⛰➾➾
መጋቢት 11/2018 ዓ.ም
ከሽንዲ ወንበርማ በመነሳት ባህርዳር ላይ በበይነ መረብ ስልጠና በመውሰድ በሽርፍራፊ ጥቅም የአማራን ህዝብ ለድጋሜ 5 ዓመት ቀንበር ለመጫን ቢቡኝ ወረዳ ወረዳ ምርጫ አስፈፃሚወችን ለማሰልጠን የመጣው ወጣት #_ቸኮለ_ሙላቱ በንስሮቹ 2ዐ1ኛ ኮር 54ክፍለ ጦር ኬላ ላይ በቁጥር ስር ውሏል ።
ሌሎች ወጣቶችም በጥቅም ተታላቹህ የአማራን ህዝብ ስቃይና መከራ ለማራዘም ከስርዓቱ ጎን በመሆን ምርጫ እናስተባብራለን በማለት የተሰማራቹህ ወጣቶች ከድርጊታቹህ እንድትቆጠቡ እያለን በዚህ ድርጊት ተባባሪ የሆኑን የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑን በመገነዘብ ከድርጊታቹህ ተቆጠቡ በማለት የማስጠንቀቂያ መልክታችን እናስተላልፋለን።
የአፋብን ቴወድርስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሰበር ዜና
ዳግማዊ ቴዎድሮስ (5ተኛ ) ኮር ሬሽን ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ጠላት ላይ እር*ምጃ ወሰደ ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ኮር ዛሬ መጋቢት 11/2018 ዓ/ም በጠዋት ከማክሰኝት ከተማ ወደ ደጎማ ከተማ ሬሽን ጭኖ በሁለት ዙ 23 እና በዲሽቃ ታጅቦ ለማለፍ ሲሞክር ልዩ ቦታው ደጎላና ድንዛዝ ቀበሌ ላይ በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቴውድሮስ እና ጎንደር ብርጌድ እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ክፍለ ጦር በኩል ደግሞ ድል በር ብርጌድ የተወጣጡ አባላት በተሳተፋበት አውደ ውጊያ የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት ከፍተኛ ምት ደርሶበታል ።
በአውደ ውጊያው ተጨማሪ ሶስተኛ ዙ 23 የተሳተፈ ቢሆንም ከሞት ሳይተርፋ 17 የአገዛዙ አባላት ላይመ*ለሱ ሲ*ሸኙ 12 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ክፍኛ ቆስለዋል ።
በተመሳሳይ ዜና
ያለ ስራው ክብሩን አውርዶ ምርጫ አስፈፅማለሁ ብሎ ከአምባጊወርጊስ ከተማ ወደ ኮሶየ ቀበሌ ምርጫ ለማስፈፀም የሞከረው የአገዛዙ ተላላኪ ጥምር ሀይል በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቴውድሮስ ብርጌድ አባላት ድንገተኛ ምት ገጥሞት 3 አባላቱን አስመ*ትቶ እንደ ምርጫ ቁሳቁስ ተሸክሞ ወደ መጣበት እየፈረጠጠ ተመልሷል ።
በአጠቃላይ የዛሬው እርምጃ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5 ተኛ ኮር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ህዝባችን በምርጫ ሰበብ
የሚያጭበረብሩና የሚያወናብዱ የአገዛዙ ተላላኪዎ ላይ የማያዳ*ግም እር*ምጃ እንደምንወስድ ማሳያ ነው ።
በቀጠናው ሌሎች አውደ ውጊያዎች እንየተካሄዱ ይገኛሉ ዝርዝር መረጃዎችን ወደ በኃላ እናደርሳለን ።
አንድነት ሀይልም መዳህኒትም ነው !!!
©አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከፍተኛ አመራሮችና ማህበረሰብ 147ኛውን የኢድ አል-አድሃ በዓል በአንድነት አከበሩ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደቡብ አማራ ቀጠና የአሳምነው ዕዝ፣ 1447ኛውን የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓልን በዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር በሚገኙ ቀጠናዎች ከነዋሪው ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር በደመቀ ሁኔታ አክብሯል። በበዓሉ ላይ የአሳምነው ዕዝ ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ (ሽዋ) እና ምክትል መሪው አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ ጨምሮ የኮርና የክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። በዓሉ የአማራ ህዝብ የቆየ የሃይማኖት መከባበርና የፅናት መገለጫ በሆነ መልኩ ተከናውኗል።
እምነታችን ውበታችን ነው የዕዙ አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክት የፋኖ ትግል የሁሉንም አማራ እኩልነትና ማንነት የሚያስከብር መሆኑን አጽንኦት በመስጠት የአብይ አህመድ አስተዳደርና ተላላኪው ብአዴን አንድነታችንን ለመሸርሸርና በሃይማኖት ለመከፋፈል ቢሞክሩም፣ እኛ ግን የንጹህ አማራ ማንነትና የኢትዮጵያዊነት ኩራት ያለን በመሆናችን ሴራቸው አይሳካም ብለዋል። አክለውም አርበኛ መሪዎቻችን እኛ ዘመን የወለደን የሚኒልክ የበላይ የአሳምነውና የቴዎድሮስ አጥንት በውስጣችን የታተመብን ጀግኖች ነን። ክንዳችን ለጠላት የማይበገር አስተሳሰባችን ንጹህ የጥቁር ህዝቦች መፍለቂያ የሆነችው ምድራችን ቅድስት መሆኗን በተግባር እናረጋግጣለን።
በመጨረሻም በበዓሉ ላይ የተገኙት የሃይማኖት አባቶችና እናቶች ፋኖዎች ሃይማኖታዊ በዓላት ላይ መገኘታቸው ትልቅ ክብር መሆኑን ገልጸዋል። የባዓሉ ባለቤት ሙስሊሙ ማህበርሰብም ባስተላለፉት የምስጋና መልዕክት ፋኖዎች የዛሬው የአማራ የመኖር ነፃነት ባለቤቶችና የነገዋ ኢትዮጵያ ባለአደራዎች መሆናችሁን ስንገልፅ ሁሌም ቤሆን እኛ ከጎናቸው ለመቆም በነብዩ መሐመድ ስም ቃል እንገባለን አላህ አንድነታቸውን አጽንቶ ለድል እንዲያበቃቸሁ ጸሎትና ምኞታችን ነው። ሆኖም በዓሉ ከታናናሾች እስከ አዋቂዎች ድረስ በታላቅ ደስታና ምስጋና የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ይህም በደቡብ አማራ ቀጠና ያለውን ጠንካራ የህዝብና የፋኖ ትስስር ዳግም ያሳየ ነው በማለት ተጠናቋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው!!!!!!
መጋቢት 11 /07/2018 ዓ.ም
የማይቀረው የኢትዮጵያ ትንሳኤና ዘመኑ ያበቃለት አምባገነን ስርዓት
ሰሞኑን በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን የሰላም እጦት ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያዊያን ከሁለት ጎራ ተከፋፍለው ሲከራከሩ እያየሁ በጣም እያስገረሙኝ ነበር። ከምንም በላይ ደግሞ አብይ አህመድ United Arab Emirates ከኢራን የሚሰነዘርበትን የሚሳይል ጥቃት አወገዘ የሚል ዜና ስሰማ በእጅጉ አስገርሞኛል። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች የሚለው አባባል ምንኛ እውነት ነው! ከጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ የኢትዮጵያ ሁኔታ አሁን አሳሳቢ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ሀገሪቱ በታሪክ እንደ አሁን አይነት ፈተና ገጥሟት አያውቅም። አስተዳደራዊ መዋቅሩ በመበላሸቱ ሃገሪቱ በጦርነት እየታመሰች ሲሆን የኑሮ ውድነቱም ህዝቡን እያማረረው ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብ በማንኛውም ሁኔታ ተስፋ ቆርጦ ይገኛል።
የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ለምን እንደተጀመረ አቅጣጫ ከማስቀመጤ በፊት ስለ ኢትዮጵያ መከራና ስለሚሆነው ነገር ልነግራችሁ እፈልጋለሁ። አመናችሁም አላመናችሁም ወደዳችሁም አልወደዳችሁም ሊሆን ያለው ይሆን ዘንድ ግድ ነው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ፈተና ላይ ትገኛለች። ከዘመናት በፊት እናት አባቶቻችን ሲጠብቁት የነበረው ዘመን እነሆ አሁን ነው (መጽሐፈ ኪዳን፣ፍካሬ ኢየሱስ፣ራዕዬ ሲኖዳ፣ፊቅጦር፣ድርሳነ ዑራኤል ፣ራዕዬ ሳቤላ፣ መጽሐፈ ምስጢርና ትርጓሜ ወንጌልን ተመልከቱ::)
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ላይ እየተካሄደ ያለው ውጊያ በጥልቁ መንፈስ በሚመሩ የሰውን ልጅ የመከራ ቀንበሩን ባከበዱ አምባገነኖችና የሰውን ልጅ ፍጹም ሰላም ወይንም ትንሳኤ ብለን የምንጠራውን ለማጎናጸፍ በሚጥሩ በእግዚአብሔር በተመረጡ መካከል ነው።
ኢትዮጵያ አሁን ልክ በእሳት ተፈትኖ ነጥሮ እንደሚወጣ ወርቅ ትልቅ ፈተና ውስጥ ናት። ከኮሮና ቫይረስ መምጣት በፊት ጀምሮ ይህ ህዝብ እንዲነቃ ለብዙ ዓመታት ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ:: ምን መልእክት ሳስተላልፍ እንደነበር የሰሜን ወሎ በተለይም ደግሞ የላስታና የግዳን ህዝብ ያውቃል። ነገር ግን ይህ ትውልድ አመጸኛ ነው ከመንቀፍና ስም ከመስጠት የዘለለ ምን ምን አያደርግም። በዚህ ሁኔታ ስለሚፈጸመውና ስለሚሆነው ነገር ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልገው በርካታ እውነተኛ አባቶች ሰማይ ስሚ ምድርም አድምጭ እያሉ ተናግረዋል። ግን የሚሰማ ትውልድ የለም ሁሉ ነቃፊ ሁሉም ተሳዳቢ ነው። እኛ ተናግረናል ስላልሰማችሁን እሳት እየበላችሁ ነው ወደፊትም ካልሰማችሁ የመከራችሁ ቀንበር ይከብዳል።
ከዚህ አምባገነን ስርዓት ጋር ሆናችሁ የሰው ልጅ መከራ የምታራዝሙ ሁሉ ዋጋ ትከፍላላችሁ። ከህዝብ ጀምሮ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችና የመንግስት ባለስልጣናት ሁላችሁም ነፍሳችሁን እና ስጋችሁን የምታድኑበት ሰዓት አሁን ነው። የብልጽግና ስርዓት ይዟችሁ ይጠፋል። በተለይ ደግሞ አገልጋይ አባቶች ንቁ! ጸልዩ፣ መጽሐፍትን አገላብጣችሁ መርምሩ ፣ ስለ ጊዜውም በደንብ ለመረዳት ልቦናችሁን ክፈቱ፣ ነቃፊዎች ብቻም አትሁኑ ለሆዳችሁም አትሙቱ፣ አድርባይም አትሁኑ! ከምድራዊ ንጉስ ይልቅ ሰማያዊውን ንጉስ ፍሩ። አባቶች ይህንን አምባገነን ስርዓት አንድ ሆናችሁ ማውገዝ አለባችሁ:: ቀደምት አባቶቻችን ነገስታትን የማይፈሩ ለእግዚአብሔር ቃልና ለሚጠብቋቸው ምዕመናን የሚኖሩ ነበሩ:: አሁን አሁን የምናያቸው አባቶች በጣም ያሳዝናሉ:: አባቶች ሆይ ህዝብን (ኢትዮጵያን) ወክላችሁ ይህንን አምባገነን ስርዓት መቃወም አለባችሁ:: ይህን ካላደርጋችሁ ዋጋ ትከፍላላችሁ::
ስለሆነም ከመንግስት ጎን ሆነው የሚጨፈጭፉ ማንኛቸውም ኃይላትና በማንኛውም መንገድ የሚተባበሩ ሁሉ ፍጻሜያቸው የከፋ ነው የሚሆነው። የእግዚአብሔር የፍትህ ሰይፍ ወርዳለች። ኢትዮጵያ እንደወደቀች አትቀርም ትነሳለች። ትንሣኤዋ ተረት ተረት አይደለም በእውነተኛ ልጆቿ በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅርብ እውን ይሆናል። ሁላችሁም ወደዳችሁም አልወደዳችሁም የማይቀር ነገር ነው። በዓለም ሁሉ የምትሰሙት የጦርነት ጉሰማ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ መቅረብ አመላካች ናቸው። ከኢትዮጵያ ትንሳኤ በኋላ የቀሩት ሃገራት ይናወጻሉ። ከዚያም ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል የሚባለው ትንቢት ይፈጸማል ማለት ነው። "መልእክተኞችን በባሕር ላይ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣኖች መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥ ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ወደ ሆነ ወገን፥ ወደሚሰፍርና ወደሚረግጥ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።በዓለም የምትኖሩ ሁሉና በምድር የምትቀመጡ ሆይ፥ ምልክት በተራሮች ላይ በተነሣ ጊዜ እዩ፤ መለከትም በተነፋ ጊዜ ስሙ።" ትንቢተ ኢሳይያስ ፲፰፥፪
ኢትዮጵያ ከጨለማ ወደ ብርሃን ስትሸጋገር ሌሎች ሀገራት መከራቸው ይከብዳል:: ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ጽኑ መናወጥ ምክንያት በርካታ ህዝቦች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ለመጠለል ይለምናሉ። ይህ ከመፈጸሙ በፊት ግን የኢትዮጵያ ትንሳኤ ይጀምራል። ኢትዮጵያ የመከራው ቀን መሸሸጊያ ናት የሚባለው ለዚህ ነው:: ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ተራ አድርጋችሁ የምታስቡ ይህ ምስጢር ሊሰወርባችሁ ተረትም ሊመስላችሁ እንደሚችል አውቃለሁ! ግን ሊሆን ግድ ነው::
ስለዚህ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማምጣት ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይኖርብናል። ከንሰሃ እንዲሁም ከጸሎት ጀምሮ ሀገርንና ሃይማኖትን ለማስጠበቅ ከሚደረጉ ማንኛውም መልካም የሆኑ እንቅስቃሴዎች ልንሳተፍ ግድ ይለናል። ኢትዮጵያውያን ንቁ ንቁ ንቁ!
ተንሳኤው አይቀርም ግድ ነው፤ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!
ቆሞስ አባ ጳውሊ ከግንባር
