es
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
3 260
Suscriptores
+2224 horas
+2707 días
+65730 días
Archivo de publicaciones
አፋብን የአማራ ሕዝብ የህልውና ቀይ መስመር!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) መመሥረት፣ ባለፉት ጊዜያት በታሪክ አጋጣሚዎችና በፖለቲካዊ ሴራዎች ምክንያት ሲከሽፉ ለቆዩት የሕዝባችን ጥረቶች ሳይንሳዊና ስትራቴጂካዊ ምላሽ ነው። ቀደም ባሉት ጊዜያት እንደ “መላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ)” ያሉ ንቅናቄዎች በሕዝባዊ ስሜትና በእውነት ላይ ተገንብተው ቢነሱም፣ በወቅቱ በነበረው ሥርዓታዊ አፈና እና በውስጣዊ መዋቅራዊ ድክመቶች ምክንያት ግባቸውን ሳይመቱ ቀርተዋል። ዛሬ ግን “አፋብን” በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የቁርጥ ቀን ልጆች ደም፣ አጥንትና መራራ መሥዋዕትነት የተገነባ የህልውናችን የመጨረሻ ምሽግ ነው። እንደ አፋብን ያለ ውስብስብ ስብስብ (Complex System) ስኬቱ የሚወሰነው በክፍሎቹ መካከል ባለው 'መዋቅራዊ ቅንጅት' (Structural Integrity) ላይ ነው። በሳይንስ ህግ፣ የአንድ ሰንሰለት ጥንካሬ የሚለካው በደካማው ቀለበት (Weakest Link) መጠን እንደሆነ ሁሉ፣ የንቅናቄያችንም ጥንካሬ የሚለካው በውስጣችን በሚኖር የአንድነት ጥራት ነው። ማንኛውም ሰርጎ ገብ 'ባንዳ' ወይም የአንጃነት ስሜት በድርጅታዊ መዋቅሩ ውስጥ እንደ 'ኢንትሮፒ' (Entropy) የሚቆጠር ሲሆን፣ ይህም ስርዓቱ ከውስጥ እንዲበሰብስና ለውጫዊ ግፊት በቀላሉ እንዲንበረከክ ያደርገዋል። ስለዚህ አፋብንን እንደ አይን ብሌናችን መጠበቅ ምርጫ ሳይሆን የግዴታ ግዴታ ነው። ይህ ንቅናቄ የአማራ ሕዝብ ሞትና ሕይወት የሚወሰንበት ማኅጸን ነው። በአፋብን ላይ የሚቃጣ ማንኛውም ዓይነት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊ ጥቃት በቀጥታ በእያንዳንዱ አማራ የህልውና ትርታ ላይ የተቃጣ ነው። ጠላት ከውጭ ቢያሴር፣ ባንዳ ከውስጥ ቢወጋ፣ ለዚህ ድርጅትና ለቆመለት ዓላማ ደረታችንን እንደ ጋሻ አጋልጠን ለመስጠት ዝግጁ ነን። ዛሬ የምናሳየው ፅናትና የምንገነባው አንድነት፣ ነገ ልጆቻችን በነፃነትና በክብር የሚኖሩባትን ምድር የመመሥረቻ ዋስትናችን ነው። ንቅናቄያችንን ከውስጥ ባንዳና ከውጭ ጠላት መጠበቅ ማለት ትግሉን መጠበቅ ማለት ነው። የአፋብን መጠናከር የአማራ ትንሣኤ ማብሰሪያ፣ መዳከሙ ደግሞ የታሪክ ዳግም ውድቀት መሆኑን ተገንዝበን፣ በአንድ ልብና በአንድ ክንድ ለድል እንነሳለን! አፋብን የህልውናችን ማማ ነው!!

ከ1ቲም በላይ የፓራ ኮማንዶ አባላቱ እና የ25ክ/ጦር የመረጃ እና ደህንነቱ ፖሊስ አባሎች 201ኛ ኮር 54ኛ እና 74ኛ ክ\ጦርን ተቀላቅለዋል❗️ ..............ሚያዚያ 05/2018 ዓ.ም በተጠኑ ቦታዎች የጠላት ሀይል ላይ በደረሰበት ጉዳት ስነልቦናው የተሸረሸረው የስርአቱ አገልጋይ አባል የነበሩት በየተራ ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ ነው። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ 1ኛ.ነፃው ተስፋየ...............ፓራኮማንዶ 2ኛ.ተከታይ በለው.............ፓራ ኮማንዶ 3ኛ.የሽዋስ ሙናየ...........ፓራ ኮማንዶ 4ኛ.ወንድማለም ደምስ.......ፓራ ኮማንዶ 5ኛ.ሲሳይ ማረጉ....የ25ክ/ጦር መረጃ እና ደህንነት 6ኛ.እንቻለው አገኘሁ ..........ፓሊስ 7ኛ.ገረመው መኮነን..........ሚሊሻ 8ኛ.ስንታየሁ ካሳ..............ፓራ ኮማንዶ 9ኛ.ሞላ አንዳርጌ............ፓራኮማንዶ 10ኛ.አቢቲ ተስፋው..........ፓራ ኮማንዶ 11ኛ.አበበ ዋለ..............ሚሊሻ የአብይን ስልጣን ለማስጠበቅ ብቻ እንጂ ስርዓቱ ምንም አቅም የሌለው መሆኑን በሰሞኑ የተሰሩ ስራወችን በአይናችን አይተናል ሴራውን ተረድተናል ያለ አግባብ መተኪያ የሌለው ህይወታችን መገበር አንፈልግም በማለት በመኮብለል በዛሬዉ እለት ቆንጆወችን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ኑ❗️ ህዎታችሁን አድኑ ቤተሰቦቻችሁን ለጥቁር ልብስ አትጯቸዉ‼️ አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በባህርዳር ጣና ክፍለ ከተማ ህዝብ እየደበደቡ ካርድ ካላወጣችሁ በማለት ህዝብ እየተሰቃየ ነው። 1)ጌትነት የተባለ የክፍለከተማው አስተዳዳሪ ነኝ የሚል #ዘራፊ ሲሆን ከዚህ በፊት የክፍለ ከተማው _አፈ ጉባኤ ታግቶ ወደ ዘጌ ተወስዶ በነበረበት ጊዜ እኔ 40,000 (አርባ ሽህ ብር )ስለከፈልኩ ፋኖወች አይነኩኝም ሲል የነበረ ነው።አሁንም የክፍለ ከተማውን ሰራተኞችን የምርጫ  አስወጡ (አስመዝግቡ) በሚል በግዴታ የሰራተኛውን አሰማርቷል። 2) ሙሉቀን  የቀበሌ አስተዳዳሪ ነኝ የሚል(ከዚህ በፊት ከሌሎች ግብረ አበሮች ጋር በመሆን ለሚሻ #ቀለብ ብር አውጡ እያለ ህዝብ ሲያሰቃይ የነበረ ነው። 3)ወርቁ የተባለ  ከዚህ በፊትም ሰው #በማገት ከሚሊሻዎች ጋር የጥቅም ተጋሪ የነበረ ወንጀለኛ ። እንዲሁም ሌሎች በስም ለጊዜው  ያልተጠቀሱ ከሀዲዎች ሲሆኑ። በአማራ በትን ታጣቂዎች እና በፖሊስ በመታገዝ በቀበሌ 13 ህዝቡን በማንገራገር  ለምርጫ እያስመዘገቡ ነው። ምርጫው በሲስተም መሆን ካሁኑን ጀምሮ ብልጽግና  በምርጫው  ማንም በሌለበት  ብቻውን ተወዳድሮ  አሸነፍኩ ሊል እንደሆነ ግልጽ  ነው። 😡😡ህዝቡም እንዲህ ይላል፦ እነዚህን ሰወች ፋኖም ዝም ካላቸው  እኛ ብቻ ለውጥ አናመጣም አማራጫችን መመዝገብ ነው ይላል።የመንግስት ሰራተኛውም ካርድ አውጥቶ ማስመዝገብ ግዴታ ነው ተብሏል። አንዳንድ መስሪያ ቤቶችም ስራተኞች ስራ አቁመው ለምርጫ ቅስቀሳ እንዲወጡ ተደርጓል። እንደነዚህ አይነት የስርዓቱ  ሎሌወች ላይ  እርምጃ ቢወሰድ።

#ሰበር_ዜና👌 የአገዛዙን አላማ አንግበው የቅዱሱን የአማራ ህዝብ የነፃነት ትግል በፊትአውራሪነት እየመራ ያለውን የአማራ ፋኖን ከድተው ወደ ብልፅግና የገቡ ከሀዲዎች በሚሊሻ አዛዣቸው ተገደሉ።     ሚያዚያ 05/2018ዓ.ም "ክርስቶስን በ30ዲናር አሳልፎ የሸጠው በትንሳኤውም የተጠራጠረው ይሁዳ በክህደቱ እራሱን አንቆ እንደገደለ ሁሉ፣ የፋኖን ቅዱስ ትግል አሸነፊነት ተጠራጥረው ለአገዛዙ እጅ የሚሰጡ የዘመናችን ይሁዳዎችም የመጨረሻ እጣ ፈንታቸው የውሻ አሟሟት ይሆናል!" የዘመናችን ይሁዳዎች ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ወጥተው ቃል የገቡለትን የትግል ጓዶቻቸውን የመስዋዕትነት የቃል ኪዳን አደራ በ94,000ብር የበሉ ሆድ አደሮች የአማራ ህዝብ ንብረት የሆነውን የፋኖን መሳሪያ ይዘው ለብልፅግና እጃቸውን የሰጡ ከሀዲ የፋኖ አባላት በትላንትናው ዕለት በፋሲካው ምሽት በአዲሱ አለቃቸው በወረዳው የሚሊሻ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ሰጭነት መገደሉን ኮሩ በመረጃው ሲያረጋግጥ ፋኖን የከዳ አለበት ዕዳ ነውና መጨረሻቸውም የውሻ አሟሟት መሆኑን ኮሩ በፅኑ መግለፅ ይወዳል። በወረሀ ክረምቱ ነሃሴ 08 ቀን 2017ዓ.ም የክፍለጦሩን እንቅስቃሴ ለጠላት መረጃ በመስጠት በሰራዊቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የነበሩ ሲሆን፤ ሆኖም ግን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ጀግኖቹ የአፄ ዳዊት ክፍለጦር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በኮላሽ ቀበሌ የጠላትን 101ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ተፋልመው ድል ሲቀዳጁ፣ በተመሳሳይ ሰዓት ከውጊያ ግምባር ከድተው በሚዳ ወረዳ መራኛ ከተማ መሽጎ የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ ለሚገኘው የብልፅግናው አገዛዝ እጃቸውን ከሰጡት ውስጥ አቶ አሽኔ ተስፋዬ የተባለ ከሀዲ በትላንትናው ምሽት 2:00 ላይ በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚሊሻ ጽ/ቤት ስምሪት ኃላፊው በአቶ ጌታው አለሙ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተደብድቦ መገደሉን ኮሩ አረጋግጧል።        ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''     ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽኝ ክፍል     ሚያዚያ 05/2018ዓ.ም

📌የነፃነት ቃል-ኪዳን እስረኞች! እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ! ዛሬ መላው የክርስትና እምነት ተከታይ የትንሳኤን በዓል በደስታና በጭብጨባ ሲያከብር፣ እናንተ ግን ስለ ሕዝባችሁ ክብርና ስለ እውነት በቆማችሁበት ጽኑ አቋም ምክንያት በጨለማ ክፍሎችና በወህኒ ቤቶች ውስጥ ትገኛላችሁ። ይሁን እንጂ፣ ዛሬ የምናከብረው ትንሳኤ ትልቁ ምስጢሩ ግፍ በጽናት፣ ጨለማ በብርሃን፣ እስርም በነፃነት እንደሚሸነፍ ማብሰሩ ነው። እናንተ በአካል ከወገኖቻችሁ ብትለዩም፣ በሐሳባችሁና በሞራል ልዕልናችሁ ግን ከማንም በላይ ነፃ ናችሁ። እናንተ የታሰራችሁት ወንጀል ስለፈጸማችሁ ሳይሆን፣ በውስጣችሁ ለተሸከማችሁት ኃያል እውነትና ለአማራ ሕዝብ ሕልውና ስላላችሁ ቆራጥነት ነው። አገዛዙ እናንተን ከሕዝብ በመነጠልና በብረት በሮች ውስጥ በመቆለፍ የሕዝቡን ድምፅ ማጥፋት የሚችል ይመስለዋል። ነገር ግን፣ የታሰረ አካል እንጂ የታሰረ ሐሳብ የለም! እናንተ ለእውነትና ለፍትሕ የከፈላችሁት ዋጋ፣ ለሕዝባችን የትግል ነዳጅና የነፃነት ቀንዲል እየሆነ ነው። የዛሬው እስራችሁ ነገ ለሚመጣው ታላቅ ትንሳኤ የሚከፈል መራራ ግን ደግሞ ቅዱስ መስዋዕትነት ነው። አምባገነንነትና ግፈኝነት ሁልጊዜም የሚፈሩት የታጠቀን ኃይል ብቻ ሳይሆን፣ እውነትን የጨበጠና በጽናት የቆመ ህሊናን ነው። እናንተን ማሰር የፈሩት፣ የእናንተ ሐቀኝነት እና ባለማንነት የእነርሱን የባህሪ ዝቅጠትና የሞራል ውድቀት ስላጋለጠባቸው ነው። በሐሰት ክስና በፈጠራ ትርክት እናንተን ለማንበርከክ ቢሞክሩም፣ እናንተ ግን በፈተና ውስጥ የምትጸኑ ጀግኖች ናችሁ። ከመከራ በኋላ ደስታ፣ ከእስር በኋላ ነፃነት፣ ከሞት በኋላም ትንሳኤ እንዳለ የታሪክ ምስክር ነው። በዚህ የትንሳኤ ዕለት፣ መላው ሕዝባችን ከእናንተ ጋር መሆኑን ልትረዱ ይገባል። እናንተ የሕዝቡ ሕያው ሰማዕታት፣ የነፃነታችን ምልክቶች ናችሁ። በቆርቆሮ ቤትና በጠባብ ክፍሎች ውስጥ ሆናችሁ የምታሳዩት ጽናት፣ በሜዳው ላይ ካለው ተጋድሎ ባልተናነሰ ለጠላት ድንጋጤ፣ ለሕዝባችን ደግሞ ኩራት ነው። እስር ቤቱ የእናንተን ማንነት አይቀይረውም፤ ይልቁንም እንደ ወርቅ በእሳት ውስጥ አልፋችሁ ይበልጥ እንድትነጥሩና እንድትጠነክሩ ያደርጋችኋል። ጽኑ! በርቱ! የጽናትና የሕሊና እስረኞች በሙሉ፤ ጊዜው ቢረዝምም የእውነት ትንሳኤ ግን አይቀሬ ነው። የሕዝባችንን የሕልውና ትግል ማንም ሊቀለብሰው እንደማይችል ሁሉ፣ የእናንተንም የነፃነት ቀን ማንም ሊያግደው አይችልም። እናንተ በጽናት የምትቆዩት የነፃነት አርበኞች፣ የታሪክ ማኅደር በወርቅ ቀለም ይዘክራችኋል። የጨለማው ግዛት ፈርሶ፣ የግፍ ቀንበር ተሰብሮ፣ ሁላችንም በነፃነት አደባባይ የምንገናኝበት የትንሳኤ ቀን ሩቅ አይደለም። ድል ለእውነት! ነፃነት ለኅሊና እስረኞች! (Kemila Ahimed) (አውሎግሶን አንድነት ፣ ሚያዝያ 4/2018)

የትንሳኤ መልዕክት፦ ከጽናት ወደ ድል ​ለተከበራችሁ የአማራ ፋኖ አመራሮችና አባላት፣ በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ የትግሉ ደጋፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና መላው የትግሉ ምህዋር አካላት፤ ​እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ​የትንሳኤ በዓል ከጨለማ በኋላ ብርሃን፣ ከሞት በኋላ ሕይወት፣ ከስደትና ከስቃይ በኋላ ደግሞ ድል መኖሩን የምናይበት የታላቅ ተስፋ ቀን ነው። ይህ ዕለት ለእኛ ለኢትዮጵያውያንና ለተገፋው የአማራ ሕዝብ ትግል ትልቅ መንፈሳዊና ስነ-ልቦናዊ ትርጓሜ አለው። ​1. ትንሳኤና የፋኖ ጽናት የትንሳኤው ጉዞ በቀራንዮ ስቃይና በመቃብር ውስጥ ማለፍን እንደሚጠይቅ ሁሉ፣ ዛሬ ፋኖና መላው ሕዝባችን እየከፈለ ያለው መስዋዕትነት የነገዋን ነፃና ሉዓላዊት ኢትዮጵያ ለመውለድ የሚደረግ ምጥ ነው። መቃብሩ ተንክባሎ የሞት ኃይል እንደተሸነፈ፣ በጽናት የምናደርገው የህልውና ትግልም ግፉንና ጭቆናውን አሸንፎ ለሕዝባችን የነፃነት ትንሳኤን እንደሚያበስር ጥርጥር የለውም። ​2. ለአመራሮችና ለአባላት በየዱር ገደሉ ለፍትህና ለክብር የምትዋደቁ የቁርጥ ቀን ልጆች፤ የክርስቶስ ትንሳኤ የታላቅ ትዕግስትና የመስዋዕትነት ውጤት እንደሆነ ሁሉ፣ እናንተም በመከራ ውስጥ ሆናችሁ ለሕዝባችሁ የምታሳዩት ጽናት የታሪክ ማህተም ነው። አንድነታችሁን በማጠናከር፣ በዲሲፕሊንና በላቀ ሞራል ወደፊት በመራመድ የሕዝባችንን የነፃነት ቀን እንድታቀርቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ​3. ለሃይማኖት አባቶችና ለማህበረሰቡ የሃይማኖት አባቶች በጸሎታችሁ፣ ማህበረሰባችን ደግሞ በጉልበታችሁና በሀብታችሁ ለጽድቅና ለፍትህ የምታደርጉት ድጋፍ ከትንሳኤው በረከት ጋር ይቆጠራል። እውነትን ይዞ መታገል መጨረሻው ድል መሆኑን አውቃችሁ፣ ከታጋዮች ጎን መቆማችሁን አጠናክሩ። ​4. በውጭ የምትገኙ የትግሉ ደጋፊዎች በዓለም ዙሪያ ሆናችሁ የሕዝባችሁን ድምፅ ለዓለም ለማሰማት የምትለፉ ወገኖቻችን፤ ትንሳኤው ርቀትን ሳይገድበው ዓለምን በብርሃን እንደሞላ፣ እናንተም በዲፕሎማሲውና በፋይናንሱ ረገድ የምታደርጉት እገዛ ለትግሉ የጀርባ አጥንት ነው። ይህ በዓል አዲስ የትግል መንፈስና አንድነት የምታድሱበት ይሁንላችሁ። ​ማጠቃለያ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው ጌታ፣ ሕዝባችንንም ከገባበት የመከራ መቃብር አውጥቶ ለታላቅ ትንሳኤ ያብቃው። ትግላችን በፍጹም ጽናት ይቀጥላል፤ ድል ለተገፋው ሕዝባችን! ​ብርሃነ ትንሳኤው የሰላም፣ የፍቅርና የነፃነት ይሁንልን! ፶,/ አለቃ ቁሜ አዲስ

‎ስናይፐር እና ጥቁር ክላሽ በመያዝ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝን የተቀላቀሉ የአገዛዙ ሰራዊቶች የትንሳኤ በዓልን በድምቀት እያከበሩ ነው። ‎~ ‎ሚያዚያ:04/2018 ዓ/ም ‎~~ ‎ በአብይ አህመድ የሚመራ
+2
‎ስናይፐር እና ጥቁር ክላሽ በመያዝ አፋብን ቴዎድሮስ  ዕዝን የተቀላቀሉ የአገዛዙ ሰራዊቶች የትንሳኤ በዓልን በድምቀት እያከበሩ ነው። ‎~ ‎ሚያዚያ:04/2018 ዓ/ም ‎~~ ‎ በአብይ አህመድ የሚመራውን  አረመኔያዊ  የብል(ፅ)ግና  ስርዓትን በማገልገል ላይ የነበሩ ሰራዊቶች የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅንቄን /አፋብን/ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ  ዕዝን ተቀላቀሉ። ‎ከነዚህም መካከል :- ‎1_መሀመድ አብዲሳ (ሶማሌ) ‎2_ሌንጮ ዲማ (ኦሮሞ) ‎3_ፉአድ ዛኪር ( ደቡብ ስልጤ) ‎4_አቢ ሁሴን (ሀረር ) ‎5_ረዲዋን መዜን( ጅማ) ‎ 6_አግማስ የኔወርቅ (ፋራ ኮማንዶ) ‎7_ይገረም አላምነህ (ፋራ ኮማንዶ) ‎8_ መግባር ዳኜ (ፋራ ኮማንዶ)  እስከነሙሉ ትጥቃቸው ተቀብለናቸዋል። ‎ ‎ አብይ አህመድ በብድር እየገዛ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም የሰጣቸውን ስናይፐር እና የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ  መሳሪያ አፋብን ቴዎድሮስ  ዕዝ #ገቢ አድርጓል። ‎በሌሎች ቀጠናዎችም #ስቦ ማስከዳት የቀጠለ መሆኑ ታውቋል። ‎---- ይቀጥላል። ‎ ‎አዲስ ትውልድ፤ አዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ ተስፋ፤ ‎ሚያዚያ  04/2018 ዓ/ም ‎ የአፋብን ቴዎድሮስ  ዕዝ ማህበራዊ  ሚዲያ ክፍል! ‎

የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ብሬን ተኳሹን ጨምሮ 18 ጠላት ሲደመሰስ ከ25 በላይ ቁስለኛ አስተናገደ!      የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር አካል የሆነው ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ በአሁኑ 16ኛ ክፍለ ጦርና እሸት ክፍለ ጦር በአሁኑ 19ኛ ክፍለ ጦር የተውጣጡ በቁጥር አነስተኛ ፋኖዎች የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ መከላከያ ጦርን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት በጥምረት ታላቅ ድል ተጎናፀፉ። ሚያዚያ 03 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ መነሻውን ከላሊበላ ከተማ በማድረግ ወደ ጋሸና ከተማ ሬሽን ለማሳለፍ የተንቀሳቀሰው የጁላ ሰራዊት ባላሰበውና ባልጠበቀው ሁኔታ ከአወባይ ዳቦ ከተማና ከድብኮ ቆጋ በተደረገበት የደፈጣ ጥቃት ጠላት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አስተናግዷል። በዚህ አውደ ውጊያ 18 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ25 በላይ ቁስለኛ ያስተናገደ ሲሆን ከላሊበላ ከተማ ተጨማሪ ሦስት መኪና ኃይል በመጨመርና ሽፋን እንዲሰጡት በማድረግ የተረፈው ኃይል ራሱን በማውጣት ያሰበውን ሳያሳካ ወደነበረበት ላሊበላ ከተማ ተመልሷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 04/2018 ዓ/ም

ለእውነት፣ ለማንነታችሁና ለራዕያችሁ በጠባብ ክፍሎች ውስጥ ለታሰራችሁ የአማራ ልጆች! እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ። የታምኑበት ዓላማና የቆማችሁለት እውነት እስር ቤት ቢያስወረውራችሁም አላማችሁ በየቤታችንና በየልባችን አለ። ለጋዜጠኞች፦ ብዕራችሁ ታስሮ፣ ድምፃችሁ ታፍኖ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እውነት አይታሰርም። እናንተ ለአማ ለህዝብ ጆሮና አይን ለመሆን የከፈላችሁት መስዋዕትነት የነፃነት መንገድን የሚጠርግ ብርሃን ነው። ለፖለቲከኞች፦ ለፍትህና ለዴሞክራሲ ያላችሁ ፅናት በመከራ ውስጥ ይበልጥ እንደሚጠነክር እናምናለን። የግፍ እስር የጊዜ ጉዳይ እንጂ የሀሳብን ልዕልና በፍጹም ሊያሸንፍ አይችልም። ለምሁራንና ለአማራ  ጭንቅላቶች፦ የእውነት ምስክር በመሆናችሁና አእምሯችሁን ለህዝብ ጥቅም በማዋላችሁ ዋጋ እየከፈላችሁ እንደሆነ እናውቃለን። አካላችሁ በሰንሰለት ቢገደብም፣ ብሩህ አእምሯችሁና ያሰረጻችሁት ዕውቀት ግን ምንጊዜም ነፃ ነው። እናንተ በመከራ ውስጥ ሆናችሁ ለትውልድ የምታሳዩት የፅናት ትምህርት ከምንም በላይ ታላቅ ነው። በአማራነታችሁ ብቻ ተመርጣችሁ  መከራን ለምትቀበሉ ወንድም እና እህቶቻችን፦ ማንነት ወንጀል ባልሆነበት ህሊና ውስጥ እናንተ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁ። ጨለማው ቢበረታም፣ ከጨለማ በኋላ ብርሃን፣ ከሞት በኋላም ትንሳኤ እንዳለ ሁሉ፤ የናንተም የፅናት ጉዞ ወደ ድልና ወደ ነፃነት እንደሚያደርስ አንጠራጠርም። ​ክርስቶስ መከራን በትዕግስት፣ ሞትን በትንሳኤ እንዳሸነፈ ሁሉ፤ እናንተም ይህንን የፈተና ጊዜ በፅናት አልፋችሁ ለታላቅ የነፃነት ብርሃን እንደምትበቁ ተስፋ እናደርጋለን። ​ የታሰረ አካል እንጂ የታሰረ አዕምሮ የለም! ​ብርታት፣ ጤናና የልቦና መረጋጋት ለእናንተ ይሁን! መልካም የትንሳኤ በዓል!

የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከሌሊቱ 5:30 ሰዓት በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀመው የቦምብ ጥቃት 24 የአድማ ብተና አባላት ከነ አመራራቸው ህይወታቸውን አጠዋል። ሚያዚያ 4/2018 ዓ.ም ========
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከሌሊቱ 5:30 ሰዓት በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀመው የቦምብ ጥቃት 24 የአድማ ብተና አባላት ከነ አመራራቸው ህይወታቸውን አጠዋል። ሚያዚያ 4/2018 ዓ.ም ======================================= በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 5:30 ከጎዛምን ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ተነስቶ ወደ ጎታራ እየተንቀሳቀሰ በነበረ ሰሌዳ ቁጥር 56721(3) Isuzu የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በነበሩ  የ32ኛ ዙር ተመራቂ አድማ ብተናዎች ላይ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በፈፀመው የቦምብ ጥቃት 24 የሚሆኑት ወዲያውኑ ህይዎታቸው ሲያልፍ 3 አድማ ብተናዎች ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል። ጥቃቱ ሸበል ሆቴል አቅራቢያ የተፈፀመ ሲሆን ጠላት ሲጠቀምበት የነበረው ተሽከርካሪ ወድሞ አመራሮችም መሞታቸው ታውቋል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ለመላው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሰራዊት አባላትና ለጽኑ ደጋፊዎቻችን፦ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ​መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከሰማያት ሰማይ ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግ
ለመላው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሰራዊት አባላትና ለጽኑ ደጋፊዎቻችን፦ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ​መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከሰማያት ሰማይ ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ፣ በሞቱ ሞትን ድል አድርጎ ዓለምን ያዳነበት ፍቅሩ እጅግ ይደንቃል! ይላሉ አበው!! ዛሬም እኛ አማራዎች፣ በመስቀል ላይ ካለው መከራ በኋላ የሚመጣውን ትንሳኤ በተስፋ የምንጠብቅ ሕዝቦች ነን። ይህ ታላቅ ሕዝብ በገዛ ምድሩ ላይ የሰላም አየር እንዳይተነፍስ የአብይ አህመድ አምባገነን አገዛዝ ሌት ተቀን ክፉውን ይዶልታል። ሰማዩን በባዕድ ሀገር (ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ) ድሮኖች አጨልሞታል፤ ምድሩን ደግሞ በወንበር ጠባቂ መከላከያ ሰራዊትና "ዳይፐር" በታጠቁ የብአዴን ሚሊሻዎች፣ የአድማ መከላከልና የሕዝብ ፖሊስ ጋር በፈጠረው "የአላቻ ጋብቻ" ደም እንዲነባ አድርጓል። ​ያ የዋህና ሰፊ ሕዝብ፣ አማርኛ በመናገሩ ብቻ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ሊጠፋ ከታደነ እነሆ ስምንት ክፉ ዓመታት አልፈዋል። ነገር ግን ሞትን የማይፈራው የተራራዎች ንጉሥ የአማራ ልጅ ፋኖ ይህንን አረመኔያዊ ሥርዓት ከምድረ ገጽ ለማጥፋትና የሕዝቡን ክብር ለመመለስ በየሸንተረሩ እየተዋደቀ ይገኛል። ውድ ሰራዊታችንና ጽኑ ሕዝባችን ሆይ! የፋሲካን በዓል ስታከብሩ፣ ይህ "ሰው በላ" ሥርዓት በጭንቀትና በሽንፈት ውስጥ ስላለ፣ በበዓል አጋጣሚ ጥቃት እንዳይሰነዝር ከወዲሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ፍኖተ አማራ ሚዲያ ከጦር ግንባር መልእክቱን ያስተላልፋል። ​ድል ለአማራ ሕዝብ! የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አፋብን ሸ/ጠ/ግ አሳምነው ዕዝ ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ እንኳን ለትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ ሚያዝያ 4 2018 ዓ/ም የአማራ ህዝብ ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ በሕማማት ውስጥ ኖሯል የስቃይ የመከራ ዘመናትን አሳልፎ ትንሳዔውን ለማየት አሁን በዕለተ ስቅለት ላይ ደርሷል። የአማራ ህዝብ ያሳለፈው በርካታ የጭለማ አመታት ልክ አዳም በዲያቢሎስ ስር በባርነት የኖረባቸው ዘመናትን እንደሚመስሉ እና አዳምን እና ልጆቹን ከዲያቢሎስ አገዛዝ ለማውጣት ክርስቶስ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞት ግድ እንደሆነ ሁሉ አሁን ላለነው እና ለሚመጣው የአማራ ትውልድ ክብር እና ነፃነት የዛሬው የእኔ እና የእናንተ ትውልድ ዋጋ መክፈሉ ግድ መሆኑን ማስገንዘብ አስፈላጊ ነው። ይህ የእኛ ዘመን ትውልድ ራሱን ከጭለማ ነፃ ለማውጣት ለአማራነት ማንነቱ ደሙን እያፈሰስንለት ነው። በዚህ ትግል ውስጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳትፎ ያላቸው የአማራ ልጆች ለህዝባቸው ፍቅር እና ለትውልድ ለነፃነት የሕማማትን አይነት መከራ እየተቀበሉ ደም እያፈሰሱለት አጥንት እየከሰከሱለት ነው። የሰው ልጅ ሲፈጠር ጀምሮ ከነ ሙሉ ነፃነቱ የተፈጠረ ፍጡር ነው ይህንን ነፃነቱን የሚነጥቀው ዲያቢሎስ እና የዲያቢሎስ ተገዢ የሆነ ኃይል ብቻ ነው። እኛም አማሮች ከፈጣሪያችን በነፃ የተሰጠንን ነፃነት ስለተነጠቅን ከዚያም ሲያልፍ በዚህ ምድርእንዳንኖር የዘር ፍጅት ስለተፈረደብን ነው የምታገለው። ነፃነታችንን ለማስከበር የመኖር መብታችንን ለማረጋገጥ የምናደርገው ተጋድሎ በዚህም የሚከፈለው የትኛውም መስዋዕትነት ልክ እንደ ዕለተ አርቡ ስቅለት የተቀደሰ መስዋዕትነት ነው። አማራነት መሞቻችን ብቻ ሳይሆን መዳኛችንም ነው!! አርበኛ ፋኖ እሸቱ ተክለሚካኤል እንኳን ለትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ

"ጽናት ለትንሳኤ፣ መስዋዕትነት ለነፃነት!!" ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ በተለይም የህልውና ተጋድሎ እያደረገ ላለው ህዝባችንና ሰራዊታችን እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ። ~ለጀግናው የፋኖ ሰራዊታችን፦ በየዱር ገደሉና በየውጊያ ግንባሩ የምትገኝ የነፃነት ፋና ወጊው ሰራዊታችን፤ የትንሳኤ በዓል ከጨለማ በኋላ ብርሃን፣ ከመከራ በኋላ ደስታ መኖሩን ማብሰሪያ ነው። አንተ ዛሬ እየከፈልክ ያለኸው መስዋዕትነት የህዝባችንን የነፃነት ትንሳኤ ለማረጋገጥ መሆኑን ድርጅታችን አፋብን በኩራት ይገነዘባል። በጠላት ምሽግ ላይ ሆነህ በዓሉን ለምታከብር ጀግናው ሰራዊታችን፣ ብርታቱና ድሉን እንመኛለን። ~ለተከበረው ህዝባችን፦ በትግሉ ሂደት ውስጥ ለደረሰብህ መከራና ግፍ ትዕግስትህና ጽናትህ የሁልጊዜም መመኪያችን ነው። ትንሳኤው የመከራ ማብቂያና የታሪካዊ ፍትህ መጀመሪያ እንዲሆንልህ እየተጋደልን እየተፋለምን እንገኛለን። ይህ በዓል በእምነትና በአንድነት የምንበረታበት እንዲሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ~ለደጋፊዎቻችንና ለበዓሉ ተሳታፊዎች በሙሉ፦ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ሆናችሁ ለትግሉ ድጋፋችሁን የምታበረክቱ ወገኖቻችን፤ የትንሳኤ በዓልን ስናከብር የተሰዉ ጀግኖቻችንን ቤተሰቦች በመጠየቅ፣ የተፈናቀሉትንና የተቸገሩትን በማሰብና በመርዳት እንዲሆን እናሳስባለን። የፋኖ ክንድ የሚበረታው በእናንተ አጋርነት ነውና። ~በመጨረሻም፦ እንደ አማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፤ ህዝባችን የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ቀልብሰን፣ የፍትህና የእኩልነት ትንሳኤ እስኪረጋገጥ ድረስ ትግላችን የማይቆም መሆኑን ዳግም እናረጋግጣለን። ~ድል ለአማራ ህዝብ!! ~ክብር ለተሰዉ ጀግኖቻችን!! ~መልካም በዓል!! ~ሚያዝያ 2018 ዓ.ም!! ~የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወታደራዊ ቃል አቀባይ አርበኛ አበበ ሙላቱ