es
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
3 260
Suscriptores
+2224 horas
+2707 días
+65730 días
Archivo de publicaciones
ስይፐር እና ጥቁር ክላሽ በመያዝ ወደ ቆንጆዎቹ ተቀላቅለዋል ‼️ በፋሲካ በዓል ስናይፐር እና ጥቁር ክላሽ በመያዝ ቆንጆዎቹን ተቀላቀሉ ‼️ 1_መሀመድ አብዲሳ 2_ሌንጮ ዲማ 3_ፉአድ ዛኪር 4_አቢ ሁ
+5
ስይፐር እና ጥቁር ክላሽ በመያዝ ወደ ቆንጆዎቹ ተቀላቅለዋል ‼️ በፋሲካ በዓል ስናይፐር እና ጥቁር ክላሽ በመያዝ ቆንጆዎቹን ተቀላቀሉ ‼️ 1_መሀመድ አብዲሳ 2_ሌንጮ ዲማ 3_ፉአድ ዛኪር 4_አቢ ሁሴን 5_ረዲዋን መዜን ከ304ተኛ ኮር 79ኛ ክ/ጦር 2ተኛ ሪጅመንት ስናይፐር እና ጥቁር ክላሽ በመያዝ ወደ 105ኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ሻለቃ ተቀላቅለዋል። እየመጡ ነዉ እኛም በፍቅር እየተቀበልናቸዉ ነዉ ።

ትንሳዔ ነጻነት ነው! ትንሳዔ አሸናፊነት ነው!  ሚያዝያ 3/2018 ዓ.ም. ​ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ በየበረሃውና በየጎሬው ለምትፋለሙ የአማራ የቁርጥ ቀን ፋኖዎች፣ እንዲሁም ለፅኑ ህዝባችንና ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ በቅድሚያ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በአይበገሬነትና በፅናት አደረሳችሁ። ​የትንሳዔ በዓል ሞት በህይወት ተረትቶ፣ ጨለማ በብርሃን ተገፎ፣ ግፍና መከራም በድል የተሸነፈበት ታላቅ በዓል ነው። ለዚህም ነው ትንሳዔ ነጻነት ነው! ትንሳዔ አሸናፊነት ነው!  የምንለው!! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የፈሰሰው ቅዱስ ደሙና በሦስተኛው ቀን መቃብርን ከፍቶ መነሳቱ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ የነፃነትና የድል ዋስትና ነው። ዛሬም በየግንባሩ የምንከፍለው መራር መስዋዕትነት ነገ ለሚመጣው የታሪካዊ ክብራችንና የማንነታችን ትንሳዔ ዋዜማ መሆኑ ጥርጥር የለውም። ​ ​የዘንድሮውን የትንሳኤ በዓል ልዩና ታሪካዊ የሚያደርገው፣ በሸዋ ምድር የሚንቀሳቀሱ ሁለት ታላላቅ ዕዞች ወደ አንድ ጠንካራ መዋቅር በመምጣት፣ በአንድ ዕዝ ስር የተጠቃለልንበት ታሪካዊ ዕለት ማግስት መሆኑ ነው። ​ይህ በወንድማማቾች መካከል የተፈጠረው ፅኑ አንድነታችን፣ የነፃነት ትንሳዔችን መቃረቡን ትልቁ አመላካች ነው! ጠላት የደቀነብንን የሞት ደብዳቤ ቀደን የጣልንበትና ብርሃን የታየበት ድል ነው። ትግላችን የቱንም ያህል ፈታኝና መራራ ቢሆንም በሞት ሸለቆ ሳይታለፍ ታሪክ አይቀየርምና ለአማራ ትንሳዔ የማይተካ ሕይወታችንን ዋጋ እየከፈልን የአማራ ሕዝብን ትንሳዔ በመስዋዕትነታችን እናረጋግጠዋለን፡፡ ​እኛ ለህዝባችን ሕልውና መረጋገጥና ክብር ስንቆም፤ እንደ አፄ ቴዎድሮስ "እምቢ ለጥላት" በማለት ለመስዋዕትነት የቆረጥን፣ እንደ አፄ ምኒልክ ጠላትን በአድዋ አውድማ አሳፍረን የመለስን፣ እንደ ንጉሥ ሚካኤል በጦር አውድማ ላይ ቆርጠን የምንፋለምና እንደ አባ ኮስትር በላይ ዘለቀ ለነፃነታችን ስንል ዳገት ቁልቁለቱን የምናስጨንቅ የጀግኖች ልጆች ነን። ​የቴዎድሮስ ፅናት፣ የምኒልክ ብልሀት፣ የንጉሥ ሚካኤል ቆራጥነትና የበላይ ዘለቀ አይበገሬነት ዛሬም በፋኖው ክንድ ላይ ደምቆ ይታያል። የነፃነት ትንሳኤያችን የሚረጋገጠው በእነዚህ ታላላቅ አባቶቻችን የጀግንነት መንገድ ስንጓዝ ብቻ ነው። የዛሬው መራር ትግላችንና የፈጠርነው ወጥ ድርጅት ነገ ወደ ብሩህ የድል ትንሳኤ መሸጋገሪያችን ነው። በመጨረሻም፡- የአማራ ሕዝብ ትግል በፈተና የተሞላ፤ መራራና ዋጋ የሚከፈልበት ነው፡፡ ነገር ግን ዋጋ የምንከፍለው ለአማራ ነጻነት ነው፡፡ ፈተናና መከራው የቱንም ያህል ቢበረታ የአማራ ፋኖ ድል አይቀሬ ነው፡፡ ​በድጋሚ መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንላችሁ። የምኒልክ አምላክ፣ የሰማዕታቱ ቃል ኪዳን ከእኛ ጋር ይሁን! ​አንገታችን አንድ፣ ዓላማችን አንድ፣ ጠላታችን አንድ፣ መዳረሻችንም አንድ ነው!! ​ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! ​አርበኛ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዋና ሰብሳቢ ሚያዝያ 3/2018 ዓ.ም.

የአፋ---ብን ምክትል ወታደራዊ አዛዠ ሩህሩሁ ፣ ቆራጡ ፣ ልበ ቀናው ፣ መሪየ  ዋርካው ምሬ ወዳጆ እንኳን አደረሰህ!🙏 የክርስቶስ ሞ--ት አንድም ለሰው ልጅ ምህረት ነው ፤ ሌላም ደሞ ለአዳም ዘር በሙሉ ለትምህርት ነው። ስለ ብዙዎች ሲባል የህይወት መሥዋ--ዕትነት ካልተከፈለ ብዙዎችን ማዳን አይቻልም። ታላቁ የዐምሓራ ሕዝብን ፣ ወገንን ማዳን ከተፈለገ መራራ መሥዋ--ዕትነት መክፈል ይገባል። ብዙወች ወንድሞቻችንም መስ--ዋትነት እየከፈሉ ይገኛል። በመስቀል ውስጥ መከራ ነው ፣ ስ--ድብ ነው ፣ ግር--ፋት ነው ፣ ውር--ደት ነው። በህልውና ትግላችንም ውስጥ መቁ--ሰል ፣ መድ--ማት ፣ መሰ--ዕዋት መሆን ያለ ወደፊትም የሚኖር ነው። ትንሳኤ ከፅናት በኋላ የሚገኝ ታላቅ ድል ነው። ትንሣኤ ተስፋ ነው። ፈተናው እንደሚያልፍ ተስፋ ይሰጣል። እለተ ዓርብ ላይ ቁመን ስናስብ እለተ እሑድ የሚመጣ አይመስልም ነበር። የመቃብሩን ድንጋይ ላየ የሚነሳ አይመስልም ነበር። ጨለማውን ላየ ብርሃን ሩቅ ይመስል ነበር። ሁሉም ግን በቅፅበት ተገለበጠ። የታሪኩ ባለቤት ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ታሪኩን በደሙ ለወጠው። የታላቁ የአማራ ህዝብ የሕማማቱ ጊዜ በስተመጨረሻም ያልፋል። በእለተ ሐሙስ አቅፈው ፣ ጉንጫችንን ስመው በዕለት አርብ በከንቱ የጮኹት ይሁዳዎች በእለተ እሁድ በድላችን ቀን ብዙዎች ያፍራሉ ይሸማቀቃሉ። ትግል ፅናት ይፈልጋል። በመከራዎች እና በውግዘቶች ፊት በፅናት መቆም ፣ በስድብና በንቀት ፊት በፅናት መቆም ፣ እንደ ፀሐይ የሚታዩት ልሂቃን ሲጠፉ ፣ እንደ ከዋክብት የሚታዩት ክቡራን ሲረ--ግፉ በፅናት መቆም። አብረው የነበሩ ፈርተውና ተሽጠው ሲከዱ በፅናት መቆም ያስፈልጋል። በሚፀኑት ዘንድ የታላቁ የዐምሓራ ህዝብ ትንሣኤ እጅግ በጣም ቅርብ ነው። በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በሁሉም ቀጠና ያላቹህ የፋኖ አመራር እና አባላት እንዲሁም ታላቁ ህዝባችን ታላቁን የትንሳኤ በዓልን ስታከብሩ ከፈጣሪ በታች ትልቅ ጥንቃቄ አይለየን እያልኩ የጌታችን የመድኃኒታችን የትንሳኤ በዓል ስናከብር በክብር የተ--ሰው የፋኖ አመራር እና አባላትን ፣ የተሰ--ው የፋኖ ቤተሰብን በማሰብ ክብረ በዓሉን ማክበረን አለብን እላለው። በሁሉም ቀጠና በአራቱም ግንባር የምትገኙ አመራር እና አባላት በድጋሜ እንኳን አደረሳቹ! መልካም የትንሳኤ በዓል!🙏

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የዘመቻ መምሪያ የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ​ "መከራን በፅናት፣ ሞትን በትንሳኤ!" ​ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ በየጠቅላይ ግዛቱ በፅናት ለምትፋለሙ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሰራዊት አባላትና አመራሮች፣ እንዲሁም ለመላው የአማራ ህዝብና ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላምና በድል አደረሳችሁ። ​የትንሳኤ በዓል ሞት በህይወት ተረትቶ፣ የባርነት ቀንበር ተሰብሮና የመከራ ደብዳቤ ተቀዶ የወጣበት ታላቅ የድል አዋጅ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስንት መከራና ስቃይ አልፎ ሞትን ድል ያደረገው፣ የሰው ልጅን ከሲኦል የባርነት ቀንበር ነፃ ያወጣው በፅናት፣ በይቅር ባይነትና በትጋት መሆኑ ለኛም የትግል ጉዞ ትልቅ ትምህርት ነው። ​ክቡር ሰራዊታችንና ህዝባችን ሆይ፤ ​ክርስቶስን ይሁዳ በሰላሳ ዲናር አሳልፎ እንደሸጠው ሁሉ፣ ዛሬም በከርሳቸው መብዛትና በግል ጥቅማቸው ምክንያት የአማራን ህዝብ ለዘላለማዊ የመጥፋት አደጋ አጋፍጠው ገሸሽ የሚሉ የዘመናችን "ይሁዳዎችን" እየተመለከትን እንገኛለን። ክርስቶስን የተከተለው ሁሉ አማኝ እንዳልነበረና እስከ ቀራኒዮም አብሮት እንዳልተጓዘ ሁሉ፣ ዛሬም የትግላችን ፅናት የሚፈተነው በመከራው አውድማ ላይ ነው። ሆኖም ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳው ሁሉ፣ የአማራ ህዝብም በቆራጥ ልጆቹ ደም አፍሳሽ መስዋዕትነት የጭቆናውን ቀንበር አሽቀንጥሮ እንደሚጥል ጥርጥር የለንም። ​ትግላችን በግለሰቦች መምጣትና መሄድ፣ መኖርና አለመኖር ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፤ በተጨቆነው ህዝባችን መኖርና አለመኖር ላይ የተመረኮዘ የታሪክ ግዴታ ነው። እናንተ በየጠቅላይ ግዛቱ ያላችሁ የንቅናቄያችን አባላትና አመራሮች እየሰራችሁት ያለው ጀብዱ ማንም ሊያስቆመው የማይችል የጭቁን ህዝብ ማዕበል ነው። ጠላቶቻችን በድዳቸው ብቻ እንዲያላምጡ እያደረጋችሁ መሆኑን ተረድታችሁ፣ እራሳችሁን ለተሻለ ኃላፊነትና ግዳጅ እንድታዘጋጁ አሳስባለሁ። ክርስቶስ በፅናትና በቆራጥነት ሞትን ድል እንዳደረገው ሁሉ፣ እኛም የጥላቻንና የሀሰት ትርክትን የእዳ ደብዳቤ ለመቅደድና ለመቅበር ሁሉን ቻይ መሆን ይጠበቅብናል። ክርስቶስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተንገላታውና የተዋረደው ለ38 ዓመት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ሲሰቃይ እራሱ በፈወሰው "መፃጉ" እንደነበረው ሁሉ፣ ዛሬም የአማራ ህዝብ እየተዋረደና እየተንገላታ ያለው በራሱ "ይሁዳዎች"ና በራሱ "መፃጉዎች" ነው። ​ሆኖም ግን አቋማችን ፅኑ ነው፦ "ላንቋጨው የጀመርነው ትግል፣ ላንጨርሰው የጀመርነው ጉዞ የለም!" የዛሬው መከራችን ነገ ወደ ብሩህ ትንሳኤ መሸጋገሪያችን ነው። ​ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ፊታውራሪ ባዩ አለባቸው ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ

በጽኑ ትግላችን ጠላቶቻችንና ከሃዲዎች የጫኑብን የጥፋት አዋጅ ይገፈፋል፤ የህዝባችን ትንሳኤም ይበሰራል። እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ። የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ  ንቅናቄ (አፋብን) ለክርስተና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ይላል። ከጌታችን ትንሳኤ የምንማረው በሀቅ እና በእውነት መንገድ የፀኑት ማሸነፋቸው አይቀሬ መሆኑን ነው። የአማራ ህዝብ በሀሰተኞች ህግና ማሰሪያ፤ በአረመኔወች ድብደባና ጭፍጨፋ አንገቱን ደፍቶ ፣ ነፃነት አጥቶ  ተሳዳጅና ተቀብዝባዥ ሆኖ እንዲኖር ዘመናትን የተሻገረ የሴራ ትብታብ የተገመደበት ቢሆንም አንገቱን ቀና አድርጎ ለማንነቱና ለክብሩ የሚዋደቀው አዲሱ የትንሳኤ ትውልድ ከመከራው ሸለቆ መሐል ተከስቷል። የአማራ ህዝብ ትንሳኤ አይቀሬነትም በሰራዊታችን ቀጣይነት እና ተከታታይነት ያላቸው ደማቅ ድሎቹ ተረጋግጧል። በጠላት ልብ ውስጥ ተሰብሮ የተቀመጠ ወይም ላይነሳ የተቀበረ ተደርጎ የተነገረበት ፣ በከሃዲውችና በሀሰተኞች ልቦና ውስጥ የትግሉ ፍሬ እንደማይታይና እንደማይበላ ተደርጎ የተተረከበት የአማራ ህዝብ  በጀግናው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሰራዊት እና ደጋፊ ህዝባችን ልቦና ውስጥ በተከተበው አዲሱ ተስፋ እና የሰመረ ተጋድሎ አማራ ህልውናዉን ማረጋገጥ የሚችል፤ ለትንሳኤው የቀረበ ሆኖ በሁሉም እዕምሮ ውስጥ ተስሏል። በዚህ አጭር ጊዜ ህዝባችን ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ጦርነት አዋጅ እና ያልተቋረጠ ሁለንተናዊ ጥቃት በጽኑ ትግል መመከት ችለናል። በትግላችን የአማራ ህዝብ የትንሳኤ መንገድ ተልመን የጀመርነው መንገድ የመከራውን ቀንበር ጨርሶ በማስወገድ ትንሳኤው የሚገኝበትን ግልፅ አስቻይ ሁኔታ ፈጥሯል። በዚህ ትልም የአማራ ህዝብ የህልውና  አደጋ ተቀልብሶ ትንሳኤው የሚበሰረው በልጆቹ ክንድ ፣ በልጆቹ ድርጅት ፣ በልጆቹ ልብና በልጆቹ የሰላ አዕምሮ በሚፈጠረው ፖለቲካዊ ንድፍ እና በዚያ ላይ የተመሠረቱ ትግል ስልቶች እና ወታደራዊ ጥበቦች መሆኑን ያስመሰከረ ተቋም ገንብተናል፣ የድል ጉዞም ጀምረናል። የህዝባችን ትንሳኤ ካለጥርጥር የሚበሰር  መሆኑን  የተረዱ የጠላት ኃይሎች ድምፃቸውና ጩኸታቸው ብቻ ሳይሆን ሴራቸውና የክፋት ሰንሰለታቸው ተበጣጥሶ ጉልበታቸውና አቅማቸው ሟሽሾ የምናይበት ጊዜ ቅርብ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚመራው የህልውና  ትግላችን የድል እንድርድሪቱን ቀጥሎ በተሟላ አሸናፊነት ትንሳኤውን ለማብሰር ወሳኝ የመታጠፊያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ይህ ለአማራ የመነሳት ዘመን ነው። በራስ ጠልነት የአማራን ህዝብ ያሻሻጡ፤ በሽራፊ ገንዘብ ደልለው የሸጡ፤ በህዝባችን ህልውና ላይ ሞት፣ ፍጅት ፣መፈናቀልና ሀገር አልባነትን ፈርደውና አውርሰው እጃቸውን ከደሙ ንፁህ ነኝ ለማለት የታጠቡና እወደድ ባይ አቂያቂረኞች የሚያፍሩበት፣ የሚፀፀቱበትና አንገታቸውን የሚደፉበት እና ጨርሰው የሚወገዱበት የታሪክ ምዕራፍ ነው። ከዚህ በተቃራኒ በህዝባዊነት የጸኑት እና በአማራዊ ብሔራዊ ቁጭት እና ንቃት ዘወትር በሁሉም የትግል መስኮች ለህዝባዊው አላማ ለሚለፉት የትንሳኤ ዘመን ነው። እርግጥ የጦርነት ዘመን ነው። በታንኩም በባንኩም ከገጠመን የአብይ አህመድ ሰራዊት ጋር ጦርነት የገጠምንበት ዘመን ነው። እንዲሁም ከአማራው አብራክ የወጡ  ግን ደግሞ በክህደት በሁሉም መስክ ህዝቡን አቆርቁዘው ለጥቃት ብሎም ለህልውና አደጋ ያጋለጡት እና በታሪኩ ሆኖ በማያውቅ ደረጃ  የህልውና አደጋ ውስጥ እንዲገባ ካደረጉት ጋር ፊት ለፊት የገጠምንበት ዘመንም ነው። አገዛዙ እና ለአገዛዙ ያደሩ "የእኛ ሰዎች" በክህደት ከሚፈጽሙት ውድመት ለመውጣት የራስን ብሔራዊ አስተውሎት፣ የራስን የትግል መንገድ ቀይሶ እና በራስ በቅነት እንዲነሳ ብሎም  አማራነትን ምሉዕነት እና ስምረት ባለው ልክ ዳግም ለመትከል የምንፋለምበት የጦርነት ዘመን ነው። ግን ደግሞ ጦርነቱ የትንሳኤ ምልክትም ነው። ለህልውና አደጋ ያጋለጡንን ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮችን እና መግፍሔወቻቸውን ስንረዳ፣ የህዝባችንን የቆዩ ብሔራዊ አስተውሎቶች ስንመረምር እና ስናውቅ ብሔራዊ ንቃት የተላበሰ ትውልድ መፍጠር እንደሚቻል በተግባር ተምረናል።  ይህ ምዕራፍ ለመራር ተጋድሎ በጋራ እንነሳ ዘንድ ያስቻለንን ብሔራዊ ቁጭት ፈጥሯል። ይህም ጠላታችንን ለይተን በየዘርፉ እንድንፋለመው በማድረግ የአሸናፊነታችን ማመሳከሪያ ሆኗል። ጥንትም ሆነ ዛሬ፣ በፖለቲካዊ ትግሉ አለም'ም ሆነ በመንፈሳዊ አስተምህሮ በሀቀኝነት እና በጽናት የሚደረግ ተጋድሎ ፍጻሜው አሸናፊነት ነው። ይህ ትውልድ ካለጥርጥር በቀራኒዮ አደባባይ በህዝባችን ላይ የተቸነኩሩ የበደል ችንካሮችን በደሙና በአጥንቱ ነቅሎ ይጥላል። ጠላቶቻችን በሴራ ቀብረነዋል ያሉትን የአማራ ህዝብ እውነት ብሎም ሀቀኛ ሀገር ወዳድነትንና ነፃነትን ዳግም ያስነሳል። በመፅናት ከስቅለት በኋላ ትንሳኤ እንዳለ ሁሉ ከትንሳኤ በኋላም ህይወት በህግና በመርህ የመመራቱ ግዴታ እንደመጣው ሁሉ ድርጅታችን አፋብን ከድል በኋላ ለህዝባችን የሚመች፥ የሚቆም፥ የሚታመን ስርአት ለመገንባት የጀመራቸውን ድርጅታዊ  የመዋቅር ዝርጋታዎች ፥  ሁለንተናዊ ትስስሮች አጠናክሮ በማስቀጠል ህልውናችን በፀና ብሔራዊ የአንድነት ክንድ እንዲረጋገጥ በየዕለቱ እየተጋ ይገኛል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተተበተቡ የሴራ ድሮችን በመበጣጠስና የተቀመጡ የአላማ መዳረሻዎችን በማጤንና በማጠናከር  ከዕለት ወደ እለት የህዝባችንን የህልውና አደጋ እየቀነሰና እያከሸፈ ወደ ሙሉ የነፃነት ጉዞ መስመር የገባ ሲሆን ድላችን እየተቃረበ ይገኛል። ዘመናትን በተሻገረ የሀሰት ድሪቶ በወለደው ፖለቲካዊ ትርክት የህልውና አደጋ ላይ የወደቀው ህዝባችን የትላንቱን ብሔራዊ አስተውሎት ከዘመኑ ጋር በስምረት በሚያዋድድ የትግል ስልት ጠላታችንን ድል እንነሳ ዘንድ አፋብን የትግል ጥሪ ያስተላልፋል። ግጭትን፣ ጭካኔን፣ አረመኔነትን፣ ህግ አልባነትን በማለማመድ ኢትዮጵያን ወደ ድንጋይ ዘመን እየመለሰ ያለውን አገዛዝ ለማስወገድ የምናደርገውን ፅኑ ተጋድሎ አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑንም እናረጋግጣለን። በድርጅታችን፣ በሰራዊታችን፣ በክንዳችን፣ በእውቀታችንና በህዝባችን የአላማ ፅናትና ድጋፍ ድል እንነሳለን፤ ትንሳኤያችንም ይበሰራል። ለዚህም እስከ ዛሬ ካደረግነው የበለጠውን በማድረግ ወሳኙን ድል ለመቀዳጀት የመጨረሻውን ፍልሚያ ለማድረግ በሁሉም መስክ እንዘጋጅ፣ እንትጋ። በመጨረሻም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ  ለሰራዊታችንና ለአመራሩ፣ በሀገር ውስጥና በወጭ ላለው ህዝብ ክርስቲያን እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ እያለ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እየተመኘ፣ የድርጅታችን አባላት በበዓል አከባበር ወቅት መደረግ ያለባቸውን የጥንቃቄ ተግባራት በሙሉ እንዲፈጸሙ እናሳስባለን።     የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ

እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደርሳቹህ አደረሰን 🙏🙏🙏 በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በሁሉም ቀጠና ያላቹህ የፋኖ አመራር እና አባላት እንዲሁም ህዝባችን የትንሳኤ በዓል ስታከብሩ ጥብቅ ጥንቃቄ አይለየን እያልኩ የጌታችን የመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል ስናከብር የተሰው የፋኖ አመራር እና አባላትን፣ የተሰው የፋኖ  ቤተሰብን በማሰብ ክብረ በዓሉን በምናከብርበት ሰዓት የአልኮል መጠጦችን በመቀነስ፣ መሰባሰብንና መዘናጋትን በመቀነስ የአገዛዙን የሰርጎ ገብ እና የድሮን ቅኝት/ጥቃት ጥንቃቄ በማድርግ በሁሉም ቀጠና የምትገኙ አመራር እና አባላት ማክበር እንዳለባቹህ ከወዲሁ እናሳስባለን። በጀግኖች ደም እና አጥንት የተገነበው አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር አመራሮች በስሩ የምትገኙ የሁለቱ የወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች፣ የሻለቃ አመራር እና አባላት የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች በዚህ ክብር በዓል ድርጅታችንን እና ክ/ጦራችንን ለማስከበር ከእውነት ጋር ቆመው ለአማራ ህዝብ መስዋት የሆኑ ጀግኖች ዕራይ እና ዓላማ አደራ ስላለብን የእነሱ አደራ በእኛ ትክሻ መውደቁን በመገንዘብ የነፃነት ታጋዩች በሙሉ የጠላትን እንቅስቃሴ በአይን ቁራኛ በመከታተል የመረጃ ስራችን ከመቸውም በላይ በፋኖ ቀጠና ለሚንቀሳቀሰው የሆላ ደጀኑ ህዝባችን የጥንቃቄ መልዕክት ይዳረስ እያልኩ በአሉ የሰላም፣ የጤና እንዲሆንላቹህ እመኛለሁ።     የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች የ64ኛ ክ/ጦር አመራሮች የእንኳን አደረሳቹህ መልዕክት አስተላልፈዋል።       ሚያዚያ 03/ዐ8/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዐ

ሬሽን ለመቀበል ከላሊበላ ከተማ ወደ ጋሸና የተንቀሳቀሰዉ የብርሃኑ ጁላ ግትልትል ሰራዊት በ303ኛ አሳምነዉ ኮር ድባቅ ተመታ! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነዉ ኮር አሃዶች የሆኑ
+1
ሬሽን ለመቀበል ከላሊበላ ከተማ ወደ ጋሸና የተንቀሳቀሰዉ የብርሃኑ ጁላ ግትልትል ሰራዊት በ303ኛ አሳምነዉ ኮር ድባቅ ተመታ! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነዉ ኮር አሃዶች የሆኑት 19ኛ ክ/ጦር  እና 16ኛ ክፍለ ጦር በጋራ በመናበብ  በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስደዉበታል። መነሻዉን ላሊበላ ከተማ አድርጎ ከወደ ጋሸና የመጣለትን ሬሽን ለመቀበል እየተንቀሳቀሰ  የነበረዉ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ የ12ኛ ክፍለ ጦር የአገዛዙ ሰራዊት በዛሬዉ ዕለት ማለትም በ ቀን 3/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 12:00 እስከ 9:00 ጀምሮ ሲቀጠቀጥ የዋለ ሲሆን ከ ወደ ጋሻና የመጣዉን ግትልትል ሰራዊት ነብሮቹ 16ኛ ክፍለ ጦር ድብኮ ላይ ሲያረግፉት የዋሉ ሲሆን ከወደ ላሊበላ የመጣዉን የአገዛዙ ሰራዊትን ደግሞ የሰማነ ግርፎች በሆኑት 19ኛ ክፍለ ጦር ዳቦ ከተማ  ላይ ጠቁር አስፖልቱን ግጥም አድርገዉ ዘግተዉ ሲወቁት ዉለዋል። በዚህም ዉጊያ ላይ ብዛት ያለዉ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን ብዛት ያላቸዉ መሳሪያዎች እና ተተኳሾችም ተማርከዋል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ (ቤተ-አማራ) ምኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 3/2018ዓ.ም

የትንሳዔ በዓል የገበያ ውሎን ለማስተጓጎል በሁለት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሰራዊት በፋኖ የተቀናጀ ጥቃት እንደተፈፀመበት ክፍለጦሩ ገለፀ። ሚያዚያ 03/2018ዓ.ም ሀይማኖታዊ በዓላትን በማስተ
+2
የትንሳዔ በዓል የገበያ ውሎን ለማስተጓጎል በሁለት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሰራዊት በፋኖ የተቀናጀ ጥቃት እንደተፈፀመበት ክፍለጦሩ ገለፀ። ሚያዚያ 03/2018ዓ.ም ሀይማኖታዊ በዓላትን በማስተጓጎል የሚታወቀው የብልፅግናው አገዛዝ ዛሬም እንደተለመደው በነገው ዕለት በህዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ በድምቀት ለሚከበረው የትንሳዔ በዓል ዋዜማ የህዝባችንን በነፃ ወጥቶ የመሸመት የቅዳሜ የገበያ ውሎ እንቅስቃሴን ለማስተጓጎል የብልፅግናው አገዛዝ በዘራፊ ሰራዊቱ በኩል ሞክሯል። ህዝባዊ ቅቡልነቱን ያጣው የአገዛዙ ሰራዊት መነሻውን ከመንዝ ማማ ወረዳ ሞላሌ ከተማ እንዲሁም ከመንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ በማድረግ ወደ ሸሾ የገጠር ከተማ ያመራ ሲሆን በቀጠናው በሚገኙ የአርበኞች ጦር ሰራዊት እና በምኒሊክ ክፍለጦር የተቀናጀ ጥቃት መፈፀሙን ክፍለጦሩ አስታውቋል። ከጠዋቱ 1:00 ጀምሮ እስከ እኩለ ቀን ድረስ በተደረገው አውደ ውጊያ የአገዛዙ 104ኛ ክፍለጦር እና እራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው ስብስብ የአማራ ህዝብ ነፃ አውጭ በሆነወ በጀግናው የአማራ ፋኖ ሰራዊት የተቀናጀ ውጊያ ጉዳት አስተናግዷል። እየተካሔደ ባለው የቅንጅት ውጊያ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የአፄ ምኒሊክ ክፍለጦር አሃድ በሆኑት የአባተ 1ኛ ሻለቃ እና የአርበኞች ጦር ሰራዊት የህዛባችን የቁርጥ ቀን ደራሽ መሆናቸውን ያሳዩበት ተጋድሎ እያደረጉ መሆኑን ክፍለጦሩ በላከው የግንባር መረጃው አስታውቋል። መረጃው👇 የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ነው ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

የትንሳዔ በዓል የገበያ ውሎን ለማስተጓጎል በሁለት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሰራዊት በፋኖ የተቀናጀ ጥቃት እንደተፈፀመበት ክፍለጦሩ ገለፀ።        ሚያዚያ 03/2018ዓ.ም ሀይማኖታዊ በዓላትን በማስተጓጎል የሚታወቀው የብልፅግናው አገዛዝ ዛሬም እንደተለመደው  በነገው ዕለት በህዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ በድምቀት ለሚከበረው የትንሳዔ በዓል ዋዜማ የህዝባችንን በነፃ ወጥቶ የመሸመት የቅዳሜ የገበያ ውሎ እንቅስቃሴን ለማስተጓጎል የብልፅግናው አገዛዝ በዘራፊ ሰራዊቱ በኩል ሞክሯል። ህዝባዊ ቅቡልነቱን ያጣው የአገዛዙ ሰራዊት መነሻውን ከመንዝ ማማ ወረዳ ሞላሌ ከተማ እንዲሁም ከመንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ በማድረግ ወደ ሸሾ የገጠር ከተማ ያመራ ሲሆን በቀጠናው በሚገኙ የአርበኞች ጦር ሰራዊት እና በምኒሊክ ክፍለጦር የተቀናጀ ጥቃት መፈፀሙን ክፍለጦሩ አስታውቋል። ከጠዋቱ 1:00 ጀምሮ እስከ እኩለ ቀን ድረስ በተደረገው አውደ ውጊያ የአገዛዙ 104ኛ ክፍለጦር እና እራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው ስብስብ የአማራ ህዝብ ነፃ አውጭ በሆነወ በጀግናው የአማራ ፋኖ ሰራዊት የተቀናጀ ውጊያ ጉዳት አስተናግዷል። እየተካሔደ ባለው የቅንጅት ውጊያ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የአፄ ምኒሊክ ክፍለጦር አሃድ በሆኑት የአባተ 1ኛ ሻለቃ እና የአርበኞች ጦር ሰራዊት የህዛባችን የቁርጥ ቀን ደራሽ መሆናቸውን ያሳዩበት ተጋድሎ እያደረጉ መሆኑን ክፍለጦሩ በላከው የግንባር መረጃው አስታውቋል።               መረጃው👇 የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ነው        ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''     ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

ከአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ የተሰጠ የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ    ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና በየግንባሩ ለምትገኙ የሰራዊታችን አባላት በሙሉ፤ በመጀመሪያ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና የትንሳኤ በዓል እንኳን በፅናት አደረሳችሁ። የሰው ልጅ በኃጢአት ቀንበር ወድቆ ሲማቅቅ፣ ክርስቶስ ለአለሙ ሁሉ መዳን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ የሰውን ልጅ የሞት ደብዳቤ ደምስሶ ለሚያምኑት ሁሉ የዘላለም ልጅነትን ሰጥቷል። ይህ ዕለት ፍቅር ድል ያደረገበት፣ የሰው ልጅ በደል የተሰረዘበት፣ የትህትና እና የቤዛነት ታላቅ ምስጢር የታየበት ታላቅ ቀን ነው። በአሁኑ ወቅት አንባገነኑ የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጆ፣ በየቀኑ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ይገኛል። ዛሬ ህዝባችን የልማትና የዲሞክራሲ ጥያቄ ቀርቶ "በህይወት የመኖር መብቱ" እንኳን ቅንጦት ሆኖበታል። በታሪካችን አይተነው በማናውቅ መልኩ፣ ከውጭ በሚሸመት የጦር መሳሪያ ድብደባ እንዲሁም በአገዛዙ ዘራፊ ጦር ግፍና መከራ እንደ ዶፍ እየወረደበት ይገኛል። ይሁን እንጂ ህዝባችን ይህንን የመኖርና ያለመኖር የህልውና ትግል አምርሮ እየታገለ፣ የተደቀነበትን የሞት ደብዳቤ ቀዶ በመጣል በቅርብ ቀን ነፃ እንደሚወጣ አንጠራጠርም። ይህ አረመኔ አገዛዝ የአማራ ህዝብ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች እንዲቋረጡ፣ ሀብትና ንብረቱም እንዲወድም ሆን ብሎ የሚሰራ ጨካኝ ስብስብ መሆኑ ዛሬ ለዓለም ግልጽ ሆኗል። በመሆኑም የዘንድሮው የፋሲካ በዓል ሲከበር እንደ ወትሮው ሁሉ አስፈላጊው ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እንዲሆን እያሳሰብን፤ ሃይማኖታዊ በዓሉን ስናከብር ይህን የመከራ ጊዜ በመተሳሰብ እንድናሳልፈው ጥሪያችንን እናቀርባለን። በተለይም፦ • በዚህ የህልውና ትግል የተሰዉ ጀግኖችን ቤተሰቦች በመጠየቅ፤ • የቆሰሉ ጀግና ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በመንከባከብ፤ • እንዲሁም ደጋፊና ረዳት የሌላቸውን ወገኖቻችንን በመርዳት እንዲሆን መላው ህዝባችንን በአክብሮት እንጠይቃለን። በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የጸሎትና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ስለ እኛ መከራን የተቀበለና ፍቅሩን በመስቀል ላይ የገለጸልን አምላክ፣ ሰላሙንና በረከቱን በሁላችንም ላይ ያሳድርብን። መልካም በዓል! "ክብር ለተሰዉት ጀግኖቻችን!" "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!" አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ

ከአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ የተሰጠ የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና በየግንባሩ ለምትገኙ የሰራዊታችን አባላት በሙሉ፤ በመጀመሪያ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና የትንሳኤ በዓል እንኳን በፅናት አደረሳችሁ። የሰው ልጅ በኃጢአት ቀንበር ወድቆ ሲማቅቅ፣ ክርስቶስ ለአለሙ ሁሉ መዳን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ የሰውን ልጅ የሞት ደብዳቤ ደምስሶ ለሚያምኑት ሁሉ የዘላለም ልጅነትን ሰጥቷል። ይህ ዕለት ፍቅር ድል ያደረገበት፣ የሰው ልጅ በደል የተሰረዘበት፣ የትህትና እና የቤዛነት ታላቅ ምስጢር የታየበት ታላቅ ቀን ነው። በአሁኑ ወቅት አንባገነኑ የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጆ፣ በየቀኑ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ይገኛል። ዛሬ ህዝባችን የልማትና የዲሞክራሲ ጥያቄ ቀርቶ "በህይወት የመኖር መብቱ" እንኳን ቅንጦት ሆኖበታል። በታሪካችን አይተነው በማናውቅ መልኩ፣ ከውጭ በሚሸመት የጦር መሳሪያ ድብደባ እንዲሁም በአገዛዙ ዘራፊ ጦር ግፍና መከራ እንደ ዶፍ እየወረደበት ይገኛል። ይሁን እንጂ ህዝባችን ይህንን የመኖርና ያለመኖር የህልውና ትግል አምርሮ እየታገለ፣ የተደቀነበትን የሞት ደብዳቤ ቀዶ በመጣል በቅርብ ቀን ነፃ እንደሚወጣ አንጠራጠርም። ይህ አረመኔ አገዛዝ የአማራ ህዝብ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች እንዲቋረጡ፣ ሀብትና ንብረቱም እንዲወድም ሆን ብሎ የሚሰራ ጨካኝ ስብስብ መሆኑ ዛሬ ለዓለም ግልጽ ሆኗል። በመሆኑም የዘንድሮው የፋሲካ በዓል ሲከበር እንደ ወትሮው ሁሉ አስፈላጊው ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እንዲሆን እያሳሰብን፤ ሃይማኖታዊ በዓሉን ስናከብር ይህን የመከራ ጊዜ በመተሳሰብ እንድናሳልፈው ጥሪያችንን እናቀርባለን። በተለይም፦ • በዚህ የህልውና ትግል የተሰዉ ጀግኖችን ቤተሰቦች በመጠየቅ፤ • የቆሰሉ ጀግና ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በመንከባከብ፤ • እንዲሁም ደጋፊና ረዳት የሌላቸውን ወገኖቻችንን በመርዳት እንዲሆን መላው ህዝባችንን በአክብሮት እንጠይቃለን። በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የጸሎትና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ስለ እኛ መከራን የተቀበለና ፍቅሩን በመስቀል ላይ የገለጸልን አምላክ፣ ሰላሙንና በረከቱን በሁላችንም ላይ ያሳድርብን። መልካም በዓል! "ክብር ለተሰዉት ጀግኖቻችን!" "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!" አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ

ከአማራ ፋኖ  ብሔራዊ ንቅናቄ  ( አፋብን )የትግል ጎን ከቆሙ  የቤተ ክርስቲያን  አባቶች  ለሞዐ ተዋሕዶ  ሥራ አስፈጻሚ አባላት የቀረበ ጥያቄ !!!!!!!! 1ኛ. በፋኖ ስም ተደራጅታችሁ ድብቅ ማንፌስቶ እና  ርእዮተ   ዓለም የያዛችሁ መሆኑን  በተመለከተ ።። 2ኛ .ሁሉም ፋኖ በእኛ አስተሳሰብ እና አደረጃጀት የተሠራ  እና የተመሠረተ ነው ማለታችሁ   ።። 3ኛ. በትግሉ መካከል ገብቶ ፋኖን ከፋኖ  የመነጣጠል ሥራ ሲሰራ መቆየቱ። ማለትም አንዱን  ክርስቲያን አንዱን ጴንጤ አንዱን የዓለም ብርሃን ሌላኛውን  ሙስሊም  ሲቀጥል አንዱን አክራሪ ጿሚ ፀሎተኛ  ሌላኛውን በላተኛ  በማለት ሲከፋፍል ቆይቷል ።። 4ኛ.የአማራ ፋኖ  በተለያየ ድርጅት እና   መሥመር ተከፋፍሎ  እርስ በርሱ ሲመታታ በበነበረበት  ሰዓት የእርቅ መድረክ ፈጥሮ አንድ በማድረግ ፈንታ  ይባስ ብሎ እንዲያውም የሞዓ ተዋሕዶን ሐሳብ ያልተቀበለ ፋኖ ካለ ገደል መግባት ይችላል ተብሎ በሚዳያ መግለጫ ተሰጥቷል ።።።። 5ኛ. ሞዓ  ተዋሕዶ በ2014  በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት በተፈጸመ  ጊዜ 7 ጥያቄ ይዞ የተቋቋመ  ግብረ ኃይል ሲሆን  ፋኖ ሁኖ  ወደ ፋኖነት  የተቀየረው  መቸ ነው? 6ኛ. የአማራ ፋኖ  የትግል ጉዳይ   የመኖር እና የአለመኖር ጉዳይ መሆኑ  እየታወቀ  የሃይማኖት ጦርነት ነው የተነሳ እያላችሁ ሙስሊሙ እና ሌላው አማኝ በአማራነቱ እንዳይታገል  እንዳይደግፍ አድርጎታል ።።። 7ኛ.  ከውስጥ እና  ከውጭ ካለው ሕዝባችን ከተለያዩ ተቋማት  በአማራ ፋኖ ስም ከፍተኛ ፋይናንስ እየተሰበሰበ  ሞዐን  ለሚደግፉ ግለሰቦች  ብቻ  ሲታደል የቆየ መሆኑ ።።። አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ እዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ  እና ስራ አስፈጻሚ አርበኛ ሸጋ ጌታቸው ህልውናችን በተባበረ ክዳችን ጎደር አማራ ኢትጵያ