ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más4 393
Suscriptores
+724 horas
+2667 días
+1 44330 días
Archivo de publicaciones
ኅዳር 21/2018 ዓ.ም
***
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች የመልሶ ማደራጀት አፈጻጸም ሂደትን የኮሩ አመራሮች በተገኙበት በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ፈጣንና ታዕማኝ መረጃዎች እንዲደርሰዎ የቴሌግራም ቻናላችንን ይወዳጁን: ሸር ሸር ሸር
👇👇
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
Ab 1
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
Ab 2 https://t.me/abcdefghijklmnopqrstuvwxyz071167
Ab 3
https://t.me/minilik28
''''' ሰበር ዜና ''''
ሲሮጥ የመጣን አህያ አጥብቀህ ጫነው ይላል ያገሬ ሰው!!
ዛሬ በቀን21/03/2018 ዓ/ም በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር 1ኛ እና 4ኛ ሻለቆች የእነብሴ ሳር ምድር ሚሊሻንና አድማ ብተናን ሲቀጠቅጡት ውለዋል።
የይብሳና ፂዮን ማርያምን ለማክበር የአማራ ፋኖ አባላት ተዘጋጅተው ባለበት ፀረ ሀይማኖቱ የብልፅግና ቡድን አሰማርቶ የላካቸው ተላላኪዎች በተለያየ አቅጣጫ አሰፍስፎ ቢመጣም በጀግኖቹ የ74ኛ ክ/ጦር አባላት ተቀጥቅጦ የተወለደበትን ቀን እየረገመ አስከሬን ሳያነሳ ፈርጥጧል። በዚህ ውጊያ ስድስት አድማ ብተናና ሁለት ሚሊሻ ወደላይኛው ሲሸኝ ስምንት አድማ ብተናና አራት ሚሊሻ ማቁሰል ተችሏል። ከነዚህ መካከልም ሶስቱ ሪፈር የተላኩ ሲሆን ድሽቃ ተኳሹ ተገድሎ መሳሪያውም ከጥቅም ውጪ ሆኗል። በተጨማሪም አንድ ብሬን ተመትቶ የተሰባበረ ሲሆን ሸንሸሉን እያንጠባጠበ ፈርጥጧል።
የ4ኛና የ1ኛ ሻለቃ ተርቦችም ያለምንም መስዋዕትነት ድል በድል ሆነው እየጨፈሩ ተመልሰዋል።
ድል ለአማራ ፋኖ!!
አማራ ያሸንፋል!!
የእ/ሳ/ም/ወ/ጊ/መ/ሚዲያና ኮምኒኬሽን ሀላፊ
ፋኖ ይበልጣል ጥሩነህ
የስለጠና ጥሪ ማስታወቂያ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር አዲስ ሰልጣኝ የፋኖ አባላትን ለማሰለጠን በዝግጅት ላይ ይገኛል። ሆኖም ማንኛውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ስልጣኞች መሰልጠን የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. ዕድሜ ከ18 አመት በላይ/የሆነች
2. ከደባል ሱስ ነፃ የሆነ/የሆነች
3. ከማንኛውም ወንጀል ነፃ የሆነ/የሆነች
4. የሚሰጠውን ማነኛውም ግዳጅ በአግባቡ መወጣት የሚችል
5. የጤና ችግር የሌለበት/የሌለባት
6. የመመዝገቢያ ቦታ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በሚንቀሳቀስበት ሁሉም ቦታዎች
7. ፆታ ወንድ/ ሴት
8. የመመዝገቢያ ቀን ህዳር 21/30/2018 ዓ.ም በማንኛውም አካባቢ የምትገኙ ወጣቶች ትግላችንን በመቀላቀል መዋል ማደር ቅንጦት ሆኖበት በሰቆቃ ውስጥ ላለው የአማራ በጋራ እንቁም!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ድል ለአማራ ህዝብ
ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ስልጠናናክህሎት መምሪያ
ህዝባዊ ክብረበዓልን ለማደናቀፍ የሄደዉ የአገዛዙ ጥምር ጦር ሽንፈትን አስተናግዶ ተመልሷል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር በሸዋ ሀገረማሪያም መስኖ ማሪያም ለሁለት ቀን የዘለቀ አዉደዉጊያ በማድረግ ድል ተቀዳጅቷል።
በአያመቱ በድምቀት የሚከበረዉን የህዳር ፅዮን አመታዊ ክብረበዓል ለማደናቀፍ እና እኩይ የጥፋት ተልዕኮውን ለመፈፀም ወደ መስኖ ማሪያም ያቀነዉ የአገዛዙ የመጨረሻ ምሽግ ሰባሪ ኃይል በጀግኖቹ የኃይለማርያም ማሞ አናብስቶች ተመቶ ወደ መጣበት ሾላ ከተማ ተመልሷል።
የአገዛዙ ብልፅግና ጥምር ጦር ከሀገረማሪያም ከሰም ሾላ ገበያ ያለ የሌለውን ሀይሉን በ አራቱም አቅጣጫ ቢያሰማራም የሃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር አናብስቶች በአራቱም አቅጣጫ የመጣውን የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው መልሰውታል ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ቦጋለ ሻለቃ በገበሬ ሸንጎ ግንባር የገበዉን የጠላት ኃይል ከፍተኛ የሆነ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰችበት ሲሆን በሌላ ግኖባር ደግሞ የነዳኛቸው ሻለቃ እና የክፍለ ጦሩ ቃኝዎች በጋራ በመሆን በመስኖ ግባር የገበዉን የጠላቶ ኃይል ከበባ ዉስጥ በማስገባት በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ችለዋል።
በቅዱስኬ እና በጎርፎ እንዲሁም በመስቀለየሱስ ግንባር የገባዉን የጠላት ኃይል ደግሞ የቤዛ ሻለቃ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወደ መጣበት እንዲመለስ ማድረግ ችላለች።
ዛሬ በዋለዉ አዉደዉጊያ ከ9 በላይ የጠላት ኃይል ሙት ሲደረግ ከ13በላይ ደግሞ ቁስለኛ አስተናግዶ ወደ ሾላ ከተማ ተመልሷል።
በአዉደዉጊያዉ አንድ ከፍተኛ የጠላት አዋጊ መቶ አለቃ እስከወዲያኛዉ መሸኘቱም ተረጋግጧል።
በአዉደዉጊያዉ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ኮር ቦጋለ ሻለቃ፣ቤዛ ሻለቃ እና ዳኛቸው ሻለቃ የተሳተፉ ሲሆን ሰላም ሰው ሻለቃ ደግሞ ከአዲስ አበባ ቅርብ ርቀት ከሰም ኮረማሽ ንዑስ ወረዳ ላይ በሚገኘው ኮረማሽ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈፅማለች።
በፖሊስ ጣቢያው ላይ በተሰነዘረ ጥቃት የደረሰዉ ጉዳት በዉል አልታወቀም።
በሸዋ ሀገረማሪያም ከሰም ወረዳ መስኑ ቀበሌ በዋለዉ አዉደዉጊያ ከፍተኛ ሽንፍትን ያስተናገደዉ የአገዛዙ ሰራዊት የአርሶአደሩን ሰብል በማቃጠል የቂም ቁርሾዉን አወራርዷል።ዉጊያዉ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተደረገ ሲሆን የሃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር በድል አጠናቋል።
የዛሬዉን አዉደዉጊያ አርበኛ መለሰ ከሳዬ የሃይለማርያም ዋና ወታደራዊ አዛዥ እና አርበኛ አስር አለቃ ደፋሩ ተክለሚካኤል የክፍለጦሩ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ እንዲሁም የክፍለጦሩ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ዋሴ ማንጉዳይ እና ም/ዘመቻ አስር አለቃ ሀይሌ ካሳ በተሳካ ሁኔታ መርተዉታል።
በተያያዘ መረጃ እራሱን ጥምር ጦር እያለ የሚጠራዉ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል በቀን 10/3/2018 የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ለምን ለማህበረሰቡ አገልግሎት ትሰጣላችሁ በማለት እገዳ በመጣል በእያንዳንዱ አሽከርካሪ 500 ብር ቅጣት በመጣል አሳፋሪ ተግባሩን በግልፅ አሳይቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአንጎለላ እና ጠራ ጫጫ ወረዳ እንዲሁም በፊጦና አላ መስኖ ቀበሌ የአብይ አራዊት ሰራዊት እና የብአዴን ቅጥረኛ ፖሊስና ሚሊሻ ወጣቱን በማፈስ ወደ አልታወቀ ቦታ መዉሰዱን የአይን እማኞች ለኃለማሪያም ማሞ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መረጃዉን አድረሰዋል።
ከታፈሱት መካከል አንድ ወጣት በሁለት ፖሊሶች ተደብድቦ ከባድ ጉዳት ማስተናገዱ ተገልጿል።አፈሳውን እየመራ እና የአገዛዙን አጀንዳ እያስፈፀመ ያለው ደግሞ አረጋ ሞገስ የሚባል የጉልባና ቃፈሮ ቀበሌ ሊቀመንበር እንደሆነም ታዉቋል።
በሌላ መረጃ በኦሮሚያ ሸኖ ከተማ ከዘጠና( 90) በላይ የአማራ ተወላጆች መታሰራቸዉ ተሰምቷል። ወጣቶቹ የታሰሩት በብሄራቸዉ ምክናየት መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል።
መድረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
መረጃዉ የሃይለማርያም ማሞ ክፍለጦ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ሀቀኘዉ ይታፈር!!
54ኛ ክ/ጦር ከሞጣ እና ሰዴ ወረዳ ከሲቪል ሰርቫንት ሰራተኞ እና ቢቡኝ ወረዳ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሄደ!
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር ከሞጣ እና ሰዴ ወረዳ ሲቪል ሰርቫንት ሰራተኞች እና ቢቡኝ ወረዳ ማህበረሰብ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች እና የፋኖ ትግል አሁን ላይ የደረሰበትን ሁኔታ በማስረዳት በቀጣይነት በሙያቸው ህዝብን ማገልገል እንዳለባቸው እና ከህዝቡ ጎን በመሆን የተጋረጠብንን አዳጋ በጋራ ማስተካከል እንደሚገባ ስምምነት መድረስ ተችሏል።
ህዳር 21/2018 ዓ.ም
አዲስትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስተስፋ
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ባለሽርጡ ክፍለጦር ለተከታታይ ሁለት ቀናቶች ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገበ‼️
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ ቁጥር 8 ጠዶት በተባለው አካባቢ የመጣው የአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ጋር በተደረገው ተጋድሎ አይበገሬው የባለሽረጡ ክፍለ ጦር ኮማንዶ ፋኖዎች ከህዳር 19 እስከ ህዳር 21/2018 ዓ.ም ሲቀጠቅጡት ዉለዉ አድረው ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት እንዲመለስ በማድረግ ድል አስመዝግበዋል::
በመርሳ አቧሬ ገብርኤል ቤተ ክረስቲያን ከ16 በላይ አስከሬኑን በጅምላ ቀብር ሲፈፅም በመርሳ ሆስፒታል ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ቁስለኛ በህክምና ላይ ይገኛል:: በዚህም የመርሳ ከተማና አካባቢው ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና ቦታው በመጨናነቁ የተነሳ በመጉላላት ላይ ይገኛሉ።
በዚህም የተበሳጨው የመከላከያ አዛዥ ሚሊሻዎችን እናንተ ናችሁ መረጃ ያወጣችሁብኝ በማለት ከአራት በላይ ሲረሽን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሚኒሻ እንደታሰረ የውስጥ መረጃችን አድርሶናል። የጠላት ሰራዊት ጠዶት ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ምሽግ ምሶ ውጊያ በማካሄድ ለሃይማኖቱ ክብር እንደለለው አሳይቷል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
21/ዐ3/2018 ዓ.ም
መራራ እውነት ነው የያዝነው።
ታሪኩን የማያውቅ ሰው ከሴቶቹ መካከል እናቱን ለይቶ እንደማያውቅ ይቆጠራል። እንደሚባለው ሁሉ
ታሪኩን ፣ እሴቱን እና ባህሉን አውቆ የህልውናውን አደጋ ተረድቶ መራራውን ሀቅ ይዞ እየመረረውም እየጣፈጠውም ፤ እየተደሰተም እየተከፋም ለትልቁ አላማ የሚታገለው አዲሱ ትውልድ (ንስሩ) የሚቆመው አላማውን ሲያሳካ ብቻና ብቻ ነው።
ታሪካቸውን የማያውቁ ቁራዎቹም ደንቀራዎቹም ፤ መሀል የበቀሉ እንግርዳዶች እና አረሞች ጠንከር ሲል እየተነቀሉ ይወድቃሉ ፤ እየደነበሩ ይበራሉ።
ሰሞኑን አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ አደረጃጀቱ ሲዘምን ፤ ተቋሙ ሲጠነክር ፤ መጠያየቅ ሲመጣ ፤ አንጃ እና ሰፈርተኝነት ሲጠፋ ፤ ለሰርጎ ገቦች የማይመች ሲሆን እና ሲነቃባቸው ተልዕኳቸውን ሳያሳኩ እየፈረጠጡ ይጠፋሉ። እነዚህ ታሪካቸውን እና አላማቸውን የማያውቁ በሆዳቸው የወደቁ ታሪክ ራሱ ይጠይቃቸዋል።
በእንግርዳድ የማይሰክር፤
በቁራዎች የማይደናበር፤
እንደንስር በከፍታ በሮ
ከአላማው ይደርሳል፤
ከከፍታው ይነግሳል።
" በቅርቡ ድል እና ደስታ አለን"
አዲስ ትውልድ❗️አዲስ አስተሳሰብ❗️አዲስ ተስፋ‼️
አፉ ባላገሩ Afework yohannes
ወጣቱ ሁለት የአገዛዙ ወታደሮችን አንገት አንቆ ባህር ውስጥ በመስጠም የአጥፍቶ ጠፊ እርምጃ ወሰደ!
ዮናስ ክንፈ ይባላል። ገና የ24 አመት ወጣት ነበር። ተወልዶ ያደገው አንጎት ወረዳ 01 ቀበሌ ውስጥ ነው። በዚህ ወረዳ ከዚህ ቀደም የወረዳው የሚኒሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በፋኖ መገደሉ ይታወቃል።
ከሚኒሻው ግድያ ጋር ተያይዞ ዮናስ ክንፈን የአገዛዙ ወታደሮች ከቤቱ አፍነው በመውሰድ ያሰቃዩታል። ለአንድ ወር ሲያሰቃዩት ከርመው ምንም አይነት የወንጀል ፍንጭ ሲያጡበት ከአንድ ወር እገታ በኋላ ተለቆ ወደ ትውልድ ቀየው ተመለሰ።
ፀረ አማራው ኃይል፡ ዮናስን"መልክህ አላማረንም" በሚል ሰበብ እንደገና የክፋትና የስቃይ መረቡን ያጠምድበታል። ዮናስ የአረመኔዎችን እንቅስቃሴ ተመልክቶ አካባቢውን ለቆ ተሰወረ። ሌላ ቦታም የቀን ስራም ቢሆን እየሰራ ለመኖር የትውልድ ቀየውን ለቆ ተሰደደ።
ዮናስ ሀገር ለቆ መሰደዱን የሰማው የብልፅግና ኃይል፡ የዮናስን አባት ከመኖሪያ ቤታቸው ሂዶ በማፈን ለእስር ይዳርጓቸዋል።
ዮናስ የአባቱን በአረመኔዎች እጅ መውደቃቸውን ሲሰማ እራሱን በአባቱ የስቃይ ቦታ ላይ ለማድረግ ወስኖ ወደ አረመኔው የአገዛዙ ሰራዊት መጥቶ እጅ ሰጠ።
የፋሽስቱ ዐብይ አህመድ ገዳይ ወታደሮች ዮናስን እደተራበ ጅብ እያፋሸጉ ተቀበሉት።
ዮናስን ልብሱን አስወልቀው እርቃኑን አቁመው ለመስማት የሚሰቀጥጥ፡ ለማየት የሚዘገንን ግፍ ፈፀሙበት።
እጆቹን የፍጥኝ ወደኋላ አመሰቃቅለው 8 ቁጥር እስር ካሰሩት በኋላ በገላው ላይ በእሳት የሚነድ ላስቲክ አንጠባጠቡበት።
በላስቲኩ የእሳት ጠብታ ተቃጥሎ ስጋው ቀልጦ አጥንቶቹ ጠቁረው እስኪታይ ድረስ እጅግ ከባድ ግፍ ፈፀሙበት።
በመጨረሻም ዮናስ፡ ከዚህ ስቃይ ይገላገል ዘንድ ጨፍጫፊዎቹን "የደበቅኩት መሣሪያ አለኝ እሱን ልስጣችሁ ወደ ደበቅኩበት ቦታ ውሰዱኝ" ይላቸዋል።
ደብዳቢዎቹም ለአለቃቸው ሂደው ይነግሩታል። "ጥሩ መሳሪያውን አምጡት ይሄማ ጥሩ ብር ነው። ሽጠን ወደ ኪሳችን እናደርጋለን። ከዚህ ጦርነትኮ ያለን ትርፍ ገንዘብ ነው።ሰለዚህ ከደበቀበት ቦታ ያሳያችሁና መሣሪያውን አምጡ" የሚል መልክት ሲሰጣቸው ዮናስን በላስቲክ የተቃጠለ አካላቱን ልብስ አልብሰውና ሸፍነው መሳሪያውን ከቀበረበት ቦታ እንዲወስዳቸው አደረጉት።
ዮናስ አንድ ውሳኔ በልቡ ወስኗል። በጋዞ ከሚገኝ እግድ ባህር ከሚባል ቦታ ላይ እንደደረሱ መንገዳቸው በባህሩ ዳርቻ ነበር።
ዮናስ፡ ከተከተሉት ሶስት የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የሁለቱን ወታደሮች አንገት አንቆ በመያዝ ወደ ጥልቁ ባህር ይዟቸው ሰጠመ።
ዮናስ ገዳዮቹን ገሎ ራሱን ከስቃይ ታድጎ የፀጋ፣ የክብር፣ የጀግና ሞትን ሞተ።
ሦስተኛው የመከላከያ ሰራዊት አባል፡ ዮናስ ሁለቱ ጓዶችህን ባህር ገፍትሯቸው እሱም ሲገባ አንተ ምን አየሰራህ ነበር በሚል ትጥቅ እንዲያወርድ ተደርጎ ተረሽኗል።
የሁለቱ መከላከያ ሰራዊት አባላት አስከሬን እና የዮናስ ክንፍ አስከሬን ከሰጠሙበት ባህር በስምንተኛው ቀን ተንሳፎ ታየ።
የአገዛዙ ወታደሮች የራሳቸውን አስከሬን ከባህሩ አውጥተው ከቀበሩ በኋላ የዮናስን አስከሬን አናስወጣም በሚል የከለከሉ ቢሆንም፡ የአከባቢው ማሕበረሰብ "ከዚህ በላይ ምን ልታደርጉት ነው?" በሚል ቁጣና እቢተኝነት የዮናስን አ*ስ*ከ*ሬን ከባህሩ አውጥተው ተወልዶ ባደገባት መንደር የጀግና ስርዓተ ቀብር ፈፀሙለት።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!
ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም
ከሰሞኑ በፋሽሽቱ አብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ገዳይ ቡድን በቀን 14/03/2018 ሰከላ ወረዳ አጉት ቀበሌ ጥልም ት/ቤት የተፈጸመውን አሳዛኝ የንጹሀንን ጅምላ ግድያ የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በዛሬው ዕለት በሰከላ ወረዳ አጉት ከተማ ተካሄደ።
የንጹሀንን ሞት እናወግዛለን!!!
በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረገውን ጅምላ ግድያ እናወግዛለን!!!
የሴትችን መደፈር እናወግዛለን!!!
የሴቶችን ግድያ እናወግዛለን!!!
መከላከያ ንጹሀንን በጅምላ ገድሏል!!!
መከላከያ ሴቶችን በቡድን ደፍሯል!!!
መከላከያ የሀይማኖት ተቋማትን አውድሟል!!!
መከላከያ ሴቶችና ህጻናትን በጅምላ ገድሏል!!!
መከላከያ ጤና ተቋማትን አውድሟል!!!
መከላከያ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል!!!
ብልጽግና ገዳይ ቡድን!!!
ብልጽግና አምባ ገነን አሸባሪ ቡድን ነው!!!
አብይ አህመድ አሸባሪ ነው!!!
አብይ አህመድ ገዳይ ነው!!!
አብይ አህመድ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል!!!
መከላከያ ከአማራ ክልል ይወጣ!!!
አብይ አህመድ በአለም አቀፍ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት መጠየቅ አለበት
አሜሪካ ለብልጽግና እርዳታዋን ታቁም!!!
አረብ ኤምሬት ለብልጽግና የምታደርገውን እርዳታ ያቁም!!!
የሚሉ መፎክሮች በአደባባይ ተስተጋብተዋል።
ፈጣሪ በግፍ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንን ይማር🙏🏽
ድል በግፍ ለሚጨፈጨፈው ለአማራ ህዝብ✊🏽
ድል በእውነት ስለውነት ታግለው ለሚያታግሉ ፋኖዎች✊🏽
" ጥቃቱን ማስቆም የሚያስችል የተገኘ መፍትሄ የለም " - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የሚፈጸመው የምዕመናን ግድያና እገታ አሁንም አለመቆሙን የአርሲ ዞን ሀገረ ስብሰትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በቤተክርስቲያኗ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መጋቢሰላም ሰለሞን ቶልቻ፣ በዞኑ ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ሰሞኑን፣ " 14 ሰዎች ታግተው ከታገቱት ውስጥ ገንዘብ ከፍለው 11ዱ ተለቀዋል፤ ሦስቱ አልተለቀቁም " ብለዋል።
ሆንቆሎ ዋቢ ወረዳ ቀቅሳ ቀበሌ ኀዳር 18 ቀን 2018 ዓ/ም " 11 ኦርቶዶክሳዊያን ተገድለዋል " የሚሉ መረጃዎች ከስፍራው ወጥተዋል፤ ይህን ሰምታችሁ ነበር ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ " እገታ ነው (የተፈጸመው) ፤ እኛ ባለን መረጃ ግድያ የለም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ባለፈው ሳምንት በዚሁ ወረዳ አንድ አርሶ አደር በታጣቂ ኃይሎች ተገድሎ ጀብ በልቷቸው፣ ጥፍርና አጥንቱ፣ ልብሱ ብቻ እንደተገኘ፣ የሟች ባለቤትም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባት አንድ የአርሲ ዞን ወረዳ ቤተ ክህነት አመራር ነግረውናል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት በበኩሉ፣ ህዳር 14 ለ15 አጥቢያ " በመርቲ ወረዳ ፈረቀሳ ጃዊ የሚባል ቦታ ሽመልስ ሙላቱ፣ አበራ ሽመልስ፣ ብርሃኑ ሽመልስ (ሁለት የሟች ልጆች ናቸው) የተባሉ ምዕመናን በቤታቸው ተገድለዋል " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ቤተክርስቲያኗ በአርሲ ዞን እየተደጋገመ ስላለው ጥቃት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለች ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ጥቃቱ በዞኑ እየተደጋገመ ቀጥሏል፤ ችግሩ እንዲፈታ ቤተክርስቲያኗ ምን እየሰራች ነው ? ሲል የጠየቃቸው በቤተ ክርስቲያኗ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መጋቢሰላም ሰለሞን ቶልቻ፣ " ከዚህ በፊት በነበረው ሁኔታም የምዕመናን ግድያው፣ እገታ እና ማፈናቀሉ እየተፈጸመ ነው። በየቀኑ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ? እያልን ነው ጥቃቱን ማስቆም የሚያስችል የተገኘ መፍትሄ የለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
" ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ተወያይቶበት አጣሪ ልዑክ ልኮ የአጣሪ ልዑካኑ መረጃ ለቋሚ ሲኖዶሱ ተሰጥቷል" ያሉት ኃላፊው፣ " ቋሚ ሲኖዶስ ወስኖ አፈናው፣ ስደቱ፣ መፈናቀሉ እንዲቆም ከሚመለከታቸው የፌደራሉና መንግስት የክልሉ አካላት ጋር ይወያያል በሚል እየጠበቅን ነው " ብለዋል።
" ሀገረ ስብከቱም ያሉትን ሪፓርቶች ይቀበላል፤ ይሰማል። ከማሳወቅ ውጭ ይሄ ነው የምንለው የተጨበጠ እስካሁን ድረስ የደረሰን ነገር የለም " ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ከግድያው፣ ከአፈናውና ከማፈናቀሉ ባሻገር ከፍተኛ የሥነ ልቦና አለመረጋጋት አለ በዞኑ፤ ነገ ምን ይመጣል? በሚል ነግቶ እስኪመሽ፣ መሽቶ እስከሚነጋ ድረስ አለመረጋጋት አለ። ስርዓተ አምልኮን ለመፈጸምም ሆነ ተረጋግቶ ህይወትን ማስቀጠል አልቻለም። ይሄ በየትኛውም መልክ በልዩ ትኩረት ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው " ብለዋል።
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ንፁሃን አማራዎችን በግፍ እየጨፈጨፈ ቀጥሏል::
የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ አንድ አቶ ብርሃኑ ተሾመ የተባለ አባት ከባለቤቱና ከአራት ልጆቹ ፊት በግፍ የገደለ ሲሆን ሁለት ዲያቆኖችንም ባደባባይ ረሽኗል::
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ንፁሃን አማራዎችን በግፍ ባደባባይ እየረሸነ ያለ ሲሆን ዛሬ ህዳር 21/2018 ዓ.ም ሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ መርጦ ከተማ ላይ አቶ ብርሃኑ ተሾመ የተባሉ የ48 አመት አባት ከባለቤቱ እና ከአራት ልጆቹ ፊት መኖሪያ ቤቱ ላይ በዱላ ደብድበው ባሰቃቂ ሁኔታ ገድለውታል::
በተመሳሳይ ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ስሙ አባርጎ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ሁለት ዲያቆኖች በፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት ባደባባይ በጥይት ተደብድበው በግፍ ተረሽነዋል::
እድሜያቸው 15 እና 18 አመት የሆኑት እነዚህ ታዳጊዎች ዲያቆንና የመድሃኒአለም ቤተክርስቲያን አገልጋይ ሲሆኑ የቀብር ስነስርዓታቸውም እዚያው ሲያገለግሉት በነበረው ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል::
ፋሽስቱ አገዛዝ ወጣቶችን ዩንቨርስቲና ትምህርት ቤቶች ብሎም ሃይማኖታዊ ቦታዎች ላይ ሳይቀር እያፈሰ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እያስገባ ያለ ሲሆን ሰሞኑን ወልድያ ከተማ ከአፈሳው ለማምለጥ የሞከሩ ንፁሃን ወጣቶችን ባደባባይ በጥይት ደብድቦ መግደሉ ይታወቃል::
ይህ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ንፁሃን ላይ ነፃ እርምጃ የመውሰድና በግፍ የመጨፍጨፍ ተግባሩ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፋኖ ትላልቅ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎች ከተጎናፀፈበት ዘመቻ "አባ ናደው" በኋላ ፋኖውን መቋቋም ሲያቅታቸው ንፁሃኑን መጨፍጨፍ በሚል በርካታ የሰው ህይወት በተናጠልና በጅምላ እያለቀ ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበሩ ክንዳችንዜ
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 21/2018 ዓ.ም
Amhara Political Detainees Taken From Detention Center to an Unknown Location
That was the news I heard yesterday. Because I still carried a vivid memory of Abdu’s condition from my visit last September, hearing this felt especially heavy.
Last September, I visited Abdurahman Ahmedin in Kilinto Prison. Abdu was one of the EDP founders I first met when I was a second-year student at AAU. He was among the people who oriented us when we visited their office near the stadium in Addis Ababa. Lidetu Ayalew and Mushe Semu were the others. I had been following Abdu’s writings and opinions on social media until about two years ago, when he suddenly disappeared. I don't even remember hearing about his arrest, but when I traveled to Ethiopia last September, I saw him in Kality with other prisoners — and it saddened me deeply. Because of his illness, he could not stand for long or hold a conversation.
Their lawyer, Solomon Gezahegn, had succeeded in getting the court to release them on bail. But shortly afterward, other officials intervened, abducted them, and took them to an unknown location. This is heartbreaking on many levels. What is even more devastating is witnessing a government involved in acts that amount to kidnapping — because that is exactly what it is when state officials seize individuals without explanation or lawful process.
Family members report that several political detainees who had been granted bail — including former House of Peoples’ Representatives member Ato Abdurahman Ahmedin — were taken from the detention center to an unknown location as they were leaving after completing the bail procedures.
Abdurahman Ahmedin, Mekonnen Desalegn, and Gizachew Tamir, who had been charged with “incitement to violence,” had been held for over a year before the court granted them bail set at 200,000 birr.
According to their families, when the three political prisoners were released today at 11:00 a.m. from Qilinto Prison, individuals who had been waiting at the gate seized them and forcibly took them away.
They added that one of the detainees — Abdurahman, a known patient with a fractured leg joint, who walks with a crutch and had relied on assistance even to use the restroom in the detention center, with sufficient medical documentation submitted — was nevertheless taken away by force in complete violation of the law, and no one knows where he has been taken.
The original Amharic news reads as follows:
የአማራ የፖለቲካ እስረኞች ከማረሚያ ቤት ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ
የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉን አቶ አብዱራህማን አሕመዲንን ጨምሮ ዋስትና የተፈቀደላቸው የፖለቲካ እስረኞች ሂደቱን ጨርሰው ከማረሚያ ቤት ሲወጡ ከበር ላይ ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ።
በሽብር ወንጀል የተከሰሱት አብዱራህማን አሕመዲን፣ መኮንን ደሳለኝና ግዛቸው ታምር
ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ በ 200 ሺ ብር ዋስትና ተፈቅዶላቸው ነበር።
በዚሁ መሠረት ሶስቱ የፖለቲካ እስረኞች ዛሬ 11:00 ላይ ከቂሊንጦ እስርቤት ሲወጡ በር ላይ ሲጠባበቁ በነበሩ ግለሰቦች ታፍነው መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።
Later, I talked to one family member/friend/lawyer who said: “This shows us another face of what we are living through. Beyond this, what more can we do? The only option we have left is to look to the heavens.”
ትግል የምትታገለው ብቻ ሳይሆን የምትጠብቀውም ነው!!
ከሰሞኑ ሰንፈጥ ያለ የማጥራት ስራ በመጀመራችን ሀቀኛ ታጋይና ህዝቡ በደስታ እየደገፈን ነው።
በአንፃሩ ወመኔዎችና ቀላዎጭ ሾተላዮች እየለየላቸው ነው።ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል በአጭር ጊዜ ታጥበን ተለቃልቀን የህዝብ ሮሮ የማይደመጥበት ሁነት እንፈጥራለን።
በተጀመረው ጥልቀት ያለው ምርመራና ጠንከር ያለ ርምጃ የነጋበት ጅብ በቀኝ በግራ እየተራወጠ ቀድሞ ባዘጋጀው ጎሬ ዘሎ እየገባ ነው።
ጥልቅ የማጥራት ርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል።ህዝብን የሚያማርሩ የትግላችን ጥገኞች መመንጠር በመጀመራቸው በአንዳንድ አካባቢዎች አንፃራዊ አዎንታዊ ለውጦች ተስተውለዋል።
ጥልቅ እርምቱ የህዝብ ቅሬታ ከመፍታትና የውስጥ ንፅህናን ከማስጠበቅ በላይ ትግልን በመጠበቅ በኩል ሁነኛ ፋይዳ ያለው መሆኑ ታምኖበት እየተከወነ ነው።ተጠናክሮም ይቀጥላል።
ከጥገኞች ጋር የዓላማ ትስስር ያላቸው ሁሉ ሳይጠሩ አለን ብለው ሲመጡ ይስተዋላል።ይህ የተንኮል ትስስር በጣጥሰን አሽቀንጥረን ከመጣል የሚገታን አንዳች ምድራዊ ኃይል ግን የለም።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
