Astu best ✍️
Ir al canal en Telegram
For Advertisement and promotion contact us on : @Bndennekek @Visionar1
Mostrar más1 155
Suscriptores
+124 horas
-47 días
+2230 días
Archivo de publicaciones
1 155
Repost from ASTU IGNITE ®️
📌 ወደ ካምፓስ ስንሔድ ምን ምን ነገሮችን ይዘን መሔድ አለብን❓
👉 ከበሶ እስከ ዳቦቆሎ
👉 ከለውዝ ቅቤ እስከ ማርማራታ
👉 ከሻንጣ እስከ .....
ሰላም ውዶች እንደምን አላችሁ ❓😊
📚 እስቲ ዛሬ ተማሪዎች ወደ ካንፓስ ሲገቡ መያዝ ያለባቸው ነገሮች እንመልከት ፦
📌 በምግብ ዘርፍ ፦
📚 እናትህ በር አንኳኩታ ከእንቅልፍ ቀስቅሳ ልጄ ቁርስ ደርሷል ብላ መጥራት ወፍ በቃ ቀርቷል ። አሁን ጠዋት 1:30 ተነስተህ ለሻይ እና ዳቦ መሰለፍ አለብህ በቀን 3ቴ ካልተሰለፍክ ዶርም ድረስ በሰሃን አይቀርብልህም መቼስ ደሞም እንደማሚ WOW የሚያስብል ግሪስ እንዳይመስል.... ናላ የሚያዞር ፈውስ ነው ሚቀርብልህ... ኮብል ከምስር ጋር ፥ ሽሮ ያለ ዘይት ፤ ስጋ ወጥ ያለ ስጋ ለመብላት ነው ተሰልፈህ የምትውለው። የASTU ግን የተሻለ ነው ከሌላው ፤ ጨውም ፣ ዘይትም ፣ ስጋም አለው 😅። አስበው በዛ ላይ ችከላ አለ ይሞረሙረሃል ከዛ እናትህ ትናፍቅሃለች ታዲያ በበሶ ካልሆነ በምንም አታገኛትም። በሶ ሆድ ብቻ መሙላት አይደለም ናፍቆት ማረሳሻም ነች ። ብትወድም ባትወድም በሶ ያዝ ፤ ኩኪስ ፤ ዳቦቆሎ ፤ የመሳሰሉ በባህላቹ ያሉ ደረቅ የስንቅ ምግቦች በደንብ ያዙ ታመሰግነኛለህ።
💡 በሶ
💬 በሶ ብትወድም ባትወድም ጥቂትም ቢሆን ያዝ መበጥበጡ ራሱ LIFE አለው ፤ ለአንድ ሴሚስተር ከ2-5 ኪሎ በቂ ነው ብዬ አስባለሁ ፍሬሽ ስትሆኑ ግን የካፌ ምግብ ስለማይስማማቹ እስከ 6 አርጋቹሁ ያዙ 😁 ። በሶ ስትይዙ ከቻላቹሁ በማሸጊያ ፌስታል አሽጋችሁ ብትይዙ ለመያዝም ያመቻቹሃል ለሙዱም አሪፍ ነው ። ፌስታል ግን ስለተከለከለ ብቻ በሆነ ነገር ያዙ።
💡 ኩኪስ ፡
📚እኔ ኩኪሲ በጣም ነው የምወደው ስለዚህ በኩንታል ልይዝ አስቢያለሁ እና በሶ ለማትወዱ አሪፍ መፍትኤ ነው ከ2-3 ኪሎ ለሴሚስተር ብትይዙ በጣም አሪፍ ነው ። ኩኩሲ ነፍስ የሆነ ነገር ነው ኩኩሲ በበሶ አስባቹሁታል ። ግን እመኑኝ ካልቆጠባቹሁ የዶርም ጀመኣ 3 ቀን አያቆያትም እና ስንቅ መሆኑን አስባችሁ ቢያንስ ሁለት ወር ማስቀመጥ ይኖርባቹሃል ። አገኘው ብላቹሁ ጨርግዳቹ ጨርግዳቹ በሳምንት ጨርሳቹሁ ጨላ ሲነጥፍ በኃላ ጉድ እንዳትሆኑ እንደውም ገንዘብ እስኪጠር ኩኪሷን አትንኳት ከነካቹሁም በቁጠባ ። 😁
💡 ዳቦቆሎ ፦
💬 ይቺም በጣም አሪፍ ነገር ናት እስከ 2 ኪሎ ብትይዙ አትጎዱም ። ስትተክዙ ማታከዣ ስትቸክሉ ማቻከያ ትሆናለች ። ዳቦ ቆሎም መቆጠብ አለበት እና ለቁጠባ አሪፉ መንገድ ማሸግ ነው ። 2 ኪሎው ዳቦቆሎ 3 እሽግ ፌስታል ቢወጣው አንድ እሽግ በወር የሚል ዕቅድ ይዛቹሁ መቆጠብ ትችላላቹሁ ።
💡 የለውዝ ቅቤ ፤ ማር ፤ ማርማራታ ፤ የመሳሰሉ የሚቀቡ ምግቦችም ፦
💬 ማር ካልሆነ አብዛኞቹ በከተማ ስለምታገኙ እዛው የዳቦ ዋጋ አጣርታችሁ የማይጎዳ ከሆነ ሸመትመት ማረግ ትችላላችሁ ነገር ግን የማር ሀገር የምትኖሩ ከሆነ በደንብ ያዙ ትፈወሳላችሁ እመኑኝ በተረፈ በቃ (ማር ሀገራቹሁ ምርጥዬ ከሆነ ይዛቹሁ ኑ ሌሎቹን ከመጣቹሁ ወዲህ በተመደባችሁበት መግዛት ትችላላቹሁ) ደሞ አንዳንድ ግቢ ፍራፍሬ በጣም ርካሽ ነው በተለይ ወደ ደቡብ ታዲያ ደቡቦች ለምግብ እንዳታስቡ ያረጋቹሃል ። አሁን ግን ኑሮ ተወዷል lol😁። ያው የጠገበ ስለትምህርቱ ስለማያስብ አትጎዱ እንጂ ሰርክ ሀሳባቹሁ ፈውስ መሆን የለበትም ተመርቋቹሁ ስራ ስትይዙ ታማርጣለቹሁ ለግዜው ያገኛቹሁትን ጠርጋቹሁ በደንብ ቸክላቹሁ በአሪፍ ግሬድ መመረቅ አስቡ ። አሪፍ ግሬድ ቢቀር እንኳን ቢያንስ የምትፈልጉትን ዲፓርትመንት ለማግኘት ታገሉ።
💬 ምግብ እንደሙዳችሁ የሚመቻችሁን እና በየሀገራችሁ ለስንቅ የሚዘጋጁ ነገሮችን ያዙ ( ግቢ መግባት የሚችሉትን ) ሽንብራም ፤ በሶም ፤ ማርም ብቻ ይሆናል ያላችሁትን እና የሚሞዳችሁን ፈውስ ያዙ ።
📌 በቁሳቁስ ዘርፍ ፦
💡 ሻንጣ ፦
📚 ብዙዎች ቀለል ብለው መግባት ይሞዳቸዋል ፥ አንዳንዶች ደሞ እንደ ሰርግ ካልታጀብን ይላሉ ብዙዎቻችሁ መረዳት ያለባችሁ ነገር ግቢ ስትገቡ የምትገቡ እናንተ እንደሞዳችሁ እና እንደአቅማችሁ ፥ እንደ አስተሳሰባችሁ እና ፍላጎቶቻችሁ እንጂ ስለ ሰዎች አትጨናነቁ እነሱ የራሳችሁ ቢዝነስ ይወርኩ ። እናንተ በራሳችሁ የሚሞዳችሁን እና የሚያስፈልጋችሁ ነገር አድርጉ ።
💬 ጀለስ 4 ግብዳ ሻንጣ ተሸክሞ ግቢ ስለሚቆሰው እኔም የሚል ፎክክር ትታችሁ ምንድነው ሚያስፈልገኝ ❓አቅሜ የቱ ያክል ነው ❓በሉ ቤተሰብ አታስቸግሩ ከሌሎች እኩል ለመሆን በሚል የFamily ኑሮ አታናጉ ። እናም እንደሙዳቹሁ ተራመዱ ። BE YOURSELF በቃ!! 😎
📚 ሻንጣ (እንደኔ) አንድ በጀርባ የሚነገት Bag ብትገዙ ( ከሌላችሁ ካላችሁ ግልግል ) እና ሌላ ትንሽዬ (የምትጎተተዋ) ብርድልብስ እና የመሳሰሉ ትልልቅ ነገሮች የምትይዙበት ሻንጣ ቢኖራችሁ አሪፍ ነው ።
💬 ለበዓል እና ለዕረፍት ወደ ቤተሰብ ስትመጡ ለቀናት የሚሆን ልብሳችሁን በጀርባ ሚነገተው Bag ትይዛላችሁ የተቀሩትን ደሞ በቀረችው ቦርሳ ግቢ ታስቀምጣላችሁ ( ሙሉ ዕቃ በየግዜው ስለማታንኳትቱ ማለት ነው) ነገር ግን እንደ ግቢው ርቀት ፥ እንደ እናንተ የሸመታ ብዛት ፥ እንደ ያዛችሁተ ዕቃ ነው የሚወሰነው ስለዚህ በፍላጎታችሁ መሰረት ብትይዙ መልካም ነው ።
🎗በተረፈ እንደኔ ከቻላችሁ ለክላስ የምትሆን አነስ ያለች በትንሽ ብር የምትገዛውን Bag እዛው ግቢ ብትገዙ አሪፍ ነው ( በፊት ካላችሁም ስትመጡ ዕቃ ነገር ያዙባት እና በዛው ትማሩባታላችሁ ። )
📌 የልብስ ሸመታ ፦
📚 ይሄም የሚወሰነው እንደደረሳችሁ ግቢ የአየር ንብረት እና የእናንተ ሙድ ነው ፤ መቼስ ሰመራ ደርሶህ መርጦ ሳትይዝ አትሄድም ፤ መቼስ ደብረብርሃን ደርሶህ ከጋቢ ማይተናነስ ጃኬት መያዝ አትረሳም ፤ ብቻ እንደግቢው እና ሙዳችሁ እና አቅማችሁ ይወሰናል ፤ ፋሽን ተከታይ ናችሁ ❓ዘናጭ ናችሁ❓ ደሃ ናችሁ ❓😁 ቀለል ያለ አለባበስ ይመቻቹሃል ወይስ ቂቅ ካካለችሁ ይጨንቃቹሃል ብቻ ሙዳችሁ ምንድነው ብላችሁ " እንደ ሙዴ " ብሎ መቀወጥ ነው። ASTU ግን ሙቀት ስላለ ቀለል ቀለል ያለ ነገር ያዙ።
ምን ያክል ልብስ ልያዝ ምናምን ለምትሉ (በግሌ)
💡 ለወንዶች ፦
📚 3-5 ሱሪ እና 1ቱታ ፤ 1 ቁንጣ ፤ 2-3 ቲሸርት ፤ 2-3 ሸሚዝ ፤ 1-2 ጃኬት ፤ 6-8 ካልሲ ፤ 3-5 ፓንት ፤ 2-3 ሽፍን ጫማ + 1 ነጠላ ጫማ ፤ 1-2 ቀበቶ ፤ የረሳሁት ነገር ካለ እጨምራለሁ ።
💡ለሴቶች ፦
📚 ሴቶች ግቢ ሲገቡ በጣም ግብዳ ሻንጣ ሲሸክፉ ሁሌ እመለከታለሁ ብዙ ግዜ በምንድነው የሚሞሉት ብዬ ጠይቄ መልሱ አላገኘሁም ። ለማንኛውም ሴቶችዬ የእናንተ አለባበስ ወዲ በሉት ወዲ ለማለት ትንሽ ይከብዳል ። ብቻ ከታይት እስከ ጉርድ እንዳሻችሁ እና እንደፍላጎቶቻችሁ ሸምቱ (ሂጃብ እና ነጠላውም እንዳይረሳ እህትአለም ... ግቢ ገባሁ ብለሽ ፈጣሪሽን አትርሺ ዋዋዋ ☝) እንደምክር Body ነገር በርከትከት አርጋችሁ ያዙ እኔ ነኝ ያልኳቹሁ ታተርፋላችሁ ።
ያም ሆነ ይህ ግን እንደሙዳችሁ እንደሚመቻችሁ እንደአቅማችሁ አድርጉ። አደራ አደራ ገና ለገና ግቢ ልገባ ነው ብላችሁ ቤተሰብ እንዳታስጨንቁ።
ይቀጥላል...
➕JOIN US👇
@Astu_Ignite
1 155
#ATTENTION 🚨
ASTU የተመደባችሁ ተማሪዎች Email Check አድርጉ ፤ መልዕክት ተልኮላችኋል። እዚያ ላይ የሚላችሁን እዚያው ላይ ጨርሱ በሚሰጣችሁ የ eStudent ሊንክ።
ሌላውን ለምዝገባ ስትመጡ ስለምትጨርሱ ተውት። አሁን የተባላችሁትን ብቻ አስተካክሉ።
@bestofastu
1 155
# Urgent Job Opening
# Qo'achistu dubara
# Adama Adababay Jawar
# Kutaa 6ffaa
# Torbeetti guyya 3
# Afaan oromo kan dubbattu
# Ji'an Qarshii 2500
# ሴት አስጠኝ
# አዳማ ጀዋር አደባባይ
# 6ኛ ክፍል
# በሳምንት 3 ቀን
# ኦሮምኛ የምትችል
# በወር 2500 ብር
Phone: 0994092795
: 0715864370
DM: @eluti_39
1 155
Repost from ASTU–POST
#የASTU_ገፅታ
(አዲስ መግባት ለሚፈልጉ ተማሪዎች Share Adrigulachewu)
1) ካፌ
👉 አብዛኛዉ ተማሪ ያማርራል እንጂ ASTU ካፌ ከሌሎች የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች ካፌ በ10 እጥፍ ይሻላል። ብያንስ ባይበላላችሁ እንኳን ይዋጥላችኃል ☺️። ሰልፉ ግን እልህ አስጨራሽ ነዉ በተለይ አድስ ተማሪዎች ግቢ በሚገቡበት ወቅት ፥ መጋፋት ፣ ሰልፍ መጣስ የተለመደ ነገር ነዉ። አቅም እና ትዕግስት ይጠይቃል ። ከመንግስት ካፌዎች በተረፈ የግል ካፌዎችም ግቢ ዉስጥ አሉ....
2) ዶርም🏢
👉 እዉነት ለመናገር ዶርሞች ሁሉም በሚባል ደረጃ ፅዱ እና ምቹ ናቸዉ ። ምን አልባት አንድ አንድ ጊዜ ከሽንት ቤት ጋር የሚያያዙ ጥያቄዎች ከተነሱ ብቻ እንጂ :☺️
3) ትምህርቱ📕
👉 ትምህርቱ ትንሽ ጠጠር ይላል Beteley 3rd Semester (kezhi befit kelal new biye yegidya mukera tedrgobgn nber ena tinsh kebad new😂) ግን የሚያስተምራችሁ የመምህር አይነት እንዲሁም be semster schedule ላይ ይወሰናል ። ቀለል ያሉ ትምህርቶችም ሲደራረቡባችሁ እና ጊዜ ሲያንሳችሁ ሳታዉቁት ዉጤት ይወርድባችኃል። ስለዚህ እዚህ ስትመጡ ብልጥ መሆን ይኖርባችኃል ።
4) ተማሪዎቹ🧑💻
👉 ከASTU ተማሪ ደስ የምለዉ ሁሉም ያጠናል በ300ም ያለፈ በ500 ምናምን ያለፈም እኩል ነዉ ሚያጠኑት ማንም ተኝቶ ሚያድር የለም። የሚያጠና ይሰራል የምተኛ ይሞታል አለቀ !....
በተረፈ....
ሳክሳም ተማሪ የሞላበት ግቢ በሉት። የሁሉንም ሳክስ የሚትሰሙ ከሆነ አትችሉም ።🙆🏽♂️
ሌላዉ Tensionaም ተማሪ የሞላበት ግቢ ነዉ። ቀን እና ማታ የሚያጠኑ እና ብቻቸዉን የሚያወሩ ብዙዎች ያጋጥሟችኃል።
5) አስተማሪዎቹ👨🏫
በጣም ጥሩ መምህራን እንዳሉ ሁሉ በጣም ጠማማ መምህራን አሉ ። አላማቸዉ እናንተን ማስባረር እስከምመስል ድረስ ዉጤታችሁን ለማዉረድ ለተ ቀን የምለፉ መምህራን አሉ ። የስማቸዉን ዝርዝር ከፈለጋችሁ ሁሉም ሰዉ በcomment section ላይ ይነግራችኃል 😂።
6) ጅብ 🦝
በጣም ወሳኝ የሆነ ነገር ነዉ ምነግራችሁ ። እዚህ ግቢ ሁለት አይነት ጅብ አለ የሰዉ ጅብ እና የእንስሳ ጅብ ። የቱ ይሻላል ? በእዉነት የእንስሳ ጅብ 100 እጅ ይሻላል አይነካችሁም አትነኩትም ከዶርም እስከ ላይብረሪ ልሸኛችሁ ይችላል ። ስለ ሰዉ ጅብ ግን ልንገራችሁ fresh ተማሪዎች ስትገቡ ብትችሉ Pc ይዛችሁ ባትመጡ እላለሁ ግቢዉን አይታችሁ ለበዓል ስትሄዱ ይዛችሁ ትመጣላችሁ ። አይይይ ብላችሁ ይዛችሁ የምትመጡ ከሆነ pc እና ስልክ የምበላ የሰዉ ጅብ አለ ። ይህ ነገር ግን ወንዶች ላይ ነዉ ምበረታዉ። በተጨማሪ ደህና ቁልፍ ይዛችሁ መምጣት እንዳትረሱ(የመጋዘን መዝግያ አይነትም ይሁን😂)
ይዛችሁ የምትመጡ ከሆነ ግን ተሸክማችሁ ለመዞር ፍቃደኛ መሆን አለባችሁ ::
7, Department
👉 ሁሉም የEngineering departmentoch(except.Applied ) ከ3 semster ቦኃላ ስለሚገቡ ከሌሎች ግቢዎች አንፃር የምትፈልጉትን departmeny የማግኘት chancachihu የተሻለ ነዉ ::
8, ጅም🏋,DSTV, football field
የተሟላ እና የተደራጀ ነዉ።
ሌሎች የምትጨምሩት ገፅታ ካለ ጠቁሙኝ......
መጥታችሁ እዩ ።😀
©Repost.
Join:-
@Astupost @Astupost
1 155
Repost from ASTU IGNITE ®️
የተወደዳችሁ የዩኒቨርሲቲያችን ነባር ተማሪዎች፤
እንደሚታወቀው አዳዲስ ተማሪዎች ወደ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሚቀላቀሉበት ወቅት አዲሱን የካምፓስ ህይወት የመላመድ፣ ህንፃዎችንና አገልግሎቶችን የመለየት እንዲሁም የመረጋጋት ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል። እኛም በነበርንበት ወቅት የነባር ተማሪዎች ድጋፍና አቀባበል ምን ያህል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደነበረው እናስታውሳለን።
ስለሆነም የኤስ.ቲ.ዩ ሰላም ፎረም ከተማሪዎች አገልግሎት ቢሮ ጋር በመተባበር ለአዲሶቹ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የተረጋጋ፣ ሰላማዊና ሞቅ ያለ አቀባበል ለማድረግ የሚያስችል የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት አዘጋጅቷል። በዚህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በመሳተፍ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለመፍጠርና ድጋፋችሁን ለማሳየት እንድትመዘገቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የበጎ ፈቃደኞች ተግባራት፦
-አዳዲስ ተማሪዎችን ከዋናው በር ጀምሮ ወደ ዶርም፣ ካፌ እና ሬጅስትራር መምራትና ማግዝ።
-ስለ ካምፓስ ህይወት፣ መመሪያዎችና አገልግሎቶች የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ መስጠት።
-በአቀባበል ወቅት ሰላማዊ፣ አዎንታዊና ፍቅር የተሞላበት አካባቢ እንዲፈጠር ማገዝ።
የምዝገባ ሁኔታ፦
በአቀባበል መርሃ-ግብሩ ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች ከታች ያለውን የGoogle Form ሊንክ በመጫን መረጃችሁን (ሙሉ ስም፣ ክፍል/Department፣ ስልክ ቁጥር እና የዶርም ቁጥር) እንድትሞሉ እንጠይቃለን።
🔗 የምዝገባ ሊንክ፦ [https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSc-M8RNz7hdpg_N3pR8o1zGi2WRV4iTEpxM94gOWuCjyeXqXw/viewform?usp=publish-editor]
📅 የምዝገባ ማብቂያ ቀን፦ [22-25 2026]
ማሳሰቢያ፦ በበጎ ፈቃደኝነት ለሚሳተፉ ተማሪዎች በፕሮግራሙ መጨረሻ ከተማሪዎች አገልግሎት ቢሮ እና ከሰላም ፎረም የእውቅና ምስክር ወረቀት (Certificate) የሚሰጥ ይሆናል።*
አዲሶቹን አባላቶቻችንን በፍቅርና በአንድነት አብረን እንቀበል!
የኤስ.ቲ.ዩ ሰላም ፎረም
@ASTU_IGNITE
1 155
Here We Go...
To All ASTU Undergraduate and Postgraduate(MSc and PhD) Regular students
=============
The 2019 E.C Official Academic Calendar is attached here.
1 155
Repost from EBR Exchange
🇪🇹 መልካም አዲስ ዓመት🌼
A new year.
A fresh start.
0% trading fees.
Celebrate with EBR and enjoy fee-free P2P trading while making every trade count.
New year.
Zero fees.
More freedom to trade.
Welcome to 2019... let’s make it count. 🚀
ebr.exchange/marketplace
https://x.com/ebrexchange/status/2098280152740302917
1 155
ይሄ platform EBR ይባላል 🔥
በዚህ platform ላይ ያላችሁን Dollar መሸጥም ሆነ መግዛት ከፈለጋችሁም ትችላላችሁ ከናንተ ሚጠበቀው Register አድርጎ መጠቀም ነው።
በመጀመሪያ ወደዚህ Website ሂዱ፦
https://ebr.exchange/
Refferal Code ሲጠይቃችሁ
👉
47D782DA (Optional ነው)
- በመቀጠል እንዳሻችሁ ገብቶ መጠቀም ነው።
እናም information ሲኖር ለመከታተል Ebr Telegram Channel Join አድርጉ
https://t.me/ebrexchange
The Best p2p platform right now in Ethiopia Even its better than closed Binance, Mexc 🤫
1 155
ሠላም የAstu Best Family
Dollar ሲያስፈልጋችሁ ከምን እየገዛችሁ ነው ምን ላይስ እየሸጣችሁ ነው 👀
እኔ ራሴ ያለሁበት platform ዶላር እንደፈለጋችሁ ምትገዙበትና ምትሸጡበት እነግራችኋለሁ 🔥
1 155
Repost from ASTU IGNITE ®️
የእርዳታ ጥሪ
ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት ወጣት ታጊ ኤልሮኢ ቅዱስ ትባላለች
የ unity university የ 2ኛ ዓመት የmanagement department ተማሪ የነበረች ሲሆን በአሁን ሰዓት ትምህርቷን አቋርጣ
የሳንባ ካንሰር በመያዟ ላይ ትገኛለች። በበሽታው ከተጠቃች አንድ ዓመት ሆኗታል።
በበሽታው ምክንያት የማራ አየር ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል። ቢሆንም ኤልሮኢ ተስፋ ሳትቆርጥ ህክምናዋን ቀጥላለች።
አሁን ግን በሽታው ወደ ሳንባዋ ተሰራጭቶ የመተንፈስ ችግር ስላጋጠማት በአዲስ አበባ Heal Venture Medical and Surgical Center NICU ውስጥ እንክብካቤ እያገኘች ትገኛለች።
በአሁን ሰዓት የሆስፒታል ወጪዋ በቀን እስከ 50,000 ብር ሊደርስ ስለሚችል ይህንን ወጪ ቤተሰቧ በቻላቸው መጠን ሊሸፍኑት አልቻሉም።
ስለዚህ የእርዳታ እጃችሁን እንድትዘረጉላት በትህትና እንጠይቃለን።
የምትችሉትን ማንኛውንም መጠን በመለገስ ለኤልሮኢ ህይወት ትልቅ ድጋፍ ይሆናል። አንድ ትንሽ እርዳታ ለእሷ ትልቅ ተስፋ ሊሆን ይችላል።
መጨመር ካልቻላችሁም ይህንን መልዕክት Share በማድረግ ወደ ሌሎች እንዲደርስ በማድረግ እንዳይቀር ተስፋ እናደርጋለን።
አንድ እንደልብ ተሰብስበን ለኤልሮኢ ተስፋ እንሁን።
Please please 🙏🙏
CBE: [1000487578828] = RAHEL AREGAY
Telebirr: [0911179293] = RAHEL AREGAY
Awash Bank: [013471629151800] = RAHEL AREGAY
1 155
Repost from Tikvah-University
47 A+ ያስመዘገበችው ተመራቂ 👏👏
ተማሪ ሩት አባተ ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እጅግ በላቀ ማዕረግ በዛሬው ዕለት ተመርቃለች።
የ Electrical Power and Control Engineering ተማሪዋ ሩት አባተ፣ አጠቃላይ ውጤት 4.00 CGPA ውጤት በማምጣት ትምህርቷን አጠናቃለች። በዚህም የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።
በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ ከወሰደቻቸው 60 ኮርሶች መካከል 47ቱን A+ እንዲሁም የቀሩትን 13 ኮርሶች A በማምጣት እጅግ የላቀ ውጤት አስመዝግባለች።
"ለትምህርቴ ልዩ ትኩረት በመስጠቴ የላቀ ውጤት አምጥቻለሁ" የምትለው ሩት፣ በቀጣይ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቷን የመቀጠል እቅድ እንዳላት ለኢዜአ ተናግራለች።
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 1,387 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ አስመርቋል።
@tikvahuniversity
1 155
Lost ID
Name: Eyobed Ashenafi
ID: UGR /39373/18
if you found this id pls dm, it is with national id
@aamedekab
1 155
Lost ID
Name: Biruk Yilfasew
ID: UGR /39144/18
Amphi akebabi tyew new meselegn bcha kagegnachu dm pls 🙌
@BirukSonOfYayo
1 155
🎉 THE Final End PARTY – Friday, May 22 🎉
Get ready for an unforgettable night at Comfort Zone Lounge, located at Bole Gate ,General hospital (Geda Square). The vibe starts at 11:30 PM local time – and you don’t want to be late.
Entry fee: Only 50 BIRR
Special offer:
1 beer for 70 BIRR
3 beers for 210 BIRR
Grab your tickets now via:
📞 +251 94 062 9680 | +251 98 172 3857
Or get them on wave2ticket
Come through, chill out, and party right. See you on the dance floor. 🔥🍻
1 155
Every Arsenal fan at ASTU, join this group! We’ll discuss how to celebrate next Sunday 🏆🔥
https://t.me/arsenalfansastu
https://t.me/arsenalfansastu
