cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አንድነት በጎ አድ. ማኀበር

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ላሉት ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለንም።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
194
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ናይጄሪያዊው ቱጃር አሊኮ ዳንጎቴ ከሀገሬ ውጭ ቤት የለኝም አሉ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጄሪያዊው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ ከሀገሬ ውጪ ቤት የለኝም ሲሉ በመግለጽ ብዙሃኑን የሀገራቸውን ዜጎች አስገርመዋል። ዳንጎቴ በትውልድ ከተማቸው ካኖ እንዲሁም በሌጎስ ካሏቸው ሁለት ቤቶች በስተቀር የመኖሪያ ቤት እንደሌላቸው ገልጸው፤ ወደ ሀገሪቱ ዋና ከተማ አቡጃ ለጉብኝት ሲሄዱ በተከራዩት አፓርታማ ውስጥ እንደሚያርፉ ተናግረዋል። በጥር ወር በፎርብስ መፅሔት በአፍሪካ ለ13 ተከታታይ ዓመታት በአፍሪካ ከፍተኛ ባለጸጋ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት ቱጃሩ ዳንጎቴ፤ ሀብታቸው ባለፈው ዓመት በ400 ሚሊየን ዶላር ከፍ ያለ ሲሆን÷ በዚህም የተጣራ 13 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር እንዳላቸው በወቅቱ ገልጿል። የ66 ዓመቱ ነጋዴ በሲሚንቶ እና በስኳር ዘርፍ ተሰማርተው ሀብት ያፈሩ ሲሆን÷ ባለፈው ዓመት በናይጄሪያ የኢኮኖሚ ማዕከል በሆነችው ሌጎስ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መክፈታቸውን የቢቢሲ ዘገባ አስታውሷል። ባሳለፍነው እሁድ በዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ከፍተኛ ሀብት ያላቸው ቢሆንም ከሀገራቸው ናይጄሪያ ውጭ የመኖሪያ ቤት እንደሌላቸው ገልጸዋል። ይህ ገለጻቸው ብዙ ናይጄሪያውያን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በበጎነቱ እየገለጹትና እየተቀባበሉት እንደሚገኙ ዘገባው አመላክቷል፡፡ ብዙዎቹ የናይጄሪያ ባለሃብቶች በለንደን፣ ዱባይ እና አትላንታ ቤቶች እንዳላቸው ይነገራል። ዳንጎቴ ከሀገራቸው ውጭ "በለንደን ወይም በአሜሪካ ቤት የለኝም ምክንያቱ ደግሞ የናይጄሪያን ኢንዱስትሪ ማሳደግ ላይ ማተኮር ስለፈለኩ ብቻ ነው" በማለት ገልጸዋል። ዳንጎቴ በፈረንጆቹ 1996 በለንደን የሚገኘውን ቤታቸውን እንደሸጡ የተናገሩ ሲሆን÷ ከሽያጩ የተገኘውን ገንዘብም ወደ ንግዳቸው እንዳስገቡት ተናግረዋል፡፡
Mostrar todo...
አይነ ስውር ና አካል ጉዳተኛ የሆነው የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ ተመራቂ ተማሪ ወጋየሁ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማረኛ ቋንቋ ስነ-ጽሑፍ እና ፎክሎር ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ እና የባለብዙ ተሰጥኦ ባለቤት ታታሪ ወጣት ነው። በፈተና የታጀበና በድል የተጠናቀቀ ጉዞ የማዕረግ ምሩቁን ሕይወት ይገልጻል። የገጠሙት ፈተናዎች ለበርካታ ዓመታት ትምህርት እንዲያቋርጥ ቢያስገድዱትም ህልሙን ለማሳካት ዳግም ወደ ትምህርት አለም ተመልሶ ትምህርቱን በጥሩ ውጤት በድል ያጠናቀቀ የማዕረግ ተመራቂ ነው። እጅግ ይደንቃል እንኳን ደስ አለክ
Mostrar todo...
👍 1
የዕለቱ ድንቅ ፎቶና ተመራቂ ከታች የምትመለከቱት ብርቱ አካል ጉዳተኛ ተማሪ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በክብር ተመርቋል! እንኳን ደስ አለህ ! በለጠ ቡቱና የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያለፉትን አምስት ዓመታት በማታው የትምህርት መርሐ ግብር በማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ተማሪ በለጠ ቡቱና ጠንካራ ስነ ልቦና ካለ የማይታለፍ መንገድ የለም ብሏል። ወጣት በለጠ ወላጅ እናትን በልጅነት ማጣትን ጨምሮ ህይወቱን በርካታ ፈተናዎችን ተጋፍጧል። የአካል ጉዳት ያለበት ወጣት በለጠ አጋዥ አባትም የሌለው በመሆኑ የመኖር ተስፋውን ሊያደበዝዝ ቢችልም ለችግርና ለፈተና እጅ ባለመስጠት ጉዞውን ማስቀጠል ችሏል። የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ሲያመጣ በሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ የ20 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ከተደረገለት በኋላ ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አቅንቷል። ዩኒቨርሲቲውም ከ1 ዓመት የትሞህርት ቆይታ በኋላ ነፃ የትምህርት፣ የማደሪያና የምግብ አገልግሎቶችን አመቻችቶለታል። ተማሪ በለጠ ቡቱና አካል ጉዳተኝነት ሳያግደው የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው 4 ሺህ 800 ተማሪዎች ውስጥ አንዱ በመሆን በ3 ነጥብ 2 አጠቃላይ ውጤት የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። አካል ጉዳተኝነት አለመቻል አለመሆኑን በተግባር አሳይተሃል እንኳን ለዚህ ቀን አበቃህ ቀሪ ዘመንህ ይመር ። መልካሙ ሁሉ ይግጠምህ 🏆🏆 🌻🌻🌻Congratulation 🌻🌻🌻
Mostrar todo...
የሚወለዱት ህጻናት ብቻ ናቸው! አንዲትን ከብዙዎች ሰዎች እይታ ርቃ የምትገኝን መንደር በመጎብኘት ላይ የነበሩ ሰዎች ገና እንደደረሱ የገረማቸው የዚያች መንደር ርቀት ነው፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ጎብኚዎች የመጡባት አትመስልም፡፡ በዚህች መንደር በመዘዋወር እያሉ በአንድ ሜዳ ላይ የሚጫወቱትን ወጣቶች ቁጭ ብለው የሚያዩ አንድ አዛውንት አገኙና ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ እንዲህ የሚል ጥያቄ ጠየቋቸው፣ “በዚህ መንደር ታላላቅ ሰዎች ተወልደው ያውቃሉ?” ጥያቄው ግልጽ ቢሆንም፣ አዛውንቱ፣ “ምን አይነት ጥያቄ ነው” በሚል እይታ ከቃኟቸው በኋላ አጅግ ቀላልና ግልጽ የሆነ መልስ ሰጧቸው፡፡ የእኝህ አዛውንት ፈጣን መልስ ጎብኚዎቹን አስገረማቸው፡፡ መልሳቸው፣ “በዚህች መንደር የሚወለዱት ህጻናት ብቻ ናቸው”፡፡ አስገራሚ መልስ! ወደዚህች ምድር በውልደት የመጣ ሰው ሁሉ የመጀመሪያ ስሙ “ሰው” ይባላል - ከዚህ ውጪ ማንነት የለም፡፡ ሁሉም እኩል የመተንፈስ እድል ይዞ ነው የተወለደው፡፡ ለሁሉም የተሰጠው አንድ አስገራሚ ስጦታ “ህይወት” ይባላል፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ የለም፡፡ እውነት ነው፣ ብዙ ሃብት ባለበት ቤት ውስጥ የመወለድ እድል ያጋጠማቸው ሰዎች አሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በእጦት ተወልደው በእጦት ያደጉም አሉ፡፡ በሃብት ተወልደው በድህነት ኖረው የሞቱ፣ በድህነት ተወልደው ደግሞ በብልጽግና ኖረው የሞቱም ያንኑ ያህል ቁጥራቸው ብዙ ነው፡፡ አንድ ሰው ከምን አይነት ቤተሰብ ሊወለድ እንደሚፈልግ ምርጫ ባይኖረውም ከተወለደ በኋላ ምን አይነት ጎዳና መከተል እንደሚችል ግን የመወሰን ምርጫ አለው፡፡ የትኛው ይሻላል? የአወላለድን ሁኔታ መርጦ ከተወለዱ በኋላ ለእድል ታልፎ መሰጠት ወይስ የአወላለድን ሁኔታ የመምረጥ እድል ሳያገኙ ከተወለዱ በኋላ የሚሄዱበትን ጎዳና የመምረጥ እድል? እኔ ሁለተኛው ያጓጓኛል! አንድ ሰው ጾታውን፣ ቤተሰቡን፣ የቆዳ ቀለሙንና ዜግነቱን መርጦ አይወለድም ከተወለደ በኋላ ግን በእነዚህ ልዩ ስጦታዎች ተጠቅሞ ወደየት እንደሚሄድ የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንን መብት ለማስከበር ማስታወስ የሚገቡን ሶስት እውነታዎች አሉ፡፡ 1ኛ እውነታ - ወሳኙ ነገር አመጣጥህ (Background) ሳይሆን አካሄድህ (Your future) ነው፡- “ተሸናፊዎች በትናንትና ውስጥ ይኖራሉ፡፡ አሸናፊዎች ግን ከአለፈው በመማር፣ በዛሬዋ ቀን ላይ ሆነው በደስታ ለወደፊቱ ይሰራሉ” (Denis Waitley)፡፡ 2ኛ እውነታ - ወሳኙ ነገር እለድኛ መሆንህና አለመሆንህ ሳይሆን በእድል ላይ ያለህ አለካከት ነው፡- “በእድል አጽንቼ አምናለሁ፣ ጠንክሬ በሰራሁ ቁጥር ብዙ እድል እንደማገኝም አምናለሁ” (Thomas Jefferson)፡፡ “ትጋት የእድሎች ሁሉ እናት ነች” (Benjamin Franklin)፡፡ 3ኛ እውነታ - ወሳኙ ነገር ውስንነትህና ገደብህ ሳይሆን በዚያ ላይ የምትወስደው እርምጃ ነው፡- “ውስንነትህን ለይተህ እወቅ፣ ነገር ግን በፍጹም አትቀበለው”(Unknown Source)፡፡ join joinshare share https://t.me/tobecharitable https://t.me/tobecharitable
Mostrar todo...
አንድነት በጎ አድ. ማኀበር

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ላሉት ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለንም።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

Repost from Dr. Eyob Mamo
የሚወለዱት ህጻናት ብቻ ናቸው! አንዲትን ከብዙዎች ሰዎች እይታ ርቃ የምትገኝን መንደር በመጎብኘት ላይ የነበሩ ሰዎች ገና እንደደረሱ የገረማቸው የዚያች መንደር ርቀት ነው፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ጎብኚዎች የመጡባት አትመስልም፡፡ በዚህች መንደር በመዘዋወር እያሉ በአንድ ሜዳ ላይ የሚጫወቱትን ወጣቶች ቁጭ ብለው የሚያዩ አንድ አዛውንት አገኙና ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ እንዲህ የሚል ጥያቄ ጠየቋቸው፣ “በዚህ መንደር ታላላቅ ሰዎች ተወልደው ያውቃሉ?” ጥያቄው ግልጽ ቢሆንም፣ አዛውንቱ፣ “ምን አይነት ጥያቄ ነው” በሚል እይታ ከቃኟቸው በኋላ አጅግ ቀላልና ግልጽ የሆነ መልስ ሰጧቸው፡፡ የእኝህ አዛውንት ፈጣን መልስ ጎብኚዎቹን አስገረማቸው፡፡ መልሳቸው፣ “በዚህች መንደር የሚወለዱት ህጻናት ብቻ ናቸው”፡፡ አስገራሚ መልስ! ወደዚህች ምድር በውልደት የመጣ ሰው ሁሉ የመጀመሪያ ስሙ “ሰው” ይባላል - ከዚህ ውጪ ማንነት የለም፡፡ ሁሉም እኩል የመተንፈስ እድል ይዞ ነው የተወለደው፡፡ ለሁሉም የተሰጠው አንድ አስገራሚ ስጦታ “ህይወት” ይባላል፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ የለም፡፡ እውነት ነው፣ ብዙ ሃብት ባለበት ቤት ውስጥ የመወለድ እድል ያጋጠማቸው ሰዎች አሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በእጦት ተወልደው በእጦት ያደጉም አሉ፡፡ በሃብት ተወልደው በድህነት ኖረው የሞቱ፣ በድህነት ተወልደው ደግሞ በብልጽግና ኖረው የሞቱም ያንኑ ያህል ቁጥራቸው ብዙ ነው፡፡ አንድ ሰው ከምን አይነት ቤተሰብ ሊወለድ እንደሚፈልግ ምርጫ ባይኖረውም ከተወለደ በኋላ ምን አይነት ጎዳና መከተል እንደሚችል ግን የመወሰን ምርጫ አለው፡፡ የትኛው ይሻላል? የአወላለድን ሁኔታ መርጦ ከተወለዱ በኋላ ለእድል ታልፎ መሰጠት ወይስ የአወላለድን ሁኔታ የመምረጥ እድል ሳያገኙ ከተወለዱ በኋላ የሚሄዱበትን ጎዳና የመምረጥ እድል? እኔ ሁለተኛው ያጓጓኛል! አንድ ሰው ጾታውን፣ ቤተሰቡን፣ የቆዳ ቀለሙንና ዜግነቱን መርጦ አይወለድም ከተወለደ በኋላ ግን በእነዚህ ልዩ ስጦታዎች ተጠቅሞ ወደየት እንደሚሄድ የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንን መብት ለማስከበር ማስታወስ የሚገቡን ሶስት እውነታዎች አሉ፡፡ 1ኛ እውነታ - ወሳኙ ነገር አመጣጥህ (Background) ሳይሆን አካሄድህ (Your future) ነው፡- “ተሸናፊዎች በትናንትና ውስጥ ይኖራሉ፡፡ አሸናፊዎች ግን ከአለፈው በመማር፣ በዛሬዋ ቀን ላይ ሆነው በደስታ ለወደፊቱ ይሰራሉ” (Denis Waitley)፡፡ 2ኛ እውነታ - ወሳኙ ነገር እለድኛ መሆንህና አለመሆንህ ሳይሆን በእድል ላይ ያለህ አለካከት ነው፡- “በእድል አጽንቼ አምናለሁ፣ ጠንክሬ በሰራሁ ቁጥር ብዙ እድል እንደማገኝም አምናለሁ” (Thomas Jefferson)፡፡ “ትጋት የእድሎች ሁሉ እናት ነች” (Benjamin Franklin)፡፡ 3ኛ እውነታ - ወሳኙ ነገር ውስንነትህና ገደብህ ሳይሆን በዚያ ላይ የምትወስደው እርምጃ ነው፡- “ውስንነትህን ለይተህ እወቅ፣ ነገር ግን በፍጹም አትቀበለው”(Unknown Source)፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Mostrar todo...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

እጅግ እጅግ እጅግ እናመሰግናለን (ጌታ ሆይ ) #አንድነት_በጎ_አድራጎት_ማኅበር ማኅበራችን ባለፈዉ የካቲት ወር ላይ የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና በሚደንቅ ሁኔታ ያካሄደ መሆኑ ይታወቃል ።በጊዜው አስገራሚ ለውጥ የታየበትና የታድሶ ጊዜ ያሳልፍን ሲሆን የማኅበሩ አካላት በሙሉ ጥሩ ነገር እንዲጠቀሙበት ብሎም የሚያዛልቅ ግንዛቤ አግኝተው ለወደፊቱ ሩጫ ጠንካራ ትጥቅ እንደታጠቁ የማይታበል ሀቅ ነው ። አሁን ደግሞ በድጋሜ ለሁለተኛ ጊዜ ድንቅ ጊዜ ለማሣለፍ ሽር ጉዱን እያገባደድን ነው ። ስለሆነም የነገ ዕለት ከ2:00 ጀምሮ እስከ 9:00 በሚኖረን በሥልጠናና በምክክር ጊዜ ለሕይወት ዘመናችን የሚሆን ሥንቅ እንደምንቀስም በሙሉ እምነት ይጠበቃል 👍✋ ጌታ ቢረዳንንና ቢፈቅድ ውጤታማ ጊዜ እንደሚሆን አልጠራጠርም ። እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲሆንልን ጌታ አየሩንና ጊዜውን ፈቅዶና አሳልፎ እንድሰጣን ተማጽኖቴ ነው ። እንግዲህ ከማኅበሩ ጋር አብራችሁ ለመቀጠል ፍላጎት ያላችሁ በዕለቱ ተገኝታችሁ ሥልጠናውን እንድትካፈሉ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን ❤❤❤👍 ፍስሐ ተመስገን (የማኀበሩ ዋና ሰብሳቢ )
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የአንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር ቤተሰቦችና ወዳጆቻቸው ለሁላችሁም ሰላምና ጤና እንድሆንላችሁ እየተመኛን ከፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም በማኅበራችን የተዘጋጀ ድንቅ የሥልጠና ጊዜ ይኖረናል ። በመሆኑም ሁላችንንም የአንድነት ቤተሰቦች በሙሉ ልክ 2:00 ማስታወሻና ደብተር ይዛችሁ እንድትገኙ በታላቅ ፍቅር እናሳስባለን ። በዕለቱ የሥልጠና የምክክር የውይይት ጊዜ ይኖረናል ። ስለዚህ እባካችሁ ማናችሁም አትቅሩ ከበረከቱም አትጓደሉ እእእእንንንወወወዳዳዳችችችኃኃኃለለለንንንንንን😍😍😍❤❤❤❤
Mostrar todo...
📚ርዕስ:- ሕይወቴ 📝ድርሰት:- ተመስገን ገብሬ 📜ይዘት:- ግለ ታሪክ 📆የመጀመሪያ ዕትም:- 2001 📖የገፅ ብዛት:- 190 📌አዘጋጅ:- 📌ማጋራት አይዘንጋ! @ETHIO_PDF_BOOKS1 @ETHIO_PDF_BOOKS @YETMHRTPDF @BHERE_TREKA
Mostrar todo...
ንባብ ለሕይወት-1.pdf17.71 MB
ሰርቫይቫል-101-መሪ-ሃሳብ.pdf5.94 MB
ሕይወቴ (ግለ ታሪክ) በተመስገን ገብሬ.pdf36.57 MB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.