es
Feedback
Biruke Fact

Biruke Fact

Ir al canal en Telegram
6 998
Suscriptores
-1724 horas
+1127 días
+4530 días
Archivo de publicaciones
ቤተሰቦች እገዛቹና ድምፃቹ ያስፈልገኛል። በአሁኑ ሰዓት በ"የቅን ልቦች (Yekinlbochaward)" የሶሻል ሚዲያ አዋርድ ላይ በእጩነት ቀርብያለው። በዚህ የውድድር ሂደት ውስጥ የእናንተ ድጋፍ በጣ
+1
ቤተሰቦች እገዛቹና ድምፃቹ ያስፈልገኛል። በአሁኑ ሰዓት በ"የቅን ልቦች (Yekinlbochaward)" የሶሻል ሚዲያ አዋርድ ላይ በእጩነት ቀርብያለው። በዚህ የውድድር ሂደት ውስጥ የእናንተ ድጋፍ በጣም ያስፈልገኛል። ከታች ባለውን ሊንክ በመግባት ድምፅ በመስጠት ፍቅራቹንአሳዪኝ።👇 https://yekinlibochaward.org/nominees/biruk-tizazu በስሜ ስር Vote የሚለው በመጫን አንድ ጊዜ በነፃ ድምፅ መስጠት ትችላላቹ። በገንዘባቸው ድምፅ የሰጡም አሉ ።የእናንተ በነፃ ነው።ደስ የሚለው እነማን ድምፅ እንደሰጡኝ የማህበራዊ ሚዲያ ስማችሁን ጠቅሶ ያሳውቃል። እኔም እናንተ ቤተሰቦቼን የማይበት ይሆናል። በጣም አመሰግናለሁ! 🔗 የድምፅ መስጫ ሊንክ፡👇 https://yekinlibochaward.org/nominees/biruk-tizazu

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም ውጤታቸው ማየት ጀምረዋል። ውጤት ለማየት ፦ 👉 በድረ ገጽ ፡ https://r
+1
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም ውጤታቸው ማየት ጀምረዋል። ውጤት ለማየት ፦ 👉 በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et 👉 ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram 👉 አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ስለሚሞክሩ የኔትዎርክ መጨናነቅ ሊያጋጥም ስለሚችል ደጋግሞ መሞከር ይገባል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ምላሹንም በዛው ማስፈንጠሪያ መከታተል እንደሚችሉ ገልጿል።

" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የ
+1
" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል። በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች  ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል። ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡- - በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et - ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram - አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ! በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 የትምህርት ዘመን 97.48% የሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች 50% እና በላይ በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መዘዋ
ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ! በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 የትምህርት ዘመን 97.48% የሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች 50% እና በላይ በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መዘዋወራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ። የ2018 የትምህርት ዓመት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ዘንድሮ ፈተናውን ከወሰዱ 84,257 ተማሪዎች መካከል 82,137 የሚሆኑ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ሆኖ የተቆረጠውን 50 በመቶ እና በላይ አስመዝግበዋል። 768 ትምህርት ቤቶች ፈተና አስፈትነው 543 ያህሉ ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸው ተገልጿል። ተፈታኝ ተማሪዎች ይህን ሊንክ https://aa6.ministry.et/#/result በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

ተማሪዎች ውጤታቸው መመልከት ይችላሉ። በ2018 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና 95.85% ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ
ተማሪዎች ውጤታቸው መመልከት ይችላሉ። በ2018 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና 95.85% ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል። የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤትን ይፋ ተደርጓል። ተማሪዎች ውጤታቸውን ይህንን ማስፈንጠሪያ https://aa.ministry.et/#/result በመጫን መመልከት ይችላሉ። ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ/ም

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያ
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት እንደነበር ፋና ዲጂታል ከቤተሰቦቹ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እንመኛለን።

አርሰናል የ 2025/26 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆነ ከ22 አመታቶች ቡሀላ ሊጉን ማሳካት ቻለ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
አርሰናል የ 2025/26 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆነ ከ22 አመታቶች ቡሀላ ሊጉን ማሳካት ቻለ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም'' ''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም'' ''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ'' ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።

🕋ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። በዓሉ የሰላም ፥ የመተሳሰብ እና የፍቅር እንዲሆን እንመኛለን።🕌 EID MUBARIK - ኢድ
🕋ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። በዓሉ የሰላም ፥ የመተሳሰብ እና የፍቅር እንዲሆን እንመኛለን።🕌 EID MUBARIK - ኢድ ሙባረክ

እንኳን ለ130 ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳቹ!!
እንኳን ለ130 ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳቹ!!

ሰበር ዜና‼️ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኔኢ ተገደሉ! በእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ላይ የወጡ ዘገባዎችን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ የኢራን ከፍተኛው መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኔኢ
ሰበር ዜና‼️ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኔኢ ተገደሉ! በእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ላይ የወጡ ዘገባዎችን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ የኢራን ከፍተኛው መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኔኢ ህይወት አልፏል። የሪፖርቱ ምንጮች እንዳመለከቱት፣ የካሜኔኢ አስከሬን መገኘቱ ተነግሯል። ይህ ዘገባ በአካባቢው ያለውን የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ወደ ከፍተኛ ደረጃ የሚያደርሰው ተብሎ ይጠበቃል። Via BBC , Aljazeera , Reuters

የቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር (round ኦፍ 16)ድልድል ይፋ ሆኗል
+1
የቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር (round ኦፍ 16)ድልድል ይፋ ሆኗል

መድፈኞቹ ዶሮዋን በገዛ ሜዳዋና በደጋፊዎቿ ፊት 'እያጣጣሙ ሲበሏት አመሹ። እነሆ የሰሜን ለንደን ሰማይ ስር በቀይና ነጭ ቀለም አሸብርቋል። አዎ ዛሬ ምሽት የለንደን ንጉስ ማንም ሳይሆን አርሰናል መሆ
መድፈኞቹ ዶሮዋን በገዛ ሜዳዋና በደጋፊዎቿ ፊት 'እያጣጣሙ ሲበሏት አመሹ። እነሆ የሰሜን ለንደን ሰማይ ስር በቀይና ነጭ ቀለም አሸብርቋል። አዎ ዛሬ ምሽት የለንደን ንጉስ ማንም ሳይሆን አርሰናል መሆኑን በድጋሚ አስመስክሯል። ብዙዎች 'አርሰናል ዛሬ ይንሸራተታል፣ የዋንጫው ግስጋሴው እዚህ ጋር ያከትማል' ብለው ቢጠብቁም፤የሚካኤል አርቴታ ልጆች ግን ሜዳው ላይ የታዩት እንደ አንበሳ ተቆጥተው ነበር። አረሰሰናሎች ቶትነሃምን በገዛ ጎጆው ድባቅ በመምታት፣ ለሲቲና ለሌሎች ተፎካካሪዎቻቸው ግልጽ መልእክት አስተላልፈዋል ​ይህ ድል ለአርሰናል ደጋፊዎች ከሶስት ነጥብ በላይ ነ

ረመዷን ነገ ይጀምራል። በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የታላቁና ቅዱሱ የረመዳን ወር ጾም ነገ ረቡዕ ይጀምራል።
+1
ረመዷን ነገ ይጀምራል። በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የታላቁና ቅዱሱ የረመዳን ወር ጾም ነገ ረቡዕ ይጀምራል።

አሜን በሉ ልመርቃችሁ🙏 የጾሙ መጀመሪያ "ዘወረደ" ተብሎ እንደ ተጀመረ፣ ማጠቃለያውም በዓለ ሆሳዕናን በድል አድራጊነት እንድንቀበል፣ ከዚያም የትንሣኤውን ብርሃን ለማየት ፈጣሪ ያብቃን። አምላካችን
አሜን በሉ ልመርቃችሁ🙏 የጾሙ መጀመሪያ "ዘወረደ" ተብሎ እንደ ተጀመረ፣ ማጠቃለያውም በዓለ ሆሳዕናን በድል አድራጊነት እንድንቀበል፣ ከዚያም የትንሣኤውን ብርሃን ለማየት ፈጣሪ ያብቃን። አምላካችን እግዚአብሔር ይህንን የተቀደሰ የጾም ወቅት የበረከት፣ የፈውስ እና የኃጢአት ማስተሰሪያ ያድርግልን። ​በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ፣ ዐቢይ ጾም የሆድን መታቀብ ብቻ ሳይሆን የነፍስን መታደስ የሚጎናጸፉበት የታላቅ ምስጢር ወቅት ነው። ይህ ጾም፣ የሰው ልጅ በኃጢአት ጨለማ ውስጥ ወድቆ ከፈጣሪው ተለይቶ በነበረበት ዘመን፣ አምላክ ፍጥረቱን ፍለጋ ያደረገውን የፍቅር ጉዞ የምናስብበት የታሪክ መዝገብ ነው። ​ከገነት የተሰደደውን አዳም እንባ ለማበስ፣ የአለማት ጌታ ዙፋኑን ትቶ በምድር የተንከራተተበት፣ የተራበበትና በመጨረሻም በመስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰበት የመስዋዕትነት ምስጢር በዚህ ጾም ውስጥ ተቀብሯል። ​በነዚህ 55 ቀናት ውስጥ፣ በአካልም በመንፈስም በመታቀብ፣ በጸሎት እና በምጽዋት በመጽናት፣ ከፈጣሪ ጋር ያለንን ግንኙነት እናድሳለን። ፈጣሪ ጾሙን የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ያድርግልን እንኳን ለታላቁ የዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ!

መረጃ‼️ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ይሰጣል - ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ2018 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረ
መረጃ‼️ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ይሰጣል - ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ2018 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም መድረክ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዚህ ዓመት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ጠ/ሩ ስለ ህዳሴ ግድቡ እውነታ በይፋ ተናግረዋል። ለህዳሴው ግድብ አንድ ብር ብድርም ሆነ እርዳታ አልተቀበልንም ሲሉ ተናግረዋል። በዚህም የትራምፕ አሉባልታ ውሸት መሆኑ ታውቋል። ​ጠቅላይ ሚኒስትር
ጠ/ሩ ስለ ህዳሴ ግድቡ እውነታ በይፋ ተናግረዋል። ለህዳሴው ግድብ አንድ ብር ብድርም ሆነ እርዳታ አልተቀበልንም ሲሉ ተናግረዋል። በዚህም የትራምፕ አሉባልታ ውሸት መሆኑ ታውቋል። ​ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በፓርላማ እንደተናገሩት ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የፋይናንስ ምንጭን በተመለከተ ለዓመታት ሲነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች  ምላሽ ሰጥተዋል። ግድቡ ከአንድም የውጭ ሀገር ወይም ተቋም "አንድ ብር" እርዳታ ሳይጠየቅበትና ሳይወሰድበት፣ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህዝቡ የላብ ጠብታ ብቻ እዚህ ደረጃ መድረሱን ገልጸዋል።

ላስታውሳቹ እንዳትረሱ 5ሺ ብር ለመቀጣት ምን ያህል ዝግጁ ናቹ። ዛሬ ገበያ ከመውጣታችሁ በፊት ይሄን ፅሁፍ ካላያችሁ ኪሳችሁ ባዶ ሊቀር ይችላል! ከ2 ሺህ እስከ 5 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት ዛሬ ተጀ
ላስታውሳቹ እንዳትረሱ 5ሺ ብር ለመቀጣት ምን ያህል ዝግጁ ናቹ። ዛሬ ገበያ ከመውጣታችሁ በፊት ይሄን ፅሁፍ ካላያችሁ ኪሳችሁ ባዶ ሊቀር ይችላል! ከ2 ሺህ እስከ 5 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት ዛሬ ተጀምሯል። ምን እንደተፈጠረ እነግራችኋለሁ፣ እስከመጨረሻው አድምጡኝ። ​"የፊስታል አጠቃቀምን ለመቀነስ የወጣውን አዲስ መመሪያ ተከትሎ፣ ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ፊስታል ይዞ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል። መንግስት አካባቢያችንን ከፕላስቲክ ብክለት ለመጠበቅ ጥብቅ ቁጥጥር ጀምሯል። ስለዚህ ዛሬ ወደ ገበያም ሆነ ወደ ሱቅ ሲሄዱ ፊስታል እንዳትይዙ ተጠንቀቁ፤ ራሳችሁን ከማያስፈልግ ቅጣት ጠብቁ መልዕክቴ ነው።

ማሳሰቢያ‼️ ከነገ ጀምሮ የፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም በህግ ያስቀጣል! ​የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ባወጣው መመሪያ መሰረት፣ ከነገ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውንም አይነት ቀጭን የፕላስቲ
ማሳሰቢያ‼️ ከነገ ጀምሮ የፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም በህግ ያስቀጣል! ​የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ባወጣው መመሪያ መሰረት፣ ከነገ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውንም አይነት ቀጭን የፕላስቲክ ፌስታሎችን መጠቀም፣ ማምረትም ሆነ ማከፋፈል በጥብቅ ተከልክሏል። 🚫 ​⚠️ ማወቅ ያለባችሁ የቅጣት መጠኖች፡በእጅ ይዞ ለተገኘ ግለሰብ፡ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር ቅጣት። 💸 ​ለአምራቾች እና ለአከፋፋዮች፡ እስከ 200,000 ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና እስከ 5 ዓመት የሚደርስ እስራት። ⚖️ ​💡 መፍትሄው ምንድነው? ከነገ ጀምሮ ለገበያም ሆነ ለማንኛውም ጉዳይ በፌስታል ፋንታ የጨርቅ ከረጢቶችን ወይም እንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ ቦርሳዎችን እንዲጠቀሙ ይመከራል። ​ወዳጅ ዘመድዎ ሳይታወቅበት ተቀጥቶ እንዳይቸገር አሁኑኑ Share በማድረግ መረጃው እንዲደርሳቸው ያድርጉ! 🙏 ​ለበለጠ መረጃና አዳዲስ ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡

ቲክቶከሩ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ‼️ ሴት እህቶችን ወደ መዝናኛ ቦታዎች በመውሰድ፣በሚጠጡት መጠጥ ውስጥ አደንዛዥ ዕጽ በመጨመር፣ .ያልተገባ ድርጊት እንዲፈጽሙ በማድረግና በምስል በመቅረጽ፣ ምስሉን
ቲክቶከሩ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ‼️ ሴት እህቶችን ወደ መዝናኛ ቦታዎች በመውሰድ፣በሚጠጡት መጠጥ ውስጥ አደንዛዥ ዕጽ በመጨመር፣ .ያልተገባ ድርጊት እንዲፈጽሙ በማድረግና በምስል በመቅረጽ፣ ምስሉን በማህበራዊ ሚዲያ  በማሰራጨት ወንጀል እንደተጠረጠረ ፖሊስ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ከሀገሪቱ ባህልና እሴት ውጪ የሆኑ ተግባራትን ሲፈጽም የነበረውን ንጉሰ ዳዊት (ግብዳው) የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።