es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Ir al canal en Telegram
1 330
Suscriptores
+324 horas
+87 días
+8330 días
Archivo de publicaciones
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ፍትሃዊ ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን የሚረጋገጡ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸው ተገለፀ፤ **** የሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት በሴቶች፣ በአካል ጉዳተኛ ለሚመሩ  ኢንተርፕራይዞች፣አንቀሳቃሾች እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ለሚያደርጉ ለግል ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ከድጋፍ ማእቀፍ አንዱና ዋነኛ  የሆነውን የንግድ ክህሎት እና የሂሳብ መዝገብ አያያዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡ በስልጠናው ላይ የኢንተርፕሩነርሺፕ ምንነትና የንግድ ክህሎታቸውን ሊያዳብሩ የሚችሉና የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ጋር ያለባቸውን ክፍተት ከመሙላት አንጻር ያለው አስተዋፅኦ በሰፊው የተዳሰሰ ሲሆን ሰልጣኞች ከዚህ በፊት የነበራቸውን እውቀትና ግንዛቤ እንዲያሳድጉ የሚያስችል እድል የፈጠረላቸው ሆኗል፡፡ ኢንተርፕራይዞቹ እርስ በእርስ ያላቸውን መስተጋብር ይበልጥ በማጠናከር የልምድ ልውውጥና የእውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ ያስቻለ ሲሆን  ለኢንተርፕራይዞች የተሻለ ትኩረት በማድረግ ውጤት ተኮር ተግባር ማስመዝገብ የሚቻለው ከጊዜው ጋር የዘመነ ስልጠና በመስጠት እንደሆነ  ተገልጿል፡፡ ከኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾቹ ጋር በስልጠናው የተሳተፉት የግል ኮሌጆች አሰልጣኝ መምህራን ኤጀንሲው ከግል ከኮሌጆቹ ጋር በደረሰው የጋራ መግባባት ለሚያደርጉት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን  የድጋፍ አይነቶች አቅማቸውን ለመገንባት ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ታውቋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተደርጎ በመሰራቱ በርካታ ወጣቶች የስራ ባለቤት መሆናቸው ተገለፀ በዛሬው እለት የኢፌድሪ ማዕድን ሚንስተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ ወረዳ ሁለትና ሶስት አስተዳደር በውበት ሳሎን ስራ፣ በእንጨት ስራ ውጤቶች እንዲሁም በህትመት ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶችን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል። በአጠቃላይ በድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተሰቶበት እየተሰራበት በመሆኑ በርካታ ወጣቶች የስራ ባለቤት መሆናቸው ተገልፆ፤ ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቁሟል። በጉብኝቱ ወቅት ያነጋገርናቸው የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች በበኩላቸው በዚህ መልኩ የስራ ቦታቸው በመጎብኘቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፤ አስተዳደሩ ላበረከተላቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አመስግነዋል። ©️ የድሬዳዋ መንግስት ኮምኒኬሽን

የኢፌድሪ ማዕድን ሚኒስተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በወረዳ 9 አስተዳደር ስር እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ቱሩፋት እንዲሁም የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ስራዎችን ጎበኙ፤ በዚህም የወረዳ 9 አስተዳደር በ 5 ወራቶች ውስጥ በአካባቢ ፅዳትና ውበት፣ በስራ እድል ፈጠራ ፣ በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች እንዲሁም በሌማት ቱሩፋትና በሌሎችም ዘርፎች ያከናወናቸው ስራዎች ላይ ለእንግዶች ገለፃ የተደረገ ሲሆን፤ በመስክም በልብስ ሽያጭ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶችን በተጨማሪም በሌማት ቱሩፋት ስራም የማር ምርትን እንግዶች ተመልክተዋል። ©️ የድሬዳዋ መንግስት ኮምኒኬሽን

የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የፈጠራ ሃሳብ ማበልጸጊያ ማዕከል እንዲሁም የኢንተርፕራይዞች መፍለቂያ ተቋማት መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ፡፡ በዛሬው እለት የኢፌድሪ ማዕድን ሚንስተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገ
+6
የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የፈጠራ ሃሳብ ማበልጸጊያ ማዕከል እንዲሁም የኢንተርፕራይዞች መፍለቂያ ተቋማት መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ፡፡ በዛሬው እለት የኢፌድሪ ማዕድን ሚንስተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት የኮሌጁን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል። በኮሌጁ የተሰሩ የተለያዩ ስራዎች በልህቀት ማእከል ግንባታ፣ ተቋሙ ከኢንትርፕራይዞች መፍለቂያነት አንጻር፣የፈጠራ ሃሳብ ማበልጸጊያ ማዕከልነት አንጻር ፣ከቴክኖሎጂ ማእከልነት ፣ኮሌጁ በሚያስገነባቸው ፕሮጀክቶች አንጻር እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች ላይ ለእንግዶች ማብራሪያና ገለፃ በኮሌጁ ዲን አቶ ሰልሃዲን አብዱልሃሚድ በኩል ገለጻ ተደርጓል። በአጠቃላይ በኮሌጁ የፈጠራ ሃሳብ ማበልጸጊያ ማዕከል እንዲሁም የኢንተርፕራይዞች መፍለቂያ ተቋማት ላይ ትኩረት ተሰቶበት እየተሰራበት በመሆኑ በርካታ የኮሌጁ ሰልጣኞች የፈጠራ ሃሳባቸውን ወደ ተግባር በማውረድ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን በምልከታው ወቅት ተብራርቷል፡፡ የኮሌጁ ኮምሚኬሽን ታህሳስ 6/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

#ዜና የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ከሌጅ መካኒክ አሽከርካሪዎችን በዛሬው እለት አስመረቀ፡፡ በሀገራችን እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳድር መካኒክ አሽከርካሪዎችን በማፈራት የትራፊክ አደጋን መቀነስ እና አለም አ
+8
#ዜና የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ከሌጅ መካኒክ አሽከርካሪዎችን በዛሬው እለት አስመረቀ፡፡ በሀገራችን እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳድር መካኒክ አሽከርካሪዎችን በማፈራት የትራፊክ አደጋን መቀነስ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ አሽከርካራችን ማፍራት ማፍረት ላይ ትኩረቱን ያደረገ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ያጠናቀቁ አሽከርካሪዎችን በዛሬው እለት አስመረቀ፡፡ በምርቃቱ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንዳሉት ይህ ስልጠና መካኒክ አሽከርካሪዎችን በማፈራት የትራፊክ አደጋን መቀነስ ዋናው አላማ ነው በተጨማሪም ብቃት ያለውና ተወዳዳሪ አሽከርካሪ በማፍራት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የሚያግዝ ትልቅ ስልጠና ነው ይህንን ስልጠና በምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በሆነው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመሰጠቱ ልባዊ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡ በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰላሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆን በንግግራቸውም የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወት፣በንብረት በአጠቃላይ አምራች የሆነውን ማህበረሰብ የሚጎዳ ነው ይህንን አደጋ ደግሞ ለመቀነስ ብቁና ተወዳዳሪ አሽከርክሪዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን አያይዘውም ብቁ እና ተወዳዳሪ አሽከርካሪዎችን ለማፍራት ደግሞ ዛሬ እንደተመረቃችሁት አይነት አሽከርካሪዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡በመጨረሻም ይህንን ስልጠና እንዲሳካ ላበረከቱ በሙሉ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ መካኒክ አሽከርካሪዎች ስልጠና ይህ የመጀመሪያ ዙር ሲሆን በዚህም ስልጠና 47 አሽከርካሪዎች የተሳተፉበት እንደሆነና ሁለተኛ ዙር ስልጠናም እንደተጀመረ በእለቱ ተገልጿል ፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 6/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በድሬዳዋ ፌደራል ማረሚያ ቤት ውስጥ ላሉ የህግ ታራሚዎች ለተከታታይ 7 ቀናት ሲሰጥ የነበረውን የህይወት ክህሎት የመጀመሪያ ዙር ስልጠና አጠናቀቀ፡፡ በስልጠናው ማጠናቀቂያ
+6
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በድሬዳዋ ፌደራል ማረሚያ ቤት ውስጥ ላሉ የህግ ታራሚዎች ለተከታታይ 7 ቀናት ሲሰጥ የነበረውን የህይወት ክህሎት የመጀመሪያ ዙር ስልጠና አጠናቀቀ፡፡ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ወቅት የተገኙትና ስለ ስልጠናው ያብራሩት በድሬዳዋ ፌደራል ማረሚያ ዳይሬክተር የሆኑት ረ/ኮምሽነር ሙላት ጫንያለው ሲሆኑ በንግግራቸውም ከኮሌጁ ጋር ከዚህ ቀደም የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመናል ዛሬ የተጠናቀቀው የመጀመሪያ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠናው የስምምነቱ አንድ አካል ነው ያሉት ረ/ኮምሽነሩ አያይዘውም ይህ ስልጠና ማረሚያ ቤት ውስጥ ያሉ ታራሚዎች ባህሪያቸውን እንዲያሻሽሉ፤ወደ ህብረተሰቡም ሲቀላቀሉ ግላዊ ማህበራዊ ስሜቶቻቸውን እንዴት ማንጸባረቅ እንደሚችሉ ያሳየ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡ለዚህ ስልጠና መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱት የኮሌጁ ኃላፊዎች እንዲሁም መምህራን ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በስልጠናው መዝጊያ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሰልሃዲን አብዱልሃሚድ እንደተናገሩት ይህ ስልጠና ለታራሚዎች መሰጠቱ የግል ክህሎቶቻቸውን እንዴት ማዳበር እንዳለባቸው እንዲሁም በቀጣይ ከማህበረሰቡ ጋር ሲቀላቀሉ በራሳቸው የሚተማመኑ ከቀድሞ ስህተታቸው ተምረው ማህበረሰቡን እንዴት መካስ እንዳለባቸው ያስገነዘበ ስልጠና ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ታራሚዎችን ስብእና መገንባት የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን ሁሉ አካላት በጋራ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡በመጨረሻም ይህ ስልጠና በህይወት ክህሎት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በተመረጡ ሞያዎች የክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠት የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡ ይህ የመጀመሪያ ስልጠና ለ73 ታራሚዎች ለ7 ቀን የተሰጠ ስልጠና መሆኑን ከአስተባባሪዎቹ መረዳት ተችሏል፡፡ የኮሌጁ ኮምንኬሽን ታህሳስ 5/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬደዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለአንድ ማዕከል አመራሮች እና ባለሞያዎች ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ስልጠናው በዘርፉ የእሳቤ ዘረመል (DNA)፤ የቤተሰብና የማህበረሰብ ንግድ፤ የሞዴል ኢንተርፕራይዞች መመሪያ፤ የጥሪት ማፍሪያ መመሪያ እና የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ አተኩሮ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍና ኢንተርፕራይዝ ልማት ላይ አትኩሮ የአስተዳደሩን የማክሮ ኢኮኖሚው ትልቁ የትኩረት አቅጣጫ የሆነውን ሥራ አጥነትን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ የሚያስችል ተልዕኮ የተወሰደበት ሆኗል፡፡ ይህም ተልዕኮውን ለማሳካትም የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎቻችን ከኢኮኖሚ ልማቱ ጋር በማስተሳሰር የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የአስተዳደሩ የወረዳ አንድ ማዕከላትን አቅም በመገንባት ተግባራዊ እንቅስቃሴውን ከፍ ባለ መነቃቃትና ተነሳሽነት ለመፈጸም አቅጣጫ  የተቀመጠበት ሲሆን በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ በአስተዳደሩ የሚካሄዱ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎች በአጠቃላይ ዕለታዊ ችግሮችን ከማቃለል ባሻገር ሀብት መፍጠርና ማካበት እንዲሁም ጥሪት ማፍራት ላይ የሚያተኩሩ በዋናነትም ክህሎት መር መሆኑ ተመላክቷል፡፡ እንደ አስተዳደር ያለውን ፀጋ አልምቶ መጠቀም እንዲቻል የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎቻችን የየአካባቢውን ፀጋ የለዩ እና በሂደቱ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች በሙሉ የእሴት ሰንሰለትን መሰረት ያደረጉ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ለሥራ ፈጣሪዎች ምቹ የሆነ ስነ ምህዳር ለማመቻቸት ከባለድርሻ፣ አስፈፃሚ እና አጋር አካላት ጋር የተጀመሩ ስራዎችም ተስፋ የሚሰጡ መሆናቸውና ከዚህ አንፃር የተለያዩ አካላትም ለሥራ ፈጠራ እየሰጡ ያለው ትኩረት እየተሻሻለ መምጣቱ ይህም ስነ-ምህዳሩን ለማስፋት የተጀመረው ጥረት ተስፋ ሰጪ መሆኑንና የተፈጠረውን እድል ዜጎችን ተጠቃሚ በሚያደርግ አግባብ መጠቀም እንደሚገባ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት አቶ ሰኢድ አሊ አስገንዝበዋል፤ በስልጠናው ማጠናቀቂያም የማደግ አለኝታ ያላቸው ኢንተርፕራይዞች በማክሮ ኢኮኖሚው እድገት ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ  የሚያግዙ የሥልጠና፣ የብድር፣ የገበያ ትስስርና መሰል መንግስታዊ ድገፎችን እንዲያገኙ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑና ከሥራ ፈጠራ ባሻገር የአስተዳደሩን ነዋሪ ችግር ሊፈቱ የሚችሉ፣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎቻችን የሚያፋጥኑና በተለይ እንደ ሀገር ተኪ ምርቶች ላይ አቅም ለመፍጠር የሚያስችል ውጤት ለማስመዝገብ ስልጠናውን ወደ ተግባር መቀየር እንደሚገባ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ አሳስበዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 5/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ጠቃሚ አገር በቀል እውቀቶች፣ ክህሎቶችና ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችል መድረክ ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና ለባለድርሻ አካላት አዘጋጀ። በግንዛቤ ማስጨበጫና በውይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆኑ አገር በቀል እውቀቶችንና ክህሎቶች ለሀገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገት ያላቸው ፋይዳ ቀላል አለመሆኑ በዚህም  በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተማሪዎች እያዳበሩ የሚያድጉበት አመቺ ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚገባ ከመድረኩ ተነስቷል፡፡ በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ በተመላከተው መሰረት አገር በቀል እውቀቶችና ክህሎቶችን ማልማት ትኩረት መሰጠቱ ትልቅ አቅም መሆኑም የቢሮው ም/ኃላፊ እና የኤጀንሲው ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል። ኃላፊዋ አክለውም በአስተዳደሩ የሚገኙ አገርበቀል እውቀቶችንና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ስርዓተ ትምህርት ለማስገባት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስታውሰው ይህን የማህበረሰብ ሀብት ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገርና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የመምህራን ሚና ላቅ ያለ እነደሆነ አስረድተዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 5/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር በሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የኮሌጆችን አቅም ለማሳደግና የአሰልጣኝ መምህራን
+6
የድሬዳዋ አስተዳደር በሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የኮሌጆችን አቅም ለማሳደግና የአሰልጣኝ መምህራንን የክህሎት ክፍተት መሙላት የሚያስችል ስራዎችን በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡ በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የማኑፋክቸሪንግ ትምህርት ክፍል እና የአውቶሞቲቭ ትምህርት ክፍል የውስጥ የሚገኙ በተለያየ ምክንያት የተበላሹ ሶስት ማሽኖች በማኑፋክቸሪንግ ትምህርት በኩል CNC lathe machine እና CNC milling machine የተጠገኑ እና ወደ ስራ የገቡ ሲሆን በቀጣይ የSpot welding machine ፣ Circular sheet metal cutter ፣ Surface grinding machine ተሰርተውና ተጠግነው ወደ ስራ እንዲገቡ በእቅድ የተያዙ ሲሆን፤ በአውቶሞቲቭ ትምህርት ክፍል ደግሞ የመኪና ማጠቢያ ማሽን እንዲሁም የተሸከርካሪ አመታዊ መመርምሪያ ማሽን (ቦሎ ማሽን) ጥገና ተደርጓል፡፡ የማሰልጠኛ ማሽኖቹ ጥገና በአሰልጣኝ መምህራኑ መካከል የልምድና የእውቀት ሽግግር አንዳቸው ለሌላቸው በማድረግ አሰልጣኝ መምህራኑ የክህሎት አቅማቸውን በአንድ በኩል ሲያሳድጉ ከዚሁ ጎን ለጎን ማሽኖቹን ጠግነው ለትምህርትና ስልጠናው ዝግጁ በማድረግ ጥቅም ላይ እንዲውሉ አድርገዋል ያሉት የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ሲሆኑ ለ15 ቀናት በተከናወነው የጥገና ስራ በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን ዘንድ ያለውን የክህሎት ክፍተት መሙላት መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ይህ ተግባር በኮሌጁ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ክፍሎች እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 4/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

#ዜና | በቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ የሚሰጡ የሞያ ስልጠናዎች በሀገር ውጥ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ማእከል ማድረግ እንዳለበት ተገለፀ። #Diretv አማርኛ ታህሳስ 3/2017 የድሬዳዋ አስተዳደር ኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአስተዳደሩ ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሔደ። እንደ ሀገር አቀፍ ያለውን የስራ እጥ ችግርን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። በዚህ የቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች ደሞ ያላቸው ሚና ቀላል የሚባል አይደለም። ይሁን እንጂ የሞያ ኮሌጆች የሚሰጡት ስልጠና ክህሎትን ከስራ ቅጥር ጋር ያገናኘ ባለመሆኑ ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች የሚወጡ ሰልጣኞች በስራ እጦት ሲቸገሩ ይስተዋላል። የድሬዳዋ አስተዳደር ኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአስተዳደሩ ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ጋር ተቀራርቦ መስራት በሚቻልባቸው የስልጠናና የትምህርት መስኮች ላይ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ የሚሰጡ የሞያ ስልጠናዎች በሀገር ውጥ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ማእከል ማድረግ እንዳለበት የገለፁትና የኢንዱስትሪዎች ፍላጎት ተለይቶ ስራ እጥነትን መቅረፍ ያስችላል፣ ለዚህም ኢንዱስትሪዎች በራሳቸው የሚሰጡትን ስልጠና በማቆም ለኮሌጆች ሀላፊነቱን መስጠት አለባቸው ሲሉ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን የሆኑት አቶ ታደለ አሰፋ ተናግረዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በአስተዳደሩ ባሉ ሁለት የሞያ ኮሌጆች የሚያሰለጥኑት ኢንዱስትሪ መር ስልጠናዎች ውጤት እያመጡ በመሆኑ ኢንዱስትሪዎች ከኮሌጆች ጋር በፈቃደኝነት ተቀራርበው መስራት አለባቸው ሲሉ ገልፀዋል። የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ Education and Skills for Employ Ability ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፋሲል ማዘንጊያ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ተቀራርቦ መስራት ኮሌጁ የኢንዱስትሪዎች ፍላጎትን በማጤን ከውጪ የሚመጡ ባለሞያዎችን በመተካት የኮሌጁ ምሁራንን በማብቃት ምሁራን ብቁ የሆኑ ሰልጣኞችን በማውጣት የተሻለ አፈፃፀም ማምጣት ያስችለናል ሲሉ ገልፀውልናል። በመድረኩ የተገኙት ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተወጣጡና ባለድርሻ አካላት ውይይት አካሒደዋል። ይህ Education and Skills for Employ Ability ፕሮጀክት ከአለም ባንክ በተገኘ 6.7 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ በኮሌጁ ለኢንዱስትሪው ተፈላጊ የሆኑ የስራ ትስስሮችን መፍጠር የሚያስችል የ5አመት የስልጠና መርሀግብር መሆኑ ታውቋል። ©️ ድሬቲቪ

#ዜና | ከአራቱም የገጠር ክላስተሮች ለተዉጣጡ ከ30 በላይ የሴት ኢንተርፕራይዞች ከ360 በላይ ፍየሎች ድጋፍ ተበረከተ። #Diretv አማርኛ ታህሳስ 3/2017 ድጋፉን የሰጠው የድሬደዋ የስራና ክህሎት ቢሮ ሲሆን ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት (snv) በተገኘ የገዘብ ድጋፍ ነው። የድሬደዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ድጋፉን በተበረከተበት ወቅት እንዳሉት ይህ ድጋፍ ከአራቱም የገጠር ክላስተሮች ለተዉጣጡ ከ30 በላይ የሴት ኢንተርፕራይዞች የተሰጠ ሲሆን ሁሉም በቤተሰብ ደረጃ በማህበር የተደራጁ ናቸው ብለዋል። አቶ ሮቤል አክለውም ይህ ድጋፍ እንደሀገር ለተጀመረው የሌማት ትሩፋት መርሀግብር ራስን በምግብ ከመቻል አንጻር ብሎም ከተረጅነት ለመላቀቅ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ በተደረገ የዶሮዎች ድጋፍ ኢንተር ፕራይዞቹ ከራሳቸው ፍጆታ አልፈው ዶሮ እና እንቁላል ለገበያ በማቅረብ የዋጋ ንረትን በማረጋጋት በኩል አበረታች ውጤት እያሳዩ ነው ብለዋል። በተያያዘ ዜና የድሬደዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ለአንድ ማዕከል አመራሮች እና ባለሞያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል። የቢሮው ሀላፊ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት ስልጠናው በ4 ዋናዋና ነጥቦች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀዋል እነዚህም የተቋም ግንባታ፣ተግባር ወይም ክህሎት መር የስራ እድል ጠራ፣ የስልጠና ዘርፎች እና የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳዮች ናቸው። ሀላፊው በወቅቱ ቢሮው በጀመራቸው አዳዲስ እሳቤዎች ላይ አቅም በመገንባት የእሴት ሰንሰለት በጠበቀ መልኩ የስራ እድል መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል። ስልጠናዉም በነገው እለት እንደሚጠናቀቅ ከመርሀ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል። ©️ ድሬቲቪ

ጠቃሚ አገር በቀል እውቀት፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ ተካሄደ።       በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ጠቃሚ አገር በቀል እውቀት፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ምንነትና መረጃ አሰባሰብ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችል መድረክ ለወረዳ አንድ ማዕከላትና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አዘጋጀ።      በግንዛቤ ማስጨበጫና በውይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆኑ አገርበቀል እውቀቶችንና ክህሎቶችን በመለየትእያዳበሩ የሚያድጉበት አመቺ ሁኔታ ማመቻቸት ላይ በተለይ በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ በተመላከተው መሰረት ለአገርበቀል እውቀቶችንና ክህሎቶችን ማልማት ትኩረት መሰጠቱ ትልቅ አቅም መሆኑም ተገልጿል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 3/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ