1 330
Suscriptores
+324 horas
+87 días
+8330 días
Archivo de publicaciones
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ጋር በመተባበር የኩባንያ ውስጥ ስልጠና ለማጠናከር የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ይህም ስልጠና በ2017 ዓ.ም የኩባንያ ውስጥ ስልጠና ለመስጠት በአስተዳደሩ ከሚገኙ ለትብብር ስልጠና መስጫነት ከተመረጡ ኩባንያዎች በ4 የሙያ ዘርፎች ማለትም በማኑፋክቸሪንግ፣ ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ፣ በሆቴልና ቱሪዝም እንዲሁም በአውቶሞቲቭ ሙያዎች ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች በተውጣጡ አሰልጣኞች የኩባንያዎቹን ሰራተኞች ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት በመለየት ስልጠና ለመስጠት ያስችል ዘንድ ከ4ቱ ዘርፎች ለተውጣጡ አሰልጣኝ መምህራንና ስልጠና አስተባባሪዎች የአሰልጣች ስልጠናው መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ የኩባንያ ሰራተኞችን በማብቃት፤ የቴክኖሎጂ ክፈተቶችን በመሙላት ምርትና ምረታማነትን ማሳደግ ሲሆን በተጨማሪም የአሰልጣኝ መምህራንን አቅም በማሳደግ በትብብር ስልጠና ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጥራት ችግሮችን ከወዲሁ ለመፍታት ማስቻል ነው ሲሉ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ጀማል አደን ገልጸዋል ፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
ADRA ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) በፕሮጀክቱ አፈፃፀም ላይ በየጊዜው የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ከባለድርሻ እካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ::
በመድረኩ የመጀመርያ ዙር ተመራቂ ሰልጣኞችን በማደራጀት ሂደት ውስጥ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች ለመለየት እና የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ በአስተዳደሩ ከከተማና ከገጠር የተወጣጡ አራት ክላስተሮች በተገኙበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል::
በእለቱ ባለድርሻ አካላቱን ያወያዩት የስራና ክህሎት ቢሮ ም/ሀላፊና የኤጀንሲው ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጥፋ ለተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት ዘርፉ አዲስ ከመሆኑ አኳያ ብዙ ያልተነኩ የስራ ዕድሎችን መፍጠር የሚያስችል በመሆኑ እንዲሁም በእስተዳደሩ በሚገኙ ገጠር ወረዳዎች ውስጥ ከተወሰኑት በቀር የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተደራሽ እለመደረጉን እስታውሰው ይህን ሁሉ አጋጣሚ በእጃችን ይዘን ሰልጣኞቹን ለማደራጀትና ወደ ስራ ለማስገባት ምክንያት ምንደረድር ከሆን ችግሩ ያለው እኛው ጋር ነውም ብለዋል::
በዘርፉ የገጠሙ ችግሮችን ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው ሰፋ ያለ ውይይትም የመጀመርያ ዙር ሰልጣኞች በገጠርም ሆነ በከተማው በአፋጣኝ ወደ ስራ የሚገቡበት ሁኔታ ምችችት እንዲደረግና ለዚህም ጉዳዩን በባለቤትነት የያዙት ባለድርሻ አካላት ተቀዳሚ ተግባራቸው አድርገው ሊወስዱትና ጉዳዩንም ከዳር ሊያደርሱት እንደሚገባ ተገልፇል::
በተጨማሪም ሰልጣኞች የወሰዱት የሙያ ክህሎት ወደ ሀብት እንዲለወጥ እንዲሁም ያሰለጠንናቸው ወጣቶች ወደ ስራ መሰማራታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ዘርፉ ላይ ያለውን የሀብት ብክነት እንደሚታደግ የተገለፀ ሲሆን ሁሉም የባለድርሻ አካላት በመረባረብ የስልጠናውን ውጤት ማሳየት እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል::
በመጨረሻም ለሁለተኛ ዙር ስልጠና በተደረገው የሰልጣኝ የምልመላ ሂደት ላይ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮች በመድረኩ በዝርዝር ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በገጠሩ ያሉ ወጣቶችን በምልመላው መስፈርት መሰረት ተመልምለው ለክላስተር ሀላፊዋች ወደ ስልጠናው እንዲገቡ ጠንከር ያለ መልእክትም ተላልፏል።
በመድረኩ ማገባደጃም በአስተዳደሩ ከሚገኙ የከተማ እና የገጠር አራት ክላስተሮች የተወጣጡ የአንድ ማዕከል ባለሞያዎች እና ሀላፊዎች የጋራ ውይይት አካሂደዋል::
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ህዳር 29/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዘንድሮ ዓመት በተቋሙ ለሚጀመረው የEASE ፕሮጀክት SIP Validation እና የፕሮጀክት ማስጀመርያ መድረክ አካሄደ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከአለም ባንክ ባገኘው 6.7ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በኮሌጁ ለኢንዱስትሪው ተፈላጊ የሆኑ የስራ ትስስሮችን መፍጠር የሚያስችል የስልጠና መርሀ-ግብር SIP(Strategic Investment Plan) ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በእለቱ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የስራና ክህሎት ቢሮ ም/ሀላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ሲሆኑ በንግግራቸውም ይህን የEASE ፕሮጀክት ትግበራ ላይ ሲውል የከተማና የገጠር ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ መሆን እንደሚገባው ተናግረው አያይዘውም መሰል ፕሮጀክቶች በአግባቡ ካልተመሩ እና በትክክል ለተቀመጠላቸው አላማ ማይውሉ ከሆነ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው እንደሚያመዝን ጠቅሰው ኮሌጁ ከሌሎች ትምህርት በመውሰድ ፕሮጀክቱን በተቀመጠለት እቅድ መሰረት እንዲመራና የሚፈለገውን ግብ እንዲመታ አደራ ብለዋል::
በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ እሰፋ ሲሆኑ በንግግራቸውም ይህ ፕሮጀክት የኮሌጁ የፈንድ ራይዚንግ ክፍል የመጀመርያ ስራ የሆነው የEASE (Education and Skills for Employability) ፕሮጀክት መሆኑን አስታውሰው በብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ታልፎና ብዙ ኮሚትመንት ተጨምሮበት ዛሬ ለደረስንበት ደረጃ መብቃቱን ጠቅሰው በነበረው ሂደት ላይም ቀላል ማይባሉ እድካሚና እሰልቺ መንገዶች ታልፈው እዚህ እንደደረሰ በመግለፅ ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት ትልቁን ሚና ለተወጡት የፕሮጀክት አስተባባሪዎች ትልቅ ምስጋና አቅርበዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም ይህ ፕሮጀክት በቀጣዮቹ 5 አመታት ውስጥ አንድ የራሱን አሻራ አሳርፎ የሚያልፍ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀው ዛሬ ይህ ፕሮጀክት ለሰራተኛው ሲቀርብም በተቻለ መጠን የሰራተኛውን ተሳትፎና የሁሉንም ሰው ርብርብ እንደሚጠይቅ ግንዛቤ ለመፍጠር ሲሆን የፕሮጀክት ውጤታማነት የሚለካውም በሁሉም የጋራ ተሳትፎ መሆኑንም አፅዕኖት ሰተው ተናግረዋል::
በመድረኩ የEASE (Education and Skills for Employability) ፕሮጀርት ሰነድ በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ለተቋሙ ሰራተኛ የቀረበ ሲሆን በዚህም ይህ ፕሮጀክት ከምን ተነስቶ እንደተጀመረና አላማውስ ምንድነው ከሚለው ጀምሮ የፕሮጀክቱን ዋና ሰነድ በዝርዝር አቅርበዋል::
በመጨረሻም የፕሮጀክቱን SIP(Strategic Investment Plan) እንዲሁም ከፕሮጀክቱ የሚጠበቁ ውጤቶችን በተመለከት የEASE ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ በሆኑት አቶ ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት የቀረበ ሲሆን አጠቃላይ በመድረኩ በቀረቡ ሰነዶች ላይ ሰፋ ያለ ውይይትም ተደርጎበታል::
ፕሮጀክቱ በዋናነት የስራ እድል ትስስርን ይፈጥራል የተባለ ሲሆን ይህም በአስተዳደሩ የሚገኙ የገጠርና የከተማ ወረዳዎችን ጨምሮ በርካቶችን የሞያ ክህሎትን በማሰልጠን ከገበያው ጋር የሚያስተሳስር መሆኑም ተገልፇል።
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ህዳር 28/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በአስተዳደሩ የሚገኙ የገጠርና የከተማ ወረዳዎች ወጣቶችን የስራ እድል ትስስርን የሚፈጥር ኘሮጀክት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስትራቴጂክ ፕላን ቀርቦ ውይይት ተካሄደ::
የድሬዳዋ አስተዳደር ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከአለም ባንክ ባገኘው 6.7 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በኮሌጁ ለኢንዱስትሪው ተፈላጊ የሆኑ የስራ ትስስሮችን መፍጠር የሚያስችል የስልጠና መርሀ-ግብር ስትራቴጂክ ፕላን ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ለአምስት አመት እንደሚቆይም ተገልጿል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከአለም ባንክ ባገኘው 6.7 ሚልየን ዶላር EASE (Education and Skills for Employability) ኢዱኬሽን ኤንድ ስኪል ፎር ኢምፕሎይቢሊቲ ፕሮጀክትን የማስጀመር መርሀ-ግብር ተካሒዷል።
ፕሮጀክቱ በዋናነት የስራ እድል ትስስርን ይፈጥራል የተባለ ሲሆን ይህም በአስተዳደሩ የሚገኙ የገጠርና የከተማ ወረዳዎችን ጨምሮ በርካቶችን የሞያ ጥበብን ወይም ስኪልን በማሰልጠን ከገበያው ጋር እንደሚያስተሳስርም ተገልፇል።
በዚህ EASE ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ተገኝተው መርሀ-ግብሩን ያስጀመሩት በድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ጌታቸው ባስተላለፉት መልእክት ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ጠንካራ አመራር ሰጪነት ወሳኝ እንደሆነ ገልፀው ለታለመለት አላማም መሰረት አድርጎ መከናወን እንዳለበት አሳስበዋል።
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በማኒፋክቸሪንግ ፣ በኤሌክትሮ ቴክኖሎጂና በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ የስልጠና መስኮች ከመማርና ማስተማር ጋር ያሉ የትምህርት ጥራትን አካቶ ተወዳዳሪነትን የሚጨምሩ የኢንዱስትሪ ፍላጎት የሚያሟሉ አዳዲስ የስልጠና መስኮችን ለመቅረፅ የሚያስችል ፕሮጀክት ነው ሲሉ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን የሆኑት አቶ ታደለ አሰፋ ተናግረዋል።
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በፊት በመደበኛ ከሚሰጠው ስልጠና በተጨማሪ ይህ የEASE ፕሮጀክት በዋናነት አካታች የሆነ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስልጠና ይሰጣል ሲሉ የፕሮጀክቱ ዋና ኮርድኔተር አቶ ፋሲል ማዘንጊያ ገልጸዋል።
ይህ EASE (Education and Skills for Employability) ፕሮጀክት ኮሌጁ ከአምስት አመት በኋላ አሁን ካለበት ስልጠና የመስጠት አቅም በቴክኖሎጂ የተደገፈ መሰረተ ልማት የተሟላለት ኮሌጅ እንዲሆን ያስችለዋልም ተብሏል።
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ህዳር 26/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
‹‹ከወጣቶች ጋር በመተባበር ሙስናን መከላከል፣ የነገን ስብዕና ለመቅረጽ ›› በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ በኮሌጃችን በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፀረ- ሙስና ቀን በፓናል ውይይት እንዲሁም በስልጠና በዛሬው እለት ተከበረ፡፡
ሙስና የጋራ ጠላት ነው በህብረት ሆነን ያማንታገለው ከሆነ ወደምናስበው የብልጽግና ጉዞ እንዳንሄድ አስሮ ወደኋላ የሚያስቀረን ነው ስልዚህ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ሁሉ ሙስናን የሚጠየፍ ማህበረሰብ በመፍጠር ሙስናን በጋራ ሆነን ልንታገለው ይገባል ፡፡ በኮሌጅም ደረጃ ሙስናን ለመከላከልና ለመታታገል አዳዲስ የአሰራር ስርአቶችን በማዘጋጀት የሙስና፣የብልሹ አሰራሮች እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በጋራ ሆነን በመስራት ይህንን መጥፎ ተግባር ልንከላከለው ብሎም ልናጠፋው ይገባናል ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሳላሃዲን አብዱልሃሚድ ናቸው፡፡
የኮሌጁ ዲን አያይዘውም ኮሌጃችን እንደ ስሙ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል እንዲሆን እንዲሁም ለሌሎች አቻ ኮሌጆች አርአያ መሆን የሚችል ተቋም ለመገንባት ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ በጋራ በመስራት ሙስናን መከላከል ይገባናል ያሉ ብለዋል፡፡ ሃገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ብዙ ወጣቶች የሚገኝባት ሃገር እንደመሆኗ መጠን ወጣቶች ሙስናን የሚጠየፉ ለማድረግ በስልጠና ስርአታችን ውስጥ አካተን ማስተማር ይገባናል ብለዋል፡፡
በማስቀጠል በፓናል ውይቱና የስልጠና መድረኩ ላይ በአቶ በለጠ እሸቱ የኮሌጁ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና መከታተያ ባለሙያ ሙስና በአለም አቀፍ እንዲሁም በሀገራችን ደረጃ አሁናዊ ሁኔታ የሚዳስ ሰነድ ለከኮሌጁ ማህበረሰቦች በማቅረብ የተለያዩ ውይይቶች እንዲሁም ግልጽነት የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ተሳታፊው በጋራ ሙስና የጋራ ጠላት እንደ ሆነ በመረዳት ሁሉም ሰው ከወጣቶች ጋር በጋራ ለመታገል ቃል በመግባት መድረኩ ፍጻሜ አግኝቷል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ህዳር 28/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ እና በአስተዳደሩ ካይዘን ኢንስቲትዩት መካከል የካይዘን ትግበራ ድጋፍ፣ ክትትል እና ግምገማ ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
በዋናነት መድረኩ ኤጀንሲው ከኢንስቲትዩቱ ጋር የተናበበ የጋራ ዕቅድ ባለመኖሩ የተመላከቱ አለመናበቦችን ለማጥራት ይህም ኢንዱስትሪዎች ላይ የካይዘን ትግበራ ሲከናወን ኢንዱስትሪዎች ፍላጎታቸውን በሚጨምር እና በአሰልጣኞች ላይም የጊዜ ብክነትን በማይፈጥር መልኩ ውጤታማ ስራ ለመስራት መግባባት ላይ ያተኮረ ሆኗል፡፡
በዚህም መድረክ ላይ በአጠቃላይ በኮሌጆች እየተሰጠ ያለውን የካይዘን ትግበራ ድጋፍን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እና እየሰፋ የመጣውን የካይዘን ጽንሰ ሃሳብና ትግበራን ለማዘመን የሚያስችሉ ስልጠናዎች ሊሰጡ እንደሚገባ የቢሮው ም/ኃላፊ እና የኤጀንሲው ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል፡፡
በተያያዘ ለአሰልጣኞች በካይዘን ደረጃዎች በመመዘን ሰርተፍኬት የመስጠቱ ሁኔታ እየታደሰ የሚሄድ እና ቀጣይነት ያለው ሊሆን እንደሚገባው፤ በተለይ ኮሌጆች በካይዘን ትግበራ የተሻለ ልምድ ቢኖራቸውም ከኢንስቲትዩቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የተበቀ በማድረግ በካይዘን ትግበራ የተገኙ ውጤቶችን እንደ አስተዳደር አንጸባራቂ ሆነው እንዲወጡ ማድረግ ላይ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ተነስቷል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 27/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በምስራቅ ዕዝ ደረጃ-3 ሪፈራልና ማስተባበሪያ ሆስፒታል ውስጥ የተቋቋመው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ላይ የ2017 ዓ.ም የሰልጣኞች ቅበላ ዶክመንት ለማጣራትና የሰልጣኝ መረጃ አደረጃጀት የሚመለከት የድጋፍና ክትትል ስራ ተከናወነ።
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የማሰልጠኛ ተቋማት ህጋዊ የማሰልጠን ፈቃድ የሚሰጥና በሰጠው ፈቃድ መሠረት በየጊዜው ድጋፍና ክትትል በማድረግ የስልጠናው ጥራት መጠበቁን ያረጋግጣል።
በዚህም በምስራቅ ዕዝ ደረጃ-3 ሪፈራልና ማስተባበሪያ ሆስፒታል ውስጥ የተቋቋመው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በነርሲንግ ሙያ ዘርፍ በደረጃ አራት ወንድ 555 ሴት 81 በአጠቃላይ 636 የተቀበላቸው ሰልጣኞችን የትምህርት ማስረጃ ህጋዊነትና ትክክለኛነት ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ለተቋሙ የስልጠናውን ጥራት እንዲያስጠብቅ ሙያዊ ድጋፍ አግኝቷል።
በተያያዘ በአስተዳደሩ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሚያከናውኗቸው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተግባራት ቢሮው በቅርበት በመከታተልና በትብብር መንፈስ የመረጃ አያያዝ ስርዓታቸውን እንዲያሳድጉና ጥራት ያለው ስልጠና መስጠት እንዲችሉ የሚደረገው እገዛና ድጋፍ በሌሎችም ተቋማት በተመሳሳይ የሚቀጥል እንደሚሆን አቶ ታሪኩ ለገሰ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገልጸዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 27/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
