es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Ir al canal en Telegram
1 317
Suscriptores
Sin datos24 horas
+287 días
+14730 días
Archivo de publicaciones
በዛሬው ዕለት ክቡር ጠቅላይስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚኒስትር ዴዔታዎች ሹመት ሰጥተዋል። በዚህ መሰረት 1. ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት 2. ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እና 3.ክቡር አምባሳ
+2
በዛሬው ዕለት ክቡር ጠቅላይስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚኒስትር ዴዔታዎች ሹመት ሰጥተዋል። በዚህ መሰረት 1. ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት 2. ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እና 3.ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሹመዋልአሕመድ መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ! #የመደመርመንግሥት

የድሬደዋ አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ቡድን በሥራና ክህሎት ቢሮ አካሄደ። በተደረገውም የድጋፍና ክትትል ምልከታ የሱፐርቪዥን ቡድኑ በዋናነት ቢሮው በሩብ ዓመቱ ያከናወናቸውን ስራዎች አፈጻጸም በመገምገም ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ነው። በዚህም ቡድኑ በምልከታውም ቢሮው በሩብ አመቱ የተከናወኑ በርካታ የሪፎርም ስራዎች መመልከት የቻለ ሲሆን የተሰሩ ስራዎችን መረጃ በአግባቡ በማደራጀት እረገድም ጅምሩ ጥሩና ከዚህ በበለጠ እያጠናከሩ መሄድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ቢሮው የስራ ቦታ ምቹነትን ከማረጋገጥ አንጻር ያለውን ጅምር ስራ አድንቀው ለሠራተኛ ምቹ ከማድረግ አኳያ ይህንኑ ተግባር ማስፋት እንደሚገባ አመላክተዋል። በአጠቃላይ በዝግጁነት ምዕራፍ ከዕቅድ ዝግጅት ወደ ታች እስከ ማውረድ፤ ከቢሮው ሰራተኛ እስከ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረኮች መዘጋጀታቸው እንዲሁም የግዢ ፍላጎቶችን በመለየት ወደትግበራ ከወዲሁ መገባቱ በመልካም ታይቷል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መስከረም 29/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬደዋ አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ቡድን በሥራና ክህሎት ቢሮ አካሄደ። በተደረገውም የድጋፍና ክትትል ምልከታ የሱፐርቪዥን ቡድኑ በዋናነት ቢሮው በሩብ ዓመቱ ያከናወናቸውን ስራዎች አፈጻጸም በመገምገም ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ነው። በዚህም ቡድኑ በምልከታውም ቢሮው በሩብ አመቱ የተከናወኑ በርካታ የሪፎርም ስራዎች መመልከት የቻለ ሲሆን የተሰሩ ስራዎችን መረጃ በአግባቡ በማደራጀት እረገድም ጅምሩ ጥሩና ከዚህ በበለጠ እያጠናከሩ መሄድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ቢሮው የስራ ቦታ ምቹነትን ከማረጋገጥ አንጻር ያለውን ጅምር ስራ አድንቀው ለሠራተኛ ምቹ ከማድረግ አኳያ ይህንኑ ተግባር ማስፋት እንደሚገባ አመላክተዋል። በአጠቃላይ በዝግጁነት ምዕራፍ ከዕቅድ ዝግጅት ወደ ታች እስከ ማውረድ፤ ከቢሮው ሰራተኛ እስከ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረኮች መዘጋጀታቸው እንዲሁም የግዢ ፍላጎቶችን በመለየት ወደትግበራ ከወዲሁ መገባቱ በመልካም ታይቷል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መስከረም 29/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ

የሙያ ደህንነትና ጤንነትን ለማጠናከር የፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ የአደጋ ስጋት ግምገማ (Risk Assessment) ሰነድ ተገመገመ በተከታታይ በተከናወኑ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ቁጥጥር ሥራዎች መነሻነት፣ ፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ የአደጋ ስጋት ግምገማ (Risk Assessment)ሰነድ አዘጋጅቶ ለድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊና ለአሰሪና ሠራተኛ ዳይሬክቶሬት አቅርቧል። በሰነዱ ላይ በተካሄደው ውይይት፣ የተዘጋጀው የአደጋ ስጋት ግምገማ (Risk Assessment) ይዘትና በቀጣይ መከናወን የሚገባቸው የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሥራዎች ላይ ትኩረት ተደርጓል። የውይይቱ ዓላማም በሥራ ቦታ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን በመለየት፣ በመገምገምና ተገቢ የመከላከያ እርምጃዎችን በማቀድ የሠራተኞችን ደህንነትና ጤንነት የሚያጠናክሩ ተግባራትን ማሳደግ ነው። ቢሮው በዘርፉ የሚያከናውናቸውን የቁጥጥርና የክትትል ሥራዎች በማጠናከር፣ በሥራ ቦታዎች የደህንነትና ጤንነት ስጋቶችን በቅድሚያ የመለየት፣ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥርዓትን ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት/ድሬዳዋ መስከረም 29/2019 ዓ.ም

የድሬዳዋ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ሴት አሰልጣኞች ፎረም በይፋ ተቋቋመ የድሬዳዋ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ሴት አሰልጣኝ መምህራን ፎረም፣ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የምስረታ መመሪያና የአፈጻጸም ሰነድ መሠረት ተመሥርቷል። ፎረሙ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በሰልጣኝነት፣ በአሰልጣኝነትና በአመራር ደረጃ ያለውን የሴቶች ተሳትፎ ለማሳደግ፣ በውሳኔ ሰጪነት ያላቸውን ሚና ለማጠናከር፣ የልምድ ልውውጥና የጋራ ድጋፍ ባህልን ለማሳደግ እንዲሁም ሴቶች ከጾታ ተኮር ጥቃቶች የሚጠበቁበትንና በተለያዩ የሙያ መስኮች በበለጠ የሚሳተፉበትን ሁኔታ ለማጠናከር ያለመ ነው። ፎረሙ አካታችነትና ፍትሃዊነትን፣ አሳታፊነትና ውክልናን፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን፣ ማብቃትና መተሳሰብን፣ ቁርጠኝነትንና በሥነ ምግባር አርዓያ መሆንን እንደ ዋና የአሠራር መርሆቹ የያዘ ሲሆን፣ የሥራውን ውጤታማነት ለመከታተልና ለመገምገም የሚያስችል ሥርዓትም ተዘርግቶለታል። በአደረጃጀቱ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ፣ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ የትምህርትና ሥልጠና ኮሚቴ፣ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እንዲሁም የሀብት ማፈላለግና የፋይናንስ አስተዳደር ኮሚቴ ተዋቅረዋል፤ በኮሚቴዎቹም የሚሳተፉ ሴት አሰልጣኞች ተመርጠዋል። በማጠቃለያው፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ሴት አሰልጣኝ መምህራን የፎረሙ ዓላማ በተግባር እንዲሳካ የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች ድጋፋቸውንና ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት/ድሬዳዋ መስከረም 29/2019 ዓ.ም

ክቡር አቶሉ አብዲ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ካቢኔያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል። በዚሁ መሠረት አቶ አወሉ አብዲ የሥ
ክቡር አቶሉ አብዲ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ካቢኔያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል። በዚሁ መሠረት አቶ አወሉ አብዲ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ምክር ቤቱ የአስፈጻሚ አካላትን ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ትናንት በሙሉ ድምፅ ማጽደቁ ይታወሳል። ረቂቅ አዋጁም አዋጅ ቁጥር 1440/2019 ዓ.ም. ሆኖ ጸድቋል። አቶ አወሉ አብዲ በአዲሱ የኃላፊነት ዘመናቸው ስኬታማ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን። #የመደመርመንግሥት

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም የተመሩት ልዑካን ቡድን በተለያዩ የመንግሥት ተቋማትና ወረዳዎች እያካሄደ ያለውን የመስክ ጉብኝትና የሥራ ግምገማ በመቀጠል የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮን ጎብኝቷል። በጉብኝቱ ወቅት በተቋሙ እየተከናወኑ ባሉ ዋና ዋና የአገልግሎት አሰጣጥ ሥራዎች ዙሪያ ከቢሮው የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል። ውይይቱም የተቋሙን የሥራ አፈጻጸም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እና በሥራ አፈጻጸሙ የሚታዩ ጠንካራ ጎኖችንና ማነቆዎችን በመለየት ቀጣይ ማሻሻያ ላይ ትኩረት አድርጓል። የቢሮው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም በተሰማሩባቸው የሥራ ዘርፎች እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት፣ ስለተመዘገቡ ስኬቶች እና በአፈጻጸም ሂደት እያጋጠሙ ስላሉ ማነቆዎች ለልዑካን ቡድኑ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። የጉብኝቱ ዓላማ የተቋሙን የሥራ አፈጻጸም በመስክ በመገምገም የአገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማነት ለማጠናከርና የሚታዩ ማነቆዎችን በመለየት ተግባራዊ መፍትሔ ለመፍጠር ያለውን ትኩረት ያሳያል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት ድሬዳዋ | መስከረም 27/2019 ዓ.ም

የተንቀሳቃሽ ሥልጠና አፈጻጸም ላይ የጋራ ውይይት ተካሄደ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ፣ ከሁለቱ የመንግሥት ኮሌጆችና ከገጠር ወረዳዎች የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር “ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ለገጠሩ ማህበረሰብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል በ2019 የሥልጠና ዘመን የታቀደውን ተንቀሳቃሽ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አፈጻጸም በመገምገም የጋራ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ላይ ከዚህ በፊት በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሠረት የተከናወኑ ሥራዎችና የደረሱበት የአፈጻጸም ደረጃ በሪፖርት ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይትና ግብረመልስ ተደርጓል። የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደገለጹት፣ የተንቀሳቃሽ ሥልጠናው ዋና ትኩረት የገጠር ማህበረሰብን ማዕከል በማድረግ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ነው። በዚህም በግብርናና ከግብርና ውጭ በሆኑ ሙያዎች ላይ 4,000 አርሶና አርብቶ አደሮችን የገበያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን በመስጠት የሙያ አቅማቸውን ለማጎልበትና የሥልጠና ተጠቃሚነትን ወደ ገጠር ማህበረሰብ ለማስፋፋት ትኩረት ተደርጓል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት ድሬዳዋ | መስከረም 27/2019 ዓ.ም

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ ከቢሮው አጠቃላይ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ። በመርሃ ግብሩ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ ለቢሮው ሠራተኞች እስካሁን ለነበረው አፈጻጸም የምስጋና መልዕክት በማስተላለፍ፣ በቀጣይ የሚከናወኑ የሥራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል። ተቋሙ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃትና በተቀናጀ አሠራር በመወጣት የሚጠበቀውን ውጤት ማምጣት እንደሚገባ በአቅጣጫው አጽንኦት ተሰጥቷል። የቢሮው ሠራተኞችም በቀጣይ በትኩረት ሊሠራባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳብና አስተያየታቸውን በማቅረብ፣ ለተቋሙ የሥራ ውጤታማነትና ቀጣይ አፈጻጸም የሚያግዙ ጉዳዮችን አንስተዋል። የትውውቅ መድረኩ አዲሱ አመራርና የቢሮው ሠራተኞች በጋራ ራዕይ፣ በተቀናጀ አሠራር እና በውጤት ተኮር አፈጻጸም የቀጣይ የሥራ ምዕራፍን ለማጠናከር ያለውን ትኩረት አሳይቷል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት ድሬዳዋ | መስከረም 27/2019 ዓ.ም

መልካም የሥራ ዘመን! ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን እንደ አዲስ ከማቋቋም ጀምሮ የዘርፉን አዳዲስ እሳቤዎች በመቅረጽና በመምራት ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ የሥራና ክ
መልካም የሥራ ዘመን! ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን እንደ አዲስ ከማቋቋም ጀምሮ የዘርፉን አዳዲስ እሳቤዎች በመቅረጽና በመምራት ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ዘርፍ ክህሎት የተላበሱ፣ ብቁና ተወዳዳዳሪ ዜጎች ማፍሪያ ብሎም የዘላቂና አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ እንዲሆን ላደረጉት ጥረት ምስጋናችን የላቀ ነው። በመደመር መንግሥት ምስረታ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው በመሰየምዎ የተሰማንን ደስታ እየገለጽን፤ አዲሱ የሥራ ኃላፊነት ዘመንዎ እጅግ ስኬታማ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

ከአፈጻጸም ግምገማ ወደ ውጤት ተኮር አቅጣጫ ክቡር ከንቲባ አብዱላሂ አደን ለድሬዳዋ ሥራና ክህሎት ዘርፍ የ2019 ዓ.ም የሥራ አቅጣጫ አስቀመጡ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደን የሥራና ክህሎት ቢሮ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸምን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና የ2019 ዓ.ም የሥራ ዕቅድን በመገምገም ለቀጣይ አፈጻጸም የሥራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ክቡር ከንቲባው በዛሬው ውሎ የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ ያቀረቡትን የ2018 ዓ.ም አፈጻጸምና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ በዝርዝር በመገምገም፣ የዘርፉ ሥራዎች በተለይም በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው አመላክተዋል። በተለይም በአስተዳደሩ የሚገኙ ወጣቶች በ‹‹ብቃት›› የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት በመመዝገብ የሥራ ልምድ፣ የገቢ አቅም እና የኑሮ ሁኔታቸውን ማሻሻል እንዲችሉ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ክቡር ከንቲባው አሳስበዋል። በተጨማሪም በአስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ የተደረገበትን የኮሪደር ልማት ሥራ ከገቢ ማስገኛና ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ጥቅም እንዲያስገኝ የግሪነሪ ልማቱን በአግባቡ መንከባከብ እና በዘርፉ የሚሰማሩ ማህበራትን በማደራጀት የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት ድሬዳዋ | መስከረም 26/2019 ዓ.ም