ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
Ir al canal en Telegram
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 t.me/FinoteBooks1623
Mostrar más3 483
Suscriptores
-124 horas
+37 días
-130 días
Archivo de publicaciones
🌻 መስከረም 21 — እመ ብዙሃን 🌻▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬ 📖🕯️ ክርስቲያኖችን ሰብስባ የያዘች ሰፊ መጋረጃ ሐዋ 10፥11 ➜
እንኳን ለእመቤታችን ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ! 🌻 መስከረም 21 ስለ ሁለት ታላላቅ ምክንያቶች ይከበራል።
1ኛ፦ እመ ብዙሃን ማርያም
በ325 ዓ.ም. የነበሩ ሃይማኖትን ያቀኑ፣ ሃይማኖታቸውም የቀና 318ቱ ሊቃውንት አባቶቻችን አርዮስን ያወገዙበት፣ ክርስቶስን አምላክ፣ እመቤታችንንም Mother of God ብለው የመሰከሩበት ታላቅ በዓል ነው።
ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው፣ እመ ብዙሃን ማለት የብዙዎች እናት ማለት ነው። ይህም የሊቃውንቱን ብዛት ያመለክታል።
ታሪኩም እንዲህ ነው፦
አርዮስ ወልድ ፍጥረትን ለመፍጠር የተፈጠረ መሣሪያ እንጂ ፍጹም አምላክ አይደለም ብሎ ተነሳ። እንደውም አልበቃ ብሎት፣ ክርስቶስ ሰው ሲሆን ለሚዋሐደው ፍጡር ሥጋ የተነገረውን በማምታታት፣ ለመለኮት እንደተነገረ እየጠቀሰ ምእመናንን ግራ አጋባቸው።
የመናፍቃን አንዱ ችግራቸው የአንዱን ጥቅስ ለሌላው ያለ አውዱ ማምታታት ነው።
በዚህ ምክንያት በየሀገረ ስብከቱ የነበሩ ሊቃነ ጳጳሳት ተሰበሰቡ። ቁጥራቸውም በትውፊታችን 2448 መሆኑ ይነገራል። ከእነዚህ ውስጥ 318 አባቶች ክርስቶስ በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ ነው ሲሉ፣ ሌሎቹ ግን ያላፈሉት ክህደት የለም።
ይህን መጻፍ ያስፈለገው አባቶቻችንን በደንብ እንድናውቅ ነው። «አባቱን የማያውቅ ልጅ...» እንደተባለው እንዳንሆን ነው። አባቶቻችንን እንድናውቃቸው ይርዳን!
ከዚያ በኋላ ሊቃውንቱ አርዮስን በመጽሐፍ ቅዱስ ተከራክረው አውግዘው፣ «ሐዋርያት እንዲህ አላስተማሩም» ብለው፣ የክርስቶስ አምላክነት ከአብ ጋር አንድ ነው በሚል ታወጀ።
ይህ ማለት ግን ሙስሊም ወንድሞቻችን እንደሚሉት፣ ክርስቶስን ፈጣሪ ሳይሆን በኒቂያ ፈጣሪ አደረጉት ማለት አይደለም። ይልቁንም ራሱ ባለቤቱ፣ ቅዱሳን ሐዋርያት እና ሐዋርያውያን አበው ያስተማሩት ከአርዮስ ክህደት ተለይቶ ጸና፤ አባቶቻችንም አጸኑት ማለት ነው።
የንጹሐን አባቶቻችን በረከት ይደርብን! ✝️
ይህ ጉባኤ ኒቂያ በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ቤተ ክርስቲያን ከምትቀበላቸው ሦስቱ ዓለም አቀፍ ጉባኤያት አንዱና የመጀመሪያው ነው።
እናም «እመ ብዙሃን ማርያም» የሚለው የሊቃውንቱን ብዛት ያመለክታል።
ሁለተኛ፦ በጸጋ የሁላችን እናት ስለሆነች «እመ ብዙሃን» የሚል ትርጉም ተሰጥቷታል።
«ሰው እናታችን ጽዮን» ይላል። መዝ. 86፥3።
2ኛ፦ የመስቀል በዓል ✝️
ሁለተኛው የመስቀል በዓል ነው። «መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አኑር» በሚል መርህ፣ እንደ ትውፊታችን ንጉሣችን አጼ ዳዊት መስቀሉን ከእስክንድርያ አስመጥተው፣ በመንገድ ቢያርፉም፣ ልጃቸው በሀገራችን የነገሠው ሁለተኛው ቆስጠንጢኖስ፣ ማለትም አጼ ዘርዓ ያዕቆብ፣ መስቀሉን ወደ ግሸን ያገቡበት ነው።
ዛሬ ብዙ ሰው ወደዚያ የሚጎርፈው ምክንያትም ይህ ነው። መስቀሉም እንደገባ ሀገሪቱ የነበረባትን ቸነፈርና ረሃብ ያራቀበት ነው።
እኛም የቀድሞ በረከት እንዲደርሰን፣ እናታችንን፦
«በልጅሽ መስቀል አጥርነት ሀገራችንን፣ ሕይወታችንን፣ ሃይማኖታችንንና ኑሯችንን ጠብቂልን» እያልን እንለምናት። 🙏
🌻 መልካም በዓል! 🌻
++++++++++++
✍️መምህር ታምራት ሀብተማርያም
+ጸልዩ ለነ ከመ ይሩጽ ቃለ እግዚአብሔር+
©️ጉባኤ ደብረ ምጥማቅ
፳፩/፩/፪፻፲፱ - ዓ.ም🌻 መስከረም 21 — እመ ብዙሃን 🌻▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬ 📖🕯️ ክርስቲያኖችን ሰብስባ የያዘች ሰፊ መጋረጃ ሐዋ 10፥11 ➜

፳፩/፩/፪፻፲፱ - ዓ.ም📚ኦሪት ዘፍጥረት 📚
✍️ #በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
...ኦሪት ዘፍጥረት የኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ዋና ትምህርቶች ማለትም የነገረ ድኅነት፣ የነገረ ሰብእ፣ የነገረ ሥነ-ፍጥረት፣ ... መሠረት ነው፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት ብዙ መተርጉማን ትኩረት ሰጥተው በስፋትና በጥልቀት ካብራሯቸውና ከተረጎሟቸው ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡
#እኔ_ያደረግሁት ከእነዚህ የተለያዩ አባቶች፣ ሊቃውንት እና መተርጉማን ሐሳቦች መካከል የተወሰኑትን አሰባስቦ ማቅረብ ነው፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን መርሐ ግብር በተከታታይ ከቀረበው የኦሪት ዘፍጥረት ማብራሪያ ትምህርት የመጀመሪያዎቹ ዐሥር ምዕራፎች ትምህርት (ከምዕራፍ 1 -10) በዚህ መጽሐፍ ቀርቧል፡፡
በመጻሕፍት ትርጓሜ ውስጥ ልብ ሊባሉ የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ። ከእነዚህ አንዱ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ አስተምህሮ (ዶክትሪን) እና በመተርጉማን ግላዊ አስተያየቶች መካከል ያለውን ልዩነት በሚገባ ለይቶ ማወቅ ነው፡፡
..... በዚህ #መጽሐፍ የቀረቡትን የመተርጉማን ትርጓሜዎችና ማብራሪያዎች በአግባቡ ተረድተን #ለሕይወት እንድንጠቀምበት #የቃሉ ባለቤት #እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን!
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
#ኦሪት ዘፍጥረትን ብትን አድርጎ የሚያብራራ ብሎም ገቢውን #ማኅበረ_ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት የተበረከተ ነው።
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
📚ዜና አበው
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ አለ፦ ወንድሜ ሆይ! ከማር ይልቅ የሚጣፍጥ አርምሞን ገንዘብ አድርግ፤ ከኀዘንና ከትካዜ ጋር ከሚሆን ከሚጣፈጥ መብል ይልቅ ከአርምሞና ከዕረፍት ጋር እንጀራ በጨው ይበልጣልና። ምዕ ፩፥፫ ከአበው አንዱም እንዲህ አለ፦ "የድንጋይ መወርወር እስከ ሰማይ አይደርስም፤የግብዝ ሰው ጸሎትም ወደ እግዚአብሔር አይወጣም።" ምዕ ፫፥፳፫
[ከውስጥ ገጽ]
በሚያስገርም የሕይወት ተሞክሮ የታጀቡ የሚያንጹ ሕይወታዊ ምክሮች የያዘ መጽሐፍ ነው!📚ፍኖተ መጻሕፍት [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 ◉Telegram t.me/FinoteBooks1623
📚ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
«ከቅዱስ ያሬድ ቀጥሎ ታላቅ ቦታ የያዘ ኢትዮጵያዊ ሊቅ፡፡ ዐፄ ዳዊት ደግሞ “ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ”ብለውታል፡፡»📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 Join us ◉Telegram t.me/FinoteBooks1623 ◉Facebook facebook.com/FinoteBooks1623 ◉Tiiktok tiktok.com/@finotebooks1623
📚ቃልኪዳን በነገረ ድኅነት
✍️በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
...ቆየት ካሉ ነገር ግን እንደ መጽሐፉ ብስለት ብዙዎች እጅ ካልገቡ፣ በጥልቅ ትንታኔ ከተዘጋጁ መጻሕፍት አንዱ የዲ/ን ያረጋል አበጋዝ “ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት” በሚል ርእስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ ያነበቡ አንባቢያን ትልቅ መንፈሳዊ መረዳትን ስለሚጠይቀው ስለ ቃል ኪዳንና ነገረ ድኀነት በቂ ግንዛቤ አግኝተውበት እምነታቸውን በማጽናት ከክርስቶስና ከቅዱሳን ጋር ተጣብቀው በምድር ሰማያውያንን መላእክትን መስለው ተዋሕዶዊ አኗኗርን ገንዘብ አድርገው ተመላልሰውበታል፡፡
ይህ መጽሐፍ ቅዱሳን ከአምላካቸው ጋር ያደረጉትን ቃልኪዳንና በተሰጣቸው ቃል ኪዳን እኛ እንዴት መጠቀም እንዳለብን የሚተነትን ብቻ ሳይሆን፣ ነገረ ድኅነትን ተተርሰው ለሚነሡ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ፣ ተግባራዊ ምልልሳችን በክርስትና ሕይወታችን ውስጥ ያለውን ፋይዳ፣ ስለንስሐና ሒደቶቹም በቂ ግንዛቤ እንዲኖረን ያበቃናል፡፡
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
..« - በእውነት አምላክን መበደል ፥ ከቅጣት ይልቅ እጅግ ያማል። በአኹኑ ዘመን ግን እኛ ያለን አመለካከት ፥ በጣም መጥፎ ከመኾኑ የተነሣ ፥ ገሃነምን መፍራት ባይኖር ኖሮ መልካም ለማድረግ እንኳን ባልመረጥን ነበር። ለዚኽ አመለካከታችን እንኳ የገሃነም ፍርድ ይገባናል ፤ ምክንያቱም ከክርስቶስ ይልቅ ገሃነመ-እሳትን እንፈራለንና። ቅዱስ ጳውሎስ ግን እንዲኽ አልነበረም። እኛ ግን አመለካከታችን ከዚኽ የተለየ በመኾኑ ለገሃነም ፍርድ የተገባን ኾነናል። ክርስቶስን እንደሚገባ ብንወደው ኖሮ ፥ የምንወደውን አካል መበደላችን ፥ ከገሃነም በላይ የሚያመን መኾኑን እንረዳ ነበር። ነገር ግን እርሱን መውደድ በእኛ ውስጥ ስለሌለ የቅጣቱን ታላቅነት ማስተዋል አልቻልንም። እኔም ከኹሉ በላይ አጥብቄ የማዝነውና የምቆጨው በዚኽ ምክንያት ነው።
ለመኾኑ እግዚአብሔር እርሱን እንወደው ዘንድ ምን ያላደረገልን ነገር አለ!? ምንስ ያልሰጠን ተስፋ አለ!? ምንስ ያስቀረብን ነገር አለ!? እርሱ ምንም ሳይበድለን ቊጥር በሌለውና ሊነገር በማይችል በረከቱ እያጽናናን ፥ እኛ ግን በክፉ ሥራችን ስሙን አሰደብነው። በብዙ መንገድ እኛን ወደ ራሱ ሲጠራንና ሲስበን ፥ እኛ ግን ከእርሱ ዘወር አልን ፤ እንዲኽ በማድረጋችን እንኳን ፈጥኖ አልተቆጣብንም ፤ ይልቁኑ እኛ ስንርቀው እርሱ ፈጥኖ እጆቻችንን ይዞ ከጥፋት ያወጣናል ፤ እኛ ግን እጆቹን ከእኛ ላይ በማስለቀቅ ለዲያብሎስ ራሳችንን አሳልፈን ሰጠን።
ኾኖም እንዲኽም አድርገነው እንኳ ከእኛ አልራቀም ፤ ይልቁንም ወደ እርሱ እንድንመለስ ቊጥር የሌላቸው መልእክተኞቹን ነቢያትን ፣ መላእክትን እና ቅዱሳን አባቶችን ላከልን። -»..
════════
[ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፥ የሮሜ መልእክት ማብራሪያ ትምህርቶች መካከል ፥ የተወሰደ]
@MARY_THE_MOTHER_OF_GOD
📚ፍኖተ መጻሕፍት
....« - በእውነት አምላክን መበደል ፥ ከቅጣት ይልቅ እጅግ ያማል። በአኹኑ ዘመን ግን እኛ ያለን አመለካከት ፥ በጣም መጥፎ ከመኾኑ የተነሣ ፥ ገሃነምን መፍራት ባይኖር ኖሮ መልካም ለማድረግ እንኳን ባልመረጥን ነበር። ለዚኽ አመለካከታችን እንኳ የገሃነም ፍርድ ይገባናል ፤ ምክንያቱም ከክርስቶስ ይልቅ ገሃነመ-እሳትን እንፈራለንና። ቅዱስ ጳውሎስ ግን እንዲኽ አልነበረም። እኛ ግን አመለካከታችን ከዚኽ የተለየ በመኾኑ ለገሃነም ፍርድ የተገባን ኾነናል። ክርስቶስን እንደሚገባ ብንወደው ኖሮ ፥ የምንወደውን አካል መበደላችን ፥ ከገሃነም በላይ የሚያመን መኾኑን እንረዳ ነበር። ነገር ግን እርሱን መውደድ በእኛ ውስጥ ስለሌለ የቅጣቱን ታላቅነት ማስተዋል አልቻልንም። እኔም ከኹሉ በላይ አጥብቄ የማዝነውና የምቆጨው በዚኽ ምክንያት ነው።
ለመኾኑ እግዚአብሔር እርሱን እንወደው ዘንድ ምን ያላደረገልን ነገር አለ!? ምንስ ያልሰጠን ተስፋ አለ!? ምንስ ያስቀረብን ነገር አለ!? እርሱ ምንም ሳይበድለን ቊጥር በሌለውና ሊነገር በማይችል በረከቱ እያጽናናን ፥ እኛ ግን በክፉ ሥራችን ስሙን አሰደብነው። በብዙ መንገድ እኛን ወደ ራሱ ሲጠራንና ሲስበን ፥ እኛ ግን ከእርሱ ዘወር አልን ፤ እንዲኽ በማድረጋችን እንኳን ፈጥኖ አልተቆጣብንም ፤ ይልቁኑ እኛ ስንርቀው እርሱ ፈጥኖ እጆቻችንን ይዞ ከጥፋት ያወጣናል ፤ እኛ ግን እጆቹን ከእኛ ላይ በማስለቀቅ ለዲያብሎስ ራሳችንን አሳልፈን ሰጠን።
ኾኖም እንዲኽም አድርገነው እንኳ ከእኛ አልራቀም ፤ ይልቁንም ወደ እርሱ እንድንመለስ ቊጥር የሌላቸው መልእክተኞቹን ነቢያትን ፣ መላእክትን እና ቅዱሳን አባቶችን ላከልን። -»....
═══════════════
[ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፥ የሮሜ መልእክት ማብራሪያው ውስጥ ካሉ ትምህርቶች መካከል ፥ ከአምስተኛው ድርሳን ላይ የተወሰደ]
📚#ፍቅር
--
ወንድሞቼ ሆይ፡- ሃይማኖት ቀላል ቅድስና ወይም እርግማን አይደለም! ወይም ደግሞ ቀላል ትእዛዝ ወይም ክለከላ አሊያም ተራ ሕግ ወይም ጸጋ አይደለም በሚቻለው ሁሉ ለእግዚአብሔርና ለሰዎች የሚሆን ፍቅር እንጂ፡፡ ከዚህ ፍቅር የሚመነጨውም ሁሉ መልካም ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔርንና ሰዎችን የማትወዱ ከሆናችሁ የተፈለገውን ያህል ብትጸልዩ ወይም ብትጾሙ ወይም ብታነቡ ወይም በተመስጦ ብትቆዩ ወይም አሥራት ብታወጡ ወይም ብታገለግሉ ወይም ብትሰብኩ የሃይማኖት ሰዎች ልትሆኑ አትችሉም፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው ፍቅርን እንጂ ቀላል ተግባራትን አይደለም፡፡ ከእናንተ የሚፈልገው እርሱ እናንተን እንደ ወደዳችሁ እናንተም እርሱን እንድትወዱት ነው።
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
❝ሰላም ለሥዕልኪ ሐፈ ማኅየዌ። በጼዴንያ ወግብፅ ዘአውኀዘት በኢሕሳዌ። ለመጸብሐዊ ማቴዎስ ማርያም እንተ ረሰይኪዮ ወንጌላዌ። ይኩነነ ወትረ ጸሎትኪ እምዘመነ ኵሉ ምንሳዌ፡፡ ዓቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ሀላዌ ።
--
ትርጉም ፦ በጼዴንያና በግብፅ ያለ ሐሰት ፈዋሽ ወዝን ላፈሰሰ ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል:: ቀራጭ ማቴዎስን ወንጌላዊ ያደረግሽው #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ ጸሎትሽ ከጥፋት ዘመን ሁሉ ዘወትር የመዓልትና የሌሊት ቋሚ ጠባቂ ይሁነን::❞
ለበለጠ ማብራሪያ እና ታሪክ መጽሐፉን ተመልከቱ።መልካም በዓል! 📚ፍኖተ መጻሕፍት

📚#ፍኖት_መንፈሳዊት
[The way of Pilgrim ]
በእግዚአብሔር ቸርነት ክርስቲያን ነኝ፤ በምግባሬ ግን ታላቅ ኀጢአተኛ፤ አጠራሬም ቤት አልባና የትሕትናን ምንጭ በመፈለግ ላይ ያለ ከርታታ፤ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወር የሚል ነው። ንብረቶቼ በጀርባዬ ያዘልሁት ደረቅ ዳቦ ያለው የከረጢት ቦርሳና በእቅፌ የያዝሁት መጽሐፍ ቅዱስ ናቸው፤ ይኸው ነው ያለኝ።ከበዓለ ኀምሳ በኋላ በኻያ አራተኛው እሑድ ወደ ቤተክርስቲያን በቅዳሴ ላይ ለመሳተፍ ኼድሁና ልክ [የቅዱስ ጳውሎስ] መልእክት እየተነበበ ሳለ ገባሁ። ንባቡ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ከላከው የመጀመሪያ መልእክት የተወሰደ ሲሆን፥ ይህም «ሳታቋርጡ ጸልዩ» ይላል።እነዚህም ቃላት በእኔ ላይ ጥልቅ ስሜት ፈጠሩብኝና እንዲህ ስል ዐሰብሁ፤ “አንድ ሰው ለሕይወት የሚያስፈልጉትን ነገሮች በመፈለግ ብዙውን ትኩረቱን በሚይዝበት በዚህ ዓለም ሳያቋርጥ እንዴት መጸለይ ይቻለዋል?” መጽሐፍ ቅዱሴን ከፍቼ ...
[ከመጽሐፉ የተወሰደ]
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
📚 #ገድለ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ
☞ይህ ገድለ ቅዱስ መርቆሬዎስ መጽሐፍ ከዋናው ጥንታዊ የብራና መጽሐፈ ገድል የተቀዳ ነው፡፡ የተዘጋጀበትም ዓላማ፣ አንባብያን በአጭር ጊዜ አንብበው እንዲረዱትና፣ ዘወትር እንዲጸልዩበት ታስቦ ሲኾን፣ በገድሉ ላይ ሌላ ፈጠራ የተጨመረ ታሪክ የለም፡፡
አሳታሚ፡- ደብረ ጽባሕ ጸዶየ ቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተክርስቲያን
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
📚#የነገረ_መለኮት_መግቢያ
.....ጌታችን ኅብስቱን ቆርሶ፥ ወይኑን ቀድቶ በሰጠባት በዚያች ዕለት ከተናገራቸው ቃላት “ይህ ሥጋዬ ነው፣ ይህ ደሜ ነው” የሚለውንና ከራሱ ጋር አያይዞ የምሥጢሩን አማናዊነት የሚገልጸውን ብቻ አይደለም ለአስተውሎት የምንወስደው፣ “ስለ ብዙዎች” የሚለውን ጭምር እንጂ (ማቴ 26፥26)። በዚህ አንድ ምሥጢር ብዙዎች አንድ መኾናቸው ከድኅነት ጋር የምሥጢረ ቁርባን ፋይዳ ታላቅ መኾኑን የሚያስረዳ ነው።ከእነዚህ ምሥጢራት ያልተለየ ማኅበራዊ ሕይወት (koinonia) ለጨለማው ዓለም ብርሃን ነው። ለመለያየት፥ ጸብና ክርክር፥ ሰላምና ፍቅር ለማጣትም መፍትሔ ነው። ምክንያቱም በዚህ መንገድ ውስጥ ሰው...
[ከመካከል]
የተወሰኑ ቅጂዎች ይኖሩናል..📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 Join us ◉Telegram t.me/FinoteBooks1623 ◉Facebook facebook.com/FinoteBooks1623 ◉Tiiktok tiktok.com/@finotebooks1623
📚#ወንጌለ_ዮሐንስ_የሰባቱ_ዕለታት_ጸሎት_እና_መልክአ_ዮሐንስ_በአማርኛ
...በቅዱሳን በእነ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት፣ #አቡነ_ሀብተ_ማርያም፣ #አቡነ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ እንዲኹም በሌሎች ቅዱሳን ገድላት ላይ ወንጌለ ዮሐንስን በየዕለቱ ሲጸልዩ እንደነበርና የጸሎተ ወንጌልን ክብርም በሰፊው ተጽፏል።
በንጽሕና ጸልየን እንድንጠቀም የአምላክ ቅዱስ ፈቃዱ ይኹን።📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 Join us ◉Telegram t.me/FinoteBooks1623 ◉Facebook facebook.com/FinoteBooks1623
📚#ሥርዐተ_ቤተክርስቲያን
✍️በሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ
☞የኑዛዜ ጸሎት
በተአምኖ ኃጣውእ የሚቀርብ ጸሎት አለ፡፡ አባቶቻችን በእግዚአብሔር ቤት ይቅርታን ለራሳቸውና ለሕዝባቸውም ባቀረቡ ጊዜ ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ ይጸልዩ ነበር፡፡ ዳንኤል በባቢሎን ማቅ ለብሶ አመድ ነስንሶ ስለ ሀገሩ ኢየሩሳሌም ስለ ወገኖቹ እስራኤላውያን የቀረበውን ጸሎት ወደ አምላኬም ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ ተናዝዤም እንዲህ አልሁ..." ዳን ፱÷፬ ብሎ ይጀምረዋል፡፡ በዚህ ጸሎቱ ባቀረበው መናዘዝ የእስራኤልን ኃጢአት ዘርዝሮ በእግዚአብሔር ፊት አቅርቦታል። ኃጢአትን ተናዝዞ የሚያቀርቡት ጸሎት ፈጥኖ ይሰማልና እኔም ገና ስናገርና ስጸልይ በኃጢአቴና በሕዝቤም በእስራኤል ኃጢአት ስናዘዝ በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራዕይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ ዳን ፱÷፳ በማለት የራሱንና የወገኖቹን የእስራኤልን ኃጢአት በዘረዘረ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለው ይናገራል፡፡ቅድመ ጼዋዌ የነበሩ ነቢያት የጸለዩት የኑዛዜ ጸሎት በዘመነ ጺዋዌ ለነበሩ ሰዎች አርዕስት ተሰጥቶት ይተረጎማል፡፡ በዳዊት መዝሙራት ውስጥ...
[ከውስጥ ገጽ]
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
📚#የሐዋርያው_የቅዱስ_ጳውሎስ_አሥራ_አራቱ_መልእክታት
ትርጓሜው በአንድምታ
------
የሮሜ መልእክት ምዕራፍ፪ ፥፫-፬
፫/፡በእንተ፡ወልዱ፡ዘተወልደ፤አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ስለ ተወለደ ስለ ልጁ ያናገረ።
ወመጽአ #እምዘርዐ_ዳዊት_በሥጋ_ሰብእ ፤#ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ስለሆነ ስለ ልጁ ያናገረ ሥጋ እንስሳ አለና፤ ከዚህ ሲለይ ሥጋ ሰብእ አለ፤ ዘርአ ዳዊት ያለው አይበቃ ውም ቢሉ ነፍስ እንደነሣ ለማጠ የቅ ያውስ ቢሆን ዘርአ አብርሃም አልዐል እንዲል ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዘርአ ዳዊት ያለው አይበቃም ቢሉ በከዊን ሲል ነው፡፡
፬/ ወአርአየ ከመ ወልደ እግዚአብ ሔር ውእቱ በኃይሉ ወበመንፈሱ ቅዱስ፤ኃይሉ ሕይወቱ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ #ከእመቤታችን በመወለዱ ወልደ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ስለአሳየ ስለልጁ ልደት ቀዳማዊ ተአወቀ በደኃራዊ ልደት እንዳለ ሱኑትዩስ፤ አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም እርሷ ያለ አባት ብትወልደው ቅድመ ዓለም ከአብ ያለእናት መወለዱን ያስረዳልና፡፡ አንድም በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና በመወለዱ ወልደ እግዚአብሔር እንደሆነ ስለአሳየ ..... [ከውስጥ ገጽ] 📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 Join us ◉Telegram t.me/FinoteBooks1623 ◉Facebook facebook.com/FinoteBooks1623 ◉Tiiktok tiktok.com/@finotebooks1623
...በንጉሡ ልደት በዓል ቀንም ንጉሡ ሰከረ። ከደንባሪ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንዲሉ በስካሩ ላይ የሄሮድያዳ ልጅ ዘፈን ታከለበት። የመንግሥቴን እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ብሎ ማለ፡፡ ይህቺም እናቷን ብታማክራት መላውን ቤተ መንግሥት ማን ነስቶሽ ይልቁንስ #የዮሐንስን_አንገት ቆርጠህ ስጠኝ በይው አለቻት፡፡ እንዳለቻትም አደረገች። ንጉሡም አዘነ። ያዘነው ለዮሐንስ አይደለም። ሁለት ነገር አስጨነቀው። መጀመሪያ ዮሐንስን ሕዝቡ ይወደዋልና። ሁለተኛ እንዳይተወው ደግሞ በባለሥልጣናቱ ፊት ቃል ገብቷልና ለክብሩ ተጨነቀ። አንገቱን እንዲቆርጡት አዘዘ፡፡ በማይረባው ክብሩ የእግዚአብሔርን ክብር ለወጠ። ጌታም አስቀድሞ “ሕዝቤ ክብሩን ለማይረባ ነገር ለወጠ ሲል የተናገረው ተፈጸመበት (ኤር፪፥፲፩)።
..ልጅቱም በወጭት አድርጋ የዮሐንስን አንገት ይዛ ወደ እናቷ ሔደች። ምሥጢር ያቀኑ አባቶቻችን ደግሞ እርስዋ የተጸየፍሁ መስሏት በወጭት አድረጋ አንገቱን ይዛ ሔደች እንጅ ምሥጢሩስ በረከሰው እጇ ክቡሩን ዮሐንስን እንዳትዳስሰው እግዚአብሔር ያደረገው ነው ይላሉ፡፡
--
ቤቱም በሁከት ተሞላ፡፡ ወስዳም ለእናቷ ሰጠቻት፡፡ ይቺ አንገትም ከወታደሮቹ እጅ ወደ ዘማዊቷ ሄሮድያዳ በወጭት ስትሰጥ ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም፥ እርስዋ እኅትህ ናትና እያለች ትጮህ ነበር።
[ከውስጥ ገጽ]
#ሰናይ_በዓል
📚ፍኖተ መጻሕፍት