cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Thoughts

ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው? እናንተስ ጎራ አትሉም? Since: Dec-10-2022 discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
2 714
Suscriptores
+324 horas
+397 días
+15830 días
Distribuciones de tiempo de publicación

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Análisis de publicación
MensajesVistas
Acciones
Ver dinámicas
01
“ለምን ትመጫለሽ? ወና መሆን ለምዷል ባይተዋር ነው ሆዴ ትራስ አቅፎ ማደር ለምዶበታል ክንዴ። ገላዬ ቀዝቅዟል ልቤ ተሰቅዟል እንስት እንዴት ልመን? ዜሮ ነኝ ስተመን ብትመጭም ከንቱ ነው መመለስሽ ምንም ስታወሪ አልስቅም በእንባሽ አልቆዝምም በድን ነኝ አልድንም ። የለሁም በድሮ ሌላ ነኝ ዘንድሮ ግዴ አይደለም ነገ ወጋገን ማለዳው ለዛሬ ሶስት ዓመት ዛሬን ነው ‘ምቀዳው። አትገርመኝም ጀንበር ብራና ክረምቱ ቢዛወር ዓመቱ ጨፍሬ አልደክርም አልመታም አታሞ ዓመት አንድ ቀን ነው ለከሸፈ ታሞ ። ለምን ትመጫለሽ ? መምጣትሽ እንደ ቧልት መመለስሽ ምንም ...” ይህንን እያልኩኝ ብናገር ብገጥምም ስትመጪ ስዳበስ በጣት በመዳፍሽ ያልኩትን ዘንግቼ አዲስ ሰው ሆንኩልሽ። አትሄጂም አይደለ ?🙄 (ሚካኤል አ)
2124Loading...
02
እውነት ፈጣሪ ግን ህይወትን ማመጣጠን ሲያውቅበት በመስጠት ብቻ ሳይሆን በመንሳትም ጭምር፣ በፍቅር ብቻ ሳይሆን ምቶዱትን ሰው በማራቅም፣ በማስደሰት ብቻ ሳይሆን በሀዘንም በማስተማር ጭምር፣ ባሳለፍነው ህይወት ሁሉን ነገር አመዛዝኖ በመስጠት ማቆየቱ፣ በደስታ መክነፍን ብቻ ሳይሆን በሀዘንም ብዙ ትምህርት ማስጨበጡ፣ መኖርን የማጣጣም ስርአቱና አግባቡ ያስገርማል፣ እውነትም በህይወት መቆየት ደግ ነው ብዙ ያስተምራል!!
2413Loading...
03
Media files
5930Loading...
04
Media files
10Loading...
05
"ካልጠፋ ቀን ዛሬ መንገድ መዘጋጋት ነበረበት" ትላለች እየደጋገመች መዘጋጋቱ ሳያንሰ አሁን ደግሞ መብራት ይዟት መሀል መንገድ ላይ ቆማለች። መንገዱ መፈናፈኛ ስለሌለው ዘና ብላ መቀመጥ ስትችል ወደ ፊት ተጥግታ መሪውን አጥብቃ ይዛ ነው የተቀመጠችው። "ቆየሽ በሰላም ነው?" የሚለውን መልዕክት ለሶስተኛ ጊዜ ሲልክላት ጭንቀቷ በእጥፍ ጨመረ ።የትራፊክ መብራቱን ስታየው አረንጓዴ ሆኗል ወዲያው ከዚህ በፊት አድርጋ እንደማታውቀው እየተሽሎከሎከች መንዳት ጀመረች። ለይስሙላ ነዳች ይባል እንጂ ሀሳቧ ያለው ሰለሞን የላከላት መልዕክት ጋር ነው። "በተቻለሽ ፍጥነት ነይ ጥሩ ስሜት ላይ አይደለሁም" ይላል 'ደሞ ምን ሆኖ ይሆን አምላኬ አደራህን እስክደርስ ምንም መጥፎ ነገር እንዳያደርግ' እያለች በደመነፍስ ስታሽከረክር ያምባረቀባት ጡሩንባ አባነናት ለምንድነው በእሷ አቅጣጫ ከፊትለፊቷ መኪና እየመጣ ያለው? ለካ በባለሁለት አቅጣጫ መንገዱን መመለሻውን አስፋልት ለመሄጃ ተጠቅማበት ነው መኪኖች ከፊት ለፊት እየመጡባት ያሉት ብቻ በደመነብስ አዙራ ነው ወደ ትክክለኛው መስመር የተመለሰችው 'ልሞት እችል ነበረ ለራሴም ለእሱም አልሆንም ነበ'ረ እያለች ከድንጋጤዋ ለመረጋጋት እንኳን ሳትሞክር አንዴ ፀሎት አንዴ ምሬት ለራሷ እያልጎመጎመች ስትሄድ አንዲት አሮጊት ቀስ እያሉ ሲሻገሩ እሷ አንደ እብድ ስትነዳ ለጥቂት እስትንፋሳቸውን ነጥቃቸው ነበረ ምስጋና ለመኪናዋ ምርጥ ፍሬን እንቅ አድርጎ ይዞላት ከሞት ያዳናቸው እሷንም ከነፍሰ ገዳይነት ያዳናት ወይ ደግሞ ጠዋት 'ሰላም አውለኝ' ብለው የፀለዩት ፀሎት ነው ያዳናቸው ብቻ ግን እሳቸውም ካለፉ በኋላ እግሯን ከፍሬኑ ላይ አላነሳችውም የቅድሙ ድንጋጤ ሳይለቃት ሌላ ቅድም ለራሴ ሞቼ ነበረ አሁን ደግሞ ሰው ያውም አሮጊት ሴት ገድዬ ነበረ ብላ እጇ መንቀጥቀጥ ጀመረ። "ቀረሽ እንዴ?" የሚል መልዕክት ላከላት ሰለሞን ለካ ሰለሞን እየጠበቃት ነው አንዴ በሰላም እንድትደረስ አንዴ በሰላም እንዲቆያት ፀሎቷን እያደረሰች ከአስራ ምናምን ደቂቃ በኋላ የቀጠራት ቦታ ደረሰች ስትገባ አስተናጋጆቹ በፈገግታ ተቀበሏት ለራሷ በፍርሀት እና በድንጋጤ መሀል ሆና ተመሰቃቅላለች ጭራሽ ፈገግ ይላሉ?! ወደውስጥ ስትገባ ሰለሞን እየሳቀ መጥቶ አቀፋት ግራ ገባት "ሶል ደህና ነህ ግን?? ምንድነው ብለህ የጠራኸኝ እና ነው የምትስቀው?!" አልኩት ጭራሽ ግራ ገብቶኝ እስኪ ወደጀርባሽ ዙሪ አለኝ የማውቀው ድምፅ...አሹ ሊሆን አይችልም ስዞር surprise ብለው ጮሁ ወዳጆቼ የምላቸው በሙሉ ተሰብስበው ሆቴሉን ዲኮር አሰርተውበታል... አሹ ከፊት ቆሟል "የኔ ምርጥ እና ብቸኛ እህት" ብሎ ተንደርድሬ እንደማቅፈው አይነት እጆቹን ዘረጋ ብዥዥ አለብኝ ለአስራ ምናምን አመት ያላየሁት ወንድሜ እዚህ ምን ይሰራል? ምንም ሳልላቸው ሄጄ አጠገቤ ያገኘሁት ወንበር ላይ ተቀመጠች ግራ ተጋቡ የልብ ጓደኛዋ ፌቨን "ነግሬያችሁ ነበረ እሷ እንደዚህ አይነት ነገር አይመቻትም ሰው አትሰሙ" እያለች ስትበሰጫጭ ይሰማታል ሶል መጥቶ ከፊቷ መጥቶ በርከክ አለና "ምነው እናቴ" አላት ስታኮርፍ እንደሚለማመጣት አይን አይኗን እያየ ወንድሟም ወገቡን ይዞ ቆሞ ያያታል የደገሰውን ስላበላሸችበት "ለእናንተ የማይረባ ድራማ አንተ አንድ ነገር ትሆናለህ ብዬ ስንቀዠቀዥ አንዴ የመኪና እራት ልሆነ አንዴ ደሞ የሰው ህይወት በእጄ ሊጠፋ ነበረ ምክንያቱም እናንተ surprise ማድረግ እውቀት መስሏችሁ" አለችው አንዴ ሶልን አንዴ ወንድሟን እያየቻቸው ከተቀመጠችበት ተነስታ ሁለቱንም አፈራርቃ እያየች "ከsurprise በላይ ምን እንደሚበልጥ ታውቃላችሁ እንኳን እንደሚፈጠር እርግጠኛ የተሆነበት ነገር ይቅርና ተስፋ የሌለው ነገር እንኳን ተስፋ በማድረግ እንደሰት የለ? ሌላውን ተዉት ህፃን ሆነን ሎተሪ ተቆርጦ አስኪወጣ ድረስ ያለውን ደስታ ትዝ አይላችሁም ምን ምን እንደሚደረግበት ማሰብ ብቻ ለሳምንታት ያስደስተን ነበረ" ወደ ወንድሟ በደንብ ዞረችና "አባ ምን እንሚል ትዝ አይልህም 'የበዓል ዋዜማው ከእለቱ ይበልጣል' ሲል ትዝ አይልህም?! ሰርግስ ቢሆን ከቀኑ በላይ እስኪደርስ ቀን መቁጠሩ እያሰቡ ብቻ መደሰቱ አይበልጥም? ግን ለምን ይሄ ከፈረንጅ ቀጥታ ከምትገለብጡት ከንቱ ልማድ አንዱ ነው surprise የምትሉት ጉድ ሰዎች ጀሚያስደስታቸውን ነገር ፈልጎ አምጥቶ ድንገት ማስደንገጥ ከዛ ከደስታቸው እና ከድንጋጤያቸው ጋር ሲወናበዱ እያዩ ቪድዮ መቅረፅ ከዛ surprise ተደርጋ ስትደነግጥ ብሎ tik tok መስራት በቃ ይኸው ነው አይደለ ከብዙ አመት በኋላ ስንገናኝ እንደዚህ ባይሆን ደስ ይለኝ ነበረ" ብላ በሩን አጋጭታ ጥላቸው ሄደች ሁሉም ደንግጠው ቀሩ።
6558Loading...
06
Media files
4 0002Loading...
07
Check out Daniel Aweke(ዮዳA): https://t.me/danielaweke
6220Loading...
08
"ያለ እነርሱ እንዴት እኖራለሁ ያልካቸው ሰዎች መኖራቸው ሰላም እስኪነሳህ ድረስ ካሳነሱህ አስብበት....ከስሜታቸው በታች ከሆንክም አስብበት...ለራስህ ያለህን ዋጋ እያሳነሱት ከሆነ...ውስጥህን እያቀጨጩት ከሆነ እመነኝ የእነሱ አለመኖር ሳይሆን መኖራቸው ብቻ አያኖርህም...".....ከልቧ ነው....ታስታውቃለች። "ዛሬ ደግሞ ጫን ያለው ነው....ማንያዘዋል ነው ወይስ ዳዊት ድሪምስ....."....በእኔ ቤት መቀለዴ ነው...እርሷ ቀልዴ እንጨት እንጨት ያላት ይመስል ገልመጥ አርጋኝ ማውራቷን ቀጠለች። "ይኧውልህ ሰው የማይጎትትህ አይነት ሰው ከሆንክ ካንተ በላይ የታደለ የለም...እስቲ አስበው አንተ እናትህ ልጅነቷን አጥታብህ ላንተ ብላ አፈር መስላ ሰው ሆንክልኝ ብላ ተደስታ ገና አረፍ ከማለትዋ ፍቅረኛዬ ጥላኝ ሄደች ብለህ እናትህ የገነባችውን ማንነት ስትንድ...የእናትህ ላብ በዜሮ ሲባዛ....." "ምን አይነት ምሳሌ ነው የምትሰጪው....አሁን ምሳሌ ጠፍቶ ነው...?" "ምሳሌ መሆን በራሱ ያስጠላል አይደል...እሺ ተውኩህ...ማንም አይኑርህ...ማንም አይልፋልህ...እንዲሁ ብቻ ነገ የተሻለ ይሆናል ብለህ ብቻህን ታግለህ ያለህበት ደረስክ...አንተ እና ፈጣሪህ የገነባችሁትን ማንነት በግንባታው ሂደት ያልተሳተፈ ሰው ሲንደው በጄ የምትትል አይነት ሰው ከሆንክ ወደፈጣሪህ አልቅስ..."..."ሌላው ቀርቶ የገነባህ ሰው እንኳን እንዲያፈርስህ መፍቀድ የለብህም.... አንዳንዴ እምቢ ማለትን የመሰለ ነገር የለም" ጨረሰች መሰለኝ በረጅሙ ተነፈሰች። "ሰላም ራሱ አላልሺኝም እኮ ምን ጉድ ነው ዛሬ...."...ህልም የመሰለ ፈገግታዋን አሳይታኝ እቅፌ ውስጥ መሸገች... "እኔስ ስልጣን አለኝ.?"..ከእቅፌ ሳትወጣ በሹክሹክታ ጠየቅኩ። "እንዳታስበው..." "እንዴ ማለት አትወጂኝም...? " "ጥያቄህን ለራስህ ጠይቀው...." "ስትይ...." "ከወደድከኝ ለምን ታፈርሰኛለህ....አለመኖርህ እንዲያፈርሰኝ ለምን ትመኛለህ...ይህ ስልጣን ምን ይጠቅምሀል...ወይስ እንደ ዘመኑ ፖለቲከኞች ስሙ ስልጣን ስለሆነ ብቻ ሰው የሚገል ስልጣን ታሯሩጣለህ....የምርህን ግን ትወደኛለህ....?" ዝም ብዬ ባቅፋትስ...ምኑ ቀሽም ነኝ...? ✍Shewit https://t.me/shewitdorka
1 0918Loading...
09
A Hungarian psychologist named Laszlo Polgar theorized that anyone could become a genius because geniuses were made and not born. To prove this, he used his own daughters as experiments and trained them to become great at chess. The three Polgar sisters then became chess prodigies, and the youngest, Judit Polgar, become a grandmaster at just age 15. #History Join and share @SHOCKINGFACT
1 0973Loading...
10
“ተስፋ የመኖር ምክንያት ነዉ፣ ሰዉን እንዲኖር የሚያደርገዉ መለወጥ አለመለወጡ ሳይሆን የመለወጥ ተስፋዉ ነዉ”
7652Loading...
11
እሺ እናንተስ እንዴት ነው የተገናኛችሁት #4 ጀማው ተሰብስቦ ማምሸት የተለመደ ተግባር ሆኗል ግን የጎረምሳ ጀማ ተሻሽሎ የብዙ ጥንዶች ስብስብ ሆኗል ወሬ ሲጠፋ ሁሉም ብርጭቆውን ይዞ መቆዘም ሲጀምር እንዴት ውሀ አጣጫችንን እንዳገኘን በየተራ እናወራለን ታዲያ ድባቡ ካልጣመው ናቲ ነው ቶሎ ሀሳቡን የሚያመጣው "እስኪ ፈላስፎች የእናንተን ደግሞ እንስማ" ብሎ ወደ እኛ ዞረ። ሳያት "አንተ ንገራቸው" የሚል አስተያየት አየቺኝ አፌን አሟሽቼ ጀመርኩ እኔ ማየት የምወደው ጀምበር ስታዘቀዝቅ ማየት ነበረ ይኸው እሷ ከመጣች በኋላ ዶሮ ሳይጮህ እየተቀሰቀስኩ የፀሀይን መምጣት እጠባበቃለሁ የሆነኛውም ቀን ላይ ጠርታኝ የሰፈራችን ጉብታ ላይ ቁጭ ብለን እየጠበቅን እያለ "ስማ አንተ አለቺኝ" አይኗን ከጠየመው ሰማይ ላይ ሳትነቅል ምን የተለየ ነገር አይታ ምን የተለየ ነገር ልትነግረኝ ነው ብዬ አንዴ እሷን አንዴ ሰማዩን አፈራርቄ እያየሁ "ምን ልስማሽ?" አልኳት "ሰዎች ለምን ይመስልሀል ጀምበር ስታዘቀዝቅ ወይም ስትወጣ ብቻ ማየት የሚወዱት?" አለች አይኗን ከሰማዩ ላይ ሳትነቅል "ተፈጥሮን ስለሚያደንቁ?!" አልኳት በልበ ሙሉነት "ተፈጥሮን የሚያደንቁማ ጨረቃንም ከዋክብቱንም ዛፉም ውቅያኖሱም አይቀራቸውም እኔ የምልህ ከአጠቃላይ 24 ሰዓት ውስጥ ለምን የሁለቱ ክስተት ብቻ ትኩረት ይስባል?" አለች አሁን እንደዚህ አይነት ፍልስፍና ከጀመረች ግምቴ ራሱ ዋጋ አይኖረውም "አንቺ ለምን ይመስልሻል?" ከማለት ውጪ "አየህ አጠቃላይ 24 ሰዓቱ ቀን እና ማታ ብለን ነው የምናስበው ቀኑም ቢሆን ፀሀይ ከወጣች ጀምሮ እስክትጠልቅ ድረስ እንዳነደደችን ነው ማታውም ቢሆን እየጨለመ ሄዶ ድቅድቅ ጨለማ እንደሆነ ይነጋል። አየህ ይሄ በብዙ ክስተት የተሞላ አይደለም የጀንበር መውጣት እና መጥለቅ ግን ለውጥን ያበስራል የሆነ ልዩ ስሜት የመፍጠር አቅም አለው። ሰውም ለምን እንደሆነ በማይረዳው ምክንያት ሰዓት ባይጠብቅም እንኳን የጀምበር መውጣት ቅድሚያ በጨረሮቿ ሲበሰር ልቡን ይሞቀዋል ጀምበር ስታዘቀዝቅም ሆዱን ባር ባር ይለዋል ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?" ብላ ፈገግ አለች ስመሰጥባት ቆይቼ ፈገግ እንዳለች ሳይ አይኗን ወደአሳረፈችበት አቅጣጫ ስዞር ፀሀይዋ በቀስታ መውጣት ጀምራ ስስ ብርቱካናማ ብርሀን አልብሳናለች። "ለምንድነው" አልኳት አወራሯ ወሬዋ የምታወራበት ጉጉት ይበልጥ እየሳበኝ "ምክንያቱም ሁሉም ሰው ማየት የሚፈልገው ለውጥን ብቻ ስለሆነ ያውም ውብ የሆነውን ለውጥ ብቻ" ግንባሬን ሸበሸብ አድርጌ አይኔን አጥብቤ ስመለከታት እንዳልገባኝ ተረዳች "ይኸውልህ ፀሀይና ምድር እንደምንም ሆነው ይቆዩ ማንም ግድ የሚሰጠው የለም ምድር በእኩለ ቀን በፀሀይ ንዳድ ብትቃጠል የሚገደው የለም እኩለ ለሊትንም ቢሆን ማንም ለማድነቅ አይወጣም እያንዳንዱ ደቂቃ ለውጥ ቢሆንም ከለውጥም ቆንጆውን ለውጥ ብቻ መርጠን ነው ለማድነቅ የምንገናኘው" አለቺኝ "ይገርማል" አልኳት "በጣም" አለች ስለ ለውጥ ያወራችው ወሬ ያደነቅኩት መስሏት እኔ ግን የገረመኝ ሁሉ ነገሯ ነው አስተሳሰቧ ... የእለት እለት ቀላል የምንላቸውን ተግባራት በጥልቀት ማመሳሰል መቻሏ... ብቻ በጀንበር መውጣት ቢሆን እሷን ማግኘቴን አመሰገንኩት "ጀንበር ስታዘቀዝቅስ አንገናኝም?" አልኳት "እሺ" አለች ሌላው ከቁብ የማይቆጥረውን ተራ ተፈጥሯዊ ክስተት ቤቴን ገነባሁበት እላችኋለው" ብዬ አበቃሁ "ቺርስ ለፀሀይ" ብለን ብርጭቆ አጋጨን ✍nani
1 2065Loading...
12
Media files
7 9652Loading...
13
እንባ እንባ ይለኛል      ይተናነቀኛል እንባ የት አባቱ ደርቋል       ከረጢቱ ሳቅ ሳቅም ይለኛል   ስቆ ላይስቅ ጥርሴ     ስቃ እየነደደች መከረኛ ነብሴ             ፨ ፨ ፨ ❇️በአሉ ግርማ
1 3899Loading...
14
"ሆጵላስ!" ይሄን ያውቃሉ ? ይህ ቃል የተፈጠረበት አጋጣሚ  አንድ ፈረንጅ በሀገራችን የድንጋይ ናዳ መንገድ ይዘጋበታል። ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ድንጋዩን ከዘጋው መንገድ ለማስወጣት አብሮ መግፋት ይጀምራል። እየገፋም "hopeless!" (ተስፋ የለሽ!) ይላል። ይህንን በሰሙት የአበሻይቱ ልጆች አማካኝነት "ሆጵላስ!" ማበረታቻ ሆና በቋንቋችን ውስጥ ተፈጠረች። ሆጵላስ ደና ደሩ 😂
1 82815Loading...
15
https://www.instagram.com/reel/C3npBpfrfDw/?igsh=MWNuN2h6d21haGF2Mw==
1 5420Loading...
16
Denzel 🙏🙏
1 7353Loading...
17
" ያ ደግ ሰው በመንገዱ እየኼደ ሳለ ሽፍታ አገኘ፡፡ ያ ደግ ሰው፤ “ሰላም ለአንተ ይኹን! በዚህ ስፍራ ለምን ብቻህን ትዘዋወራለህ?” አለው። ያ ሽፍታም፡ “እኔ ሽፍታ ነኝ! ለዚህም ነው በዚህ ሰዋራ ስፍራ የምዘዋወረው:: ይልቅ ምን ይዘሃል? ወዲህ በል የያዝኸውን ኹላ! አምጣው!” አለው። ያ ደግ ሰው፡ “ለምን ግን ሠርተህ አትበላም? ሰው የደከመበት ገንዘብ ላንተ ምን ያደርግልሃል?" አለው፡፡ ያ ሽፍታ እየሣቀ፡ “ስማ! ማር በልተህ ታውቃለህ?" አለው:: ያ ደግ ሰው፡ “እንዴታ! በደንብ አድርጌ ነዋ የምበላው!" አለው:: ያ ሽፍታ፡ “ሠርተህ ነው ወይስ ከንብ ቀምተህ ነው? በጭስ እያስፈራራህ፣ እንዳትታይ በጭንብል እየተከለልህ ነው ንብ ለፍታ የሠራችውን የምትቀማት” አለው፡፡ ያ ደግ ሰው፤ ኹሉም ስው “ለፋኹበት” በሚለው ጕዳይ ወስጥ መዝረፍ እንዳለበት ዐወቀ። ከዚያም፣ ለሽፍታው “ብዙ ገንዘብ የለኝም:: ምናልባት ይህቺ ኹለት ፈረንካ ከበቃችህ እንካ” አለው፡፡ ያ ሽፍታ፡ “ለዛሬው ምሬሃለኹ፣ ከዚህ በኋላ ግን በማያገባህ ጕዳይ አትግባ" አለው፡፡ ያ ደግ ሰው፡ “እንኳን ማርኸኝ እንጂ በል ደኅና ሰንብት" ብሎት ፈጠን ፈጠን እያለ ተራመደ፡፡ በመንገዱም ላይ ሳለ እንዲህ እያለ እያሰበ ነበር፡፡ “አኹን ግን የእውነት እንቁላልን ዶሮ የምትሸጠው ቢኾን ዋጋው ስንት ይኾን ነበር? ሰው ከዕቅፏ ፈልቅቆ ይወስድባታል እንጂ መቼ ይጠይቃታል። እና፣ ከደምና ከዐጥንቴ ያልሠራኹትን ገንዘብ ሽፍታ ወስዶብኝ እንዲህ ከተንገበገብኹ ልጅ ይኾነኛል ያልኹትን፣ ከብቤ ያኖርኹትን ቢያነሡብኝ ቀድሜ አበድኹኝ” እያለ ኑሮውን እየታዘበ ኼደ፡፡ " " ግርባብ ያ ደግ ሰው " በፍቃዱ አየልኝ መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል :: @jafbok
1 63214Loading...
18
⭐#ዋጋህን_እወቀው! መነበብ ያለበት አስተማሪ ታሪክ "ትናንት ማታ አንድ ቪዲዮ እያየሁ ነበር። ሰባኪው የመቶ ብር ኖት ይዟል። እንዲህ ሲል ሰማሁት 'ይህ የብር ኖት እንደታተመ ምንም ዓይነት መጨማደድ አልነበረበትም። ከዚያ በኋላ ግን ሰዎች፦ ➡️እጽ ለመግዛት ተጠቅመውታል። ➡️ ለዝሙት ከፍለውታል። ➡️ጭቃ ውስጥ ነበር። ➡️ተቀዷል፣ ➡️ጠርዞቹ ተቆርጠዋል። ✅️ከዚህ ሁሉ ቀኋላ ይህ የመቶ ብር ኖት አሁን ዋጋው ስንት ነው? አሁንም ዋጋው ያኔ አዲስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ዋጋ ነው። አምላካችንም እኛንም የሚያየን እንደዚህ ነው። ያለፈው ታሪካችን ምንም ሆነ ምንም፣ የቱንም ያህል የተጎዳን እንሁን፤ ለእሱ ዋጋችን ያኔ ሲፈጥረን እንደነበረው ነው።' " ✅️👉#የተሰቀለው_ንጉሥ መጽሐፍ (አዲስ መጽሐፍ) 👉 #The_Crucifixion_of_the_King_of_Glory ✅️@Enmare1988 ✅️✅️@Enmare1988
7893Loading...
19
ሁለቱም እኩል ደወሉ እነማናቸው? ሳባ እና ዳዊት ለማንኛቸው እንደማነሳ ግራ ስጋባ ተዘጋ ሳባ መልሳ ደወለች እሱ text ላከ "ሚኪዬ ተቆጣኝ" አለቺኝ ይሄንን ሀረግ አውቀዋለው  የእሱም መልዕክት "ዛሬ ቀኑ ፈካ አላለብህም?" ይላል የሁለቱም ሀሳብ ትርጓሜው አዲስ ሰው ተዋውቀው ተመችተዋቸዋል ማለት ነው። "ኧ? ተቆጣኛ" አለቺኝ ምን ልበላት? ሁለቱም ጓደኞቼ ናቸው እሷ የመጨረሻ ኮስታራ ወንድ አጠገቧ የማታደርስ አይነት ሴት ናት የመጀመሪያዬ ጥሎኝ ሲሄድ ነው እንደዚህ የሆንኩት ትላለች እሱ ደግሞ የለየለት ሱሰኛ ነው እሱም  "ተከድቼ ነው" ነው ሰበቡ   በአንድ የተቀደሰ ልበለው የተረገመ ቀን አስተዋወቅኳቸው አጠገባቸው እኔ የሌለው ያህል በነፃነት ተሸኮረሟመሙ ከዛማ በቃ እፍ አሉ ሌላ ሰው የሌለ ያህል በየጎዳናው በየጥጋጥጉ በየቦታው አብረው ታዩ ከዛ ምን እንደተፈጠረ እንኳን ሳያብራሩልኝ በቃ ተደባበርን ብለው ተለያዩ ከዛ ዳዊት የሆነ ቅዳሜ ቀን መጥቶ "በቃ ንሰሀ ገብቼ መጣሁ ለእስከዛሬው ከዚ በኋላ ሱስ ደጅ ብደርስ" ብሎ እየተንጎራደደ ነገረኝ "ወገኛ! ሲሉ ሰምተሀል" ብዬ ችላ አልኩት እውነቱን ነው ብዬ አላሰብኩማ!! እሱ ግን አምርሮ ኖሯል እንዳለውም እርግፍ አድርጎ ተወው ሳባ እንዲተው እንዴት ትፈልግ እንደነበረ አስታውሼ "በእሷ ምክንያት ነዋ?" ብዬ ስጠይቀው ፊቱ ልወውውጥ ብሎ "ምንም ከሷ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም" አለኝ መልሴን ከፊቱ ላይ ስላገኘሁ "እሺ" አልኩት በሳምንቱ ከሳባ ጋር ተገናኝተን እያወራን እያለ በመሀል "እና በቃ ረሳሽው?" አልኳት ፊቷ ድምን ሲል እያየሁት "ማንን" አለቺኝ "ሳባ አትቀልጂ የእውነቴን..." ስላት ስልኳ ጠራ "ዳጊ" ይላል "ወዪዬ ዳጊዬ"  ብላ አነሳችው ዳግም ሲቆላመጥ ዳጊ ቆይ ዳጊዬን ምን አመጣው?! ደግሞ እኔ የማላውቀው ዳግም ማነው? እያልኩ ሳሰላስል "እኔም ናፍቀኸኛል እንገናኛለን" ብላ የውሸት ጥርስ በጥርስ ሆና ዘግታው "ዳግም ማነው" ስላት "አለ ባክህ የሚያዝገኝ" አለች "ፈገግታሽ እያዛገሽ አይመስልም" አልኳት "እ" አለች ከስልኳ ላይ ቀና ሳትል ከእጇ ላይ ነጥቄ ሳየው "እዩ" ይላል "መቼ ነው የማገኝሽ" ብሏት ሳትመልስለት ነው የተቀበልኳት "ተው ይደብረዋል ልመልስለት" ብላ መልሳ ወሰደችው "ምንድነው" አልኳት ዝም አለቺኝ የመጀመሪያው ፍቅረኛዋ ዝምተኛ አደረጋት የኔው ጉድ ጋር ስትለያይ ደግሞ የማንም ሆነች እሱ ደግሞ የመጀመሪያዋ ሱስ ውስጥ ዘፈቀችው ሳባ ስትተወው ደግሞ ሱስ ለምኔ አለ። ዛሬ ሁለቱም አዲስ ሰው እንደተዋወቁ እና ያ የተረገመ "ልዩ ስሜት" ስለተሰማቸው ነው የደወሉልኝ። እሺ አሁንስ ደግሞ እንዴት ያደርጋቸው ይሆን ምን አይነት ተፅዕኖ አሳድሮ ምን አይነት አሻራ ጥሎባቸው ያልፍ ይሆን? "ሄሎ ሚኪ አይሰማም እንዴ ተቆጣኝ እያልኩህ እኮ ነው" አለቺኝ ለካ እያናገርኳት ነው "ለምን እቆጣሻለው ጥፋት እኮ አይደለም" አልኳት "በምን አወቅክ" አለች በጥርጣሬ "አዲስ ነገር አይደለም ይሄ ለሶሰተኛ ጊዜ ስናስተናግደው ነው ብቻ አንድ የምልሽ ምንም ነገር እንደዚ እንዲያናውጥሽ እንዳትፈቅጂ እሺ" አልኳት "እሺ" ብላ ስልኩ ተዘጋ ወዲያው ለዳዊት መለስኩለት "ገና ለገና ሌላ ሴት መጣች ብለህ ወደዛ ሱስህ እመለሳለሁ ብትል እፈነክትሀለሁ" ብዬ መለስኩለት ✍nani
1 7233Loading...
20
ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ይህን👆 የገብረ ክርስቶስ ደስታን ገጠመኝ እና ስዕሉን ባየ ጊዜ ልቡ ተነካና ብዕሩን አንስቶ እንዲህ ሲል ተቀኘለት እዩት ይህን ጠቢብ ሸራው እስኪደማ በቀይ እየወጋ በደም እየሳለው እንጨት አመሳቅሎ ዳግም ክርስቶስን ጨርቁ ላይ ሰቀለው። ቀራኒዮ ሆነ የወጠረው ሸራ ጎለጎታ ሆነ የወጠረው ሸራ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ። ደም ከደም አረገው አበዛበት ጣር ብሩሹን አሹሎት እንደጎኑ ጦር። እየወጋ ሳለው በጣም ጨከነበት ገብረ ክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፋ የቆዳው አይነቱ በደም ተከልሎ ዘሩ እስከሚጠፋ። እየወጋ ሳለው እየሳለ ወጋው ደሙ እስከማይለይ መልኩ ዝም ብሎ ደሙ እስከሚናገር የትም ያለ ፍቅር እንዳይኖረው አገር። እንዳንለው ፈረንጅ እንዳንለው ጥቁር እንዳንለው ቀይ በመስቀል ላይ ሞቶ ያየውን ስቃይ። በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው። ከቀናት ባንዱ ለት ሰዎች ሲሟገቱ በቀለሙ ጉዳይ ሲከራከሩበት በተመፃዳቂ የምሁር አንደበት። በአንዱ አፍ ሲጠቁር በአንዱ አፍ ሲነጣ መታገስ አቃተው ሰዓሊው ተቆጣ ስሜቱ ገንፍሎ በብሩሽ ጫፍ ወጣ ሀሳቡን የሚገልፅ ቀለም እስከሚያጣ። ሸራ ላይ ሰቀለው እንጨት አመሳቅሎ አልወጣልህ አለው ፍቅርን ስሎ ስሎ ስሎ ስሎ ስሎ ፍቅርን ስሎ ስሎ በሳለው እየወጋ በደማው እየቀባ። ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀለም እንጨቱ ላይ ያለው እውነት ይሄ አይደለም። እያለ እስኪናገር የስዕሉ አንደበት ገብረ ክርስቶስም ለክርስቶስ ’ሚሆን ቀለም እስኪያልቅበት በነጩ ሸራ ላይ እስካሁን የሚወርድ ደም አፈሰሰበት። ቀለም ቀይ ቀለም የደም ቀለም የጥላ ቀለም የሁሉም ነው እንጂ የማንም አይደለም ፍቅር ዘር አይደለም። @wegochi
1 8446Loading...
21
You realize you wouldn't have learned how to ride a bike if someone you trusted hadn't let you go. God works differently
2234Loading...
22
ሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ስእል በሚያስተምርበት ወቅት ተማሪዎቹ የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል ስለዉ እንዲያመጡ በቤት ስራ መልክ አዘዛቸው ። ሁሉም በመሠለዉ መልክ ኢየሱስ ክርስቶስን ስሎ ሲያመጣ አንድ ተማሪ ግን የክርስቶስን ስዕል በጥቁር ወይም አፍሪካዊ መልክ ስሎ ያስረክባል ። ገብረ ክርስቶስ በስእሉ ተገርሞ ለምን ክርስቶስን ጥቁር አድርጎ እንደሳለው ሲጠይቀው ተማሪው «ክርስቶስ ፈረንጅ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ፈረንጆች በጣም ጨካኞች ናቸው። ኢየሱስ ነጭ ሳይሆን ጥቁር ነው» ብሎ ይመልሳል። ይህን ግዜ ነው ገብርዬ ወደቤቱ ሲበር ሄዶ ኢየሱስ ክርስቶስን ቀለም እንዳይኖረው ፣ ዘር እንዳይኖረው ፣ ነገድ እንዳይኖረው አርጎ ከፀጉሩ እስከእግር ጥፍሩ ድረስ በደም ለውሶ ሳለው። ገብርዬ በስዕሉ "ፍቅር ዘር የለውም። ፍቅር ቀለም የለውም። ፍቅር የነገድና የቀለም አጥርን ይሻገራል። ክርስቶስ ሲያድነን ዘር ቀለም ፆታ አልመረጠም። ክርስቶስ ያዳነን በደሙ እንጂ በቆዳው ቀለም ወይም በዘሩ አይደለም። በመስቀል ላይ የፈሰሰው የክርስቶስ ደም ለሁሉ ይበቃል።እኔነት ባለበት ፍቅር በዚያ የለም!!!" ሲል ይህን ዘመን ተሻጋሪ ስዕል ሊስለው ችሏል። ገጣሚና ሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ኢትዮጵያዊ ባይሆን ኑሮ በዚህ ስዕሉ ከዳቪንች እኩል በመላው ዓለም እውቅና በተጎናጸፈ ነበር። . እንኳን አደረሳችሁ!!! @wegochi
1 58311Loading...
23
" ሰዎች ፍቅር እውር ነው ይላሉ፣ እንዲህም የሚሉት የፍቅርን ትርጓሜ ስላላወቁ ነው፣ እኔ ግን እላቹሀለው ፍቅር ብቻ ነው አይን ያለው። ከፍቅር ውጪ ሌላው በሙሉ እውር ነው።" ✍🏼 ተሰብሰቡ
1 5980Loading...
24
ስብሐት ስለ ደራስያን ምን ይላል? ማስተርፒስ ወደ አማርኛ ስነፅሁፍ እየመጣች ነው ―ስብሐት ገብረእግዚአብሔር የዘነበ ወላን "ልጅነት" ካነበበ በኋላ ዶስቶቭስኪ ሲፅፍ ዝርክርክ ነበር። በቴክኒክ ረገድ ያልተዝረከረከው ‘ወንጀልና ቅጣት’ ብቻ ነበር። ታድያ ማንበቡ ሲጥምህ እንኳንም ተዝረከረከ ነው የምትለው። ―ስብሐት ስለ ዶስቶቭስኪ በአማርኛ ስነፅሁፍ ውስጥ እንደ አዳም ረታ የተዋጣለት የአጭር ልብወለድ ደራሲ የለም። ―ስብሐት ስለ አዳም ረታ(ልብ ማለት ያለብን ስብሐት አብዛኛዎቹን የአዳም ረዣዥም ልብወለዶች ለማንበብ አልታደለም ካፒታልን ያነበብኩት በደርግ ዘመን መፅሀፉን ወደ አማርኛ እንዲመልስ በተዋቀረው ኮሚቴ አባል ሆኜ ነው። ሰዎች ማርክስ ቤተሰቡን አስርቦ ነው የፃፈው ይላሉ። ፍልስፍናው ሲገባህ አውራጃም በተራበ ነው የምትለው። ―ስብሐት ስለ ካርል ማርክስ አደፍርስን ሳነበው "ሌቱም አይነጋልኝን" በእንግሊዝኛ የተተየበ 65 ገፅ ላይ ደርሼ ነበር። ከዛ በፊት አማርኛ ለስነፅሁፍ ብቁ አይደለም የሚል እምነት ነበረኝ። ዳኛቸው በአማርኛ መፃፍ እንደሚቻል ከሰተልኝ። ―ስብሐት ስለ ዳኛቸው ወርቁ ፍሩይድ ተአምረኛ ነበር። ወደ ራሱ ውስጥ ገብቶ የመረመረ ጂኒየስ ነው። እራሱ በርቶለት የኔንም ውስጤን አበራልኝ። ―ስብሐት ስለ ፍሩይድ በአሉ ጎበዝ አለቃ ነው። ከዛ ቀጥሎ ነው ደራሲነቱን የማደንቀው። በአሉ ባህሪውም መልኩም የስነጽሑፍ ችሎታውም ያማረ ሰው ነበር። ‘አይገኝም እንጂ እንዳማሩ መሞት’ የሚለውን የአንዳንድ ግዜ ህግ ጥሶታል። ―ስብሐት ስለ በአሉ ግርማ በዛኛው አለም አራት የአጭር ልብወለድ ጠበብቶች አሉ። አንደኛው ጊ ደ ሞፓሳ ነው። ሞፓሳ በ43 አመቱ ከ400 በላይ አጭር ልብወለድ ያመረተ ጎበዝ ደራሲ ነበር። ምን ያደርጋል ቂጥኝ በአጭር አስቀረው(ስብሐት ከአይኑ እንባ ዱብ አለ) ―ስብሐት ስለ ጊ ደ ሞፓሳ ፀጋዬ የኛ ዎሌ ሾይንካ ነው። ኦክስፎርድ ድረስ ሄዶ ስነፅሁፋችንን አለማቀፋዊ ያደረገ ደራሲ ነው። ―ስብሐት ስለ ፀጋዬ ዲክንስ የታችኛውን ማህበረሰብ ህይወት ነው የፃፈው። እንደ ሩስያ ስነፅሁፍ እንባ በእንባ ነው የሚያደርግህ። የእንግሊዝ ነገሥታትና ልኡላን ዲክንሰን አነበቡት። ከዛ በኋላ ነው ድሆችን የሚረዳ ድርጅት በእንግሊዝ መቋቋም የጀመረው። ዲክንስ በስነፅሁፉ ጉልበት በሃገር ደረጃ ማህበራዊ ተፅእኖ መፍጠር የቻለ ታላቅ ደራሲ ነው። ―ስብሐት ስለ ቻርልስ ዲክንስ ኃይለመለኮት መዋእል ‘ጉንጉን’ ውስጥ አማርኛን ከነለዛዋ ከነማእረጓ ፅፎ አስደነቀኝ። ደግሞም ኃይለመለኮት ብእሩ ብቻ ሳይሆን አንደበቱም ርቱእ ነው። ―ስብሐት ስለ ኃይለመለኮት ፕሩስት አይሁድ ነው። የፈረንሳይ አይሁድ። ጂንየስ ነው። አይሁድ መሆን ጂኒየስ ያደርጋል መሰለኝ። ሰባት ልብወለድ ጽፏል። ስለ ራሱ ነው የፃፈው። በልብወለዱ ውስጥ ያሉት ሁለት መቶውም ገፀባህሪያት ፈረንሳይ ውስጥ በሕይወት ያሉ ሰዎች ናቸው። በፈረንሳይኛ ነው ያነበብኩት። ፈረንሳይኛን እንደሱ የሚያውቅበት ደራሲ የለም። ―ስብሐት ስለ ማርሴል ፕሩስት ጋሽ ሐዲስ አለማየሁ ቆንጆ ስታይል ነው ያላቸው። ተረታዊ አቀራረባቸውን እወደዋለሁ። በአማርኛ የሚፅፉ ቶልስቶይ ልትላቸው ትችላለህ። ―ስብሐት ስለ ሐዲስ አለማየሁ ኒቼ ከዘመናዊ ታላላቅ ፈላስፎች አንዱ ነው። ግማሽ ጎኑ ፖላንድ ነው። በጣም ብሪሊያንት ነበር። ከኤግዚስቴንሽያሊዝም አያቶች አንዱ ነው። ፍልስፍናው በጣም ተፅእኖ ፈጣሪ ነው አሁን ድረስ። ኒቼ የቂጥኝ በሽታ ነበረበት። በዚሁ ጦስ አብዶ ነው የሞተው። ―ስብሐት ስለ ፍሬድሪክ ኒቼ ከበደ ሚካኤል በዘመናቸው ለነበረ ትውልድ ትክክለኛ ደራሲ ናቸው። ለአሁኑ ትውልድ ግን እንጃ። ምክንያቱም ስራቸው ግብረገብ ይበዛበታል። ቢሆንም መደነቅ ይገባቸዋል። ―ስብሐት ስለ ከበደ ሚካኤል አልቤር ካሙ ጋዜጠኛም ፈላስፋም ደራሲም ነበር። ደግሞም ሰው ነው። ላመነበት ነው የሚኖረው። በእኛ ዘመን ካሙን እና ሳርትርን ያላነበበ ኢንተሌክችዋል ወጣት አልነበረም። ስራቸው ፍልስፍናም ምርምርም ነበር። ―ስብሐት ስለ አልቤር ካሙ ከተርጓሚዎቻችን መሐል ያነበብኳቸው እና የወደድኳቸው ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም፣ ባሴ ሃብቴና መስፍን አለማየሁ ናቸው። በተለይ ባሴ በሲራኖ ትርጉሙ አስደንቆኛል። ―ስብሐት ስለ ተርጓሚዎች ገተ የጀርመን የስነጥበብና የባህል አባት ነው። በአውሮፓ የመጀመሪያውን ሮማንቲክ የሆነ አብይ ልብወለድ የፃፈው ገተ ነበር። ፎስት ይባላል። ፎስት የታወቀ የጀርመን ሌጀንድ ሲሆን ገተ በስነፅሁፍ ህያውና ዘለአለማዊ አድርጎታል። ―ስብሐት ስለ ዎልፍጋንግ ገተ ብርሃኑ ዘርይሁንን ሳገኘው ከኔ የባሰ አይናፋር ነው። ማእበልን ጀምሬ መጨረስ አልቻልኩም። አፃፃፉ ጥሩ ነበር። ግን የረሃብ ሰቆቃውን ተቋቁሜ ማንበብ አልቻልኩም። እንዴት ችሎት ጻፈው! ―ስብሐት ስለ ብርሃኑ ዘርይሁን © Tewodros Shewangizaw
1 8807Loading...
25
ሮፍናን ZETEGN | HARAMBEE አልበም ታምሪያለሽ 👇👇👇 @old_musica ሼር🙏
1 4916Loading...
26
⭐አንዳንድ ግንኙነቶች አሉ. . በዝምታ የሚያልቁ ንግግሮች፤ ያልተጨበጡ ደቂቃዊ ደቃቅ ቆይታዎች፤ ያልታቀፉ ገላዎች፤ ድፍረት ያልጎበኛቸው አሳቦች፤ የሽቶ ጠረን፤ በዓይን በአንገት የሚናገሩት፤ መነካካት፣ መሳሳም፣ መተቃቀፍ፣ መላፋት የናፈቁ፤ አንዳንድ ግንኙነቶች አሉ ላለመገኘት የተገናኙ.. ⭐@Enmare1988 ✅️@Enmare1988
1 3165Loading...
27
"ተናጋሪው" ቅዳሜ ጠዋት ከቤተክርስቲያን ተመልሰን አረፍ ከማለታችን ሚጣዬ ሄዳ ቲቪ ከፈተች አሻንጉሊቷን ልታይ መሆኑ እኮ ነው ተቆጥቼ አስቀየርኳት "ቅዳሜ እንኳን የእኛ ተራ ይሁን ብዬ" ከዛ channel ቀይራ እጇን አጣምራ ተቀመጠች ማኩረፏ እኮ ነው ሆ ሆ የዘንድሮ ልጅ እያልኩ በሆዴ... ቁርስ ቀራርቦ መብላት ጀመርን። እንደዛ ተቆጥቼ ያስቀየርኩትን ቲቪ ሳየው አንድ ተናጋሪ ነኝ ባይ መድረክ ሙሉ ህዝብ ሰብስቦ ያወራል። "እኔ ልዩ ነኝ ማለት አለብን ምክንያቱም ሁላችንም የተለያየን ነና..."ሲል "እማ እማ" አለቺኝ "ወዬ ሚጣዬ" ስላት "እኔ ልዩ ነኝ ማለት ምን ማለት ነው?" አለቺኝ እውነት ግን ልዩ ነን ምን ማለት ነው? ከመሰረታዊ ፍላጎቶቻችን አንፃር ሁላችንስ ከእንስሳት በምን እንሻላለን? ፍቅር የማያሸንፈው አለ? አንዳንድ ማህበራዊ ተፅዕኖዎች ከፈጠሩብን የባህሪ እና የቀለም ልዩነት ውጪ አብዛኛው ነገራችን እኮ አንድ ነው። "እ መልሺልኛ?" አለቺኝ ለአራት አመት ህፃን ምን ተብሎ ይሄ ይብራራል "ይሄ የትልቅ ሰው ወሬ ነው አልኳት" እሺ ብላ ዝም አለች። በሚገባት ባብራራላት ይሻል ነበረ ወይስ ስታድግ ራሷ ትጋፈጠው እያልኩ ከራሴ ጋር ስሟገት ተናጋሪ ነኝ ባዩ ሰውዬ "በቃ ስኬታማ ለመሆንም በሉት የውስጥ ሰላም ለማግኘት ልባችሁን አዳምጡት ልባችሁን ተከተሉት" አለ። የፈራሁት አልቀረልኝም "እማ ልብ መከተል ምን ማለት ነው" አለቺኝ። ዛሬስ እኔም ግራ ገባኝ ልብ መከተል? ልብን ለመከተል እኮ በራስ መተማመን ያስፈልጋል፥ ራስን ማዳመጥ፥ ከራስ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል ታዲያ አሁን ያለው አለም ይሄንን የሚፈቅድ ነው? ሁሉም የራሱን ሀሳብ የሚጭንብህ እንጂ እንድታስብ የሚፈልግ የለም። እኔ ራሴ እንኳን ቅድም ያደረግኩትን ሳስብ ራሴን ታዘብኩት "የትልቅ ሰው ነው ምንም አያደርግልሽም" ስላት የማሰብ አድማሷን እያጠበብኩት እኮ ነው። "እንዴ እማ የጠየኩሽን ረሳሽው እንዴ?" ስትለኝ አሁንም ቢሆን እንዴት እንደማስረዳት ማወቅ አልቻልኩም ቀና ብዬ ሳየው አሁንም እያወራ ነው ሰውየው ሌላ እኔም ያልተረዳሁት ጥያቄ ከመጠየቋ በፊት ብዬ "በቃ ቀይሪው ወደ ምትፈልጊው አታድርቂኝ" አልኳት ወዲያው ቀይራ አሻንጉሊቷን ማየት ጀመረች። ✍nani
1 7004Loading...
28
Media files
9 1902Loading...
29
👍'' በምሽት ብልጭ የምትል አንዲት ሐሳብ ለታላቅ ክብር አሊያም ለስደት ትዳርጋለች ...የአንዲት ሴት ዓይኖች ቅፅበታዊ ዕይታ የዓለማችን ደስተኛ ሰው ሊያደርግህ ይችላል... ከሰው ልጅ ከናፍር የሚወጣ አንድ ቃል ሀብታም ወይም ደሃ ሊያደርግህ ይችላል ።❤️❤️
1 3484Loading...
30
franz kafka
3250Loading...
31
Media files
3310Loading...
32
Media files
3700Loading...
33
At 40, Franz Kafka (1883-1924),who never married and had no children, walked through the park in Berlin when he met a girl who was crying because she had lost her favourite doll. She and Kafka searched for the doll unsuccessfully. Kafka told her to meet him there the next day and they would come back to look for her. The next day, when they had not yet found the doll, Kafka gave the girl a letter "written" by the doll saying "please don't cry. I took a trip to see the world. I will write to you about my adventures." Thus began a story which continued until the end of Kafka's life. During their meetings, Kafka read the letters of the doll carefully written with adventures and conversations that the girl found adorable. Finally, Kafka brought back the doll (she bought one) that had returned to Berlin. "It doesn't look like my doll at all," said the girl. Kafka handed her another letter in which the doll wrote: "my travels have changed me." the little girl hugged the new doll and brought her happy home. A year later Kafka died. Many years later, the now-adult girl found a letter inside the doll. In the tiny letter signed by Kafka it was written: "Everything you love will probably be lost,but in the end,love will return in another way."
4063Loading...
“ለምን ትመጫለሽ? ወና መሆን ለምዷል ባይተዋር ነው ሆዴ ትራስ አቅፎ ማደር ለምዶበታል ክንዴ። ገላዬ ቀዝቅዟል ልቤ ተሰቅዟል እንስት እንዴት ልመን? ዜሮ ነኝ ስተመን ብትመጭም ከንቱ ነው መመለስሽ ምንም ስታወሪ አልስቅም በእንባሽ አልቆዝምም በድን ነኝ አልድንም ። የለሁም በድሮ ሌላ ነኝ ዘንድሮ ግዴ አይደለም ነገ ወጋገን ማለዳው ለዛሬ ሶስት ዓመት ዛሬን ነው ‘ምቀዳው። አትገርመኝም ጀንበር ብራና ክረምቱ ቢዛወር ዓመቱ ጨፍሬ አልደክርም አልመታም አታሞ ዓመት አንድ ቀን ነው ለከሸፈ ታሞ ። ለምን ትመጫለሽ ? መምጣትሽ እንደ ቧልት መመለስሽ ምንም ...” ይህንን እያልኩኝ ብናገር ብገጥምም ስትመጪ ስዳበስ በጣት በመዳፍሽ ያልኩትን ዘንግቼ አዲስ ሰው ሆንኩልሽ። አትሄጂም አይደለ ?🙄 (ሚካኤል አ)
Mostrar todo...
3❤‍🔥 2😁 2
እውነት ፈጣሪ ግን ህይወትን ማመጣጠን ሲያውቅበት በመስጠት ብቻ ሳይሆን በመንሳትም ጭምር፣ በፍቅር ብቻ ሳይሆን ምቶዱትን ሰው በማራቅም፣ በማስደሰት ብቻ ሳይሆን በሀዘንም በማስተማር ጭምር፣ ባሳለፍነው ህይወት ሁሉን ነገር አመዛዝኖ በመስጠት ማቆየቱ፣ በደስታ መክነፍን ብቻ ሳይሆን በሀዘንም ብዙ ትምህርት ማስጨበጡ፣ መኖርን የማጣጣም ስርአቱና አግባቡ ያስገርማል፣ እውነትም በህይወት መቆየት ደግ ነው ብዙ ያስተምራል!!
Mostrar todo...
9👍 3
👍 8 3🎉 2
"ካልጠፋ ቀን ዛሬ መንገድ መዘጋጋት ነበረበት" ትላለች እየደጋገመች መዘጋጋቱ ሳያንሰ አሁን ደግሞ መብራት ይዟት መሀል መንገድ ላይ ቆማለች። መንገዱ መፈናፈኛ ስለሌለው ዘና ብላ መቀመጥ ስትችል ወደ ፊት ተጥግታ መሪውን አጥብቃ ይዛ ነው የተቀመጠችው። "ቆየሽ በሰላም ነው?" የሚለውን መልዕክት ለሶስተኛ ጊዜ ሲልክላት ጭንቀቷ በእጥፍ ጨመረ ።የትራፊክ መብራቱን ስታየው አረንጓዴ ሆኗል ወዲያው ከዚህ በፊት አድርጋ እንደማታውቀው እየተሽሎከሎከች መንዳት ጀመረች። ለይስሙላ ነዳች ይባል እንጂ ሀሳቧ ያለው ሰለሞን የላከላት መልዕክት ጋር ነው። "በተቻለሽ ፍጥነት ነይ ጥሩ ስሜት ላይ አይደለሁም" ይላል 'ደሞ ምን ሆኖ ይሆን አምላኬ አደራህን እስክደርስ ምንም መጥፎ ነገር እንዳያደርግ' እያለች በደመነፍስ ስታሽከረክር ያምባረቀባት ጡሩንባ አባነናት ለምንድነው በእሷ አቅጣጫ ከፊትለፊቷ መኪና እየመጣ ያለው? ለካ በባለሁለት አቅጣጫ መንገዱን መመለሻውን አስፋልት ለመሄጃ ተጠቅማበት ነው መኪኖች ከፊት ለፊት እየመጡባት ያሉት ብቻ በደመነብስ አዙራ ነው ወደ ትክክለኛው መስመር የተመለሰችው 'ልሞት እችል ነበረ ለራሴም ለእሱም አልሆንም ነበ'ረ እያለች ከድንጋጤዋ ለመረጋጋት እንኳን ሳትሞክር አንዴ ፀሎት አንዴ ምሬት ለራሷ እያልጎመጎመች ስትሄድ አንዲት አሮጊት ቀስ እያሉ ሲሻገሩ እሷ አንደ እብድ ስትነዳ ለጥቂት እስትንፋሳቸውን ነጥቃቸው ነበረ ምስጋና ለመኪናዋ ምርጥ ፍሬን እንቅ አድርጎ ይዞላት ከሞት ያዳናቸው እሷንም ከነፍሰ ገዳይነት ያዳናት ወይ ደግሞ ጠዋት 'ሰላም አውለኝ' ብለው የፀለዩት ፀሎት ነው ያዳናቸው ብቻ ግን እሳቸውም ካለፉ በኋላ እግሯን ከፍሬኑ ላይ አላነሳችውም የቅድሙ ድንጋጤ ሳይለቃት ሌላ ቅድም ለራሴ ሞቼ ነበረ አሁን ደግሞ ሰው ያውም አሮጊት ሴት ገድዬ ነበረ ብላ እጇ መንቀጥቀጥ ጀመረ። "ቀረሽ እንዴ?" የሚል መልዕክት ላከላት ሰለሞን ለካ ሰለሞን እየጠበቃት ነው አንዴ በሰላም እንድትደረስ አንዴ በሰላም እንዲቆያት ፀሎቷን እያደረሰች ከአስራ ምናምን ደቂቃ በኋላ የቀጠራት ቦታ ደረሰች ስትገባ አስተናጋጆቹ በፈገግታ ተቀበሏት ለራሷ በፍርሀት እና በድንጋጤ መሀል ሆና ተመሰቃቅላለች ጭራሽ ፈገግ ይላሉ?! ወደውስጥ ስትገባ ሰለሞን እየሳቀ መጥቶ አቀፋት ግራ ገባት "ሶል ደህና ነህ ግን?? ምንድነው ብለህ የጠራኸኝ እና ነው የምትስቀው?!" አልኩት ጭራሽ ግራ ገብቶኝ እስኪ ወደጀርባሽ ዙሪ አለኝ የማውቀው ድምፅ...አሹ ሊሆን አይችልም ስዞር surprise ብለው ጮሁ ወዳጆቼ የምላቸው በሙሉ ተሰብስበው ሆቴሉን ዲኮር አሰርተውበታል... አሹ ከፊት ቆሟል "የኔ ምርጥ እና ብቸኛ እህት" ብሎ ተንደርድሬ እንደማቅፈው አይነት እጆቹን ዘረጋ ብዥዥ አለብኝ ለአስራ ምናምን አመት ያላየሁት ወንድሜ እዚህ ምን ይሰራል? ምንም ሳልላቸው ሄጄ አጠገቤ ያገኘሁት ወንበር ላይ ተቀመጠች ግራ ተጋቡ የልብ ጓደኛዋ ፌቨን "ነግሬያችሁ ነበረ እሷ እንደዚህ አይነት ነገር አይመቻትም ሰው አትሰሙ" እያለች ስትበሰጫጭ ይሰማታል ሶል መጥቶ ከፊቷ መጥቶ በርከክ አለና "ምነው እናቴ" አላት ስታኮርፍ እንደሚለማመጣት አይን አይኗን እያየ ወንድሟም ወገቡን ይዞ ቆሞ ያያታል የደገሰውን ስላበላሸችበት "ለእናንተ የማይረባ ድራማ አንተ አንድ ነገር ትሆናለህ ብዬ ስንቀዠቀዥ አንዴ የመኪና እራት ልሆነ አንዴ ደሞ የሰው ህይወት በእጄ ሊጠፋ ነበረ ምክንያቱም እናንተ surprise ማድረግ እውቀት መስሏችሁ" አለችው አንዴ ሶልን አንዴ ወንድሟን እያየቻቸው ከተቀመጠችበት ተነስታ ሁለቱንም አፈራርቃ እያየች "ከsurprise በላይ ምን እንደሚበልጥ ታውቃላችሁ እንኳን እንደሚፈጠር እርግጠኛ የተሆነበት ነገር ይቅርና ተስፋ የሌለው ነገር እንኳን ተስፋ በማድረግ እንደሰት የለ? ሌላውን ተዉት ህፃን ሆነን ሎተሪ ተቆርጦ አስኪወጣ ድረስ ያለውን ደስታ ትዝ አይላችሁም ምን ምን እንደሚደረግበት ማሰብ ብቻ ለሳምንታት ያስደስተን ነበረ" ወደ ወንድሟ በደንብ ዞረችና "አባ ምን እንሚል ትዝ አይልህም 'የበዓል ዋዜማው ከእለቱ ይበልጣል' ሲል ትዝ አይልህም?! ሰርግስ ቢሆን ከቀኑ በላይ እስኪደርስ ቀን መቁጠሩ እያሰቡ ብቻ መደሰቱ አይበልጥም? ግን ለምን ይሄ ከፈረንጅ ቀጥታ ከምትገለብጡት ከንቱ ልማድ አንዱ ነው surprise የምትሉት ጉድ ሰዎች ጀሚያስደስታቸውን ነገር ፈልጎ አምጥቶ ድንገት ማስደንገጥ ከዛ ከደስታቸው እና ከድንጋጤያቸው ጋር ሲወናበዱ እያዩ ቪድዮ መቅረፅ ከዛ surprise ተደርጋ ስትደነግጥ ብሎ tik tok መስራት በቃ ይኸው ነው አይደለ ከብዙ አመት በኋላ ስንገናኝ እንደዚህ ባይሆን ደስ ይለኝ ነበረ" ብላ በሩን አጋጭታ ጥላቸው ሄደች ሁሉም ደንግጠው ቀሩ።
Mostrar todo...
👍 14💯 4👌 1
Photo unavailableShow in Telegram
Check out Daniel Aweke(ዮዳA): https://t.me/danielaweke
Mostrar todo...
Daniel Aweke(ዮዳA)

🔊ዳኒ ነኝ! Follow አታድርጉ Fan ብቻ ሁኑ። 🔊ምክንያት ካላችሁኝ "Only God wanna Followers not Fans! " 🔊እናም ይኸ ገጽ የኔን ስራዎች የሚያገኙበት ቻናል ነው። "✍️ዮዳA " Facebook:

https://www.facebook.com/daniyeuodit.lij

Tiktok:@daniel_aweke

https://vm.tiktok.com/ZMM7JCXbQ/

💯 1
"ያለ እነርሱ እንዴት እኖራለሁ ያልካቸው ሰዎች መኖራቸው ሰላም እስኪነሳህ ድረስ ካሳነሱህ አስብበት....ከስሜታቸው በታች ከሆንክም አስብበት...ለራስህ ያለህን ዋጋ እያሳነሱት ከሆነ...ውስጥህን እያቀጨጩት ከሆነ እመነኝ የእነሱ አለመኖር ሳይሆን መኖራቸው ብቻ አያኖርህም...".....ከልቧ ነው....ታስታውቃለች። "ዛሬ ደግሞ ጫን ያለው ነው....ማንያዘዋል ነው ወይስ ዳዊት ድሪምስ....."....በእኔ ቤት መቀለዴ ነው...እርሷ ቀልዴ እንጨት እንጨት ያላት ይመስል ገልመጥ አርጋኝ ማውራቷን ቀጠለች። "ይኧውልህ ሰው የማይጎትትህ አይነት ሰው ከሆንክ ካንተ በላይ የታደለ የለም...እስቲ አስበው አንተ እናትህ ልጅነቷን አጥታብህ ላንተ ብላ አፈር መስላ ሰው ሆንክልኝ ብላ ተደስታ ገና አረፍ ከማለትዋ ፍቅረኛዬ ጥላኝ ሄደች ብለህ እናትህ የገነባችውን ማንነት ስትንድ...የእናትህ ላብ በዜሮ ሲባዛ....." "ምን አይነት ምሳሌ ነው የምትሰጪው....አሁን ምሳሌ ጠፍቶ ነው...?" "ምሳሌ መሆን በራሱ ያስጠላል አይደል...እሺ ተውኩህ...ማንም አይኑርህ...ማንም አይልፋልህ...እንዲሁ ብቻ ነገ የተሻለ ይሆናል ብለህ ብቻህን ታግለህ ያለህበት ደረስክ...አንተ እና ፈጣሪህ የገነባችሁትን ማንነት በግንባታው ሂደት ያልተሳተፈ ሰው ሲንደው በጄ የምትትል አይነት ሰው ከሆንክ ወደፈጣሪህ አልቅስ..."..."ሌላው ቀርቶ የገነባህ ሰው እንኳን እንዲያፈርስህ መፍቀድ የለብህም.... አንዳንዴ እምቢ ማለትን የመሰለ ነገር የለም" ጨረሰች መሰለኝ በረጅሙ ተነፈሰች። "ሰላም ራሱ አላልሺኝም እኮ ምን ጉድ ነው ዛሬ...."...ህልም የመሰለ ፈገግታዋን አሳይታኝ እቅፌ ውስጥ መሸገች... "እኔስ ስልጣን አለኝ.?"..ከእቅፌ ሳትወጣ በሹክሹክታ ጠየቅኩ። "እንዳታስበው..." "እንዴ ማለት አትወጂኝም...? " "ጥያቄህን ለራስህ ጠይቀው...." "ስትይ...." "ከወደድከኝ ለምን ታፈርሰኛለህ....አለመኖርህ እንዲያፈርሰኝ ለምን ትመኛለህ...ይህ ስልጣን ምን ይጠቅምሀል...ወይስ እንደ ዘመኑ ፖለቲከኞች ስሙ ስልጣን ስለሆነ ብቻ ሰው የሚገል ስልጣን ታሯሩጣለህ....የምርህን ግን ትወደኛለህ....?" ዝም ብዬ ባቅፋትስ...ምኑ ቀሽም ነኝ...? ✍Shewit https://t.me/shewitdorka
Mostrar todo...
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

8👍 3🔥 2
Repost from Shocking Facts®
Photo unavailableShow in Telegram
A Hungarian psychologist named Laszlo Polgar theorized that anyone could become a genius because geniuses were made and not born. To prove this, he used his own daughters as experiments and trained them to become great at chess. The three Polgar sisters then became chess prodigies, and the youngest, Judit Polgar, become a grandmaster at just age 15. #History Join and share @SHOCKINGFACT
Mostrar todo...
👍 2
00:19
Video unavailableShow in Telegram
“ተስፋ የመኖር ምክንያት ነዉ፣ ሰዉን እንዲኖር የሚያደርገዉ መለወጥ አለመለወጡ ሳይሆን የመለወጥ ተስፋዉ ነዉ”
Mostrar todo...
18