cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 627
Suscriptores
+224 horas
-117 días
+14130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የእርዳታ ጥሪ ‼️ ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እናት "የተማሪ ናትናኤል ደመላሽ እናት" ስትሆን ከዚህ በፊት የልብ ህክምና ስትከታተል ነበር። አሁን ላይ ግን ችግሩ ከፍ ስላለ ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልጋት ተነግሮናል። ይህንን ቀዶ ጥገና ለማካሄድ የተጠየቀው ገንዘብ እስከ 760,000 ብር ነው። የሰው መድሃኒቱ ሰው ነውና የአቅማችንን በማጋራት የእኝህን እናት ህይወት እንታደግ። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አካውንቶች በመጠቀም የአቅማችንን እንደግፋቸው። ንግድ ባንክ 1000298948935 Natnael Demelash አቢሲኒያ ባንክ 69362826 Natnael Demelash Contact: +251993655876 ተማሪ ናትናኤል ደመላሽ የ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአምስተኛ ዓመት የፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ ተመራቂ ተማሪ ነው።
Mostrar todo...
👍 7 2🤯 1
"አንቺ ጦጣ ምንድን ነው የምትሰሪው...."....አባቴ ነው...ከድሮም ቀጫጫ ስለነበርኩ መሰለኝ 'ጦጣ እኮ ነው የምትመስይው ስሙኒ' ማለት ልማዱ ነበር በቁም ነገር ቆም ብሎ እያየኝ.... "አትክልቶቹን ውሀ እያጠጣኃቸው...." "ታዲያ አፈሩ ላይ እኮ ነው ማፍሰስ ያለብሽ ልጄ...."...በርግጥም ቅርንጫፎቹ ላይ እያፈሰስኩ ነበር... "ስሩ ከራሰ ይበቃል...ስሩ ሙሉ ቅርንጫፉን ያለመልማል"...አለኝና ፊቴን ለመጠጠኝ....በእርሱ አሳሳም ቢሆን ኖሮ እስከ አሁን ዲምፕል አውጥቼ ነበር...በእርግጥ እማዬም እርሱም ከስራ እንደገቡ እግራቸው በራችንን አልፎ እንደገባ ከንፈራቸው ከንፈራችን ላይ ያርፋል...እኛን እንደሚስሙት እነርሱ ራሱ እርስ በርሳቸው እንዲህ የሚሳሳሙ አይመስለኝም..... ልጅ እያለሁ ያባባዬ ቀኝ እጅ ነበርኩ...ከስሩ አልጠፋም ነበር....እንዲህ እንዳሁኑ እሳትና ጭድ ከመሆናችን በፊት እጅና ጓንት ነበርን.... "ነበር" ለእኔ የሶስት ሆሄያት ድምር ብቻ አይደለም...አዎ "ነበር" ለእኔ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ ያለ ተራ ቃል አይደለም....ነበር ለእኔ እሾህ ነው...ሌባስ ሰርቆ ትንሽ ያስቀራል እሳት ግን ሁሉን አመድ ያደርጋል አይደል...ግድ የላችሁም "ነበር" እሳት ነው.... ✍Shewit ከመፅሀፌ የተወሰደ...(ወደፊት ከማሳትመው)🙄 https://t.me/shewitdorka
Mostrar todo...
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

👏 32 13😁 13👍 8❤‍🔥 2
✨✨የጠማኝ ውሀ ነው....✨✨ " 'ኖራ ኖራ ሞተች'..መባል አትፈልጊም አይደል...በቃ ጠንከር በይ..."....አላት...ከልቡ ነው...በቃ በእሱ ቤት የመኖርያ ምክንያት በበቂ ሁኔታ አቅርቦላታል። ሳቀች...ከት ብላ ሳቀች...ከልቧ ነው። "ያስቃል...."...ጠየቀ። "እንዴት አያስቅም...ካካካካ"....ቀጠለች.... "እፈልጋለሁ....ኖራ ኖራ ሞተች መባል እፈልጋለሁ...በጣም እፈልጋለሁ...."....እምባ የአይኗን ሲሞላው ድንብርብሩ ወጣ....አላቆመችም.... "እፈልጋለሁ አልኩህ እኮ....'ኖራ ኖራ' እኮ ትልቅ ቃል ነው...ውስጡ መኖር አለው...ከኖርኩ በኃላ ብሞት ችግሩ ምንድን ነው....ትግሌ ኖራ ኖራ ሞተች ለመባል ነው... "...ትንፋሿ ባናት ባናቱ መጣና ንግግሯን ገታው.... "ለማለት የፈለኩት ምንም ሳትሰሪ ህይወትሽ ላይ ....".....አላስጨረሰችውም.... "እሱም የመኖር አካል ነው...ስሞት ስለሚነበበው የህይወት ታሪክ ገፅ መሙያ ብዬ አይደለም...ለመኖር ነው ማልሞተው...እስኪ ልጠይቅህ በመሞቴ ምን የሚፈጠር ይመስልሀል...ፀሀይ መውጣትዋን ታቆማለች...ነፋሳት መንፈሳቸውን ያቆማሉ...ሰማይ ያለቅስልኛል...ንገረኝ ምን ይፈጠራል...." "...ምናልባት እናትሽ ጥፋቷ ይገባት ይሆናል እንጂ...."....አሁንም አቋረጠችው... "አይገባትም....አይገባትም....ልጄን አሰከፉብኝ እንጂ ልጄን አስከፋዋት አትልም...ከአንድ ሳምንት ካርታ ጨዋታ የዘለለ ትውስታ አይኖረኝም...እንደማስበው የእግር እሳት አልሆንባትም...ህይወት ይቀጥላል...ለማንም አይደለም ጭንቅላቷ ለራሱ ብሎ ይረሳኛል...ከአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት አላልፍም...ሞኝ አትሁን...ኖራ ኖራ ሞተች ላለመባል አይደለም ለመባል ነው የምታገለው....." "ጥያቄ ልጨምርልህ...."....አንገቱን በይቻላል አይነት ነቀነቀ... "ጭው ያለ በረሀ ላይ ሆነህ ውሀ ክፉኛ ቢጠማህ እና ሰዎች ደግሞ ወተት ቢያመጡልህ  ምንድን ነው የምታደርገው..." "ወተቱን እጠጣለሁ...." "ከዛስ....ውሀ ማለትህን ታቆማለህ..." "በሚገባ...."....አላት በእርግጠኝነት.... "በአፍህ ውሀ ማለት ታቆም ይሆናል...ምክያቱም ወተት እየሰጡህ ላሉት ጥሩ ሰዎች ብለህ...ግን ውስጥህ ውሀ መጠማቱን አያቆምም....ለእኔ እናቴ ውሀ ናት...ዙሪያዬ ብዙ ወተት አለ...ግን ደግሞ ውሀ የተጠማው ጎኔ ጠውልጓል...አንዳንዴ የሰው ነገር መጋራት ያስጠላሀል...የጓደኛህ እናት እናትህ ነኝ ቢሉህ አንተ የምትፈልገው እናትህን ብቻ ነው...አንዳንድ የማይተኩ ነገሮች አሉ..."....አፉን ከፍቶ ያዳምጣታል.... "ስትሞት የምድር መሽከርከር የሚቆምልህ ይመስልሀል....ዝምምምም የሚል...በቃ ይመስልሀል...ቅድም አንተ እንዳልከው እናቴ ጥፋቷ አይገባትም...ቢገባትም ለውጥ አያመጣም...እኔ በድኛለሁ...በድን የበሰበሰ አንጀቱ አይርስም...የሟች ቤተሰብም አመት አያለቅስም...ደግመው የሚስቁ ያልመሰላቸው ጥርሶች ይስቃሉ....ስምህ አልፎ አልፎ ብቻ ይጠራል....ተፈጥሮአችን እንግዲህ እንዲህ ነው።" "እና ለምን ...ይሄን ሁሉ እያወቅሽ ለምን...." "ይቅርታ ልጠይቀው ደጁ ሄድኩ...አምላኬን....ስላሳፈርኩህ ይቅርታ...ታሸንፋለች ፈትናት ላልከው ሰይጣን ድል ስለሆንኩ ይቅርታ ልለው...እናቱንም ይቅርታ ልላት...ከዛ በኃላ ነገሮች ተቀየሩ...በእርምጃዬ ቁጥር እየተረጋጋሁ መጣሁ...አንድ ልቤ እንድመለስ ይነግረኛል...ይቅርታ የማለት እድል ባላገኝስ ብዬ ፈራሁ...ቤቱ መሄዴን ገፋሁበት... ቤቱ ስደርስ ሁሉም ፀጥ አለ..."...ትንሽ አርፋ ቀጠለች.... "ማሰብ ጀመርኩ...ስሜቱ ሲሄድ ጭንቅላቴ መጣ...ያቺን ጊዜ አሳለፋት....ከዛ ጭንቅላቴ ላይ የሆነ ቃል መጣ.... " "ምን...." "ነብሱን እና እናቱን የሰጠኝ ጌታ ምን ይነሳኛል...ምናል ብታገስ...ምናል እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ ባልል...ምናል ባላሳፍረው..."....ፈገግ አለ። "ልመክርሽ መጥቼ መከርሺኝ እኮ...."....ሁለቱም ፈገግ አሉ.... "በይ አሁን ስራ ልሂድ...."....አለኝና ደንገጥ ብሎ ቁጭ አለ.... "ብሞትም እንዲህ ነበር እንዳልልህ ነው...."....ሳቁ አሁንም.... ."በል ሂድ...ብሞትም ልክ ነህ...እኔ ስለሞትኩ የልጆችህ ሆድ ምግብ ማለቱን አያቆምም...የራስህን ሆድ እንኳን ፊት ብትነሳ ማለቴ ነው....ህይወት ይቀጥላል..." "እንዳልኩህ ግን ከመሞትህ በፊት ኖረ ኖረ ተብሎ ለመሞት መኖር አለብህ...መኖርህ ውስጥ ነው ስራህ ያለው...መተንፈስ አይደለም...ፈጣሪ ያዘጋጀልህ አንድ ቀን አለ...እሱ ጋር ድረስ...እሱ ጋር ስትደርስ መኖር ይጀምራል...ምናልባት አንድ ቀን ይሆናል እኮ...ግን እስከ አሁን ለታገልከው ሽልማትህ ነውና አመት ያደርግልሀል..." "ይገርማል...ከሰአታት በፊት መታነቂያዋን የገዛች ልጅ አትመስይም...." "እግዚአብሔር ይመስገን..." ✍Shewit https://t.me/shewitdorka
Mostrar todo...
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

👍 35 19🔥 6👏 2❤‍🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
2🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
26👍 4
"ታድለሀል...አዝነህ ቢሆንም ቢያንስ ስሜት አለህ...አመስግን...."....ያልኩት ለግማሽ ሰአት ያሀል ስላስከፋው ነገር ከነገረኝ በኃላ ነበር.... "በደንብ ሰምተሽኛል ግን..."...ግራ እንደተጋባ ፊቱ ላይ ቅልብጭ ብሏል... "አዎ በደንብ...." "እና ደስ ይላል የሆነብኝ ነገር...?...እያሾፍሽ ነው...?"...ድምፁ ላይ ፀብ አለ... "የሆነብህ ነገር ደስ ይላል አላልኩም...የሆነብህ ነገር ግን ስሜት አልባ አላደረገህም...ይሰማሀል...አየህ አዝነሀል...ከማዘንህም በላይ ለሰው ማስረዳት አልደከመህም...'ደህና ነህ ወይ' ላልኩህ ጥያቄ...መልስህ 'ምን ደህንነት አለ ባክሽ'...ብሎ የሚጀምርና ደህንነትህን ያሳጣህን ነገር የሚያብራራ ነው...በግርድፉ 'ደህና ነኝ' ብለህ አላለፍክም...ስሜት አለህ...አልደነዘዝክም...ቢያንስ እንደ እኔ አልበደንክም ነው ያልኩህ...አመስግን"... "ደህና ነሽ...?"...በወረደ ድምፅ ጠየቀኝ...እንደደነገጠ ያስታውቅበታል.... "አዎ በጣም ደህና ነኝ...." "ምንድን ነው የሆንሺው...." "ምንም...."....አተኩሮ አየኝ...አስተያየቱ ፊቴ ላይ የጣለው እቃ ያለ አይነት ነው...አይኔ ላይ ምንም ማንበብ አልቻለም..... "ቅድም ነገርኩህ እኮ..." "ምኑን..." "የሀዘን ስሜት ስለተሰማህ አመስግን ያልኩህ እኔ ስለደነዘዝኩ ነው...ምንም ስሜት ለማንበብ አትሞክር..." "ምን ማለት ነው...." "ያለ ስሜት አይታሰብም...ያልታሰበ አይፃፍም...ያልተፃፈ ደግሞ አይነበብም!.."....ይሄኔ አይኑን ከአይኔ አሸሸ። ✍Shewit https://t.me/shewitdorka
Mostrar todo...
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

👍 27 8🤯 5🔥 3👏 3🤔 1
...ከውሀ ጥም እና ከእናት ጥም ....የእናት እጥረት ስም ወጥቶለታል...?...ቫይታሚን ምን ትሆን...ምን ያሀል ጠቃሚ ንጥረ ነገር ብትሆን ነው እንዲህ ባዶ የምታደርገው... እንጃ ብቻ.... https://t.me/shewitdorka
Mostrar todo...
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

41❤‍🔥 10👍 5🤯 2🤬 1
ለመላው የእስልምና ተከታይ ቤተሰቦቻችን እንኳን እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በኣል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን💛 ያሳለፍነውን 30 ቀናት የረመዳን ፆምችንን እና ኢባዳ አላህ ይቀበለን🤲 ኢድ ሙባረክ❤️     
Mostrar todo...
32👍 4
እንደዚህ ነው አልያም እንደዛ ብላ ማስረዳት ደክሟታል....ደግሞ እንዴትስ ቢሆን ማን በራስ ልክ ራስን ይረዳል....ብቻ ግን እንደ ትናንት ነበር...ቅፅበት ነገር....ብልጭ የሚል ቅፅበት ነገር...ሽውታ...ደረስ መለስ....'የሆነ ጥሩ ጊዜ ነበር....ድሮ መሰለኝ...ብቻ ከልቤ ስቄ ነበረ...መቼ ነበር...ብቻ እንደዛ...'....በውስጧ ታነበንባለች..... አለመቻል በጣም የሚያስጠላ ስሜት ነው....በተለይ ማድረግ እየቻልን ከቁብ የማንቆጥራቸውን ነገሮች...አንዳንዴ መተንፈስም የሚከብድበት ቀን አለ....ነገሩ ከዚህም ይከብዳል...ከህመሙ በላይ መኖር ያማል...."በእርግጥም ጥሩ ጊዜያቶች ነበሩ...ያኔ የሚታይ ህመም ያልነበረበት ጊዜ ነው ጥሩ ጊዜ ወይስ የምፈልገው እጅ እጄን ይዞ የነበረበት....?"...ራሷን ትጠይቃለች....."ጊዜ ሲቆጣጠር እንዴት ያስጠላል...."....ጊዜን ትጠየፋለች.....እግሯ አልታዘዝ ከማለቱ በላይ አልታዘዝ ያለ ነገር አለ....ከእጇ በላይ የምትፈልገው እጅ አለ....ስሜቷ ልክ በአመድ ውስጥ እንደተዳፈነ እሳት ነው....እዛው ተከድኖ ይብሰል የሚባልለት አይነት....እንፋሎቱ እሷኑ እንዳይጨርሳት ስጋቷ ነው.... ከፈጣሪ ጋር ሰላም ናት...ስታማርር ሰምቻት አላውቅም...."እንደፈቀደ..."....ባይ ናት....ራሳችን እንኳን ለራሳችን ከፈጣሪ በላይ እንደማናስብ የገባት ትመስላለች.... ችግሯ ከነዛ ድምፆች ነው...."የጎደለ ነገር አለ..."...ትላለች....ለእኔ ያልተብራሩ እና ጥያቄ የሆኑ ነገሮችም አሉ...ጀምራ የተወቻቸው...."እውነታውን መቀበል አቅቶኝ ነው እንደዚህ የምሆነው"...."ምኑ ነው እውነታው....?"...."ተይው ስንገናኝ እነገርሻለው....."......ተዘጋ።....በእርግጥ ስልጣኑ የፈጣሪ ቢሆንም ከፈጣሪ በታች እሷ ላይ ስልጣን ያለው አንድ ሰው ያለ ይመስለኛል.... ማነው ያ ሰው.....? የገና እለት ነበር ትዝ ይለኛል.... "ዛሬ እኮ የጌታ ልደት ነው የምንፈልገውን እንጠይቅ...."....የሚል መልዕክት ስፅፍ....ነገሩ ቀየር አለና "እሺ የምትመኚልን ነገሪኝ እኔም ልንገርሽ"...የሚል ሆነ.... "ከውጭ ስትገቢ በጉጉት የሚቀበልሽ ቤተሰብ...."....የእሷ ምኞት ነበር...ለእኔ። "አባትሽ አንዴ እጅሽን እንዲይዝሽ እና ይቅርታ ልጄ እንዲልሽ...."....የእኔ ምኞት ነበር ለሷ....ቀጠለች...."ፈጣሪ አንዴ ምን ላድርግልሽ ብሎ ቢጠይቀኝ አባባዬን መልስልኝ ነበር የምለው...የማይሆን ነገር አታሳስቢኝ ተይ...."....ብላ ጨረሰች። ችግሩ ያለው እዚ ጋር ነው ወይ ደሞ እዛ ጋር ለማለት አልደፍርም...ግን የጎደለው ነገር አንድም ይሄ ይመስለኛል.... ጊዜ አንዳንዴ ደግ ነው....አጉሊ መነፅር...እንዳልኳችሁ ነው...የወደቀ ዛፍ ላይ ምሳር ይበዛበት የለ...ዘንበል ካለች በኃላ ምሳር አላጣትም...ዘንበል ማለት አንዳንዴም ጥሩ ነው...ወረድ ስትል ምሳሮቿን አየች...እንክርዳዱን ከስንዴው ለየች....ላለቀሱላት ሁሉ ልቧ መራዱን ተወ..."አንዳንዴም ሰዎች ሲያለቅሱልህ አዝነውልህ ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ይሆናል"....ማለት ጀመረች። እርሷ እንዲህ ናት...መኖር እየደከማትም ቢሆን ያልጨረሰችው ሩጫ እንዳለ ታውቃለች...ያልካሰቻቸው ሰዎች....አዎ በእርሷ መኖር ፈገግ ስለሚሉ ጥርሶች ታስባለች...እግረ መንገዷን ያን ድምፅ ትጠብቃለች....ህልሞቿን ለማሳካት የሚሆን postive energy አላት...አሁን አልፎ ስለ ምትበቀላቸው ሰዎች አታስብም...ብታስብም ከእርሱ በላይ የሆነባት ነገር አለ.... "ሁሉም ነገር ይደርሳል ብቻ አሁን ልዳን"....ትላለች። ልክ ናት....ሁሉም ይደርሳል ብቻ ትዳን። 💙 https://t.me/shewitdorka
Mostrar todo...
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

👍 40🥰 9 3🔥 3🤯 1
ሀበሻ Romance አያውቅም ! "ምንድነው ? ምንድነው ? ምንድነው ግን ? እተነፍሳለኹ ይኽው ኽኽኽኽኡፍፍፍፍ፣እበላለሁ፣እጠጣለሁ፣እቀመጣለሁ፣እነሳለኹ ደህና ነኝ አይደል ? ኸረ አዎ ደህና ነኝ ! ታዲያ ለምንድንነው እኔም እንደ ሰው የማልወደው? ፍቅር የማይዘኝ ? " -ስል ራሴን ጠየቅኹ። ይሄ የተረሳ ሐሳብ የመጣብኝ ሶስት Romance film አከታትዬ ካየኹ በኋላ ነበር።"እኔ ለፍቅር ቦታ የለኝም " የሚለውን የትህቢት መፈክር ካወረድኩ ዘገየው እድሜ አስተምህሮኝ ነው መሠለኝ አኹን በፍቅርም ኾነ የፍቅር አጋር በመያዝ ዙሪያ ያለኝ ሐሳብ ዝምታ ነው።ዛሬ ግን እኔም መወደድ አማረኝ በኾነ ሰው ሐሳብ ውስጥ መንገስ፤የኔ መባል ፈለግኹኝ።መወደድ ብቻም አይደለም የፈለግኹት መውደድም ነው ያማረኝ።ፍቅሬን የምገልፅበት ቃላት እስከማጣ፤እስክኮላተፍ መውደድ ተመኘው።ያለመስፈርት፣ያለሚዛን መውደድ በቃ ውድድድድ በፍቅር መስከር፤በፍቅር መስከን አማረኝ። ይሄ ሁሉ የመጣብኝ ደበረኝ በሚል ተልኳሻ ምክንያት 3 romantic film በማየቴ አይደለምን? (የሰው ልጅ የሚያነበውን፣የሚሰማውንና የሚያየውን ነው የሚሉት እውነት ነው ማለት ነው?) አምሮኝ ብቻ አይቀርም።እኔ ከፈለግኹ ፈለግኹ ነው በዚህም በዛም ብዬ ወደምፈልገው ነገር እሄዳለኹ። ....በአይን ውበቷን አደንቅላት የነበረች አንድ የአክስቴ ልጅ ጓደኛ አለች።መቼም ውብ አይገልፃትም፤ግን ልጅነት አለባት።ይኹን ከብቸኝነት ይሻላል።(ከብቸኝነት ለማምለጥ ብለን ስንት ችግር ውስጥ ገባን?)።አክስቴ ልጅ ጋር ደወልኹ።የተለመደውን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ...አንቺ ያቺ ጓደኛሽን አታጣብሺኝም ? አልኋት Dating App መኾኗ ነው። ስለአንተ ጀማምሬላታለኹ...ትንሽ ጥረት ከጨመርክበት ያንተው ነች። ቃላት ከቸገረኽ ከአማርኛ ፊልም Cathy phrase ውሰድ እሷ አማርኛ ፊልም ብዙ አታይም።ይቅናሽ አባቴ ብላ ስልኳን ሰጠቺኝ። በነገራችን ላይ Dating App ተጠቅሜ አውቃለሁ። ገና በለጋ እድሜዬ፤ፎቶ ላይ በጣም እኩያዬ የምትመስል መልከመልካም ጉብል ቀጠርኩ።እንደ አጋጣሚ የቀጠርኳት (የቀጠርኳቸው) ሴት በቀጠሯችን ቦታ ለ date መጥተው ተቆጥተውኝ ተመለሱ(ልጅ የሚያደርግ filter ተጠቅመው ነበር?እንጃ።) "ምነው ምነው ልጄ ገና ሳታድግ?" ብለው ገሰፁኝ። አስታውሳለሁ እኔ መኾኔን ደጋግመው እንደጠየቁኝ ከዛም ደጋግመው እንዳማተቡ። ሲቆጡኝ። በልቤ እንዲህ እንዳልጎመጎኹም ትዝ ይለኛል "እርሶስ በዚህ እድሜዎ ቤተስኪያን ሊሳለሙ የመጡ መሠልዎ? እናቶትንናላዎ።" ከአክስቴ ልጅ የልጅቷን (የኤዶምን) ስልክ ወሰድኹና መላ social media አጠቃቀሟን መረመርኹ።ዝንባሌዋን አጠናኹ...የ western ባህል ተፅዕኖ የሚንፀባረቅባት ቀለል ያለች ሰው እንደኾነች ከ investigation-ኔ ተረዳኹ።ከዛ ስልክ ልደውልላት ወሰንኹ...ሶሻል ሚዲያ Instagram ላይ ደስተኛ እንደኾነች ስታሳውቅ ጠብቄ ደወልኹ።በጥሩ ሙድ ኾና ላወራት ስለፈለግኹ። ደውዬ የገሊላ ወንድም...ሶፊ ነኝ ስላት ይበልጥ  ቀለል አድርጋ አወራቺኝ። (I think she has already known i was into her.) ...አንድ ሳምንት ካወራን በኋላ ቅዳሜ ቀን ምሳ አንድ ላይ እንብላ ብዬ ቀጠርኋት።..."is it a date ?"ብላ ጠየቀችኝ። እሱ ፀባይሽ ታይቶ የሚወሰን ይኾናል አልኋት። ቅ ዳ ሜ ከስራ እንደወጣኹ ተጣድፌ ወደ ቀጠርኋት ስፍራ ተንደረደርኹ።ቀደም ብላ ደርሳ ካፌ እየጠበቀቺኝ ነበር።በቻልኹት መጠን ለመዘነጥ ሞክሬያለሁ...ካፌው ፊት ለፊት ቆሜ ደወልኹላት።በአይምሮዬ የቀደመ ውበቷን እያስታወስኹ ቆየዋት።ስትመጣ...እንደጠበኹት ተሽቀርቅራለች...ቀይ ቀሚስ...በክፍት ጫማ ደማምቃ ጣ ጣ እያለች ወደኔ መጣች።አቅፌ ሰላም ካልኋት በኋላ እንዳማረባት ነገርኋት።ፈገግ ብላ "አንተም ለመዘነጥ ብዙ የደከምክ ይመስላል " አለች። ምግብ እንድንበላ ወዳሰብኹት ቦታ ተያይዘን ሄድን...ቤቱን ስታየው ወደደችው ቅልል ያለ ቤት፤ጥሩ ምርጫ ነው አለቺኝ። ምግብ ተመግበን ቡና ከጠጣን በኋላ...ቤቱ እዛው እንደ ባር ነገር አለው በረንዳው ላይ ቁጭ ብለን የልባችንን ልናወጋ ቆርጠን የሚጠጣ አዘዝን። እውነተኛ ስሜቴን ለማንም ገልጬ አላውቅም።በሳቅ የተሸፈኑትን ሐዘኔን ማንም አያውቅም።በቀልድ የተዋዛ ቁም ነገረኛነቴን ማንም የሚያስተውል የለም።ፌዘኛ አድርገው የሚስሉኝ ጥቂት ሰዎች አይደሉም።ምን እንደነካኝ ባላውቅም፤ለእርሷ ማንነቴን ገለጥኹላት።መለመላዬን ታየዋት...የሸፈንኹት ነገር እስኪጠፋ ማንነቴን ገላልጬ አሳየኋት።ምን ኾኜ ነው? ...እርሷም አወራቺኝ።ከውበቷ ባሻገር ያለውን ማንነት ተመለከትኹት። በሳል ብትመስልም ልጅነቷ እና ገራገርነቷ ይበልጥ ጎልቶ ይታያል። እድገቷ ላይ ጠባሳ ጥሎ ያለፈውን የቤተሰቧን ችግር በእንባ እየታጠበች አጫወተቺኝ። ቤተሰብ በሀገር በማህበረሰብ በኹለንተና ያለውን ትልቅ ሚና አስገነዘበቺኝ።ጤነኛ ትዳር ሳይኖር ጤነኛ ሀገር ጤነኛ ትውልድ መገንባት እንደማንችል እንዳስተውል አደረገቺኝ። እንዲህ እንዲህ እያወራን ሳይታወቀን ሰዓቱ 12:30 ኾኖ ነበር። አብረን የዋልን አልመስልህ አለኝ በቻልኹና ቀኑን ብገፋው በወደድኹ።1:00 ሰዓት ላይ ሌላ የስራ ቀጠሮ ስለነበረኝ ለመሄድ ልቤ ቆመ። ቢል በፍጥነት እንድታመጣ አስተናጋጇን ነገርኋት።ቢሉ ሲመጣ ደነገጥኹ። ይሄ የምግብና የመጠጥ ሂሳብ ብቻ ነውን? ነው ወይስ እጇን ልትታጠብ ስትወጣ ራቷን take away ለሞተረኛ ወደ ቤቷ ልካለች? መጠርጠሩ አይከፋም። አስተናጋጇ ጠርቼ የተጠቀምነውን ዘርዝሬ ሂሳቡ ልክ መኾኑን አረጋግጬ ካሰብኹት ብር 500 በልጦ ነበር።ለእቁብ ከያዝኹት ብር ላይ ጨምሬ ከፈልኹ።በርግጥ እርሷ ልክፈል ብላ ነበር ፤ ሌላ ጊዜ ትጋብዢኛለሽ አልኋት።የዋጋውን መጋነን ሳልደብቅ ነገርኋት። ከቤቱ ወጣን እርሷን ታክሲ ላስይዝ አንደረደርኋት እኔ ቸኩዬ ልቤ ለመሄድ ቆሞ ነበር።She was trying to be romantic ከእርምጇዬ እየገታች፤ከፊት ለፊቴ መጥታ አይኔን በሚያሰደነግጥ እይታ እያየች...እንዲህ እናደርጋለን አይደል? እንዲያ እናደርጋለን አይደል ? እያለች በውበቷ ይበልጥ ልታማልለኝ ትሞክራለች።እኔ ቸኩያለኹ...ተበሳጨኹ...ምን እንደ ማዥራት መቺ ትዞረኛለች...በጥፊ ላጣጋት እንዴ ? She was just trying to be romantic. እኔ ግን ተበሳጨኹ። ሐበሻ አይደለኹ ? ሐ በ ሻ ደግሞ romance አያውቅም። የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 22/09/2015 ©ሶፊ https://t.me/bestletters
Mostrar todo...
📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

ሶፊ 👉 @umsofi27 enjoy ✌ "I don't write words; i write sentiments." -®Sofi Do what it worth to live..." . . . በካፊያ አልደነግጥም የተዘጋጀውት ለዶፍ ነው። . . #💚💛❤ @sofimemo

😁 52👍 21 6🔥 2👏 1