cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኢትዮ ጌጥ የሬድዮ ፕሮግራም

Gette multimedia

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
198
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Repost from N/a
ታላቅ ዓመታዊ የንግስ በዓል በሰሜን ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ በእንጠራና ደብር ቀበሌ በደብረ ብስራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም ደብረ ብስራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ በእንጠራ ቀበሌ በደብር ጎጥ ይገኛል። ገዳሙ ከመዲናችን አዲስ አበባ 208 ኪ.ሜ ከዞኑ ዋና ከተማ ደብረ ብርሃን 78 ኪ.ሜ እንዲሁም ከወረዳዉ ዋና ከተማ እነዋሪ 13 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ገዳሙ የተመሠረተዉ በ1262 ዓ/ም በታላቁ ፃድቅ በአቡነ ዜና ማርቆስ ሲሆን የገዳሙን ስያሜ ያወጡለት የኢትዮጽያ ቁስጢንጢኒዎስ ይባሉ የነበሩት አፄ ዘርያቆብ ናቸዉ። ገዳሙ ደብረ ብስራት ተብሎ ከመጠራቱ በፊት የሶስት ስሞች ማለትም ናዝሬት፣ ደብረፅዮን እና ኤፍራታ ተብሎ እንደሚጠራ ይነገራል። አፄ ዘርያቆብ በዚህ ገዳም ዉስጥ ለብዙ አመታት ለፀበል እንደቆዩበት እና ፃድቁንም ልጅ እንዲሰጣቸዉ ለምኗቸዉ ነበር። አፄ ዘርያቆብ ካረጁ በኃላ ነበር የ15 አመት ልጅ ያገቡት ከዚያ በኃላም በገዳሙ ዉስጥ እያሉ ሁለት ልጆችን ፃድቁ እንደሰጣቸዉም ይነገራል። አፄ ዘርያቆብ ይህ ገዳም ብስራት የሰማሁበት በመሆኑ ደብረ ብስራት ብለዉ ጠርተዉታል። ገዳሙ ከ800 አመት በላይ በኖሩ እድሜ ጠገብ አፀዶች በመሸፈኑ ለገዳሙ ዉበትና ድምቀት እንዲሁም የመንፈስ እርካታን ይሰጣል። በዚህ ታላቅና ታሪካዊ ገዳም በየአመቱ ታህሳስ 3 የአቡነ ዜና ማርቆስ የእረፍት በዓላቸዉ በድምቀት ስለሚከበር ሁላችሁም የእምነቱ ተከታዮች በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በተጨማሪም ቦታውን እንድትጎበኙ ሲል የሰ/ሸ/ዞ/ባ/ቱ/መምሪያ ጥሪውን ያስተላል።
Mostrar todo...
Repost from Arada FM 95.1
በምዕራብ ጎጃም ዞን በ15ኛዉ ክፍለ ዘመን የተገነባ ቤተ ክርስቲያን በቁፋሮ መገኘቱ ተገለጸ:: በምዕራብ ጎጃም ዞን በሰሜን አቸፈር ወረዳ በፎረሄ ኢየሱስ ቀበሌ 702 ዓመታትን ያስቆጠረ ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለማቋቋም በተደረገ ቁፋሮ መገኘቱ ተነግሯል። መልሶ የሚቋቋመው ቤተ ክርስቲያን በአቡነ ሂሩት አምላክ እንደተመሰረተ የተገለፀ ሲሆን፤ ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ ተብሎ ይታወቃል። የተገኘው ህንፃ ቤተ ክርስቲያን በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተገነባ የሚያረጋግጥ ብዕራና መገኘቱ የተገለፀ ሲሆን፤ በታሪክ የተሰነዱ ማስረጃዎች ከእምነት አባቶች እንደተገኘ ተገልጿል። የቅዱሳን አፅም የያዘ ከኖራ የተሰራ መካነ መቃብር፣ የተለያዩ ጽናፅል፣ ቃጭል እና የመስቀል ስባሪዎች እንደተገኙ የሰሜን አቸፈር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ት ቤት ሀላፊ የሆኑት አማኑኤል ፀሀይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡ የቁፋሮ ሂደቱ አለመጠናቀቁ የተጠቆመ ሲሆን፤ እስካሁን ባለው ሂድት ከኖራ የተሰራ ከ3 ሜትር በላይ ቁመት ያለው ኹለት ቤተ መቅደስ፣ አምስት ሜትር በአምስት ሜትር ስፋት ያለው ቅኔ ማህሌት እና ቅድስት መገኘቱ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም አስር ሜትር በአስር ሜትር ስፋት ያለው በአንድ ቅድስት ኹለት ቤተ መቅደስ በሰሜን እና ደቡብ ጎን ለጎን የሆነ መሠረተ ህንፃ እንደተገኘ ተነግሯል፡፡ የእምነት አባቶች የቤተ ክርስቲያኑን ኹለንተናዊ ታሪክ የሚዳስስ መረጃ በማዘጋጀት ለወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ት ቤት መስጠታቸው ተገልጿል። @Arada_Fm
Mostrar todo...
"ጉጉት "የስዕል ኤግዚቢሽን የሰዓሊ ቤቴል ጌቱ "ጉጉት "የተሰኘ የስዕል ኤግዚቢሽን ነገ እሁድ ህዳር 11 2015 ዓ.ም ከምሽት12 ሰዓት ጀምሮ አትላስ የትራፊክ መብራት አካባቢ በሚገኘው አቶሞስፌር ጋለሪ ይከፈታል። የስዕል ኤግዚቢሽኑ ከህዳር 11 እስከ 18 ይቆያል። https://t.me/EventAddis1 https://t.me/EventAddis1
Mostrar todo...
ከራስህጋ ስትታረቅ ከሁሉምጋ ትስማማለህ! በከፈለኝ ዘለለው [ሐዋዝ] የሰው ልጅ ሕይወቱ ከገዛ ራሱ ጋር ባለው ተስማምቶ የመኖር ብቃቱ ይቆነጃል። ከራሱጋ ያልተጣጣመ ሰው ኑሮውን የጣመ ማድረግ ይቸገራል። በጎ ሰብዕና ከቀና እይታ ይመነጫል። የተዋበ ምልከታ ለሰመረ ማንነት መሰረት ነው። ብዙዎች የብዙ ዝግ በሮቻቸውን መክፈቻ ቁልፍ ከራሳቸው ውጪ ባለ ግዛትና ድንበር ይፈልጉታል። መፈለግ መልካም ቢሆንም የሚፈልጉትን ነገር የተሳሳተ ቦታ መፈለግ ሌላ ትልቅ ስህተት ነው። እውነት ነው በማንኛችንም ሕይወት ውስጥ የበረከቱ ዝግ በሮች ይኖራሉ። ነገር ግን መክፈትን ፈላጊ ካለ የተዘጉ በሮች ሁሉ ይከፈታሉ። ምክንያቱም መክፈቻ አልባ ሆኖ የተበጀ ጋን የለምና። አዎን ያለመክፈቻቸው የተሰሩ ቁልፎች አልነበሩም። አሁንም የሉም። የጋኑ ቁልፍ ጠፍቶብን ካልሆነ በቀር ጋኖች ሁሉ ከነመክፈቻ ቁልፎቻቸው የተመረቱ ናቸው። እናም ጋኖች ሁሉ ቁልፎች የነበራቸው ከሆነ ደግሞ የጋኖቹ ቁልፎች የት ገቡ ብሎ መጠየቅ መሰልጠንን ያሳያል። የሚጠይቅ የጠፋበትን ያገኛል። ያጣውን የሚሻ ሰው ደግሞ ጥሩ ሰብዕናን ፈጥሮ በሀሴት መኖሩን እውን ያደርጋል። ከልብ በሆነ አስተውሎት ስናጤን የልባችንን መሻት ጊዜ ሊያቆያት ቢችል እንጂ ሊያስቀራት አይችልም። የለፋ እንዳጣ አይቀርም። ጥሩ ሰብዕና አታጋይ ትግልና እልህ አስጨራሽ ልፋትን ይጠይቃል። ውጤቱን ለመቃረም በሚኖር ሒደት ውስጥ ደግሞ ውድቀት አይጠፋም። ግና ደግሞ ሁሌ መሽቶ ሲነጋ ከአዲስ ተስፋጋ አብረን እንወለዳለን። ሕይወትን ጣፋጭ የሚያደርጋት ተስፋ አስቆራጭ በሆነ የኑረት ትግል ውስጥ አልፎ ጥሩ ሰብዕና ያለው ሰው ሆኖ መገኘት ነው። በሮቹ ተዘጉ ማለት መንገድ የለም ማለት አይደለም። ቁልፉ ተሰውሮና ጠፍቶብን እንጂ መጀመሪያውኑም የጋኑ ቁልፍ አልነበረም ማለት አይደለም።
Mostrar todo...
Repost from N/a
አንኮበር ደብረ ምህረት ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን የአንኮበር ቅ/ሚካኤል የሚገኝው በሰ/ሸዋ ዞን በአንኮበር ወረዳ በጨፋ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጨፋ ጐጥ ውስጥ ነው፡፡ ይህ የሠው ሠራሽ መስህብ ከወረዳው ዋና ከተማ ጐረቤላ 2.5 ኪ.ሜ በሚሆን ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን በንጉስ ሸዋ ሣህለ ስላሴ በ1817 እንደተቆረቆረ የሚነገር ሲሆን በ184ዐ ንጉስ ሣህለ ስላሴ ከዚህ አለም በሞት ሲለዩም በዚሁ ቤተ ክርስቲያን ነው የተቀበሩት፡፡ መቃብራቸው ከቤተ ክርስቲያኑ በስተምስራቅ የሚገኙ ሲሆን የንጉሱም አጽም በክብር በቤተ መቅደስ ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ በወረዳው ካሉት ታላላቅ አድባራት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ሲሆን የቤተ ክርስቲያኑ አሠራር በተመለከተ በጥንታዊ የድንጋይ ጥርብ ባለ 4 ማእዘን ሬክታንግል የሆኑ ድንጋዮች የተሰራና ወለሉም የአፈር ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አንዳንድ አባቶች እንደሚሉት አፈሩ የመጣው ከእየሩሣሌም እንደሆነ ይነገራል፡፡ የውስጥ ጣራው አወቃቀር የሣር ቤት አወቃቀር አሠራር የተዋቀረ ውብ አሠራር ያለው እና በሮቹ ከመቅደሱ እስከ ቅድስቱ ባለ አንድ እና ባለ ሁለት አምድ የሆኑ እርዘመታቸው እስከ አራት/4/ ሜትር የሆኑ ወርዳቸው እስከ 2 ሜትር ይሆናል፡፡ በሩ በተለይ በሃረጋት እና በአረንጓዴ ቀለም በተፈጥሮ የቀለም ስራ የተዋቡ የአበባ ጌጥ ያለባቸው የቅድስቱ ግድግዳዎች በሙሉ በመንፈሣዊ ስእሎች የተዋቡ የጌጡ ናቸው፡፡ ቤተክርስቲያኑ 3 በር 24 መስኮቶችና 54 የበረንዳ እንጨት እየተባሉ የሚጠሩ አሉት፡፡ በተጨማሪም ጥንታዊ ይዘት ያለው ባለ 5 ደረጃ በረንዳ ያለው ሲሆን ቤተክርስቲያኑ የመንሸራተት አደጋ እንዳይደርስበት ዙሪያውን የመጠበቂያ ግንብ በሁለት ደረጃ ተሰርቶለታል፡፡ ይህኝ ጥንታዊና ታሪካዊ ቤተክርስቲያ በአሁኑ ወቅት የፌደራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በቅርስነት መዝግቦታል፡፡ ይህ ታላቅና ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ያለበት የመሬት አቀማመጥ ለተመልካች ግርምትን በሚፈጥር መልኩ እንደ እራስ ቅል ለብቻው በተቀመጠው አምባ ላይ ከቤተ ክርስቲያኑ ውጪ/ሌላ/ ግንባታን የማያስተናግድ አስደናቂ የተፈጥሮን ውብነት የሚያመለክት ቦታ መሰራቱ/መቆርቆሩ/ ነው፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን 197 ካህናት እንደነበሩት ይናገራል፡፡ እንዲሁም ቤተ-ክርቲያኑ 3 ጊዜ እንደገና ፈርሶ እንደተሠራ የሚነገር ሲሆን አሁን ባለው ይዞታ ማለትም ቆርቆሮ እንዲለብስ ያስደረጉት ንግስት ዘውዲቱ በ192ዐ ዓ/ም እንደሆነ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ይህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ከሠው ሠራሸ መስህብነት ወይም ቅርስነት በተጨማሪ ያለበት የመሬት አቀማመጥና ዙሪያውን ከበውት የሚገኙ እድሜ ጠገብ የሀበሻ ጥድ ወይራ እና ሌሎች የተፈጥሮ ዛፎች መሃል መገኘቱ ውበቱ የተፈጥሮን አስገራሚ ውበት ማሳያ ናቸው፡፡
Mostrar todo...
በገበያ ላይ 48 LOW POWER ROBERT GRRINE ኃይልን ለሚፈልጉ፣ ኃይል ለሚመለከቱ ወይም እራሳቸውን በኃይል ለማስታጠቅ ለሚፈልጉ በጣም የሚጠቅም መጽሐፍ... ኃይል የመጨረሻ ግብህ ከሆነ። ይህ የሚያስፈልግህ መጽሐፍ ነው "(ታይም መጽሔት) ሥነ ምግባራዊ፣ ተንኮለኛ፣ ጨካኝ እና አስተማሪ፣ ይህ የመብሳት ሥራ የሦስት ሺሕ ዓመታትን የሥልጣን ታሪክ ወደ አርባ ስምንት በደንብ ወደ ቀደሙ ሕጎች ያሸጋግራል፣ በይዘቱ ውስጥ እንዳለ በንድፍ ውስጥ ትኩረትን የሚስብ ቢሆንም ይህ ደፋር ጥራዝ ይዘረዝራል። የማኪያቬሊ፣ ሱን-ትዙ፣ ካርል ቮን ክላውስዊትዝ እና ሌሎች ታላላቅ አሳቢዎችን ፍልስፍና በማዋሐድ የሥልጣን ሕጎች ባልተለወጠ ምንነታቸው። አንዳንድ ሕጎች ጥንቃቄን ይጠይቃሉ። ከጌታው ፈጽሞ አይበልጡም አንዳንዱ ድብቅነት ሐሳብህን ደብቅ ለዳንዶቹ አጠቃላይ ምሕረትን አለማድረግ ጠላትህን ሙሉ በሙሉ ጨፍልቀው በንግሥት ኤልዛቤት ቀዳማዊ ፣ ሄንሪ ኪሴንገር ፣ ፒቲ ባርነም እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች በሥልጣን ላይ ያገለገሉ - ወይም በሥልጣን የተጎሳቆሉ ሥልቶች በምሳሌነት ሲገለጹ እነዚህ ሕጎች በእውነተኛ ሕይወት ውስጥ ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ አፕሊኬሽኖች አሏቸው ። የመጨረሻ ቁጥጥርን በማግኘት ፣ በመመልከት ወይም በመከላከል ላይ። Eneho books - እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። 4ኪሎ ምኒልክ ት/ቤት ፊት ለፊት ከሮሚና ዝቅ ብሎ። ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks
Mostrar todo...
በገበያ ላይ አንገረ ፈላስፋ ( የፈላስፎች አነጋገር) “ወንዞች ወደ ውቅያኖስ የሚያደርጉት ግሥጋሴ፣ እንደ ሰው ለስህተት ፈጣን አይደለም?'' ክፋትን የመሥራት ዕድል በቀን መቶ ጊዜ ነው፣ ነገር ግን በዓመት ኣንድ ጊዜ መልካም ነገርን የማድረግ ዕድል አለን፡፡ የጋራ አስተሳሰብ ውስጥ ብልህነት ብቃት ነው።'' “አምላክ ባይኖር ኖሮ እርሱን መፍጠር አስፈላጊ በሆነ ነበር።" “መግደል ክልክል ነው፤ ስለዚህም ነፍሰ ገዳዮች ኹሉ በብዛት ካልገደሉና ጥሩንባ ሲነፋ ይቀጣሉ። “ብሩህ አመለካከት ማለት፣ ሲከፋን ኹሎም ነገር ለመልካም ነው” ብሎ የመናገር እብደት ነው፡፡'' “ሰው በሚፈልገው ጊዜ ነፃ ነው፣ ሰው ራሱን የሚያስረው ራሱ ነው፡፡ “ከሌሎች ልምድ ለመማር ራሱን ያዘጋጀ ምን ያህል ብልህ ሰው አለ? “ታላላቅ ምሥጢራዊ የቃላት አጠቃቀም ማብዛት አሳባችንን መደበቅ ነው።'' “በጣም አስተማማኝ መንገድ በሕሊና ምሪት ላይ ምንም ነገር ማድረግ ነው፡፡ በዚኽ ምሥጢር ሕይወትን መደሰት እንችላለን፣ እናም ሞትን አንፈራም፡፡'' ብሏል። “ለራስህ አስብ እና ሌሎችም እንዲሁ በማድረግ በራሳቸው ልዩ መብት እንዲደሰቱ ፍቀድላቸው።' “ከእያንዳንዱ የተሳካለት ሰው በስተጀርባ አንድ የተገረመ አማች ቆሟል።" “ደስታ ከሌለ ትጋት አለ ማለት ነው። “ፍቅር ነው፣ የሰው ዘር ምቾት፣ የአጽናፈ ሰማይ ጠባቂ፣ የፍጥረት ኹሉ ነፍስ፣ ፍቅር፣ ርኅሩኅ ፍቅር፡፡" “ፍልስፍና የሰው ልጅ ስለ ኹሉም ነገር የማወቅ ጉጉት መግለጫና የዓለምን ስሜት በአዕምሮ ውስጥ ለመፍጠር የሚደረግ ሙከራ ነው፡፡ “አይስክሬም በጣም ጥሩ ነው፤ እርሱን መሳስ ሕገ ወጥ አይደለም፡፡ “እግዚአብሔር በአምሳሉ ከፈጠረን እኛ እርሱን የምንመስልበት ብዙ ነገር አለን፡፡'' Eneho books - እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። 4ኪሎ ምኒልክ ት/ቤት ፊት ከሮሚና ዝቅ ብሎ። ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks
Mostrar todo...
Eneho Books እነሆ መጻሕፍት

እነሆ መጻሕፍት | ዘወትር በልዮ ቅናሽ 0912735000 / 0905222224 ➍ኪሎ ምኒሊክ ት/ቤት ፊት ለፊት ሮሚና ዝቅ ብሎ