cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Event Addis/ሁነት አዲስ

ለአስተያየት : @Tmanaye https://eventaddis.com (Website)

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
6 589
Suscriptores
-524 horas
+1287 días
+68130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
የ13ኛው የ"ለዛ ሽልማት" ሥርሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል በሸገር 102.1 በሚተላለፍ "ለዛ" የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጅነት የሚከናወነው "ለዛ ሽልማት"ለአስራ ሶስተኛ ጊዜ ዛሬ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም አመሸሻ ላይ በሒልተን ሆቴል ውስጥ ይከናወናል። ከሐምሌ 1 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 2015 ዓ.ም ድረስ በተሰሩ የጥበብ ስራዎች የታጩ የጥበብ ባለሞያዎች በ12 ዘርፎች ይሸለማሉ። 1.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ፊልም 2.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ 3.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ተዋናይት 4.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም 5.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይ 6.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይት 7.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ አልበም 8.የአልያስ መልካ ሽልማት (ምርጥ አዲስ ድምጻዊ) 9.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዘፈን 10.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ዘፈን 11.የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ 12.የለዛ ሽልማት የህይወት ዘመን ዘርፍ የለዛ ሽልማት በቀጥታ ስርጭት በዓባይ ቴሌቪዥን እንዲሁም በሁሉም የዓባይ ቲቪ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ( በፌስቡክ፣ ዩትዩብ፣ ቲክቶክ፣ ኢንስታግራም) ይሰራጫል ተብሏል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
በድምጻዊት ህሩት በቀል ላይ ያተኮረ "አንፀባራቂዋ ኮኮብ" የተሰኘ መጽሐፍ ቀጣይ ሳምንት ለንባብ ይበቃል በዐብይ ፈቅይበሉ የተዘጋጅውና በድምጻዊት ሒሩት በቀለ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነው "አንፀባራቂዋ ኮኮብ" የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 19 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ9:00 ጀምሮ የአንደኛ ዓመት መታሰቢያዋ በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በሚታሰብበት ቀን ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። በዕለቱ የፌድራል ፖሊስ ማርሽ ባንድን ጨምሮ የፌዴራል ፖሊስ ኦኬስትራ እና የዳዊት ፅጌ ባንድ እንዲሁም የሒሩት በቀለን ስራዎች ከሚያቀነቅኑት ታዋቂ ድምፃዊያን ጋር በመሆን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል። መፅሐፉ ተፅፎ እስኪጠናቅ ድረስ 2.5 ሚልዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት የመፅሐፉ ደራሲ ዐቢይ ፈቅይበሉ ገልጿል። ከመጽሐፉም የሚገኘው ገቢ በስሟ ለሚቋቋመው በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን ምስረታ የሚውል እንደሆነም ተገልጿል። ግንቦት 4 2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ዝነኛዋ የፖሊስ ኦኬስትራ የቀድሞ ድምፃዊት በኋላም ዘማሪት ሒሩት በቀለ በሙያዋ ለሀገሯ ያበረከተችውን ጉልህ አስተዋፅኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዚህ መታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገራችን የኪነጥበብ ባለሞያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የአርቲስቷ ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
"ብርሃን ኮንሰርት" ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ ገቢው ለሰበታ መርሐ የዓይነስውራን ት/ቤት እንዲውል የተዘጋጀውና ነገ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በግዮን ሆቴል እንደሚካሄድ ሲገለፅ የቆየው"ብርሃን ኮንሰርት" ላልተወሰነ ጊዜ እንደተራዘመ ከቅርብ ምንጮች ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ላይ ድምጻዊያኑ አብዱ ኪያር ፣ ቀመር የሱፍ ፣ ይርዳው ጤና ፣ባልከው አለሙ፣ ኃይማኖት ግርማና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎችን እንደሚያቀረቡ ሲገለጽ ቆይቷል። ኮንሰርቱ በምን ምክያንት እንደተራዘመ አዘጋጆቹ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጡታል ተብሏል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን አልበም ዛሬ ይለቀቃል የሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን ቀደም ሲል ‘ደጋጎቹ‘ በሚል ርዕስ ለአድማጮች ያደረሰውና በድጋሜ ተሰርቶ "ከሁሉ የላቀው ደግ" የሚል ስያሜ የተሰጠው የኢትዮ ጃዝ አልበም ዛሬ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል ይለቀቃል። የጆርጋ መስፍን"ከሁሉ የላቀው ደግ" አልበም ከዛሬ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚካሄደው "አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል" ላይ በመክፈቻው ዕለት በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ ይመረቃል ተብሏል። በዛሬው ዝግጅት ላይ የሙዚቃ ሸክላው ለሽያጭ የሚቀረብ ሲሆን ሙዚቀኛውም የሙዚቃ ስራውን እንደሚያቀርብ ተገልጿል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
"የሁለት ጌቶች አሽከር" ተውኔት ዛሬ ይሰናበታል በካርሎ ጎልዶኒ "The servant of two Masters" በሚል የተጻፈውና ወደ አማርኛ"የሁለት ጌቶች አሽከር" በሚል ርዕስ በተስፋዬ ገ/ማርያም የተተረጎመ ተውኔት ዛሬ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ከመድረክ ይሰናበታል። በተውኔቱ ላይ ሚኪ ተስፋዬ ፣ እታፈራው መብራቱ ፣ሔኖክ ዘርዓብሩክ ፣ሳምራዊት ከበደ፣እንዳለ ብርሃኑና ሌሎችም ተሳትፈዋል። ተውኔቱ ከጥቅምት 9 2016 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሲመደረክ እንደቆየ ይታወሳል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የሳምንቱን የሥነጽሑፍ ውይይቶች በአጭሩ 📍በዛጎል መጻሕፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጽሐፍ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይካሄዳል። በዚህ ሳምንት በገጣሚ እና ደራሲ ታገል ሰይፉ "ዝንቡላ እና ካሮት"በተሰኘው መጽሐፉ ላይ  ውይይት ይካሄዳል።የዕለቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው። ይህ መርሐግብር ቅዳሜ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 10:30 ይካሄዳል። 📍በዘርዓያዕቆብ የፍልስፍና ት/ቤት በየሳምንቱ የሚዘጋጀው የሀሳብ ውይይት በዚህም ሳምንት "አዲስ አፍላጦናዊነት በቅዱስ ኦገስቲን ኑዛዜ" የተሰኘ ርዕስ መርጧል ይህም ውይይት  ቅዳሜ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ 5 ኪሎ በሚገኘው አፄ ናኦድ ት/ቤት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።"አዲስ አፍላጦናዊነት በቅዱስ ኦገስቲን ኑዛዜ"በሚል ርዕስ በዘካርያስ ደበበ መነሻ ሀሳብ ይቀርባል ተብሏል። 📍የብራና ጁፒተር የንባብ ቡድን የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም በዶ/ር መላኩ አዳል "ለሉሲ ሀገር ሰዎች" መጽሐፍ ላይ ውይይት ያካሄዳል። ይህ ውይይት ከ9:45 እስከ 12:00 ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ውስጥ ይካሄዳል። 📍 "አውደ ፋጎስ" 37ኛው ዙር የሀሳብ ውይይት የፊታችን እሁድ ግንቦት 18 2016 ዓ.ም በወመዘክር አዳራሽ ይካሄዳል።በዚህኛው ዙር "አደባባያችን እንደገና ሲብሰለሰል"በሚል ርዕሰ ጉዳይ በሚዲያ እና ኮምኒኬሽን ባለሞያዋ ነዋል አቡበከር መነሻ ሀሳብ ይቀርባል።ውይይቱ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ይካሄዳል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የሳምንቱ የኪነጥበብ ዝግጅቶች ጥቆማ 📍"ግጥም ሲጥም "ለሁሉም ክፍት የሆነ የኪነጥበብ  መድረክ ነገ አርብ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ገርጂ በሚገኘው ደስክ አዲስ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል። 📍"ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ መድረክ" የፊታችን እሁድ ግንቦት 18 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ መገናኛ ዋኣች ሕንፃ ላይ በሚገኘው "ጣዕም ባህላዊ ምግብ ቤት" ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል። የEventAddis/ሁነት አዲስ ማህበራዊ ገፆቻችን: Telegram:https://t.me/EventAddis1 Website: https://eventaddis.com Facebook:https://facebook.com/groups/2009372275938661/
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የሳምንቱ የኪነጥበብ ዝግጅቶች ጥቆማ 📍"ግጥም ሲጥም "ለሁሉም ክፍት የሆነ የኪነጥበብ  መድረክ ነገ አርብ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ገርጂ በሚገኘው ደስክ አዲስ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል። 📍"ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ መድረክ" የፊታችን እሁድ ግንቦት 18 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ መገናኛ ዋኣች ሕንፃ ላይ በሚገኘው "ጣዕም ባህላዊ ምግብ ቤት" ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል። የEventAddis/ሁነት አዲስ ማህበራዊ ገፆቻችን: Telegram:https://t.me/EventAddis1 Website: https://eventaddis.com Facebook:https://facebook.com/groups/2009372275938661/
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ታሰረ የ"እብድት በህብረት" የአንድ ሰው ቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ እንደታሠረ ከቅርብ ምንጮች ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል። የቴአትሩ አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በፖሊስ" ትፈልጋለህ" ተብሎ እንደተወሰደ እና በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል። ከወራት በፊትም "እብድት በህብረት" ቴአትርን ለማሳየት ወደ እስራኤል ሀገር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ የነበረውን አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙን ከአዲስ አበባ ኤርፖርት "ትፈልጋለህ" በሚል እንደወሰዱት እና እስካሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወሳል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ታሰረ የ"እብድት በህብረት" የአንድ ሰው ቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ እንደታሠረ ከቅርብ ምንጮች ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል። የቴአትሩ አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በፖሊስ" ትፈልጋለህ" ተብሎ እንደተወሰደ እና በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል። ከወራት በፊትም "እብድት በህብረት" ቴአትርን ለማሳየት ወደ እስራኤል ሀገር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ የነበረውን አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙን ከአዲስ አበባ ኤርፖርት "ትፈልጋለህ" በሚል እንደወሰዱት እስካሁንም በእስር ላይ እንደሚገኘን ይታወሳል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Mostrar todo...