ህብረ ቀለማት
Ir al canal en Telegram
Contact 👉 @Natiaba ምርጥ ግጥሞችን፣ አጫጭር ታሪኮችን፣ የተለያዩ ልቦለዶችን፣ አነቃቂ መልዕክቶችን፣ አስተማሪና አዝናኝ ፁፎችን፣ ከፈለጉ አሁኑኑ ይቀላቀሉን። ህብረ-ቀለማት የሁሉ ድምቀት ናትናኤል አባይነህ 👑
Mostrar más1 730
Suscriptores
+224 horas
-87 días
+530 días
Archivo de publicaciones
1 730
ውሸታም አይደለሁም።
እውነቴን ነው ትቼ ነበር ሁሉን ነገር፣ ፍቅርን ረግሜ ብቻኝነትን አፍቅሬ ነበር። ከዛ እሷ ወጣች...
ከተቃራኒ ፆታ ጋር ላልቀራረብ ምዬ፣ በተቃራኒ መንገድ እየሄድኩ ነበር። ከዛ እሷ መጣች...
ሁሉም እንስቶች ብልጣብልጥነት የሚያጠቃቸው፣ ራሳቸውን ብቻ የሚያስቀድሙ ምቾታቸውን የሚከተሉ፣ ፍቅር የማይገባቸው ሞኝ ፍጥረቶች ናቸው ብዬ ነበር። ከዛ እሷ መጣች...
እሷ መጣችና ውሸታም አደረገችኝ። ሁሉንም እንዳድስ ጀመርኩ። ማላዬን ሻርኩት፣ እሷኑ ላያት እጅግ በጣም ወደድኩ፣ አብሬያት መሆን ፈለኩ። እንስቶች አስተዋይ የዋህ ፍጠረቶች ናቸው ብዬ ደመደምኩ።
ግን ሀሳቤን ቀየርኩ እንጂ አልዋሸሁም።
ውሸታም አይደለሁም።
@getmnaleloch
1 730
ህክምና ሳይንስ ግን ምን አይነት ውስብስብ ትምህርት ነው?
በቃ ጨረስኩኝ ተገላገልኩኝ ስትል፣ የሙያ ፈቃድ ፈተና የሚባል ጣጣ ቆሞ ይጠብቅሃል🙄
ቆይ እስካሁን የተፈተንኩት ፈቃድ ለመስጠት አይበቃም?🙄🙄
@getmnaleloch
1 730
በህይወታችን ከማንም በላይ የውስጥ ስሜቶቻችንን ተረድተወትና ልባችንን ሰርቀው የሚያዘግሙት አልፎ ሂያጅ መንገደኞች ይሆናሉ።
ያአንዳንዶቹን ስም በውል ራሱ ላናውቅ እንችላለን። ከገደል ጫፍ ይመልሱናል፣ ከተስፋ መቁረጥ ይታደጉናል፣ ከከረመ ሀዘን ያጽናኑናል። ከወደቅንበት ያነሱናል። ሸክማችንን ይጋሩናል። ከየት መጡ ሳንል የማይነጋ በሚመስለው ለሊት ይደርሱልናል።
እንደተወርዋሪ ኮከብ በህይወታችን ሰማይ ላይ ድንገት ተከስተው ይከስማሉ። ግን አንረሳቸውም። የብርሃናቸው ትውስታ አይጠፋብንም።
❤
@getmnaleloch
1 730
💗💗ሁሌም ወድሻለው❤️❤️
አንቺን ብቻ እያለኝ የሚመታው ልቤ
ተቆጣጥረሽ ሳለሽ መላውን ሀሳቤ
ካንቺ ሆኖ ቀልቤ
አካል ሰውነቴ ታዞ ተገዝቶልሽ
አፌ ብቻ አልቻለም ቃላትን አውጥቶ
የውስጤን ሊነግርሽ::
:
:
ስሚኝ ይኸውልሽ
መልዕክቴን ልኬልሽ ስለያዘኝ ፍቅር
ፊትለፊትሽ ማውራት ከብዶኝ ብደናበር
ድምፄን ከፍ አርጌ ቃላት ባልደረድር
ባካል ስታገኚኝ
ሳላወራሽ ባልፍሽ ስለፃፍኩት ጉዳይ
በጆሮሽ እንድትሰሚኝ
ፈርቼ ነው አውነት ባክሽ ይቅር በይኝ
:
:
በዙሪያዬ ካሉት ወድሀለው ባዩ
ጠያቂው ቢበዛም
እኔ ሌላ ሴትን በጭራሽ አልሻም
አንቺን ለዘላለም በፍፁም አረሳም
ሁሌም ወድሻለው
እስከመጨረሻው ሳፈቅርሽ ኖራለው::
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
✍️ #BEGITIMENAWGA
@getmnaleloch
1 730
ዛሬ ሀምሌ አንድ መሆኑን ያወኩት ቅድም ጀሌስ ሲደውለልኝ ነበር።
ሃሎ ናቲ
ወዬ ጃ
አታከብርም እንዴ ቀኑን?
ዛሬ ደግሞ የምን በዓል ነው?
ረሳሃው እንደ? ሥራአጥ የሆንንበት የመጀመሪያው ሃምሌ ባስመለከተ ኬክ ተደፍቶ ልቆርስ ነው😑
አንተ ምንድነው ይሄን ያህል ቸግሮሃል እንዴ፣ እኔ እንኳ የሥራ ማስታውቂያ ቼክ ማድረግ ሁላ አልጀመርኩም፣ በዛ ላይ ሥራም አላጣሁም እዛው እበድ...ብዬ ስልኬን ጥርቅም😎
***
ዳሩ ግን ልቤ እንዲህ ይላል፣ ተማር ያለመሆን ጉዞ የሚጀመርበት የመጀመሪያውን ሃምሌ እንኳ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ጓዶች🥰
✍Natman Ab@getmnaleloch
1 730
በቀን 24 ሰዓት
በሳምንት 7 ቀን
በአመት 366 ቀን
ሳላቋርጥ እወድሻለሁ🥰
የሚል መልዕክት ልልክላት ካዘጋጀሁ በኃላ ሙድ እንደምትይዝብኝ አሰብኩና፣ ደለትኩ።
ለነገሩ እዚህም ቢሆን ማየቷ አይቀርም❤
***
ደህና ዋሉልኛ🤗
@getmnaleloch
1 730
የሆነ ቀልድ ልጽፍላችሁ ፈልጌ እንደማያስቃችሁ ሳስብ ሙዳችሁ እንዳይበላሽ አልኩና ተውኩኝ።
ወደዋናው ምርቃቴ ስገባ...
እንደግብፅ በድል ጀምራችሁ በሽንፈት ከማጠናቀቅ ይሰውራችሁ😑
እናም ደህና ዕደሩልኝ🥰
@getmnaleloch
1 730
Transition period (የሽግግር ግዜ) 🥰
ተማሪ ከመሆን ወደአለመሆን የምንቀየርበት
ላይብረሪ መሆን ቀርቶ የፖርቹጋልን ጨዋታ የምንመለከትበት
እንቅልፍ ያለገደብ ህልም ያለከልካይ የምናጣጥምበት
ይሄ የሽግግር ግዜ እንዴት የተባረከ ነው😁😑
ድል Portugal 🥰
@getmnaleloch
1 730
እውነትኛ ፍቅር ውሎህን ስለቀየርክ አይተውህም...
ትክክለኛው ናፍቆት በሰው ስለተከበብክ እንዲሁ አይለቅህም...
ምንም ይሁን ምን በትውስታ ሰርጾ ይኖራል!
ይሄው እኔም እስከዛሬ እወዳታለሁ❤
***
መልካም ሳምንት🥰
@getmnaleloch
1 730
ጓደኞቼ...
መናኻሪያ ትኬት ቆርጬ ቻው ሊሉኝ እዳቀፉኝ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ። ውሰጤ ልለያቸው እንደሆነ በቅርብ በአካል ቶሎ እንደማንገናኝ ሲነግረኝ ሆድ ባሰኝ። መኪና ውስጥ በያዝኩት ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ልረጋጋ ብሞክርም እንባዬ ትክ ትክ እያለ ይወርዳል። አንድት እንስት አጠገቤ ቁጭ ስትል፤ የሰው ቦታ ነው እማ አልኳት እንባዬን እዳታይ አቀርቅረ....ረጋ ብላ "አይ ሰው ሊሸኝ ነው"እነሳለሁ አለችና ቀጥላ "ለምንድ ነው የምታለቅሰው?" ስትለኝ "አይ ጓደኞቼ ስለተለዩኝ ነው"መልሳ "ከየት ወዴት እየሄድክ ነው?" ፤ "ከሶዶ አርባምንጭ እየሄድኩ ነው።"አልኳት።ታዲያ ምንድ ነው ሚያስለቅስህ፤ እዚህ ቅርብ ሆነህ፤ በህይወት ያለ ሰው የትም ቢሆን ይገነኛል አታልቅስ ብላ ወረደች።
ያሳለፍነውን ለማያውቅ ሰው ዝም በል አታልቅስ ማለት ቀላል ነው። ምክንያት በምን መልኩ አራት አመት ሙሉ እዳሳለፍን ካልኖሩት አይረዱም። አይፈረድባቸውም።
እውነተኛ ቤተሰብና ወንድማማቾች ነበርን። አንድ አንሶላ ለብሰን አንድ ለይ አድረን እናውቃለን። አንዱ አንዱን ንብረት እንደ ግል እቃው ይጠቀማል። ኪስህ ውስጥ አንድም ብር እንኳ ሳይኖር በልተህ፣ ጠጥተ ትመጣለህ። ካለክ ብቻ ነው የምትከፍለው።
ታዲያ እንዲህ ለአመታት ከኖረከው ሰው ድንገት ገና ጥሩ ጊዜ አሳልፋለሁ እያልክ ተለይትህ እንደቀልድ ቻው ስትልና ስትባል እንዴት ነው ሆድ ማይብሰው? እንዴት ነው ማታለቅሰው?
በዚህም መንገድ ቢሆን ሰሜትን ልግለጽ ብዬ ነው የጻፍኩት። ለሲኦሲ ፈተና ዳግም የምንገናኝ ይሆናል ውዶቼ። ስለተረደችሁን አመሰግናለሁ!
እወዳችኋለሁ!❤
✍Firew Tesfaye (Abiti Charles)
እኛም እንወድሃለን🥰
@getmnaleloch
1 730
እጅግ በጣም የምወዳቸውን ለተከታታይ አመታት አብሮኝ የኖሩትን፣ የህይወት ዘመን ወሳኝ ክፍለጊዜ ቤተሰቤ የነበሩትን የዶርም ጓደኞቼን እየተሰናበትኳቸው ነው።
እንዲህ ሆድ ይብሰኛል ብዬ አስቤ ባላውቅም፣ እንደመለያየት ከባድ ነገር የለምና ዓይኔ እንባ አቅሯል።
ሁሉም ወደየሀገሩ ይሳፈራል፣ አድስ አከባቢ ገብቶ፣ አድስ ዕቅድ አላማ ይዞ የየራሱን ህልም ለማሳካት ይሯሯጣል።
በተለይ በተለይ እንደኛ ለተከታታይ አንድ ዶርም የኖረ፣ ሙዱ የሚገም ተማሪ አንዱ አንዱን ጥሎ እስከመጨረሻው ሲሰናበት የምር ያማል።
ዳግም እንደማገኛቸው ተስፋ ባደርግም... ከዚህ በኃላ በዚህ መንፈስ አንገናኝም።
ውድ የዶርም የክላስ ጓደኞቼ እጅግ እንደምወዳችሁ መቼም እንዳትረሱኝ። ይሄ ስሜት የሚገባው ጨርሶ ለሚወጣ ተማሪ ብቻ ነውና ሌሎች አታፈዙ...
Who care's forever ❤
✍Natman Ab@getmnaleloch
