ህብረ ቀለማት
前往频道在 Telegram
Contact 👉 @Natiaba ምርጥ ግጥሞችን፣ አጫጭር ታሪኮችን፣ የተለያዩ ልቦለዶችን፣ አነቃቂ መልዕክቶችን፣ አስተማሪና አዝናኝ ፁፎችን፣ ከፈለጉ አሁኑኑ ይቀላቀሉን። ህብረ-ቀለማት የሁሉ ድምቀት ናትናኤል አባይነህ 👑
显示更多1 728
订阅者
无数据24 小时
+117 天
+1330 天
帖子存档
1 728
እግዚአብሔር ይመስገን በቀንም በማታም ሰላማችን የተጠበቀ፣ ሁከት አልባ አካባቢያችን የረጋ ነው...!
እንደተለመደው ሰላም ዕደሩልኝ😍
@getmnaleloch
1 728
ልቤ እንደመረበሽ አለ እንደመናፈቅ
ከፊቴ ላይ ሳጣሽ ሁልግዜ መጨነቅ
ሁሉን ነገር ችቼ ይቅርታ ልጠይቅ
አስታራቂ የለም እኛው እንታረቅ
***
ማውራት እየፈለጋችሁ የተኮራረፋችሁ በዚህ ታረቁ🤲
@getmnaleloch
1 728
ሰዎች መሰደዳቸውን የፍቅራቸውን ጥግ ለመግለጽ እኖርልሻለሁ ወይም እኖርልሃለሁ ሳይሆን እሞትልሻለሁ ወይ እሞትልሻለሁ ሲሉ ብዙ ግዜ እሰማለሁ።
ለምንድ ነው እኖርልሃለሁ የማይሉት? ለመሆኑ መኖር በህይወት ውስጥ የሚከሰቱ ውጣውረዶችን አብሮ የመጋፈጥ risk፡ ሌላም ሌላም ዋጋ አለው?
እሞትልሃለሁ ማለት ቀላል ነው። ምክንያቱም መሞት የአንድ ግዜ ክስተት ነው። በአንድ ቅጽበት ተሰውቶ የመጨረስ አይነት ስሜታዊ ድራማ አለው። ካልተገባ ስሜታውነት unrealistic expectation የሚመጣ የቃላት ጋጋት ነው። እኖርልሃለሁ ማለት ግን ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፣ ከአንድ ግዜ ስሜታዊ የሞት ቃል በላይ በየቀኑ አብሮ መጋፈጥ ማለት ነው።
ኑሮውን የባህሪ መጋጨትን ስሜትን እና የህይወት እውነታዎችን በየቀኑ አብሮ የመጋፈጥ risk ነው። ይሄ አንድ ጀንበር የሚያልቅ ሳይሆን ዕድሜ ልክ በተማኝነትና በሃላፍነት የሚከፈል ትልቅ መሥዋዕት ነው።
እናመ እኖርልሻለሁ❤
@getmnaleloch
1 728
ከድህነት የምትላቀቁት ገቢያችሁን በመጨመር እንጂ ወጪያችሁን በመቀነስ አይደለም... በዛሬው ዕለት ወጪ አላወጣም እያላችሁ ከምትነቁ የሆነ ገቢ ሳላገኝ አልውልም ማለት ልመዱ😃🥰
@getmnaleloch
1 728
ከስንት ደቂቃ በኃላ እንደሆነ ከተዘረረበት ነቅቶ ደወለልኝ🤕
ሃሎ ናቲ
ወዬ
ሁለት ጥርሴ ወልቋል
ምን ሆነህ ነው?
አንዷ መታችኝ
ለምን
ታርኩን ማጫወት ጀመረ...
ይሄውልህ ናቲ... (እያለቀሰ ቀጠለ...
አስር የለከፋ ዜዲዮች የሚል ቪዲዮ ከዩቲዩብ አውርጄ መጣሁና፣ 4 ጊዜ ደጋግሜ ካየሁ በኃላ በነጋታው መንገድ ዳር ቁጭ ብዬ ጀመርኩ...
እሺ ቀጥል
አንቺ ልጅ አልኳት
(ዝም አለች)
እያወራ ያለው እኮ ሰው ነው
(አሁንም ዝም)
ከዛ በጣም ተናደድኩና ጮክ ብዬ...
(እናት እንዴት አባቱ እንዳስጠላብሽ አታውቂም፣ አይኖቼ አንቺን በማየታቸው ሁሌም እንደተጸጸቱ ይኖራሉ) ... እንዳልኩ በቅጽበት ዘላ ተመለሰችና በለስላሳ ቡጥ ዘረረችኝ
ከዛስ
ይሄው እንግዲህ እንደነቃሁ ደወልኩልህ🥺
ደስ ይላል አይዞህ ለማንኛውም... ብዬ ስልኬን ጥርቅም😎😁
***
ለከፋም በተሰጦ እንጂ፣ በጥረት አይሆንምና አንዳንድ ሰዎች አድቡ😏🙄
(ከExit በፊት ካጋጠመኝ ለህብረ ቀለማት በሚመች መልኩ የቀረበ😁
***
ብቻ ደህና ዕደሩልኝ🤩
@getmnaleloch
1 728
እግዚአብሔር ይመስገን ደስ በሚል መንገድ ፈተናውን ሰርተን ወደግቢያችን ተመልሰናል። የቴክኒክ ችግር ያጋጠማቸው ተማሪዎች ቢኖሩም፣ በስተመጨረሻ በተቻለ መጠን በጥሩ አጠናቅቀናል።
እናም ደግሞ ማለት ነው...
በቀልድም በቁም ነገርም ሳወራ ኮንፊደንስ እየሆናችሁኝ የነበራችሁ፣ inbox ስገባ መዓት ቴክስት አይቼ እስኪደመም good luck ያላችሁኝ፣ በተለይ በተለይ "❤"... የምሬን ነው የምላችሁ የእናንተ አብሮነት በስራዬ ትልቅ ዋጋ ነበረውና ከልብ አመሰግናችኋለሁ🙏
ቀሪውን ውጤት ሲለቀቅ የምናይ ይሆናል...🤩
ነገና አርብ ለሚፈተኑትም መልካምን ተመኘሁ🤝
✍Natman Abህብረ ቀለማት 😘 @getmnaleloch
1 728
በነገራችን ላይ...
ነገ ጠዋት እዚህ ቻናል ላይ አልፖስትም 😕
ያው እንዳጋጣሚ ሆነና ላይብረሪ ቁጭ ብዬ ግጥም የምጽፍበትም ግዜም አይኖረኝም። በዛ ላይ ወደፈተና አዳራሽ ወረቀት ይዞ መግባት ጭራሽ ክልክል ነው በመባሉ ስዕልም የለም😔
እሺ ልቦለድስ በምን ልጻፍ 🥺
ወደቁምነገሩ ስመለስ ከኦቶና ካምፓስ ነገ የሚፈተኑ ዲፓርትመንቶች መዓት ናቸው።
Midwifery
Anesthesia
Pharmacy
Pediatrics
Emergency
Laboratory
12:00 ሰዓት Main Campus ጉዞ እናደርጋለን፣ እንፈተሻለን፣ ወደፈተና አዳራሽ እንገባለን ከዛ ሰርተን እንወጣለን።
የህብረ ቀለማት ቤተሰቦች፣ እኔና እናንተ የማንገመት እንሁንና ፈተናውን ሰቅለን እንሥራ😎
***
ብቻ እኔን ጓደኞቼንም ፈጣሪ ይርዳን🙏🥰
@getmnaleloch
1 728
እንደተለያየን ያውቃል ሳር ቅጠሉ
እንደረሰኃት ገብቶታል አለሙ
እንደበቃችኝልኝ...
እንደወጣችልኝ ሁሉም አውቆልኛል
ህም¡! ሀገር አሳምኜ ልቤ ይቀራኛል
🥺
@getmnaleloch
1 728
አቤቱ...
በሰው ጉልበቴ የምችላት ሴት
አይኗ ሁሉንም የማያሳስት
ልቧ በተንኮል ያልተነካካ
ራሷን ከሰው ሳታለካካ
በቁመቴ ልክ በጎጆ መጠን
የማይቸግራት እግሯን መመጠን
ለኔና ቤቴ እሷኑ ስጠን
አቤቱ...
ምጥ ላስተምርሽ የማልላትን
ዋጋዋ ቀሎ የማልንቃትን
ጠንካራ ግደር ቀንዷንየማይከብዳት
ቅናት መንገዷን የማይጋርዳት
አቅጣጫ ብስት ሳትስት አብራኝ
እንዳልቀላውጥ ድምጿ የሚገራኝ
እሷን ጀባ በል ወደሷ ምራኝ
አቤቱ...
የዘመን ግርዶሽ አይኗን ያልያዘው
እልኳን ፍቅር ያደነዘዘው
የሰው ምርቃት የሰው በረካ
አንተው አድለኝ አንተው በል እንካ
ላልበላው ነገር ሁሉን አልነካ
ታዴ...
***
መልካም ቀን🙏
@getmnaleloch
1 728
ከኦቶና ካምፓስ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች Comprehensive Nursing ያሉ ጓደኞቼ ናቸው። 12:30 ወደዋናው ግቢ ጉዞ ይደረጋል። 2 - 5:30 ይፈተናሉ ይጠናቀቃል...
እናም እግዚአብሔር ከጎናችሁ እንዲቆም ፀሎቴ ነው።
***
ብቻ በደህና ያሳድረን🙏
@getmnaleloch
1 728
Part 1
ወገን ይሄ ነገር እኔ ከምጽፋቸው ሀሳቦች ጋር ይገናኛል አይደል? (ለማፈቅራት ቆንጆ የተጻፈ ይመስላል...😊)
ለExit እየተዘጋጀህ እንደሆነ አውቃለሁ፣ እና በየመሃሉ ይህቺን ስማ ደስ እንደምትሰኝ እርግጠኛ ነኝ... ከሚል ጽሁፍ ጋር ከጓደኛዬ የተላከልኝ ነው።
እናም አንቺም እስከመጨረሻው ስሚ እሺ....
***
ጓዴ Dr Teme አመሰግናለሁ 🙏
@getmnaleloch
1 728
ጀለስ Exit ተንሽን ጭንቅላቱ ላይ ሲወጣ ምን ብለኝ ጥሩ ነው...
ናቲ ዛሬ ተኝቼ ረቡዕ ጠዋት የምነቃበት እንቅልፍ ቢወሰደኝ እንዴት ደስ ባለኝ🙄😎
አይዞን😁
@getmnaleloch
1 728
ፎቶዋን በAI አቀናብራ
Emoji ከስር ደርድራ
ፖስት ላደረገቺው ዝባዝንኬ
ይገባታል ወይ ሼር እና ላይኬ
አይገባትም። 100%
የተፈጥሮ ውበት አድናቂዎች ማህበር (ተውአማ) 😁
@getmnaleloch
1 728
አንዳንዴ ሲያቀብጠኝ ሰዓሊ መሆን ያምረኛል፣ ድንገት ስሞክር ደሞ ይሳካልኛል። ለዛም ብዕር እርሳስ ላጲስ እሰበስብና ቀልቤ የወደደውን ነገር በወረቀት፣ በሸራ በግድግዳ ቢሆን እቀልማለሁ፣ አሻራዬን ኣርፋለሁ... ያው እንደማንኛው ሰዓሊ ማለት ነው።
ነገር ግን ያቺን ፍቅሬን ከሳልኳት በኃላ ከወረቀቱ በስተጀርባ ተጨማሪ ነገር በጽሁፍ አሰፈርኩ...
የእርሳሴ ኩራት፣ የላጲሴ ፍርሃት
አንቺ ነሽ ውዴ፣ የስዕሌ ጥራት
ተወደሻል አንዴ፣ ልቤ አይገፋሽም
ሳፈቅር ኖራለሁ፣ ሲደላሽ ሲከፋሽም
❤
✍Natman AbMonday 🥰 @getmnaleloch
1 728
Day - 3
ምድር ቢንቀጠቀጥ፣ ሰማይ ቢናወጥ የተጻፈልን ነገር መሆኑ አይቀርም። ምንም ቢያካብዱ እስካሁን ካለፍናቸው ፈተናዎች Exit አይከብድም። ዛሬ የምትፈተኑም ተረጋግታችሁ click አድርጉ፣ ሰዓቱን ተጠቀሙ።
Good Luck 🫡
@getmnaleloch
1 728
ደረጃ ነው ቤቱ ብለሽ አውርተሻል
ድንጋይ ነው ትራሱ ብለሽ አውርተሻል
ሞፎ ነው ራቱ ብለሽ አውርተሻል
ድሪቶ ነው ልብሱ ብለሽ አውርተሻል
እኔን ለበረደኝ ምን አባሽ ቆርጦሻል
ይልቅስ ጠጋ በይ ላንቺም ያልፍልሻል! 😎
ተሾመ ደምሴ | አዳራሹ ቤቴ
ብቻ ደህና ዕደሩልኝ🥰
@getmnaleloch
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
