es
Feedback
Assaye Derbie

Assaye Derbie

Ir al canal en Telegram

📈 Análisis del canal de Telegram Assaye Derbie

El canal Assaye Derbie (@asayede) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 14 337 suscriptores, ocupando la posición 2 647 en la categoría Bloques y el puesto 2 350 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 14 337 suscriptores.

Según los últimos datos del 25 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -108, y en las últimas 24 horas de -4, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 38.62%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 12.61% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 5 538 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 808 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 33.

📝 Descripción y política de contenido

No se ha proporcionado la descripción del canal.

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 26 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Bloques.

14 337
Suscriptores
-424 horas
-317 días
-10830 días
Archivo de publicaciones
‹‹ግደሉ›› የሚሉትን ታቅፎ ‹‹አትግደሉ›› የሚሉትን አፋኙ መንግሥት‼️ አሳዬ ደርቤ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ የሚያደርጉ የመንግሥት አመራሮች፣ ፓስተሮችና በሐይማኖት ውስጥ የተደበቁ ተኩላዎች እኩይ አላማቸው በመንግሥት የሚደገፍ በመሆኑ በፍጹም ነጻነት በየሚዲያው እየወጡ ወለጋ ላይ በፈሰሰው የንጹሐን ደም ፈንታ ለተገደሉት ዜጎች የሚፈስሰውን እንባ እያወገዙ የጭፍጨፋውን ምክንያትና ተገቢነት ማስረዳታቸውን ቀጥለዋል፡፡ እኒህ ጸረ አማራ ኃይሎች ከ1600 በላይ ንጹሐንን ካስጨፈጨፉ በኋላም የተለመደ ቅስቀሳቸውን አጠናክረው ቢቀጥሉም የሚያበረታታቸው እንጂ የሚቆጣጠራቸው መንግሥት አገሪቷ ላይ የለም፡፡ በሌላ መልኩ ግን አሳፋሪው የአማራ ክልል መንግሥት ኦነጎች ወለጋ ላይ በፈጸሙት አረመኔያዊ ድርጊት የአማራ ፋኖዎችን እያፈነ ወደ ማጎሪያ ካምፕ ማስገባቱን አጠናክሯል፡፡ በአዲስ አበባም፣ በግፍ ለተጨፈጨፉ አማራዎች ኀዘናቸውን የሚገልጹትንና የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙትን እየመረጡ የማሰር ዘመቻው በበላይ በቀለ ወያ ተጀምሯል፡፡ ከባድ መሣሪያ ታጥቀው፣ ግዙፍ ሠራዊት አደራጅተው የሥልጣን ትግል ከለኮሱትና ንጹሐንን ከሚጨፈጭፉት የትሕ-ኦነግ ኃይሎች ይልቅ ‹‹ዜጎችን አታስገድል›› የሚል ሰላማዊ ትግል የሚያሳስበው የብልጽግና መንግሥት ወንጀለኞችን ታቅፎ የሚቃወሙትን እያሳደደ ነው፡፡ ከዩኒቨርስቲ ተማሪ መሀከልም አሸባሪ እያፈላለገ ነው፡፡ በንጹሐን ላይ የሚፈጸመው እልቂት ሦስተኛውን ዙር የአባይ ግድብ ሙሊት ማደናቀፍ በሚፈልጉ የግብጽና የሱዳን ተላላኪዎች የሚፈጸም ነው›› በሚል መግለጫ ተላላኪዎቹንና ጨፍጫፊዎቹን አዝሎ፣ ግድቡን በአማራዎች ደም ሊሞላው ያሰበ ይመስል ‹‹ጭፍጨፋው ይቁም›› የሚሉ ድምጾችን ለማፈን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን ከእኛ የሚጠበቀው ሦስት ነገር ነው፡፡ 1. ወንጀል አለመሥራትና ሕግን አለመተላለፍ 2. ወንጀልን እና ወንጀለኛን በመቃወም የሚመጣን የትኛውንም እርምጃ ንቆ ማለፍ እና ደግሞ…. ተገቢነት በሌለው የአምባገነኖች ቅጣት አለመሸነፍ

ፍትሕ ኦነግ በፈጸመው ጭፍጨፋ ለታሠሩ አማራዎች ሁሉ‼️ ፍትሕ በግፍ ለተጨፈጨፉ 1600 ነፍሶች‼️ ፍትሕ ለመላው የአማራ ሕዝብ‼️
ፍትሕ ኦነግ በፈጸመው ጭፍጨፋ ለታሠሩ አማራዎች ሁሉ‼️ ፍትሕ በግፍ ለተጨፈጨፉ 1600 ነፍሶች‼️ ፍትሕ ለመላው የአማራ ሕዝብ‼️

"ይነጋል ባልነው ቀን ፣ ጨለማው ገነነ "አሻጋሪ" ያልነው ፥ አሸባሪ ሆነ !" ብሎ የገጠመው ፥ በላያ ታፈነ። የሕዝብ ድምጽ የሆኑ አንቂዎችንና ገጣሚዎችን በማፈን ላይ የሚገኘው አካል፣ ከሰሞኑን "በ
"ይነጋል ባልነው ቀን ፣ ጨለማው ገነነ "አሻጋሪ" ያልነው ፥ አሸባሪ ሆነ !" ብሎ የገጠመው ፥ በላያ ታፈነ። የሕዝብ ድምጽ የሆኑ አንቂዎችንና ገጣሚዎችን በማፈን ላይ የሚገኘው አካል፣ ከሰሞኑን "በማደንዘዝ ጥበብ" ዙሪያ ሥልጠና የሰጣቸውን አክቲቪስቶች ወደ ሥራ አስገብቷል።

መገን ብልጽግና‼️ ▬▬▬ ባለፈው የቆየ ቪዲዮ ለጥፎ ከ1600 በላይ አማራዎችን ደም አፈሰሰ። የሕዝብም ቁጣ ቀሰቀሰ። ተቃውሞው ሲበረታበትም፣ የሱዳን ወታደሮችን 6 አስከሬን ለጥፎ የ1600 ንጹሐን እልቂት የፈጠረውን ቁጣ ቀለበሰ። እና ደግሞ ሲገደል የከረመው የአማራ ሕዝብ የሚሞትበትን ጦርነት ለኮሰ። የብልጽግና ነገር ይገርማል‼️ ስትደግፈው ግጭት ለኩሶ ይጨፈጭፍኻል። የተረኛ እና የብሔርተኛ ማሊያ ለብሶ ያሳድድኻል። ስትቃወመው ደግሞ አገራዊ ጦርነት ቀስቅሶ ያሰባስብኻል። በዚያም ጦርነት ላይ እራስህን መከላከል ካልቻልክ ምድርህን አስወርሮ በሱዳን እጅ ወልቃይትን ለህውሓት የማቀበል ሥራ ይፈጽምብኻል ። ብርቱ ሆነህ ከተገኘህ ደግሞ በጦርነቱ እኩሌታ ላይ ከጠላት ጋር ቁጭ ብሎ ይደራደርብኻል። ወይም ደግሞ እራሱ የለኮሰውን ጦርነት ለብቻህ አሰረክቦህ ይሰወርብኻል። የሆነው ሆኖ... ይሄን መድረክ እንደ ናትናኤል መኮነንና ደረጀ ሃብተወልድ ላሉ የጦር መሪዎች አስረክቤ ከመውጣቴ በፊት "የወገኖቻችንን ነፍስ ፈጣሪ ይማር!" እላለሁ። መንግሥት በሚል ሥም ጠላት የተሸከመው ሕዝብም ወኪል አልባ መሆኑን አውቆ አምላክ ይጠብቀው ዘንድ እመኛለሁ።

photo content

photo content

የምዕራብ ወለጋው ጭፍጨፋ ከመከሰቱ በፊት በመንግሥት የተከናወኑ ተግባራት፦ አሳዬ ደርቤ ➔ የአማራ ድምጽ የሆኑ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ከእስር ቤት ታጎሩ፤ ➔ለብአዴን የግርድና ወንበር አስጊ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 12 ሺህ ፋኖዎች ታሰሩ፤ ➔እንደ ዮሐንስ ቧያለውና አቶ ገዱ ያሉ አፈንጋጭ አመራሮች ተቀነሱ፤ ➔ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፖርላማቸውን ሰብስበው ከመንግሥት ቀርቶ ከአክቲቪስት በማይጠበቅ የጥላቻ ንግግር ሕዝብን አነሳሱ፤ ➔ከወራት በፊት ኢሰመኮ በጸጥታ ኃይሎች መፈጸሙን ገልፆ እርምጃ እንዲወሰድ የጠየቀበት ቪዲዮ "በኦሮሞዎች ላይ ፋኖዎች የፈጸሙት" ተብሎ ሶሻል ሚዲያ ላይ ተለቀቀ፥ ➔ ከዚያም ከአንድ ሺህ በላይ አማራዎችን ያስጨፈጨፈው አካል በኅዘን ሳምንት ፈንታ የችግኝ ተከላ ሳምንት አውጆ እንጦጦ ጫካ ተደበቀ። እናም እልኻለሁ... ለተገደሉ ወገኖችህ ፍትሕን፣ በሕይወት ላሉት የመኖር መብትን የምትሻ ከሆነ ...ዋነኛ ጥያቄህ "በወገኖቼ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገን ይጣራልኝ" የሚል ይሁን!! ያን ጊዜ ቶሌ ላይ ያስገደለህን አካል ቦሌ ላይ ታገኘዋለህ! Share

መግደል መብት ሆኖ ፥ ለሽፍቶች ሲታደል መደበቁን ትተህ ፥ "እንቢኝ አትንኩኝ በል" ወልዲያ
+1
መግደል መብት ሆኖ ፥ ለሽፍቶች ሲታደል መደበቁን ትተህ ፥ "እንቢኝ አትንኩኝ በል" ወልዲያ

photo content

photo content

ጽሑፉ ከላይ ስላለ አንብቡት
ጽሑፉ ከላይ ስላለ አንብቡት

ማሩኝ›› የምትልበት ከመምጣቱ በፊት ‹‹በቃኝ›› በል! አሳዬ ደርቤ ይህቺን ሕጻን አስታወሳችኋት? ከመንፈቅ በፊት ከምዕራብ ወለጋ ጭፍጨፋ አምልጠው ከተፈናቀሉ አማራዎች ጋር ያገኟት ጋዜጠኞች ሲጠይቋት የሰጠችው መልስ እንደሚከተለው ነበረ፡፡ ‹‹ስምሽ ማን ነው?›› ‹‹አንሻ ሠኢድ›› ‹‹የት ነበር የምትኖሪው?›› ‹‹ዳንዴ ቀበሌ›› (ምዕራብ ወለጋ) ‹‹በምን ምክንያት ነው ያፈናቀሏችሁ? ‹‹ነፍጠኛ ናችሁ ነው የሚሉት›› ‹‹ነፍጠኛ ማለት ምን ማለት ነው?›› ‹‹ወላሂ አላውቀውም!›› በጣም የሚያሳዝነው ነገር ታዲያ ያን ጊዜ ይህቺ ሕጻን በየዋህ አንደበቷ ብሶቷን ስታወራን ባለመቆጣታችን እና ጥቃቷን ባለማስቆማችን የተነሳ በቅርቡ ደግሞ የአንሻን የመፈናቀል እድል የተነፈጋት ሕጻን ‹‹ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም›› የሚል ልመናዋ ዋጋ አጥቶ ከሺህ ከሚቆጠሩ አማራዎች ጋር ተገደለች፡፡ እይውልህ ወንድማለም…. ያለ መንግሥት ፍላጎት የሚፈጸምን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስቆም የመጀመሪያ እርምጃ የተፈጸመውን ወንጀል ዜጎች እንዲያወግዙትና እንዲማሩበት ማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው እርምጃ ደግሞ ወንጀለኛውን መቅጣት ወይም ደግሞ ማጥፋት ነው፡፡ በአማራዎች ላይ የሚፈጸመው ጭፍጨፋ ግን በመንግሥት የሚቀነባበርና አገር አፍርሶ አዲስ አገር የመሥራት ግብ ያለው በመሆኑ በመቶዎችና በሺህዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን በተገደሉበት እለት መንግሥት አትክልት ውስጥ ሲደበቅ ታየዋለህ፡፡ አንተ ‹‹ይሄን ያህል ሕይወት ከገበርን አይበቃም ወይ?›› እያልክ ስትጮህ እሱ ‹‹መቼ ተጀምሮ ነው የሚያበቃው›› የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው በሚችል ዝምታ ያልተቀበረ አስከሬን ተራምዶ ችግኝ ሲተክል ትመለከተዋለህ፡፡ በክልሉ ውስጥ የፈጸመብህን ጥቃት የሚያስረሳ፣ ያንተን ሥም በክፉ የሚያስነሳና ለሌላ ዙር ጭፍጨፋ የሚያነሳሳ… በቪዲዮ የተደገፈ ጥቃት በክልልህ ውስጥ አቀናብሮ የወንጀሉ ተጋሪ ካደረገህ በኋላ እንባህን ቀምቶ ደምህን ሲያፈስስ ታገኘዋለህ፡፡ እናም እልኻለሁ… የተፈጸመብን ጉድ ወደፊት ከታቀደልን እቅድ ጋር ሲነጻጸር ኢምንት ነው፡፡ ያለፈው አረመኔያዊ ድርጊት ወደፊት ከሚከሰተው ጥፋት ጋር ሲወዳደር ምንም ነው፡፡ ‹‹አትንካኝ›› ብለህ መነሳት እስካልቻልክ ድረስ ከትንሽ ጊዜ በኋላ የአማራ ሕዝብን ቀርቶ ብአዴንን በሚያስደነግጥና ለመላው ዓለም በሚሰቀጥጥ አረመኔያዊ ማንነት ሲመጣ ታየዋለህ፡፡ ኦነግን ያጠፋዋል ብለህ ስትጠብቅ ብልጽግናን አክስሞ ቶሌ ቀበሌ ላይ ያየኸውን ዘግናኝ እልቂት ቦሌ ድረስ ሲያመጣው ትታዘባለህ፡፡ አሁን ላይ እንደ ሕዝብ ‹‹ወገኔን አትግደሉ›› ብሎ መቆጣት የሚያመጣውን እስራት ፈርተህ ስትርመጠመጥ፣ የሆነ ጊዜ ላይ በቤተሰብና በግለሰብ ደረጃ ከአፈሙዝ ስር ተንበርክከህ ‹‹እባካችሁ እኔን አትግደሉኝ›› እያልክ ስትማጸን እራስህን ታገኘዋለህ፡፡ እናም ይህ እንዳይሆንብን የምንሻ ከሆነ፣ እጅና እግራችንን አስረው ከገጀራ ስር ሊጥሉን የሚሞክሩ የክልል አመራሮችን እና ፖለቲከኞችን ‹‹ይሄን ማድረግ አትችሉም›› እንበላቸው፡፡ እራሳችንን አንቅተን ሕዝባችንን እንቀስቅሰው፡፡ ሥልጣን ላይ ያለው ኃይል ከፋፍሎ ሊውጠን ሲያስብ አንድ ሆነን እንትፋው፡፡ እስካሁን ለጥፋት የዳረገን አስተሳሰብ ‹‹ወገኔን አትንኩብኝ›› በሚል ሕዝባዊ ቁጣ አስፈሪ ሆነን በመገኘት ፈንታ ‹‹እኔን ምን አገባኝ›› በሚል የፍርሐት አሮንቃ ውስጥ መዘፈቃችን ነውና በጅምላ የታወጀብንን እልቂት በጋራ እናክሽፈው፡፡ share

photo content

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች "የአማራዎች እልቂት የምክር ቤቱ አጀንዳ የሚሆነው ስንት ንጹሐን ሲገደሉ ይሆን?" እያሉ ነው።
+2
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች "የአማራዎች እልቂት የምክር ቤቱ አጀንዳ የሚሆነው ስንት ንጹሐን ሲገደሉ ይሆን?" እያሉ ነው።

photo content

አዲስ አበባ ላይ ኮሽታ ሲፈጠር ሽንት በሽንት የሚሆነው አካል "አትጨፍጭፈን" የሚል መፈክር ይዘው የወጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጨፍጭፎ በትኗቸዋል። #እምቢኝ_በል-አማራ‼️
+1
አዲስ አበባ ላይ ኮሽታ ሲፈጠር ሽንት በሽንት የሚሆነው አካል "አትጨፍጭፈን" የሚል መፈክር ይዘው የወጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጨፍጭፎ በትኗቸዋል። #እምቢኝ_በል-አማራ‼️

photo content

photo content

እነዚህ ጋር አብሬ ባንድ አገር መኖር አልችልም! 😭