es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀

Ir al canal en Telegram

« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀

El canal 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 (@https_asselefya1) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 13 954 suscriptores, ocupando la posición 6 146 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 482 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 13 954 suscriptores.

Según los últimos datos del 09 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -115, y en las últimas 24 horas de 0, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 22.95%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener N/A% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 205 visualizaciones. En el primer día suele acumular 0 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 0.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 10 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

13 954
Suscriptores
Sin datos24 horas
-467 días
-11530 días
Archivo de publicaciones
SURAH_MARYAM_سورة_مريم_ሱረቱ_መርየም_M4A_128K.m4a8.95 MB

መቼም ቢሆን ከዒልም ፍለጋ ልንዘናጋ አይገባም። የትኛውም ቀናችን አነሰም በዛ የሆነ ነገር ልንሸምትበት ይገባል። በዚህ ሳምንት ምን ተምረናል? ምን አዳምጠናል? ምን አንብበናል? ለቀጣይስ ምን አስበና
መቼም ቢሆን ከዒልም ፍለጋ ልንዘናጋ አይገባም። የትኛውም ቀናችን አነሰም በዛ የሆነ ነገር ልንሸምትበት ይገባል። በዚህ ሳምንት ምን ተምረናል? ምን አዳምጠናል? ምን አንብበናል? ለቀጣይስ ምን አስበናል? በዚህ ዓመት ስንት ኪታብ አየን? ለቀጣይስ ምን አሰብን? አነሰም በዛም ጊዜያችን ከዒልም ፍለጋ የተራቆተ ሊሆን አይገባም። ጊዜ የለንም ብለን አንዘናጋ። እንደምንም ብለን ጊዜ እንስጥ። ተረጋግተን ተቀምጠን የምንከታተልበት ጊዜ ቢያጥረን ስራችንን እየሰራን ብዙ ደርሶችን፣ ደዕዋዎችን ማዳመጥ እንችላለን። በየቀኑ ከቤቱ ተነስቶ ስራ ቦታ የሚሄድ ሰው፣ ረጃጅም የወረፋ ሰልፍ ላይ የሚቆም ሰው፣ ... ፀጥታ ካለ ቁርአኑን መቅራት ይችላል። እሱ ባይመች ኪታብ ማንበብ፣ ዚክር ማድረግ፣ በኤርፎን ደርስ ማዳመጥ ይችላል። አንዴ ካስለመድነው ህይወታችን ጋር ይዋሃዳል። ቀላል የሚመስለን ጊዜ ብዙ ልንጠቀምበት እንችላለን። ዋናው ነገር ውስጣችን ለመማር ዝግጁ ይሁን። የምር ካሰብንበት በየቀኑ የሆነ እውቀት መጨመር እንችላለን። ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም። ዐብዱላህ ኢብኑል ሙባረክ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሰው እውቀትን ፍለጋ ላይ እስከሆነ ድረስ አዋቂ ከመሆን አይወገድም። እንዳወቀ ያሰበ እለት ያኔ አላዋቂ ሆኗል።" [አልሙጃለሳህ : 2/186] = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ሰዎች የማይጠየቁባቸው.mp34.05 KB

🗒️መዉሊድ እና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! ➏. ሱዩጢ፦ የመጀመሪያ ይህን ስራ የፈጠረዉ የኢርቢሉ ንጉስ መዞፈር ነዉ። {አልሓዊ:1/189} ➐. ዘርቃኒ፦ መዉሊድ መፈፀም ቢድዐህ ነዉ። (ሸርሑል መዋሂብ:1/264)ይስተዋል። እነዚህ ሁሉም የመዉሊድ ደጋፊዎች ከመሆናቸዉ ጋር ቢድዐህ እንደሆነ ግን በአንዴ ድምፀ እየመሰከሩ ነዉ። {ወሸሂደ ሻሂዱን ሚን አህሊሃ።} ❽. አሽሸዉካኒ፦ ቢድዐህ በመሆኑ ላይ ከሙስሊሞች አንድም አልተቀዋመም ይላሉ። በተጨማሪ፦ ቢድዐህ በመሆኑ ላይ የሁሉም ሙስሊምች ኢጅማዕ እንዳለበት አስረግጠናል ይላሉ።{ፈትሑርረባኒ:2/1088፣109} ❾. ሙሐመድ ረሺድ ሪዷ፦ ይሄ መዉሊድ ያለ ንትርክ ቢድዐህ ነዉ ይላሉ። (ፈታዋ ረሺድ ሪዷ: 4/1243) ❶ⓞ. ሸይኽ ዐሊ መሕፉዝ፦ ከቢድዐዎች በመሆኑ ላይ ንትርክ የለም። (አልኢብዳእ ፊ መዶሪል ኢብቲዳዕ:297) «ስለዚህ አንባቢ አንድ ቁም ነገር ሊጨብጥ ይገባል። እሱም መዉሊድ በደጋፊም በነቃፊም ኢጅማዕ መጤ ፈሊጥ ነዉ፣ ቢድዐህ። በየ መንደሩ  ከዚህ የተለየ እያስተጋቡ ለሚቤጠለጠሉ አካላት  ይሄ መብረቅ ነዉ!! "ነባሩ እስልምና" እያሉ ልባችንን ለሚያደርቁ ሁሉ አንድ መልእክት  ይድረሳቸዉ። ነባሩ ኢስላም ማለት  የነብዩﷺ ፣የሶሓቦች ፣የታቢዒዮች፣ የአትባዑት ታቢዒን ኢስላም ነዉ።  የአራቱ አኢማዎች ፣ የነ ቡዃሪ የነ ሙስሊም ኢስላም እንጅ የሱፍዮች ኢስላም አይደለም። ይሄ ኢስላም ነባር ካልሆነ  የማን ኢስላም ነዉ ነባር የሚሆነዉ? እንዳየነዉ  መዉሊድ በደጋፊዎቹም  በነቃፊዎቹም ኢጅማዕ ቢድዓ ነዉ፣መጤ ፈሊጥ።  መጤ ደግሞ በየትኛዉም አረዳድ  ነባር ሊሰኝ አይችልም። ስለዚህ  መዉሊድ ከነባሩ እስልምና ዉስጥ የለም ማለት ነዉ። ስለዚህ መዉሊድ  የሚቃወመዉ የተሀድሶ እንቅስቃሴ  ኢስላማዊ  አረዳዱ  ሀሰን ታጁ እንደሚለዉ  የሀያ እና የሰላሳ አመት እድሜ ያለዉ ፈሊጥ ሳይሆን  ከሱፍዮች  ኢስላማዊ አረዳድ በበለጠ ጥንታዊ ነዉ። «መዉሊድ ታሪክ፤ ግድፈት ፣ እርምት ለሐሰን ታጁ መዉሊድ መፀሐፍ የተሰጠ ምላሽ ከሚለዉ መፀሀፍ የተወሰዴ !»   ──────⊹⊱✫⊰⊹────── https://t.me/https_Asselefya1

«እህቴ... ወደፊት ባለቤቴ የምትዪው ሰው፣ የልጆችሽ አባት የሚሆነው የማንን ልብ እንደሰበረ አታውቂም። «ወንድሜ...ወደፊት ባለቤቴ የልጆቼ እናት የምትላት የማንን ልብ እንደሰበረች አታውቅም። «ወደፊት ባለቤቴ፣ የልጆቼ አባት የምትዪው ሰው ምን እንደተበደለ፣ ምን አይነት ሀዘን እንደተሸከመ አታውቂም። «ወደፊት ባለቤቴ የልጆቼ እናት የምትላት ምን እንደደረሰባት፣ ምን እንደተበደለች፣ ምን አይነት ሀዘን እንደተሸከመች አታውቅም። የምንተዋወቅ ሊመስለን ይችላል እንጂ አንተዋወቅም። ስለሆነ ሰው በማጠያየቅ የምናገኘው መገለጫ የሰውየውን የውስጥ እውነት አያመለክትም። ብዙ ሴቶች መልካም ስም ላለው ሰው ተድረው ደም እንባ እያነቡ የሚኖሩ አሉ። ብዙ ወንዶች መልካም የተባለችን ሴት አግብተው ተሸማቀው የሚኖሩ አሉ። ለሁሉም ነገር መዘጋጀት ተገቢ ነው። የሰዎችን ወደ አላህ መመለስ ማክበርም አስፈላጊ ነው። ከሁሉም ከሁሉም ወደ አላህ መጠጋት እና እሱ ለሚመርጥልን የተገባን፣ እና የምንገባ እንድንሆን ሰርክ መጠየቅ የግድ ይላል። ከዚያ ባለፈ ስነ ምግባራችንን ማሳመርና የምር የሰው ልጆች አይነታ የሆኑትን ውድ ነብይ ሱና ተከታይ ለመሆን ጥረት እናድርግ። በህይወት ውስጥ የሚወዱትን፣ የፈለጉትን አግኝቶ መኖር ሳይሆን አላህ የመረጠውን ተቀብሎ መውደድ ነው በላጩ ነገር። አላህ የምንወደውን ይውደድልን። » t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

ብቅ በሉ አሁን ሊጀመር ነዉ ሴቶች📣🌹

ኑ ተጋብዛችኋል በሠዓታችን ከች ብለናል 🌷🍃
ኑ ተጋብዛችኋል በሠዓታችን ከች ብለናል 🌷🍃

ለዐረብ ሀገር ወንድምና እህቶች ~ ① ከሁሉም በፊት ለዲናችሁ ቅድሚያ ስጡ። ከተውሒድ ጀምራችሁ ግንዛቤያችሁን በተለያዩ መንገዶች አስፉ። ለአላህ ምስጋና ይግባውና በዚህ በኩል ብዙ ወንድሞችና እህቶች ዘንድ ጥሩ ተነሳሽነት ይታያል። ② ለአሰሪዎቻችሁ ታማኞች ሁኑ። የሰው ሀላፊነት እስከተቀበላችሁ ድረስ አላህን ፈርታችሁ ሀላፊነታችሁን ባግባቡ ተወጡ። በሰዐትም፣ በስራም፣ በገንዘብም፣ በክብርም፣ በልጆችም የምትታመኑ ሁኑ። አማናን መወጣት ትልቅ ሃላፊነት ነው። ③ በተቻላችሁ ከአላስፈላጊ የወንድና የሴት ቅልቅል ተጠንቀቁ። በጋራ የኪራይ ቤቶች ሊፈፀሙ ከሚችሉ አደጋዎች እራሳችሁን ጠብቁ። ④ እርስ በርስ ተዛዘኑ። ስራ ለሌለው ስራ በመፈለግ፣ ለተቸገረው በብድር ወይም እራስን በማይጎዳ መዋጮ ተጋገዙ። ⑤ ከወንጀለኞች ራቁ። ዐረብ ሀገር በርካታ ኢትዮጵያውያን በወንጀል ስራ ላይ መሰማራታቸው የሚታወቅ ነው። በነሱ ሳቢያ ኢትዮጵያውያን ባጠቃላይ በተደጋጋሚ ስማቸው ይጠፋል። የሚገርመው ብዙ ለነዚህ ወንጀለኞች ሽፋን የሚሰጡ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ነው። በነሱ ጥፋት አብራችሁ እንዳትጎዱ ተጠንቀቁ። እንዲያውም ለሌላ የሚተርፍ የተረጋገጠ ወንጀል ካያችሁ ለሚመለከተው አካል ጠቁሙ። ይሄ ለዲናችሁም ለገፅታችሁም ዋጋ አለው። ⑥ ቤተሰቦቻችሁን አትርሱ። ወላጅ ወላጅ ስለሆነ ብቻ ከባድ ሐቅ እንዳለው እሙን ነው። ከዚያም ባለፈ ስንት ፍዳቸውን አይተው አሳድገዋል። ዐረብ ሀገር ትሄዱ ዘንድ የተቸገሩላችሁም ብዙ ናቸው። እነዚህን ታሳቢ በማድረግ ወላጆቻችሁን አትርሱ። በዚያ ላይ አንዳንዶቻችሁ ወደ ወላጆቻችሁ ልጅ የላካችሁ ትኖራላችሁ። በዚህን ጊዜ ሐቁ ድርብርብ ነውና ኣኺራችሁን እንዳታጨልሙ ተጠንቀቁ። ⑦ እራሳችሁን አትርሱ። የወጣችሁት እንጀራ ፍለጋ ነው። ከፋም ደላ የሰው ሀገር የሰው ነው። ህልማችሁ ቋጥሮ ወደ ሀገር ለመመለስ እንጂ በልቶ ለመውዛት፣ ለብሶ ለመድመቅ አይደለም። ለዚህ ደግሞ ብልጥ መሆን ያስፈልጋል። መስራቱን ቻሉበት። መያዙንም ቻሉበት። ወጭ ቀንሱ። ለቤተሰብ ስትልኩም አቅማችሁንም፣ ኑሯቸውንም፣ ሁኔታቸውንም እያገናዘባችሁ ይሁን። ለጎረምሳ ጫት መቃሚያና መንሸራሸሪያ አትላኩ። በዚህ ወንድሞቻችሁን ታበላሻላችሁ እንጂ አትጠቅሟቸውም። ገንዘባችሁንም አጥታችሁ ወንጀለኛም ትሆናላችሁ። ባጭሩ የምትሰሩትን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ ለማዋል ተጣጣሩ። ባዶ እጃችሁን ላለመግባት በተቻላችሁ ተጠንቀቁ። ችግር መጥፎ ነው። ቤተሰብ እንኳን እንዲገፋችሁ ያደርጋል። አገራችን ለባዶ እጅ ቀርቶ ለያዘም እየከበደ ነው። ⑧ እቅድ ይኑራችሁ። ለቆይታችሁ ገደብ አስቀምጡለት። በግምት አትኑሩ። ሁለት አመት ሰራርቼ አገሬ እገባለሁ ብለው ሃያ አመት የኖሩ አሉ። ከአላማ ካልተወጣ ክፋት አልነበረውም። እየባከኑ ሲሆን ግን ያሳዝናል። "ምን ይዤ ልግባ?" እያሉ እየተብከነከኑ መኖር ይጎዳል። ስለዚህ ገደብ ያለው እቅድ ይኑራችሁ። ለእቅዳችሁም በትጋት አስቡ፣ በትጋት ስሩ። መገናኘታችሁ እቅዳችሁን የሚያሰናክል፣ ለትርጉም የለሽ ወጭ የሚዳርግ ከሆነ ተራራቁ። ⑨ ሴቶች ሆይ! መንገደኛ አታግቡ። እስኪ አሁን ሂንዲ፣ ፓኪስታኒ፣ ባንጋሊ ማግባት ምን ይባላል? እንዲህ አይነቱ ትዳር ዘላቂ የመሆን እድሉ እጅግ የጠበበ ነው። ልጅ ከመጣም ከነ ጭራሹ አባቱ ጋር አይኖርም። ስለዚህ ለራስም ለልጅም ፈተና ነው። (10) ለኸይር ስራ እጃችሁን ስትዘረጉ ጥንቁቅ ሁኑ። ኸይር አትስሩ አይባልም። ግን በትክክል ለታለመለት ግብ የሚደርስ መሆኑን ቢያንስ ሚዛን የሚደፋ ግምት ያዙ። (11) ለትዳር ክብር ይኑራችሁ። ትዳርን መስፈርት በማያሟላ በተጨመላለቀ መልኩ ሳይሆን በሥርዓት ፈፅሙ። አትበዳደሉ። ኣኺራችሁን በማይጎዳ መልኩ በስርኣት ኑሩ። ለጋብቻ የተጋነነ ወጭ አታውጡ። ከሰሞንኛ ሆይሆይታ ይልቅ ለዘላቂው ትዳራችሁ ቅድሚያ ስጡ። መለያየት ግድ ካለም ባግባቡ ይሁን። (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 4፣ 2013) = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ቆንጆ ምላስ ፀጋ ነው። ከምትናገረው አንድ ቃል በፊት አንድ ሺህ ጊዜ ማሰብ  መቻል ከአላህ የሆነ ስጦታ ነው።  የሰዎችን ተፈጥሮና የግንዛቤ አቅምን በማስተዋል የተገራ አንደበት የተባረከ ነው።  አንዳንድ ሰዎች አሉ… ለንግግራቸው ለከት የሌላቸውና ሁኔታን የማያገናዝቡ።  ወይ የንግግር ለዛ የላቸው ወይ  ቃላት አይመርጡ…  በቃ እንደወረዱ። t.me/abdu_rheman_aman

በማያገባሽ ነገር ከገባሽ የሚያስከፋሽን ትሰሚያለሽ።

‏راحة النَّفس من الخلق في اثنتين: عدم التَّشاغل بما يقولون مدحًا أو قدحًا، والإحسان إليهم - وإن أسأوا -، ابتغاءَ وجه الله. #صالح_العصيمي

" إذا رأيت الرجل يذكر الألباني وابن باز والعثيمين والوادعي بخير فاعلم أنه على خير ". 🎙لفضيلة الشيخ : أ.د. #سليمان_الرحيلي • حفظه اللّٰه •

😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️ 🛜የመጀመሪያው ፕሮግራማችን ▶️ 🙁☹️😭🙁😭🙁☹️🙁 🎴ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ📶 🎤       ተ🎁              ጀ▶️                   መ ▶️                           ረ▶️ ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም! ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት‼  ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘ t.me/tdarna_islam?livestream t.me/tdarna_islam?livestream

«በራስሽ መቆም ተለማመጅ ማንም በሌለበት ስትወድቂ መቆም እንድትችይ!» = t.me/https_Asselefya1

በፍፁም እንዳታስመስይ ከነ ስህተትሺም ቢሆን ራስሺን ሁኝ !! =

ሚስት ከሆንሽ ባልሽን ባል ከሆንክ ደግሞ ሚስትህን ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ዐይኗን በስስት የመመልከት ልማድ አዳብር ። በዐይኗ ውስጥ ሩኋን ፈልግ ። እየተመለከትካትም ስለሷ መልካም ነገሮችን አስብ ። ወዳጄ ፍቅር እንደ ጭቃ ተጠፍጥፎ የሚሰራ የልፋት ውጤት ነው ።በጥረታቸሁ ልክ በትዳርና የፍቅር ግንኙነታችሁ ትደሰታላችሁ  ። ባረከሏሁ ፊኩም ያላገባችሁ ወንድምና እህቶች ለጊዜው መስታወት ፊት ቆማችሁ እራሳችሁ ላይ ማፍጠጥ ትችላላችሁ  ....