cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethiopia breaking news

Mostrar más
Advertising posts
323Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ትግራይ ክልልም የክልሉን ግዛት እና ህዝቡን ለመጠበቅ በቂ የፖሊስ ኃይል፣ በቂ ልዩ ኃይል ፣ በቂ ሚሊሻ ይኖረዋል " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ቅዳሜ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የሰላም ስምምነት በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት " ህወሓት "ን ትጥቅ ስለማስፈታት እና በትግራይ ክልል ውስጥ ምርጫ ተከናውኖ የክልል መንግስት የሚመሰርተው አካል ክልሉን ለመጠበቅ መሳሪያ የመታጠቅ መብቱን በመጠቀም ረገድ ላይ ግርታ ሊኖር እንደማይገባ አስረድተዋል። አምባሳዳር ሬድዋን በትግራይ በምርጫ ስልጣን የሚይዘው አካል ልክ እንደ ሌሎቹ ክልሎች በቂ የፀጥታ ኃይል እንደሚያደራጅ አረጋግጠዋል።  መንግስት ህወሓት በሽብርተኝነት የተፈረጀበትን ድንጋጌ መልሶ እንዲመለከተው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብም አምባሳደር ሬድዋን ጠቁመዋል።  አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከትጥቅ ማስፈታት ጋር በተያያዘ የተናገሩት ፦ " ህወሓትን ትጥቅ ማስፈታት ብለን ስንናገር እና የትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይል ያደራጃል ስንል ወዳጆቻችን ግርታ ሊገባቸው ይችላል። ክልሎች የራሳቸው #የተመጠነ የፀጥታ ኃይል አላቸው ትግራይ ክልልም የክልሉን ግዛት እና ህዝቡን ለመጠበቅ በቂ የፖሊስ ኃይል፣ በቂ ልዩ ኃይል ፣ በቂ ሚሊሻ ይኖረዋል ከዚህ ጋር ነው መታየት ያለበት።  አሁንም ደግሜ የምለው ግን ይህ የሚሆነው ለትግራይ ክልላዊ መንግስት እንጂ ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም። " Credit : Journalist Solomon Muchie @tikvahethiopia
Mostrar todo...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ... እያንዳንዱ የምናደርገው ነገር ፤ ሁሉም እንቅስቃሴያችን ወይም የምንፈርመው ስምምነት ሁሉ የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ ህወሓትን በመወከል በፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር ላይ የተሳተፉት እና በሰላም ስምምነት ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት አቶ ጌታቸው ረዳ  ዛሬ የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ከኬንያ ሆነው በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " እያንዳንዱ የምናደርገው ነገር ፤ ሁሉም እንቅስቃሴያችን ወይም የምንፈርመው ስምምነት ሁሉ የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል። " ሰላም ህዝባችን ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገው ነገር ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው ፤ "  የሕዝባችንን ጥቅም ለማስጠበቅ የገባውን ቃል ማክበር መቻላችን ጊዜ የሚፈታው ነው " ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ባሰፈሩት ፅሁፍ ላይ ፤ " ወደ ጦርነት የገባነው ፈልገነው ሳይሆን እንደ ህዝብ ህልውናችን አደጋ ውስጥ በመግባቱ ነው" ብለው " የሰላም ስምምነት መፈረም የትግራይን ሕዝብ ሕልውና የሚያስጠብቅ ከሆነ ፣ #ለሰላም ለምን ዕድል አንሰጠውም ? " ብለዋል። አቶ ጌታቸው ዛሬ በናይሮቢ የተጀማረው ከፕሪቶሪያ የቀጠለው የሰላም ንግግር (በኢትዮጵያ መንግስት እና ሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች መካከል) ተሳታፊ ናቸው ይኸው ውይይት ለቀጣይ ቀናት ይቀጥላል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ በግብፅ ፣ ሻርም አል-ሼይክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ እየተካሄደ ነው። በዚህ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ከ100 በላይ የሀገራት መሪዎች እየተካፈሉ ነው። ዶክተር ዐቢይ ፤ ከጉባኤው ጎን ለጎን  ከበርካታ ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ስልታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል። ከአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ጋርም በጋራ የትኩረት  ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገልፀዋል። ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሥጋትና እሳቤ የምትጋራ ሲሆን፣  የመፍትሔዎች አንድ አካል ለመሆን  ቁርጠኛ ናት። " ብለዋል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Nairobi የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ናይሮቢ ላይ የተናገሩት ፦ " የቴሌኮም፣ የኢነርጂ እና የባንክ አገልግሎቶችን መልሰን ማገናኘት አለብን። ከዚያ በፊት ግን ሰዎቻችን በቅድሚያ ምግብ እና መድኃኒት ይፈልጋሉ። ይህን ለማፋጠን እየሞከርን ነው። ክልሎችን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች በባለፉ ጉዳዮች ከመዘፈቅ ይልቅ ተስፋ እንዲፈነጥቁ እና መጪውን ጊዜ በጸጋ እንዲቀበሉ መንግስት እያበረታታ ነው። " አቶ ጌታቸው ረዳ (ከህወሓት) ፦ " በስምምነታችን የተካተቱ ብዙ መደረግ ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከእነዚህ ተግባራት መካከል የአገልግሎቶች መጀመር አንዱ ነው። የአገልግሎቶቹ ቁጥር ከፍ ሲልም በተደራዳሪ ወገኖች መካከል የሚኖረው መተማመን እና ግንኙነት አብሮ ይጨምራል፤ በሰዎች አዕምሮ ውስጥም ተስፋ ይዘራል ፤ ለማስፈን እየሞከርን ያለውን ሰላም የበለጠ ያጠናክራል። " ... እኛ የገባነውን ቃል ለማክበር ቁርጠኛ ነን። " ኡሁሩ ኬንያታ ፦ " በፕሪቶሪያ ጀመርን፣ መንገዳችን እየተጠጋ ፤ አሁን ናይሮቢ ነን ፣ በሚቀጥለው ጊዜ ስብሰባችን መቐለ እንደሚሆን ተስፋ አድርጋለሁ ፤ በመጨረሻም አዲስ አበባ ላይ አብረን እናከብራለን። ይህ ጸሎታችን ፣ ተስፋ የምናደርገው እና የምንፈልገው ነው። " * ቪድዮው እና የኬንያታ ንግግር ከCitizen TV Kenya እንዲሁም የአምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የአቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር በኢትዮጵያ ኢንሳይደር ከቀረበ ዘገባ ላይ የተወሰደ ነው። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል። ሚኒስቴሩ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የነዳጅ ዋጋ #በጥቅምት_ወር በነበረው እንደሚቀጥል ገልጿል። የነዳጅ ዋጋው ከጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚዘልቅ ነው። በሁለተኛው ምዕራፍ ከመስከረም 18 ቀን 2015 ጀምሮ ዓ.ም ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በሕዳር ወር 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ አሳውቋል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ እና የህወሓት ወታደራዊ አዛዦች ኬንያ፣ ናይሮቢ ላይ ተገናኝተዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና ጀነራል ታደስ ወረደን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮች ናቸው እየተነጋገሩ የሚገኙት። በሰላም ስምምነቱ በ5 ቀናት ወታደራዊ አመራሮች እንዲገናኙ በሚያዘው መሠረት ነው የአዛዦቹ ውይይት የተጀመረው። ይህ በተመለከተ አፍሪካ ህብረት (AU) ባወጣው መግለጫ ሁለቱ የጦር አመራሮች በደቡብ አፍሪካ በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት ነው ምክክር የጀመሩት ብሏል። ዛሬ የጀመረው ውይይት በትግራይ አስችኳይ የሰብአዊ ድጋፍ መስመር ተከፍቶ የተቋርጡ አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ምክክር ይደረግብታል። በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ያለው ንግግር ለቀጣይ ቀናትም ይቀጥላል ተብሏል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ድቻ እና ወልቂጤ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ድሬዳዋ ላይ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ 10 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ እና መቻል ባደረጉት ጨዋታ ወላይታ ድቻ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግብ ቃልኪዳን ዘላለም በ31ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ… https://www.fanabc.com/archives/165004
Mostrar todo...
Mostrar todo...
የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች ስለ ኢትዮጵያ ስንዴ ምርት ምን አሉ?

#FANA_TV #FANA_NEWS #ፋና_ዜና በጉብኝቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር አልስቴር ማክፔል ተገኝተዋል።

Mostrar todo...
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ከ2 ወራት የግንባር ቆይታ በኋላ ወደ ቢሮዋቸው ተመለሱ

#FANA_TV #FANA_NEWS #ፋና_ዜና ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ከ2 ወራት የግንባር ቆይታ በኋላ ወደ ቢሮዋቸው ተመለሱ

Mostrar todo...
በሰላም ስምምነቱ ላይ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ጋር የተደረገ ውይይት

#FANA_TV #FANA_NEWS #ፋና_ዜና በሰላም ስምምነቱ ላይ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ጋር የተደረገ ውይይት