cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Sabian Secondery & Preparatory School (ሳ\ሁ\ደ\መ\ት\ቤት)

Wel Come To Our School.

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
2 607
Suscriptores
Sin datos24 horas
+67 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#MoE ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ይፋ አድርጓል። በንቅናቄው ተፈታኝ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መርሐግብር በትምህርት ቤቶች ይሰጣል። በማጠናከሪያ ትምህርቱ የተማሪዎችን የመማር ብቃትና የሥነ-ልቦና ዝግጅት ለማሳደግ እንደሚሠራ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል። ይህን ሥራ አንዳንድ ክልሎች ቀደም ብለው መጀመራቸው የሚያበረታታ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል። ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የተቋማት ባለሙያዎች፣ ወዘተ በማሳተፉ እንዲሠሩ ጥሪ አድርገዋል።
Mostrar todo...
👍 3
የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና መርሃ ግብር ይፋ ሆነ፡፡ ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ላሉ ተፈታኞች በወረቀትና በበይነ መረብ የሚሰጠው የፈተና መርሃ ግብር የሚከተለው መሆኑን እያሳወቅን ተፈታኞችና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡ የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል!! የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት https://www.facebook.com/eaes.eaes
Mostrar todo...
የሳቢያን2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሴቶች የእግር ኳስ ቡድን በዛሬው እለት 04/09/2016 የመጨረሻውን የዋንጫ ውድድር ከማርያም ሰፈር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር ተጋጥሞ 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን ለግሉ አድርጓል። እንኳን ደስ አለን!
Mostrar todo...
👍 2
መልካም የእናቶች ቀን::
Mostrar todo...
ግንቦት 2/2016 ዓመት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በማዐከል ደረጀ ለማዘጋጀት ውይይት ተካሄደ። በውይይቱ ላይም የቢሮ ምክትል ቢሮ ኋላፊ እና የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳሪክቶሬት ዳሪክተር አቶ አቡበክር አዶሽ ለስርዓት ትምህርት ባለሞያዎች ዝግጅት አስመልክቶ አቅጣጫ ሰተዋል ።
Mostrar todo...
ግንቦት 2/2016 ዓ.ም በድሬዳዋ አሰተዳደርትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል በበይነ መረብ (ኦን ላየን) ፈተናን አሰመልክቶ ለአስፈታኝ ት/ቤት ር/መራን፣ም/ር/መ/ራንና የአይሲቲ መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ተጀመረ። በመድረኩ ላይ በመገኘት ስለስልጠናው አሰፈላጊነት እንዲሁም በቀጣይ ወደ ት/ቤት ወርደው ምን መስራት እንዳለባቸው የስራ አቅጣጫ የሰጡት ም/ቢሮ ኃላፊና የስ/ት/ት/ዝና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቡበከር አዶሽ ሲሆኑ በመቀጠልም የቢሮ ኃላፊው አቶ ሱልጣን አሊይ እንዳሉትም የኦን ላየን ፈተና የማይቀር በመሆኑ ሁሉም ት/ቤቶች አሰፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያሟሉ ያስገነዘቡ ሲሆን ይህንንም የፈተና ሂደት የሚከታተል በክቡር ከንቲባው የሚመራ ስትሪንግ ኮሚቴ የሚቋቋም መሆኑን ገልፀዋል። ለአይሲቲ መምህራን ቴክኒካል የሆኑ ስልጠናዎችን የሰጡት የቢሮው የአይሲቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይርጋ ሙሉነህ ሲሆኑም ስልጠናውም እንዴት ለፈተና የሚረዱ ብራውዘሮች እንደሚጫኑ፣ተማሪዎች እንዴት user name and password በመጠቀም ፈተና መስራት እንደሚችሉ በተግባር ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥተዋል። በመጨረሻም የቢሮው የፈተና ጉዳዮች አሰተባባሪ የሆኑት አቶ አስቻለው ሸዋረጋ ርዕሰ መምህራንና የአይሲቲ ባለሙያዎች የወሰዱትን ስልጠና ወደ ት/ቤት በማውረድ ሌሎች ባለሙያዎችን በማሰልጠን ፈተና እስከሚደርስ ድረስ ተከታታይ የሆነ ስልጠና ለተማሪዎች መሰጠት እንዳለበት ያሳሰቡና የቢሮ አይሲቲ ባለሙያዎች ተከታታይነት ያለው ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉም ገልፀዋል። ስልጠናው በነገው እለት የቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት የጋራ ውይይት በማካሄድ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
Mostrar todo...
👍 2
በድሬዳዋ እስተዳደር እና በመማር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን የጋራ ትብብ ከመጋቢት 14/2016 ጀምሮ እየተካሄደ የሚነኘው ማወቅ ያሸልማል የ12 ክፍል ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር ግንቦት 10/2016 በወጣቶች ማዕከል /ኮንጎ ሜዳ/ አዳራሽ በታላቅ ድምቀት በሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር ይጠናቀቃል። ሁላችንም የፍፃሜ ውድድሩን እንድንታደም ተጋብዘናል ። ይ ቀ ር ም!!
Mostrar todo...
👍 3
Repost from ETHIO-MEREJA®
#ጤናመረጃ ኩላሊት የሚጎዱ ልማዶች (ይነበብ) አሳሳቢ የሆነው የኩላሊት ህመም ቀድሞ መከላከያ መንገዶችን ያውቃሉ ? ብዙ ልማዶች ለኩላሊት ህመም ምክንያት ናቸው እነዚህም 1. ሽንትን መቋጠር ሽንት በፊኛ ውስጥ ረጅም ሰአት ሲቆይ በውስጡ የሚያድጉት ባክቴሪያዎች ይበራከታሉ። እንዚህ ባክቴሪያዎች የሽንት ቧንቧ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊያመጡ ይችላሉ። ሽንትን መያዝ ኩላሊት ላይ በሚያደርሰው ጫናም ኩላሊት ተጎድቶ ሽንትን የመቆጣጠር ችሎታችንን ሊያጠፋ ይችላል። 2. በቂ ውሃ አለመጠጣት አንድ ሰው በቀን ቢያንስ ከ10 እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት አለበት። 3. ጨው ማብዛት ብዙ ጨው መመገብ ኩላሊታችን ላይ ከፍተኛ ጉ በምንመገበው ጨው የሚገኘውን ሶዲየም 95% ያህሉ በኩላሊታችን ነው የሚቀየረው። ጨው ስናበዛ ኩላሊታችን ጨውን ለማጣራት ይበልጥ መስራት ይኖርበታል። 4. የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ማዘውተር የኩላሊት ህመም ካለብዎ ዶክተርዎን ሳያማክሩ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን አይጠቀሙ። 5. ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች ማብዛት 6. መጠጥ ማብዛት መጠጥ ሲበዛ ኩላሊታችን አደጋ ላይ ይወድቃል። መጠጥ ኩላሊታችን እና ጉበታችን ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። 7. ሲጋራ ማጨስ 8. ቀላል ኢንፌክሽኖችን በግዜው አለመታከም። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የኩላሊት ህመም ዋና ዋና ምክንያቶች ሆነው ይጠቀሳሉ። ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር! T.me/ethio_mereja ኢትዮ-መረጃ
Mostrar todo...
👍 3