cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Dire Dawa Administration Education Office communication

DDAEOc Telegram Channel

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 950
Suscriptores
+1324 horas
+597 días
+24730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሰኔ 4/ 2016 ዓ.ም የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ8ተኛ ክፍል አስተዳደራዊ መልቀቂያ ፈተና መስጠት ተጀመረ፡፡ አስተዳደራዊ ፈተናውን ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በማሪያም ሰፈር አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ በመገኘት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሱልጣን አሊይ በተፈታኞች ፊት ወረቀቱን በመቅደድ ፈተናውን አስጀምረዋል፡፡ በዕለቱ ፈተና እየተሰጠባቸው የሚገኙ ጣቢያዎች በከተማ 14 እና በገጠር 48 ሲሆኑ ፈተናው ንም ለመውሰድ 9337 ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ምልከታ ካደረግንባቸው የከተማ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ፣ድሬ ቤቴል አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ፣ኤልጂ ቤተናታን ሁለተኛ ደረጃ፣ሳቢያን ቁጥር አንድ፣መልካ ጀብዱ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ፣ብስራተ ገብርኤል ፣ አፈተኢሳ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ፣አዲሱ ሁለተኛ ደረጃ፣አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ፣ለገሀሬ አንደ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የገጠር ት/ቤቶች ገንደ ሪጌ ፣ ኢንጀሎ፣ ሀርላ ፣ገንደ ገበታ ፣ዱጁማ፣ ቀንጨራ፣ሀሎ ቡሳ፣ጀሎ በሊና ትምህርት ቤቶችን በተዘዋወርንባቸው ትምህርት ቤቶች የፈተና አሰጣጡ ሰላማዊ በሆኑ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ለመመልከት ችለናል፡፡ በመጨረሻም በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች በነገው እለት ቀጣይ የትምህርት አይነቶች ፈተናዎች ይሰጣል፡፡
Mostrar todo...
ሰኔ 4/ 2016 ዓ.ም የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ8ተኛ ክፍል አስተዳደራዊ መልቀቂያ ፈተና መስጠት ተጀመረ፡፡ አስተዳደራዊ ፈተናውን ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በማሪያም ሰፈር አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ በመገኘት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሱልጣን አሊይ በተፈታኞች ፊት ወረቀቱን በመቅደድ ፈተናውን አስጀምረዋል፡፡ በዕለቱ ፈተና እየተሰጠባቸው የሚገኙ ጣቢያዎች በከተማ 14 እና በገጠር 48 ሲሆኑ ፈተናው ንም ለመውሰድ 9337 ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ምልከታ ካደረግንባቸው የከተማ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ፣ድሬ ቤቴል አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ፣ኤልጂ ቤተናታን ሁለተኛ ደረጃ፣ሳቢያን ቁጥር አንድ፣መልካ ጀብዱ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ፣ብስራተ ገብርኤል ፣ አፈተኢሳ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ፣አዲሱ ሁለተኛ ደረጃ፣አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ፣ለገሀሬ አንደ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የገጠር ት/ቤቶች ገንደ ሪጌ ፣ ኢንጀሎ፣ ሀርላ ፣ገንደ ገበታ ፣ዱጁማ፣ ቀንጨራ፣ሀሎ ቡሳ፣ጀሎ በሊና ትምህርት ቤቶችን በተዘዋወርንባቸው ትምህርት ቤቶች የፈተና አሰጣጡ ሰላማዊ በሆኑ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ለመመልከት ችለናል፡፡ በመጨረሻም በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች በነገው እለት ቀጣይ የትምህርት አይነቶች ፈተናዎች ይሰጣል፡፡
Mostrar todo...
ሰኔ 1/2016ዓ ም በአስተዳደሩ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ እና የተሻለ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን በማፍራት ረገድ የግል የትምህርት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት አመራሮችና ከሌሎች የዘርፉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ። በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ እንደገለዑት የመድረኩ ዋንኛ አላማ በ2016 በጀት አመት እንደ አሰስተዳደር የትምህርት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ሲደረጉ በቆዩ ጥረቶች የግል ትምህርት ቤቶች ድርሻ እና አበርክቷቸው አፈፃፀማቸው ያለበትን ደረጃ በጋራ በማየት በ2017 የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ በሚያስችል መልኩ ቅንጅታዊ አሰራርን ይበልጥ ለማጠናከር ብሎም የቀጣይ የስራ አቅጣጫን ለማስቀመጥ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ሱልጣን አክለውም ባለፉት ወራት በትምህርት ዘርፍ የተደረጉ የዳሰሳ ጥናት ላይ ግምገማዎች፣ የድጋፍና የክትትል ስራዎችን መሰረት በማድረግ በተለይም የትምህርት ቤት አመራሮችን በሚመለከት የዳሰሳ ጥናቱ ያሳየውን ውጤት መሰረት በማድረግ በጥናቱ የተመላከቱ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለማስተካከል ረገድ መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ዘርፋን ከመደገፍ አንፃር ሚናውን በአግባቡ እንዲረዱ ለማስቻል ብሎም ለተሻለ ውጤትም እያደረጉ ያለውን  ዝግጅት በጋራ ለማየት መሆኑን ተናግረዋል። በመድረኩ የግል ትምህርት ተቋማ አመራሮች እና ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን  በግል ትምህርት ቤቶች የ2016 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፖርት በተቋሙ የእቅድ ዝግጅት ከፍተኛ ባለሙያ በወ/ሮ ጌጥበዛ ተስፋዬ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል። በመድረኩም መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት ላይ የትምህርት ጥራትን ከሚቀንሱ ተግባራት ውስጥ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የትምህርት ዝግጅት ማነስ አንዱ እንደሆነ  የተጠቆመ ሲሆን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም ሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በሙሉ በጋራ መስራት እንዳለባቸው እና በአጠቃላይ በአስተዳደሩ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ እና የተሻለ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን በማፍራት ረገድ የግል የትምህርት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡም ጥሪ የቀረበ ሲሆን በመጨረሻም ከመድረኩ የተነሱ ሀሳቦችን መሰረት በማድረግ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ከተሰጠባቸው በኋላ በ2017 የትምህርት ዘመን እንደ ክፍተት የተለዩ ውስንነቶችን ማረም በሚቻልበት አግባብም የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ሀላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ የቀጣይ የስራ መመሪያና አቅጣጫም አስቀምጠዋል።
Mostrar todo...
ግንቦት 30/ 2016ዓ ም የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል አስተዳደራዊ መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት የሚያስችለው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ ትምህርት ለአንዲት ሀገር የእድገት እና የብልፅግና ጉዞ ለማድረግ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን እሙን ነው፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸው ቢሮው በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል አስተዳደራዊ መልቀቂያ ፈተናን ለማስፈጸም የሚረዱ የቅድመ ዝግጅቶች ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ካከናወናቸው ተግባራት መካከል በሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ሞዴል ፈተና በአንድ ወቅት ከማዕከል የተዘጋጀውን መስጠት መቻሉ እንዲሁም ዋናው ፈተናም ታትሞ ዝግጁ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ አቶ ሱልጣን አሊይ አክለውም የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል አስተዳደራዊ መልቀቂያ ፈተና የሚሰጥባቸው ጣቢያዎች በከተማ 14 እና በገጠር 48 የፈተና ጣቢያዎች ሲኖሩ በስሩም የጣቢያ ሀላፊዎች ስንመለከት በከተማ 16 እና በገጠር 48 የጣቢያ ሀላፊዎች እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን አስተዳደራዊ ፈተናውም የሚሰጥበት ቀን ከሰኔ 4 - 5/2016ዓ ም ተገልጿል፡፡ በአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ለሚሰጠው ፈተና ለመፈተን በ2016 ዓ.ም 9ሺ 337 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ገልፀው በዚህ ፈተና ላይ ጥሩ ውጤት ለማስምውዝገብ በሚታደርጉ ጥረት ላይ በስነ ልቦና ሳትርበሹ ትኩረታችሁን በፈተናው ላይ በማድረግ ከማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ እንዲሁም ከአላስፈላጊ መረጃዎች በመራቅ በተረጋጋ መንፈስ ፈተናቸውን እንዲወስዱ እንዲሁም ተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ውጤት እንዲገጥማቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም ፈተና ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
Mostrar todo...
ግንቦት 30/2016 ዓ ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚሰጠውን የ8ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና አስመልክቶ ለፈታኝ መምህራን እና ለባለድርሻ አካላት ስለፈተና አሰጣጡ ሂደት ኦረንቴሽን ተሰጠ! ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ በ2016 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና ለማስጀመር የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከየትምህርት ቤቱ ለተውጣጡ ለፈታኝ መምህራንና ፣ ለሱፐር ቫይዘር እና ለርዕሳነ መምህራን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በፈተናው ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ኦረንቴሽን ተሰጥቷቸዋል፡፡ በኦረንቴሽኑ መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ እንደ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ለመስጠት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የገለጹ ሲሆን ፈታናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ በከተማ አስተዳደሩ በመንግስት፣ በግል፣ በማታ የሚማሩ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የተገለጸ ሲሆን በዚህም 9ሺ 337 ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ ተጠቁሟል። ፈተናው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን በየዘርፉ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው በኦረንቴሽኑ ተነግሯል። የፈተና አስተዳደር ከፍተኛ ባለሞያ የሆኑት አቶ አስቻልው ሸዋረጋ በኦረንቴሽኑ መድረኩ ላይ ለፈታኝ መምህራንና ፣ ለሱፐር ቫይዘር እና ለርዕሳነ መምህራን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በፈተናው ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሰነድ አቅርበዋል፡፡ ስለሆነም ተፈታኝ ተማሪዎች የመፈተኛ ጣቢያ በሚገቡበት ወቅት የፀጥታ አካላት ፍተሻ ስለሚደረግ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እና ከማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ እንዲሁም ከአላስፈላጊ መረጃዎች ርቀው በተረጋጋ መንፈስ ፈተናቸውን እንዲወስዱ የፈተና አስተዳደር ከፍተኛ ባለሞያው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ፈተናውም የፊታችን ማክሰኞ ማለትም ከሰኔ 4 እስከ ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡
Mostrar todo...