es
Feedback
Nikodimos Christian center

Nikodimos Christian center

Ir al canal en Telegram

Nikodimos Show is a unique program which is hosted by the famous Ethiopian Gospel Singer Tigist Ejigu, https://www.facebook.com/tigist.ejigu.5 This show is working on creating awareness on sensitive Christian issues inside the Church of Ethiopia.

Mostrar más
6 504
Suscriptores
-124 horas
-247 días
-4830 días

Carga de datos en curso...

Nube de Etiquetas
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Menciones Entrantes y Salientes
---
---
---
---
---
---
Atraer Suscriptores
septiembre '26
septiembre '26
+5
en 0 canales
agosto '26
+70
en 1 canales
Get PRO
julio '26
+108
en 0 canales
Get PRO
junio '26
+114
en 0 canales
Get PRO
mayo '26
+132
en 0 canales
Get PRO
abril '26
+145
en 0 canales
Get PRO
marzo '26
+263
en 1 canales
Get PRO
febrero '26
+222
en 0 canales
Get PRO
enero '26
+176
en 1 canales
Get PRO
diciembre '25
+275
en 0 canales
Get PRO
noviembre '25
+400
en 0 canales
Get PRO
octubre '25
+699
en 0 canales
Get PRO
septiembre '25
+1 887
en 0 canales
Get PRO
agosto '25
+14
en 0 canales
Get PRO
julio '25
+19
en 0 canales
Get PRO
junio '25
+16
en 0 canales
Get PRO
mayo '25
+21
en 1 canales
Get PRO
abril '25
+29
en 0 canales
Get PRO
marzo '25
+32
en 0 canales
Get PRO
febrero '25
+31
en 0 canales
Get PRO
enero '25
+64
en 0 canales
Get PRO
diciembre '24
+57
en 0 canales
Get PRO
noviembre '24
+58
en 0 canales
Get PRO
octubre '24
+170
en 0 canales
Get PRO
septiembre '24
+142
en 0 canales
Get PRO
agosto '24
+652
en 0 canales
Get PRO
julio '24
+16
en 0 canales
Get PRO
junio '24
+17
en 0 canales
Get PRO
mayo '24
+178
en 0 canales
Get PRO
abril '24
+552
en 0 canales
Get PRO
marzo '24
+2 030
en 0 canales
Fecha
Crecimiento de Suscriptores
Menciones
Canales
02 septiembre+2
01 septiembre+3
Publicaciones del Canal
2
https://youtu.be/a_TLhAq1OSg
348
3
357ኛ ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዘወትር ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ቲክቶክ live እና ቴሌግራም ላይ ኑ የእግዚአብሔርን ቃል እናጥና:: ዛሬ የምናነበው ክፍል የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 10 - 12
357ኛ ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዘወትር ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ቲክቶክ live እና ቴሌግራም ላይ  ኑ የእግዚአብሔርን ቃል እናጥና:: ዛሬ የምናነበው ክፍል የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ  10 - 12 የዩቱብ  የቲክቶክ እና የቴሌግራም ሊንኮችን ከታች  ታገኛላችሁ👇 YOUTUBE#1:- www.youtube.com/NikodimosShow YOUTUBE#2:- www.youtube.com/@thewordwithtg316 TIKTOK#1:- tiktok.com/tigistejiguwondmu TIKTOK#2:-  tiktok.com/nikodimoschrstiancenter TELEGRAM:- https://t.me/nikodimosshow
425
4
#ቶሎ_ና! 3 ቀን ብቻ ቀረው! የእህታችን አገልጋይ ትዕግሥት እጅጉ ቶሎ ና የተሰኘው የክርስቶስን ምፅአት እንድንናፍቅ የሚያስታውሰን፣ ኢየሱስን የሚሰብከን ቶሎ ና የተሰኘ ኢፒ (ግማሽ አልበም) የፊታ
#ቶሎ_ና! 3 ቀን ብቻ ቀረው! የእህታችን አገልጋይ ትዕግሥት እጅጉ ቶሎ ና የተሰኘው የክርስቶስን ምፅአት እንድንናፍቅ የሚያስታውሰን፣ ኢየሱስን የሚሰብከን ቶሎ ና የተሰኘ ኢፒ (ግማሽ አልበም) የፊታችን ቅዳሜ ነሀሴ 30 ከ8:30 ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ እነሆ 3 ቀን ብቻ ቀረው። በእለቱ የእግዚአብሔር ቃል እንዲሁም ዝማሬ ይቀርባል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡ #ኒቆዲሞስ_ክርስቲያን_ሴንተር!
465
5
#ና! #3_ቀናት_ብቻ_ቀሩን! "አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ተስፋችን ይህ ነው!" መስከረም 1 ዘፍጥረት 1 ብለን የጀመርነው ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ጉዞአችን በእግዚአብሔር ፈቃድና እርዳታ እነሆ
#ና! #3_ቀናት_ብቻ_ቀሩን! "አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ተስፋችን ይህ ነው!" መስከረም 1 ዘፍጥረት 1 ብለን የጀመርነው ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ጉዞአችን በእግዚአብሔር ፈቃድና እርዳታ እነሆ ራእይ 22 ብለን ነሐሴ 30፣ 2018 ልንጨርስና በአካል ልንገናኝ 3 ቀናት ብቻ ቀርተውናል። ቀን ፡- ነሐሴ 30/2018 ሰዓት :- ከ 8:00 ጀምሮ ቦታ :- ዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን ቦሌ አጥቢያ #ጌታ_ኢየሱስ_ሆይ_ና! #መስከረም1_ዘፍጥረት1_ጿግሜ5_ራዕይ22 ኒቆዲሞስ ክርስቲያን ሴንተር
525
6
https://youtu.be/gK5I98HsQ5o
679
7
https://youtu.be/Ek1Ole0TaZ0?si=kq46TDu1Z0XdUPeL
663
8
Sin texto...
651
9
356ኛ ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዘወትር ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ቲክቶክ live እና ቴሌግራም ላይ ኑ የእግዚአብሔርን ቃል እናጥና:: ዛሬ የምናነበው ክፍል የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 7 - 9 የዩ
356ኛ ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዘወትር ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ቲክቶክ live እና ቴሌግራም ላይ  ኑ የእግዚአብሔርን ቃል እናጥና:: ዛሬ የምናነበው ክፍል የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ  7 - 9 የዩቱብ  የቲክቶክ እና የቴሌግራም ሊንኮችን ከታች  ታገኛላችሁ👇 YOUTUBE#1:- www.youtube.com/NikodimosShow YOUTUBE#2:- www.youtube.com/@thewordwithtg316 TIKTOK#1:- tiktok.com/tigistejiguwondmu TIKTOK#2:-  tiktok.com/nikodimoschrstiancenter TELEGRAM:- https://t.me/nikodimosshow
672
10
#ና! #4_ቀናት_ብቻ_ቀሩን! "ንጉሣችን ይመጣል! እኛም ዝግጁ እንሁን!" መስከረም 1 ዘፍጥረት 1 ብለን የጀመርነው ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ጉዞአችን በእግዚአብሔር ፈቃድና እርዳታ እነሆ ራእይ
#ና! #4_ቀናት_ብቻ_ቀሩን! "ንጉሣችን ይመጣል! እኛም ዝግጁ እንሁን!" መስከረም 1 ዘፍጥረት 1 ብለን የጀመርነው ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ጉዞአችን በእግዚአብሔር ፈቃድና እርዳታ እነሆ ራእይ 22 ብለን ነሐሴ 30፣ 2018 ልንጨርስና በአካል ልንገናኝ 4 ቀናት ብቻ ቀርተውናል። ቀን ፡- ነሐሴ 30/2018 ሰዓት :- ከ 8:00 ጀምሮ ቦታ :- ዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን ቦሌ አጥቢያ #ጌታ_ኢየሱስ_ሆይ_ና! #መስከረም1_ዘፍጥረት1_ጿግሜ5_ራዕይ22 ኒቆዲሞስ ክርስቲያን ሴንተር
692
11
4 ቀን ብቻ ቀረው!
4 ቀን ብቻ ቀረው!
679
12
https://youtu.be/TCppo_VC9FM
734
13
https://youtu.be/V8AtWeXsJSI
719
14
https://youtu.be/ztlgigP4q_o?si=r8GhoUVBVkmFv9I5
685
15
355ኛ ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዘወትር ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ቲክቶክ live እና ቴሌግራም ላይ ኑ የእግዚአብሔርን ቃል እናጥና:: ዛሬ የምናነበው ክፍል የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 4 - 6 የዩ
355ኛ ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዘወትር ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ቲክቶክ live እና ቴሌግራም ላይ  ኑ የእግዚአብሔርን ቃል እናጥና:: ዛሬ የምናነበው ክፍል የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ  4 - 6 የዩቱብ  የቲክቶክ እና የቴሌግራም ሊንኮችን ከታች  ታገኛላችሁ👇 YOUTUBE#1:- www.youtube.com/NikodimosShow YOUTUBE#2:- www.youtube.com/@thewordwithtg316 TIKTOK#1:- tiktok.com/tigistejiguwondmu TIKTOK#2:-  tiktok.com/nikodimoschrstiancenter TELEGRAM:- https://t.me/nikodimosshow
688
16
#ና! #5_ቀናት_ብቻ_ቀሩን! "ኢየሱስ ይመጣል እኛንም ይወስደናል ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንሆናለን!" መስከረም 1 ዘፍጥረት 1 ብለን የጀመርነው ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ጉዞአችን በእግዚአብሔር
#ና! #5_ቀናት_ብቻ_ቀሩን! "ኢየሱስ ይመጣል እኛንም ይወስደናል ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንሆናለን!" መስከረም 1 ዘፍጥረት 1 ብለን የጀመርነው ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ጉዞአችን በእግዚአብሔር ፈቃድና እርዳታ እነሆ ራእይ 22 ብለን ነሐሴ 30፣ 2018 ልንጨርስና በአካል ልንገናኝ 5 ቀናት ብቻ ቀርተውናል። ቀን ፡- ነሐሴ 30/2018 ሰዓት :- ከ 8:00 ጀምሮ ቦታ :- ዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን ቦሌ አጥቢያ #ጌታ_ኢየሱስ_ሆይ_ና! #መስከረም1_ዘፍጥረት1_ጿግሜ5_ራዕይ22 ኒቆዲሞስ ክርስቲያን ሴንተር
696
17
 በእግዚአብሔር ምድር አይቀመጡም፤ኤፍሬም ወደ ግብፅ ይመለሳል፤የረከሰውንም ምግብ በአሦር ይበላል።”(አ.መ.ት)   ግብፅ የባርነትና ወደ ኋላ የመመለስ ተምሳሌት ናት ፡ በእግዚአብሔር የተዋጀና ነፃ የወጣ ህዝብ ባለመታዘዝ ከፀና ወደ ነበረበት ሊመለስ ይችላል   ወደ ገላትያ ሰዎች 5 1 በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።   2 ጴጥሮስ 5 20ጌታችንንና አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ እንደ ገና ተጠላልፈው ቢሸነፉ ከመጀመሪያው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታቸው የከፋ ይሆንባቸዋል። (አ.መ.ት)   ሀጢአት ነፃነት ሰጣችኋለሁ ቢለንም ወደ ባርነት ነው የሚመልሰን   7-9 ነቢዩ እንደሞኝና እንደ እብድ ተቆጥሯል   እስራኤል አመፃቸው በዝቶ መልዕክቱን በመቀበል ፈንታ መልዕክተኛው ላይ ጥቃት ይሰነዝሩ ጀመር   የደነደነ ልብ ተግሳፅን በመቀበል ፈንታ በሚገስፀው ላይ ዞሮ ጠላት ይሆንበታል   የሐዋርያት ሥራ 7 52 -53 ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም።   መልክተኛውን የሚቃወም መልዕክቱንና ላኪውን ይቃወማል   “10እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤልን ባገኘሁ ጊዜ የወይን ዘለላን ከምድረ በዳ እንደ ማግኘት ነበር፤ የቀድሞ አባቶቻችሁን ባየሁ ጊዜ ቀድሞ የጐመራውን የበለስ ፍሬ እንደማየት ነበር፤ ወደ በዓል ጴዖር በደረሱ ጊዜ ግን ራሳቸውን ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ለይተው አቀረቡ፤ እነርሱም እንደዚያ እንደሚወዱት ጣዖት የረከሱ ሆኑ።”(አ.ት)   እግዚአብሔር እስራኤልን መውደዱን አላቋረጠም ፡ ህዝቡ ግን ልቡን ለጣኦታት ፍቅሩን ለሌሎች አማልክት ሰጠ   የዮሐንስ ራእይ 2 4 ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።   11-14 ክብር እንደወፍ በረረ   “11. የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤መውለድ፣ ማርገዝና መፀነስ የለም።” (አ.መ.ት)   የህጉ እርግማን የሆኑት ፡ መካንነት ፡ ማጣት ፡ ጭንገፋ እና መገደል  ይደርስባቸዋል ፡ ይህ ደግሞ በእነርሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በልጆቻቸውም ላይ ጉዳት ያስከትላል   ሀጢአት ግለሰብን ብቻ ሳይሆን ትውልድንም ይጎዳል   15-17 አሳድዳቸዋለሁ !   “17እርሱን ስላልታዘዙ አምላኬ ይጥላቸዋል፤ እነርሱም በአሕዛብ መካከል በመንከራተት ይኖራሉ።”(አ.መ.ት)   የእስራኤል ችግር እውነትን አለማወቅ ወይንም ሀይማኖታዊ ስርአቶችን አለመፈፀም አይደለም ፡ በሚያውቁት እውነት አለመሄድ (አለመታዘዝ) ነው እንጂ   ወደ ዕብራውያን 3 15 እየተባለ። ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት፥ በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።   መታዘዝ የሌለበት መስማት አይጠቅምም   ምን እንማር   1.       መንፈሳዊ ጤንነታችንን በምድራዊ ስኬት (ብልፅግና) አንለካ   2.      ሀጢአት ወደ ነፃነት ሳይሆን መልሶ ወደ ባርነት ነው የሚያስገባን   3.      ለጌታ ያለንን የመጀመሪያ ፍቅራችንን እንጠብቀው(አናስነካው)   4.      የእግዚአብሔርን ተግሳፅ ሰምቶ ለመመለስ ያልደነደነ ልብ እንዲኖረን እንትጋ ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ 10   እስራኤል በብልፅግናዋ ታበየች   1-2 የእግዚአብሔርን በረከት አግባብ ላልሆነ አላማ አዋሉት   እግዚአብሔር አብዝቶ በባረካቸው ቁጥር ወደ እግዚአብሔር በመጠጋትና እርሱን በማክበር ፈንታ ጣኦታትን ያበዙ ነበር   ባራኪውን በበረከቱ ተክተውት ነበር   “ልባቸው አታላይ ነው”   የሰው ልጅ ዋናው ችግር ያለው ልቡ ላይ ነው   የእግዚአብሔር በረከት ወደ እግዚአብሔር ሊያስጠጋን እንጂ ሊያርቀን አይገባም   3-8 ጣኦቶቻቸው ይፈራርሳሉ   “3ሕዝቡ “እግዚአብሔርን መፍራት ስለ ተውን ንጉሥ አጥተናል፤ ንጉሥ ቢኖረንስ ምን ያደርግልናል?” ይላሉ።”(አ.ት)   በእግዚአብሔርና እርሱ በሚሰጣቸው አመራር ሳይሆን በጣኦቶቻቸው ተማምነው ነበር   የታመኑባቸው ጣኦቶቻቸው ከእነርሱ ጋር ይማረካሉ እስራኤል በጣኦቶቹ ይኖራል !   9-10 በጊብአ የሰራችሁት ሀጢአት ይታሰባል   መሳፍንት ምዕራፍ 19-21 ያለውን ታሪክ ያስታውሳቸዋል ፡ ጊብአ የእርኩሰት የአንገት ደንዳናነት እና ንስሀ ያለመግባት ምሳሌ ነው   እስራኤል በዚያው አይነት ሀጢአት እስከዚህ ጊዜ ፀንተዋል እንጂ አልተለወጡም   ተናዘን ያልተውነው (ችላ ያልነው) ሀጢአት በህይወታችን እየደጋገመ ይመጣል እንጂ በራሱ ጊዜ አያልፍም   11-13 መዝራትና ማጨድ   ፅድቅን ዝሩና ፅኑ ፍቅርን እጨዱ ብያችሁ ነበር እናንተ ክፋትን ዘርታችሁ ግፍን አጨዳችሁ አዝመራውን ያልወደደ ዘሩን ነው መቀየር ያለበት   የያዕቆብ መልእክት 3 18 የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል።   ድንገተኛ አዝመራ የለም   “እዳሪውን መሬት እረሱ”   የደነደነውን ልብ አለስልሱ ማለት ነው   14-15 ፍርድ እየመጣ ነው!   እግዚአብሔር ፅድቅን ዝሩ ፡ ልባችሁን ገር አድርጉ ፡ እኔን ፈልጉ ሲላቸው ወደ ፍርድ እንዳይገቡ ሊያስጠነቅቃቸው ነው ፡ ሰምተው ካልታዘዙ ግን የእግዚአብሔር ማስጠንቀቂያ ማስፈራሪያ ስላልሆነ እንደተናገረው መፈፀሙ አይቀርም   ምን እንማር ?   1.       የእግዚአብሔር በረከት በጥንቃቄ ካልተያዘ ከእግዚአብሔር ሊያርቀን ይችላል “በረከቴ ወደ የት እየሳበኝ ነው?”   2.      ሀጢአትን ተናዘን በመተው እንጂ ችላ በማለት ከህይወታችን አናስወግደውም   3.      የምንዘራውን እንጂ የምናጭደውን መምረጥ አንችልም   4.      የእግዚአብሔር ማስጠንቀቂያ የምህረቱና የፍቅሩ መገለጫ እንጂ ተራ ማስፈራሪያ አይደለም
621
18
የዮሐንስ ራእይ 3 15 በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። 16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።   “የሙሉ ጊዜ አዳኝ የሚፈልግ የትርፍ ጊዜ ክርስቲያን አንሁን”   “9. እንግዶች ጒልበቱን በዘበዙ፤እርሱ ግን አላስተዋለም።ጠጒሩም ሽበት አወጣ፤እርሱ ግን ልብ አላለም።”(አ.መ.ት)   እስራኤል ጉልበቱ እየተበዘበዘ (እየደከመ) ግን አላወቀም   ሀጢአት ቀስ በቀስ መንፈሳዊ ህይወታችንን ሲበዘብዝና ሲያደክም አይታወቀንም   መንፈሳዊ ድካም አደገኛነቱ እንደ አካላዊ ድካም ፈጥኖ አለመታወቁ ነው   የዮሐንስ ራእይ 3 17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥   እራስን ማታለል አደገኛ መንፈሳዊ ችግር ነው   10-12 እስራኤል አዕምሮ እንደሌላት እርግብ ነው   እርዳታ ፍለጋ ወደ እግዚአብሔር በመጮህ ፋንታ አንዴ ወደ ግብፅ አንዴ ደግሞ ወደ አሶር ይጮሀሉ   ስንፈራ መጀመሪያ የምንጮኸው ወደ ማን ነው ?   እግዚአብሔር አስቀድመን ወደ እርሱ እንድንጣራ ይፈልጋል   13-16 ከልባቸው ወደ እኔ አይጮሁም   ያስቅሳሉ ፡ የሚያስለቅሳቸው ግን የመከራው ብዛት ነው እንጂ ለንስሀ አይደለም   ከችግር ለመውጣት ማልቀስና እውነተኛ ንስሀ የተለያዩ ነገሮች ናቸው   “15. እኔ አሠለጠንኋቸው፤ አጠነከርኋቸውም፤እነርሱ ግን አደሙብኝ።”(አ.መ.ት)   እግዚአብሔር በሰጠን ነገር እግዚአብሔርን እናክብር   ምን እንማር   1.        አንዳንድ ጊዜ ለመፈወስ መታመም አለ   2.      እግዚአብሔር በግማሽ ልብ የምንከተለው አምላክ አይደለም   3.      ሀጢአት ሳያሳውቅ እንደ ምስጥ መንፈሳዊ ህይወትን ይቦረቡራል   4.      እርዳታን ከእግዚአብሔር ውጪ መፈለግ አእምሮ እንደሌለው እርግብ እንደመሆን ነው ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ 8   እስራኤል አውሎ ንፋስን ታጭዳለች   1-3 የማስጠንቀቂያ መለከት   ጠላት በእስራኤል ላይ እንደንስር እየመጣ ስለሆነ “መለከትን በአፍህ ላይ አድርግ”   “2. እስራኤልም፣ ‘አምላካችን ሆይ፤ እኛ እናውቅሃለን’ እያሉ፣ወደ እኔ ይጮኻሉ።”(አ.መ.ት)   እግዚአብሔርን ማወቅ ከንግግር ያለፈ የሚኖር ህይወት ነው   የማቴዎስ ወንጌል 7 21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። 22 በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። 23 የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።   ወደ ቲቶ 1 16 እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።   ስለ እግዚአብሔር ማወቅ እግዚአብሔርን ማወቅ አይደለም   “4. ያለ እኔ ፈቃድ ነገሥታትን አነገሡ፤እኔንም ሳይጠይቁ አለቆችን መረጡ፤በብራቸውና በወርቃቸው፣ለገዛ ጥፋታቸው፣ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።”(አ.መ.ት)   “ያለኔ ፍቃድ…እኔን ሳይጠይቁ”   የእግዚአብሔርን ጥቅሙን እንጂ ጌትነቱን አይፈልጉም   5-6 እጅ የሰራው ይህ ጥጃ አምላክ አይደለም   የተፈጠረ (እጅ የሰራው ነገር) አምላክ እንዳይሆንብን ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል   “7. “ነፋስን ይዘራሉ፤ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤አገዳው ዛላ የለውም፤ዱቄትም አይገኝበትም፤እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ባዕዳን ይበሉታል።”(አ.መ.ት)   አዝመራ (አጨዳ) ሁልጊዜም ከተዘራው ዘር በብዙ እጥፍ ይበዛል   ክፉም ይሁን መልካም የተዘራ ነገር መብቀሉ አይቀርም ሲበቅል ደግሞ የተዘራውን ያህል ብቻ አይደለም   ወደ ገላትያ ሰዎች 6 7 አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ 8 በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።   የያዕቆብ መልእክት 1 14 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። 15 ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።   8-10 እስራኤል ለእርዳታ ወደ አህዛብ ጮሁ   “ለብቻው እንደሚባዝን የዱር አህያ …ሆነዋል”   ከእግዚአብሔር ተለይቶ በራስ ለመቆም (እራስን ለመቻል) መሞከር ነፃነት ሳይሆን ባርነት ነው   የዮሐንስ ወንጌል 15 5 እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።   አፈጣጠራችን ከእርሱ ጋር ለመጣበቅና በእርሱ ለመደገፍ ነው እንጂ በራሳችን ለመቆም አይደለም   11-13 መሰዊያ ብታበዙም ሀጢአታችሁ ይበዛል !   ሀይማኖተኝነታቸው እየከረረ ህይወታቸው ግን ከእግዚአብሔር እየራቀ ይሄድ ነበረ   የማቴዎስ ወንጌል 15 8 ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ 9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።   እግዚአብሔር በሀይማኖት ሳይሆን በእውነትና በመንፈስ የሚያመልኩትን ይሻል   14“የእስራኤል ሕዝብ ለራሳቸው ታላላቅ ቤተ መንግሥቶች ሠርተዋል፤ እኔን ፈጣሪአቸውን ግን ረስተዋል፤ የይሁዳም ሕዝብ ብዙ የተመሸጉ ከተሞችን ሠርተዋል፤ ስለዚህ ከተሞቻቸውንና ምሽጎቻቸውን የሚያቃጥል እሳት እልክባቸዋለሁ።” (አ.ት)   “እስራኤል ፈጣሪያቸውን ረስተዋል”   የችግራቸው ሁሉ ምንጭ አለማወቅ ሳይሆን መርሳት ነው   አብዛኛውን ጊዜ የእግዚአብሔር ህዝብ የሚገባበት ወጥመድ ከመነሻው ግልፅ የሆነ አመፅ ሳይሆን ቀስ በቀስ የሚከሰት እግዚአብሔርን መርሳት ነው   እስራኤል ሀይማኖታዊ ስርአቶችን አስታውሰው ይፈፅማሉ ፡ እግዚአብሔርን ግን ረስተዋል   ወደ ዕብራውያን 2 1 ስለዚህ ከሰማነው ነገር ምናልባት እንዳንወሰድ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል።   መንፈሳዊ ውድቀት በድንገት (በአንድ ጊዜ) ሳይሆን ቀስ በቀስ ነው የሚከሰተው   ምን እንማር   1.       ኢየሱስን እንደ አዳኝ ብቻ ሳይሆን እንደ ጌታም እንቀበለው   2.      ክፉም ይሁን መልካም የምንዘራው ነገር በዝቶ ስለምናጭደው ምን እንደምንዘራ እንጠንቀቅ   3.      ከጌታ ተለይቶ በራስ መቆም ነፃነት ሳይሆን እውነተኛ ባርነት ነው   4.      እግዚአብሔርን መርሳት የመንፈሳዊ ውድቀት ስር ነው ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ 9   በእስራኤል ላይ የሚደርሰው ቅጣት   1-2 እስራኤል ሆይ ….. እንደ ሌሎች ህዝቦች ደስ አይበልሽ   እስራኤል ለእግዚአብሔር ጀርባዋን ሰጥታ በምድራዊ ብልፅግና ሀሴት እያደረገች ነበር   ጥሩ አዝመራ ማግኘታቸውን ሁሉ ሰላም እንደሆነና እግዚአብሔር እንደተቀበለው ማረጋገጫ አድርገው ወስደውታል   ውጫዊ ስኬት ሁልጊዜ የመንፈሳዊ ጤንነት ማረጋገጫ ተደርጎ ሊወስድ አይችልም   “2ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ከዐውድማችሁ እህልን፥ ከመጭመቂያችሁም የወይን ጠጅን ከቶ አታገኙም፤ አዲስ የወይን ጠጅም አይገኝም።”(አ.ት)   እንደ ማረጋገጫ የወሰዱትን ነገር አጠፋዋለሁ አላቸው   አንዳንድ ጊዜ ምድራዊ ስኬት መንፈሳዊ ውድቀታችንን እንዳናይ ሊጋርድብን ይችላል   3-6 ስደት (ምርኮ) እየመጣባችሁ ነው   “3.
452
19
ትንቢተ ሆሴእ ምእራፍ 6-10 ሆሴዕ(መዳን ፡ ያድናል)ማለት እንደሆነ አይተናል   722 አ.አ. (አሶር እሰራኤልን ከማፍለሷ ጥቂት ቀደም ብሎ የሰሜኑን መንግስት (እስራኤልን) ያገለገለ ነቢይ ነው   ዋና ሀሳቡ የእግዚአብሔር የኪዳን ፍቅር ታማኝ ላልሆነችው እስራኤል የሚል ነው   በሆሴዕ መጽሐፍ ላይ እግዚአብሔር ኪዳኑን ላልጠበቀው ህዝብ ፍርድ ብቻ ሳይሆን አስደናቂ ፍቅር እንዳለውም እናያለን   ሆሴዕ በትዳሩ አማካኝነት ለህዝቡ መልዕክት ያስተላለፈ ሰው ነበረ ፡ ሆሴዕ ለኪዳኑ ታማኝ እንደሆነው እንደ እግዚአብሔር ፡ ጎሜር(ሚስቱ) ደግሞ እንደ አመንዝራዋ እስራኤል ሆነው ቀርበዋል   ጎሜር በተደጋጋሚ ሆሴዕን እንደምትክደውና ጥላው እንደምትኮበልል እስራኤልም በእግዚአብሔር ላይ እንዲሁ ታደርግ ነበረ ፡ ሆሴዕ ጎሜርን በተደጋጋሚ ተከታትሎ የራሱ እንደሚያደርጋት ሁሉ እግዚአብሔርም ለእስራኤል እንዲሁ ያደርግ ነበረ   ቁልፍ ቃሉ ፡ “የኪዳን ፍቅር” ነው   ቁልፍ ጥቅሱ ሆሴዕ 6፡6 ነው ሆሴዕ 6 6. ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፣ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እሻለሁና። (አ.መ.ት)   ጌታ ኢየሱስ ይህንን ቁልፍ ጥቅስ ለፈሪሳውያን ጠቅሶታል   የማቴዎስ ወንጌል 9 13 ነገር ግን ሄዳችሁ። ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።   የማቴዎስ ወንጌል 12 7 ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ብታውቁስ ኃጢአት የሌለባቸውን ባልኰነናችሁም ነበር።   ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ 6   እግዚአብሔር ባዶ የሀይማኖት ልምምድን ሳይሆን እውነተኛ ልብን ነው የሚፈልገው   1-3 ኑ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ   “1. “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤እርሱ ሰባብሮናል፤እርሱም ይጠግነናል፤እርሱ አቊስሎናል፤እርሱም ይፈውሰናል።”(አ.መ.ት)   ሰብሮ መጠገን የእረኞች ልምምድ ነው ፡ እየባዘኑ (እየጠፉ) የሚያስቸግሩ በጎችን ጠፍተው እንዳይቀሩና የአውሬ እራት እንዳይሆኑ እረኛው ሰብሮ ይጠግናቸዋል ቁስላቸው እስከሚድን ከእረኛው አጠገብ ስለማይለዩ እረኛቸውን ማወቅ ይሆንላቸዋል   “2. ከሁለት ቀን በኋላ ያነቃናል፤በእርሱም ፊት እንድንኖር፣በሦስተኛው ቀን ያስነሣናል።”(አ.መ.ት)   ሀጢአታቸው ከተፈረደበት በኋላ ስለሚኖረው ተሀድሶ (restoration) የሚናገር ሲሆን በሌላ አቅጣጫ ደግሞ ትንሳኤን በሩቅ እንድናይ የሚያደርግ ነው   ሀጢአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በክርስቶስ መስቀል ላይ ከተፈረደበት በኋላ በሶስተኛው ቀን ክርስቶስ ተነስቷል !   “3. እግዚአብሔርን እንወቀው፤የበለጠ እናውቀውም ዘንድ እንትጋ፤እንደ ንጋት ብርሃን፣በእርግጥ ይገለጣል፤ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።” (አ.መ.ት)   የንጋት ብርሀን ሳይመጣ ቀርቶ እንደማያውቅ ሁሉ እግዚአብሔርም ሊያውቁት ለሚተጉ በእርግጥ ይገለጣል! እንደ በልግ ዝናብ ጥማታቸውን ያረካል   “4እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! እናንተን ምን ላድርጋችሁ? እናንተ ለእኔ ያላችሁ ፍቅር እንደ ማለዳ ጉምና እንደ ጠዋት ጤዛ ፈጥኖ ይጠፋል።”(አ.ት)   ስሜታዊ ሆነው ንስሀ ቢገቡም በንስሀቸው ፀንተው መቆምና መለወጥ አይታይባቸውም   ንስሀ በገባንበት ጉዳይ ፀንተን እንዳንቆም የሚደርጉ ተግዳሮቶች እንዳሉ ማወቅና መጠንቀቅ ያስፈልጋል   1.       ቃሉ በልባችን ስር አለመስደዱ   2.      የዚህ አለም ሀሳብና የሀብት ፍቅር   “6. ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፣ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እሻለሁና።”(አ.መ.ት)   ይህ የመጽሐፉ ቁልፍ ጥቅስ ነው   እግዚአብሔር እራሱ የሰጠውን የመስዋዕት ስርአት እየተቃወመ ሳይሆን ከልብ ያልሆነ (የላይ የላይ የሆነ) ባዶ ሀይማኖታዊ ስርአት አይጠቅምም እያለ ነው   ማቴዎስ 9 13. ሄዳችሁ፣ ‘ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤’ የሚለውን ቃል ትርጕም አጢኑ፤ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና።”(አ.መ.ት) ማቴዎስ 12 7. ‘ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ’ የሚለው ቃል ምን ማለት እንደሆነ ብታውቁ ኖሮ፣ በንጹሐን ላይ ባልፈረዳችሁ ነበር። (አ.መ.ት)   ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት አኗኗራችንንና ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነት ሊቀርፅ ይገባል   “7. እንደ አዳም ቃል ኪዳንን ተላለፉ፤በዚያም ለእኔ ታማኝ አልነበሩም።”(አ.መ.ት)   አዳም በኤደን ገነት ተፈትኖ እንደወደቀ እሰራኤልም በተስፋይቱ ምድር ወድቃለች   የሰው ዘር ከአዳምም ከእስራኤልም የተሻለ ወኪል (ተፈትኖ የሚያልፍ አዳኝ) ያስፈልገው ነበር   ወደ ሮሜ ሰዎች 5 19 በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።   8-11 አመፅ በሁሉም ስፍራ ተንሰራፍቷል !   ክፋት ፡ ጥቃት ፡ ደም መፍሰስ ፡ የካህናት ወንጀል ዝሙትና እርኩሰት ምድሪቱን ሞልቷታል !   ውጫዊ የሀይማኖት ስርአቶችን መፈፀም ባያቋርጡም ውስጣቸው ግን ተበክሏል   ሀይማኖታዊ ልምምድ ውስጣዊ ብክለትን አያፀዳም   ምን እንማር ?   1.       ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ልማዳዊ ነው ? ወይንስ ልባዊ ? የሚለውን እንመርምር   2.      ሀይማኖታዊ ስርአቶችን መፈፀም የመንፈሳዊ ህይወታችን ጤንነት ማረጋገጫ አይደለም   3.      እለት እለት እግዚአብሔርን ለማወቅ እንጠማ   4.      ንስሀችን እንደማለዳ ጤዛ እንዳይሆን በቃሉ ስር እንስደድ የሀብት ፍቅርን እናስወግድ ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ 7   ልቡ ከእግዚአብሔር የራቀ ህዝብ የሚገጥመው ውድቀት   1-2 ክፋታችሁን እገልጣለሁ   “እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ…..ሀጢአታቸውና ክፋታቸው ይገለጣል”   እውነት ከመፈወሱ በፊት ያሳምማል ፡ ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ለመፈወስ መታመም አለ   “2. ነገር ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ፣እነርሱ አይገነዘቡም፤ኀጢአታቸው ከቦአቸዋል፤ሁልጊዜም በፊቴ ናቸው።”(አ.መ.ት)   ከእግዚአብሔር አይን የተሰወረ አንዳች ነገር የለም   ወደ ዕብራውያን 4 13 እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።   እግዚአብሔር የተገለጠውን ድርጊታችንን ብቻ ሳይሆን የተሰወረ መነሻ ሀሳባችንንም ይመለከታልና በፍርዱ አይሳሳትም   3-7 የረከሱ መሪዎችና የረከሰ ህዝብ   ንጉሳቸው ፡ አለቆቻቸውና ገዢዎቻቸው ረክሰዋልና ህዝቡም ደግሞ ለዝሙት ፡ ለሴራና ደም ለማፍሰስ ልባቸው እንደምድጃ የጋለ ነው   እግዚአብሔርን ከመካከሉ ያስወጣ ማህበረሰብ ይህንን ይመስላል   ብዙ ማህበራዊ ቀውሶች መነሻ ችግራቸው መንፈሳዊ ነው   “8 ፤ ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፤ ኤፍሬም እንዳልተገላበጠ ቂጣ ነው።”   ያልተገላበጠ …. በአንዱ በኩል የበሰለና በሌላኛው በኩል ሊጥ የሆነ ለምንም የማይጠቅም ሆነዋል   በአንዱ በኩል ለእግዚአብሔር በሌላ በኩል ለጣኦት የተሰጠ የማይጠቅም ህዝብ ሆነዋል   እግዚአብሔርንም ይፈልጋሉ (ጥበቃውን አቅርቦቱን ምሪቱን) ደግሞም የአህዛብን ጣኦታት ይከተላሉ   እግዚአብሔር በግማሽ ልብ የምንከተለው አምላክ አይደለም   የማቴዎስ ወንጌል 6 24 ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።  
444
20
12 -13 ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤   በዚህ ዘመን ያለው አመንዝራነት የሚገለፀው በመጎምጀት ነው እግዚአብሔር በማይከብርበት ህይወት ብዙ ጊዜ ስንጎመጅ ይታያል ይሔ መንፈሳዊ ምንዝርና ነው   ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3 5 እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፥ እነዚህም ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው።   ከቁጥር 14-19 የጣኦት አምልኮ በመካከላቸው እንዴት እንደተስፋፋ እናያለን   “16. እስራኤላውያን እንደ እልኸኛ ጊደር፣እልኸኞች ናቸው፤ታዲያ እግዚአብሔር እነርሱን በመልካም መስክ ውስጥ እንዳሉ የበግ ጠቦቶችእንዴት ያሰማራቸዋል?(አ.መ.ት) ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ 5   በእስራኤል ላይ የተነገረ ፍርድ   “1. “እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ!እናንት እስራኤላውያን፤ አስተውሉ!የንጉሥ ቤት ሆይ፤ ስሙ!ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤በምጽጳ ወጥመድ፣በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።(አ.መ.ት)   እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እስራኤላዊ ስሙኝ ይላቸዋል   “3. ስለ ኤፍሬም ሁሉን ዐውቃለሁ፤እስራኤልም ከእኔ የተሰወረች አይደለችም፤ኤፍሬም፣ አንተ አሁን አመንዝረሃል፤እስራኤልም ረክሳለች።(አ.መ.ት)   ከእግዚአብሔር የተሰወረ ሀጢአት የለም   እግዚአብሔር ድካማችንን ያውቃል የተሻለ ሀጢአት የለም   “4. “የሠሩት ሥራ፣ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱአይፈቅድላቸውም፤የአመንዝራነት መንፈስ በልባቸው አለ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁትም።(አ.መ.ት)   ወደ እግዚአብሔር መመለስ ያልቻሉበት 3 ምክንያት   1 በህዝቡ ላይ በሚሰራው የዝሙት መንፈስ ምክንያት   2 እግዚአብሔርን ስለማያውቁ   3 ስራቸው ያሳፍራል!   በሀጢአት መፅናትና ሀጢአትን ማድረግ የተለያዩ ነገሮች ናቸው   የንስሀ ተቃራኒ በሀጢአት መፅናት ነው   “6. እግዚአብሔርን ለመሻት፣የበግና የፍየል መንጋ እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻቸውን ነድተው ሲሄዱ፣እርሱ ስለ ተለያቸው፣ሊያገኙት አይችሉም።(አ.መ.ት)   ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርገው ለመቅረብ ቢፈልጉም አላገኙትም   እግዚአብሔርን በሰጠን ነገር አታለን ወደ ራሳችን አንመልሰውም   እግዚአብሔር የሁሉም ነገር ባለቤት ነው በሰጠን ነገር ወደ እርሱ መቅረብ አንችልም እርሱ የሚፈለግው የተሰበረን ልብ ነው   እግዚአብሔርን አናታልልም እርሱ ሁሉን ያውቃል
455