ንግሥ
Ir al canal en Telegram
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው። ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ። በቻናሉ ላይ አስተያየት ካሎት https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
Mostrar más2 525
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
2 525
39) ኮተቤ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና መድሀኒአለም ቤተክርስትያን
ልዩ ስም:-ክ/ከ የካ ወረዳ9
40) የረር በር ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን
ልዩ ስም:- የረር በር አለማየሁ ህንፃ ፊትለፊት ባለው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ
41) በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል
ልዩ ስም :- ቄራ ጎፋ ገብርኤል
42) ደብረ መድኃኒት መድኃኔአለም ወ አቡነ ተክለሀይማኖት እና ቅዱስ ሩፋኤል ወ ቅድሰት ክርስቶስ ሰምራ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎደጎድ
ልዩ ስም :- ኮ/ቀ ክ/ከ አለም ባንክ ትሮፓካል
2 525
ጥቅምት 27
- መድሃኔአለም(ጥንተ ስቅለት)
- አቡነ መባጽዮን( መድሃኔአለም በስቅለቱ አምሳል ሁኖ የተገለጠላቸዉ)
በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት
በእነዚህ አብያተ ክርስትያናት በአለ ንግሱ ይከበራል።
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ።
በቴሌግራም https://t.me/NIGSE6
በፌስቡክ https://www.facebook.com/በኢኦተቤክ-የአዲስ-አበባ-አብያተ-ክርስትያናት-109013113871986/
ይቀላቀሉን::
በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
🤲 መድሃኔአለም ይጠብቀን 🤲
1) ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሚካኤል
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ /ክ/ከ ማሞ አካባቢ
2) ድልበር መካነ ጎልጎታ መድሃኔአለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ጉለሌ ድልበር
3) ደብረ ቀራንዮ መድሃኔአለም እና ገብርኤል
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ቀራንዮ
4) ፍኖተሎዛ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ብርጭቆ ኮንዶሚንየም
5) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል
ልዩ ስም፦አዲስ ከተማ/ክ/ከ አውቶብስ ተራ
6) አስኮ ደብረ መድሃኒት መድሃኔአለም እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አስኮ አዲስ ሰፈር
7) ደብረ መድሃኒት መድሃኔአለም እና ቅድስት ኪዳነምህረት ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ አባዶ
8) አያት መካነ ህይወት መድሃኔአለም እና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቦሌ /ክ/ከ አያት ጠበል
9) ምስራቀ ፀሐይ መድኃኔአለም ቀበና ካቴድራል
ልዩ ስም፦አራዳ /ክ/ከ ቀበና
10) ቦሌ ሰሚት መካነ ሰላም መድኃኔአለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከሰሚት ወጂ
11) ኮዬ መካነ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ኮዬ
12) ካራ አሎ ደብር ቅዱስ ደብረ ቀርሜሎስ መድኃኔአለም እና ጻድቁ አቡነ ገሪማ
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ኮተቤ ካራ
13) ቃሊቲ ደብረ መድሃኒት መድሃኔአለም እና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 12 ሰሪቲ
14) ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድሃኔአለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ ቀጨኔ መድሃኔአለም
15) መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም
ልዩ ስም፦ጉለሌ ክ/ከ እንጦጦ ቁስቋም
16) ፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ /ክ/ከ ፈረንሳይ ብረት ድልድይ
17) ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔአለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ቦሌ ቡልቡላ
18) ብሔረ ፅጌ መካነ ሰላም ቅድስት ማርያምና መድኃኔአለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ብሔረ ፅጌ
19) ረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔአለም
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 2 ካራ ቆሬ
20) ጎፋ ቤዛ ብዙሃን ቅድስት ኪዳነምህረት ካቴድራል
ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ጎፋ ካምፕ
21) ቶታል ፈለገ ህይወት ቅድስት ኪዳነምህረትና መድኃኔአለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ
22) ማህደተ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃነት መድኃኔአለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ልደታ /ክ/ከ ልደታ
23) ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ መስቀል ፍላወር
24) ደብረ ፍስሃ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ ቂርቆስ
25) ላፍቶ ደብረ ኢያሪኮ መድኃኔአለም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አብያተክርስትያናት
ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ (ላፍቶ)
26) ፉሪ ደብረ ሰላም መድኃኔአለምቤ/ክ
ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ጀሞ 1 ኮንዶሚንየም
27) ደብረ ሰሊሆን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና መድኃኔአለምቤ/ክ
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ በርታ ሰፈረሰላም
28) አቃቂ መንበረ ህይወት መድኃኔአለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ጋራው መድኃኔአለም
29) ፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ፈጬ
30) ቃሊቲ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል እና ደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ/ክ/ከ ሰፈረ ገነት
31) ቃሊቲ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል እና ደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ሰፈረ ገነት
32) ጽርሐንግስትቅድስትሐናቤ/ክ
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ፉሪ ሐና ማርያም
33) ኤርቱ ፡ ሞጆ ፡ መድኃኔዓለም ፡ እና ፡ ቅዱስ ፡ ገብርኤል ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ።
ልዩ ፡ ስም ፦ ንፋስ ፡ ስልክ ፡ ላፍቶ ፡ ክ/ከ ፡ ወረዳ ፡ 1 ፡ ኤርቱ ፡ ሞጆ ።
34) ኮዬ ፡ ፈጬ ፡ መድኃኔዓለም ፡ እና ፡ ቅዱስ ፡ ገብርኤል ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ።
ልዩ ፡ ስም ፦ አቃቂ ፡ ቃሊቲ ፡ ክ/ከ ፡ ኮዬ
ፈጬ ፡ የጋራ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ፡ አከባቢ
35) ቦሌ ፡ አራብሳ ፡ መድኃኔዓለም ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ።
ልዩ ፡ ስም ፦ ቦሌ ፡ አራብሳ ፡ የጋራ ፡ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ፡ አከባቢ ።
36) ቦሌ ፡ አራብሳ ፡ ጃርሶ ፡ መድኃኔዓለም ፡ እና ፡ ቅድስት ፡ ልደታ ፡ ለማርያም ፣ ፍቅርተ ፡ ክርስቶስ ፡ ቤተ ፡ክርስቲያን ።
ልዩ ፡ ስም ፦ ቦሌ ፡ አራብሳ ፡ አዲሱ ፡ የጋራ ፡ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ፡ አጠገብ ፡ ወይም ፡ ከቃጥላ ፡ ማርያም ፡ 1.5 ኪ.ሜ ፡ ገባ ፡ ብሎ
37) ሰሚት ፡ ዋሻ ፡ መድኃኔዓለም ፡ ቤተ ክርስቲያን ።
ልዩ ፡ ስም ፦ ሰሚት ፡ የጋራ ፡ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ፡ አከባቢ
38) ደብረ ፡ ሳሌም ፡ መድኃኔዓለም ፡ ወመጥምቁ ፡ ቅዱስ ፡ ዩሐንስ ፡ ወአቡነ ፡ አረጋዊ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን (ቦሌ ፡ መድኃኔዓለም) ።
ልዩ ፡ ስም ፦ ቦሌ ፡ ክ/ከ ፡ ቦሌ ፡ መድኃኔዓለም ።
2 525
ኤልሳዕ የስሙ ትርጒም “እግዚአብሔር ደኅንነት ነው” ማለት ነው፡፡ነቢዩ ኤልሳዕ እጅግ ባለጠጋ የሆነ ሰው ነበር።
ከዕለታት በአንደኛ ዕለት በ12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነቢዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርብኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።
የኤልያስ መንፈስ እጥፍ ድርብ ሆኖ አድሮበት ለረጅም ጊዜ እግዚአብሔርን አገለገለ፣ ብዙ ተአምራትንም አደረገ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ኢያሪኮ ከተማ በሚገባበት ጊዜ በከተማዋ የሚኖሩ ሰዎች ነቢዩ ኤልሳዕ ወደ እነርሱ እንደመጣ ባዩ ጊዜ “የዚች ከተማ ኑሮ መልካም ነው ውኃው ግን ክፉ ነው ምድሪቱም ፍሬዋን ትጨነግፋለች” አሉት፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ይህን ልመና ለኤልሳዕ ያቀረቡት እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ነገርን ሁሉ መለወጥ እንደሚችል ይታመኑ ስለነበር ነው፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ የሰዎቹን ችግር ከተረዳ በኋላ የከተማውን ሰዎች አዲስ ማሰሮ እና ጨው እንዲያመጡለት አዘዘ፡፡ ሰዎቹም ኤልሳዕ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ አዲስ ማሰሮ በውስጡ ጨው አድርገው አመጡለት፤ ነቢዩ ኤልሳዕ ወደ ውሃው ምንጭ ወደ አለበት ስፍራ መጥቶ ጨው ጣለበት እና “እግዚብሔር እንዲህ ይላል ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ ከዚህም በኋላ ሞትና ጭንገፉ አይሆንበትም” ብሎ ለከተማው ሰዎች ተናገረ፡፡ ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ውኃው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ከዛ ጊዜ ጀምሮ ንጹሕ ውሃ መጠጣት ጀመሩ፡፡ የምድሪቱንም ፍሬ ተመገቡ፡፡ እግዚአብሔር በነቢዩ አልሳዕ ድንቅ ነገር ሰለአደረገላቸው ዘወትር ያመሰግኑ ነበር፡፡
እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች።
ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል። እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነቢይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት19 ላይ በስፋት ተጽፏል ጥቅምት 20 ልደቱ ሲሆን ሰኔ 20 ቀን ደግሞ በዓለ እረፍቱ ነው።
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
2 525
ጥቅምት 20
ቅዱስ ኤልሳዕ
ልደት
በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት
በ ርእሰ አድባራት እንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤልወ ኤልያስ
ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ እንጦጦ
በአለ ንግሱ ይከበራል::
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ።
@EOTCAddisAbabaChurches
@EOTCAddisAbabaChurches
@EOTCAddisAbabaChurches
በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/danyghost7 ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
🤲 ቅዱስ ኤልሳዕ ይጠብቀን 🤲
2 525
ጥቅምት 19
ቅዳሴ ቤት
በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት
1) በመጠሊ ደብረ አሮን ፍልፍል ዋሻ ቅዱስ ገብርኤል እና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስትያን
ልዩ ስም፦አቃቂ /ክ/ከ ገላን ጉዳ ገበሬ ማህብር መጠሊ አካባቢ
2) አቡነ ሐራ ድንግል
እረፍታቸው
በ ጣፎ አቡነ ሐብተማርያም, አቡነ ሐራ, አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ቤተክርስቲያን
ልዩ ስም:- ጣፎ ገብርኤል አካባቢ ወይም ከአቡነ ኪሮስ ቤተክርስቲያን ዝቅ ብሎ
በአለ ንግሱ ይከበራል::
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ።
https://t.me/NIGSE6
በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
🤲 ቅዱስ አሮን ይጠብቀን 🤲
2 525
ጥቅምት 17፦
የሊቀ ዲያቆናት
ቀዳሜ ሰማዕት
ቅዱስ እስጢፋኖስ በአለ ሹመት
/በአለ ሲመት/
በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት በነዚህ አብያተክርስትያናት
በአለ ንግሱ ይከበራል።
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ።
https://t.me/NIGSE6
በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
🙏ቅዱስ እስጢፋኖስ ይጠብቀን🙏
1) ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ መስቀል አደባባይ
2) ደብረ ስብሐት ቅድስት ልደት እና ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ቀራንዮ ጠበል ጎጥ
3) ደብረ ገነት ቅዱስ እስጢፋኖስ እና ቅዱስ ሚካኤል
ልዩ ስም :-ኮ/ቀ ክ/ከ ካራ ቆሬ ረጲ ትምህርት ቤት ጀርባ ደግነት ኮንደሚኒየም ጥላሁን ሜዳ
2 525
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ጥቅምት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
✞✞✞ አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ ✞✞✞
✞✞✞ በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ጻድቁ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ቅድስት እድና ይባላሉ:: የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው::
+ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው:: ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል:: በኢትዮዽያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ::
+በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል:: ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር 7 ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል::
+"የት ልሒድ" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው:: ተመልሰውም ለ8 ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከ8ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ::
+በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ:: ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል:: በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ: ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል::
+ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል:: በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት:: የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል::
+እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል:: በዚህም ቦታዋ "ደብረ ሃሌ ሉያ" ተብላለች:: ጻድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል::
+ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም "አቡሆሙ ለመነኮሳት
ዘኢትዮዽያ-የኢትዮዽያ መነኮሳት አባት" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::
+ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ:: በተራራው ግር ያለችውን ኪዳነ ምሐረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች::
+ጻድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል:: ጌታም 15 ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል::
+" ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ "+
✞✞✞ በዘመነ ሐዋርያት በዚህ ስም የሚጠሩ አባቶች 2 ነበሩ:: አንደኛው ከ12ቱ ሐዋርያት ሲቆጠር ዛሬ የምናከብረው ደግሞ ከ72ቱ አርድእት ይቆጠራል:: ቅዱስ ፊልዾስ ያደገው የኖረውም በቂሣርያ አካባቢ ሲሆን ባለ ትዳር የልጆች አባት ነው::
+ጌታ ሲጠራው እንኩዋ 4 ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት:: ከጌታ ሕማማት በፊት ተልኮ አስተምሯል:: ከበዓለ ሃምሳ በኋላም 7ቱ ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: (ሐዋ. 6) በቅዱስ እስጢፋኖስ መሪነትም 8ሺውን ማሕበር አገልግሏል::
+ቅዱስ እስጢፋኖስ ተገድሎ 8ሺው ማሕበር ሲበተንም ቅዱስ ፊልዾስ 4ቱን ልጆቹን አስከትሎ ወደ ሰማርያ ወርዷል:: በዚያም መሠሪ ስምዖንን ጨምሮ የሃገሪቱን ሰዎች አሳምኖ አጥምቁዋል::
+መቼም ቢሆን እኛ ኢትዮዽያውያን የማንዘነጋው ግን ጃንደረባውን ባኮስን ማጥመቁን እና ለሃገራችን የወንጌልን ብርሃን መላኩን ነው:: ጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ ከጉዞ መልስ ትንቢተ ኢሳይያስን (ኢሳ. 53) ሲያነብ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ቀርቦ ምሥጢረ ሥጋዌን አስረድቶታል::
+ሠረገላውም ቁሞለት ቅዱስ ባኮስን አጥምቆት ተነጥቆ ሔዷል:: (ሐዋ. 8:26) ቅዱስ ፊልዾስ በቀሪ ዘመኑ ከተባረኩ 4 ደናግል ልጆቹ ጋር ሲሰብክ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::
+" ሙሽራው ቅዱስ ሙሴ "+
✞✞✞ የዚህ ቅዱስ ወጣት ታሪክ ደስ የሚልም: የሚገርምም ነው:: በሮም ከተማ በምጽዋት: በጾምና በጸሎት ከተቃኙ ሃብታሞች (መስፍንያኖስና አግልያስ) ተወልዶ: በሥርዓቱ አድጐ: መጻሕፍትን ተምሮ በተክሊል አጋቡት::
+በሠርጉ ማግስት ሙሽሪትን ቢያያት በጣም ታምራለች:: "ይህ ሁሉ ውበትና ምቾት ከንቱ አይደለምን!" ብሎ በሌሊት ጠፍቶ: ነዳያንን መስሎ ከሮም ሃገረ ሮሆ (ሶርያ አካባቢ) ሔደ::
+በዚያም በፍጹም ምናኔ: በ7 ቀን አንዲት ማዕድ እየበላ: በረንዳ ላይ እየተኛና እየለመነ ለዓመታት ኖረ:: ሁሌም ቀን የለመነውን ማታ ለነዳያን አካፍሎ እርሱ ሲጸልይ ያድር ነበር:: በአካባቢው ክብሩ ሲገለጽበትም የሐዋርያውን የቅዱስ ዻውሎስን በረከት ፍለጋ ወደ ጠርሴስ ሔደ::
+ነገር ግን ጥቅል ነፋስ መርከቧን ገፍቶ ሮም አደረሳት:: ቅዱስ ሙሴም "የአምላክ ፈቃድ ነው" ብሎ በወላጆቹ ደጅ ተኝቶ ለ12 ዓመታት ተጋደለ:: ወላጆቹ ፈልገው ስላጡት በበራቸው የወደቀው ነዳይ እርሱ ይሆናል ብለው አልጠረጠሩም::
+ከብዙ ተጋድሎም በኋላም ዜና ሕይወቱን ጽፎ በዚህች ቀን: በዕለተ እሑድ ዐርፏል:: ጌታችንም "መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ ካልተጠራጠረ እምረዋለሁ" ብሎታል:: በዚያም ሕዝቡ: ካህናቱና ሊቀ ዻዻሳቱን ጌታ አዟቸው አግኝተውታል:: ወላጆቹ ማንነቱን በለዩ ጊዜም ታላቅ ለቅሶን አልቅሰዋል:: ሥጋውም ብዙ ተአምራትን አድርጉዋል::
+" ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ "+
✞✞✞ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ በሃገራቸው ልሳን 'አብደል መሲሕ' ይባላል:: ለቅዱስ ሙሴና ለሌሎችም ሙሽርነትን ትቶ መመነንን ያስተማረ እርሱ ነው:: አባቱ ታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ሲሆን እናቱ መርኬዛ ትባላለች:: የጻድቃን ትውልድ የተባረከ ነውና (መዝ. 111:1) ታላቁ አቡነ ኪሮስ አጐቱ ናቸው::
+ስለዚህ ቅዱስ ምን እነግራቹሃለሁ! ሙሉ ታሪኩ ከቅዱስ ሙሴ ጋር ተመሳሳይ ነውና:: ልዩነቱ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ በገዛ ፍቃዱ አካሉ በመቁሰሉ ምክንያት ሰዎች ሊለዩት አልቻሉም ነበር::
+በአርማንያ: በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ደጅ ለ15 ዓመታት ሲጋደል ወደ ወላጆቹ ሃገር ቁስጥንጥንያ ተመልሶ ለ15 ዓመታት ተፈትኗል:: ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆንም የአባቱ ባሮች በጥፊ ይመቱት: ጽሕሙን (ጺሙን) ይነጩት: ቆሻሻ ይደፉበት: ሽንታቸውንም ይሸኑበት ነበር::
+ለእርሱ ወዳጆቹ ውሾች ነበሩ:: በአባቱ ደጅ ለ15 ዓመታት መከራን ከተቀበለ በኋላ "ጌታ ሆይ! የአባቴ አገልጋዮች በእኔ ላይ ያደረጉትን ሁሉ በደል አድርገለህ አትቁጠርባቸው" አለ:: በዚህች ቀን ሲያርፍም ጌታችን 7ቱን ሊቃነ መላእክት ከነ ሠራዊታቸው አስከትሎ ወርዶ በክብር አሳርጐታል:: አጠቃላይ የገድል ዓመታቱም 30 ናቸው::
✞✞✞ አምላከ ቅዱሳን ለእነርሱ ካደለው ፍቅራቸው ለእኛም አይንሳን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
+ጥቅምት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ዘሚካኤል (አረጋዊ)
2.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
3.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
4.ቅዱስ ሙሴ መርዓዊ
5.ቅድስት እድና (የአረጋዊ እናት)
6.አባ ማትያስ (የአረጋዊ ረድዕ)
++"+ ነቢይ
2 525
ጥቅምት 14
*እረፍቱ ለቅዱስ ፊልጶስ
*አቡነ አረጋዊ የተሰውሩበት
በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት በነዚህ አብያተክርስትያናት
በአለ ንግሱ ይከበራል።
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ።
https://t.me/NIGSE6
በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
🙏ቅዱስ ፊልጶስ እና አቡነ አረጋዊ ይጠብቁን🙏
1) ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል
2) ጽርሃ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
3) መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ኮተቤ
4)የረር ጎሮ ደብረምህረት ቅዱስ ገብራኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቦሌ ጎሮ
5)ቀበና ቤዛዊተ አለም ቅድስት ኪዳነምህረት ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ቀበና
6) ጽርሃ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቦሌ ሰፈራ
7)ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድሃኔአለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቀጨኔ መድሃኔአለም
8) ቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ፈረንሳይ ለጋስዮን
9) መንበር ስብሃት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ጉለሌ ሽሮ ሜዳ
10) መናገሻ ገነት ጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ አራዳ ጊዮርጊስ
11) አፍሪካ ህብረት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቂርቆስ አፍሪካ ህብረት
12) ጎፋ ቤዛ ብዙሃን ቅድስት ኪዳነምህረት ካቴድራል
ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ጎፋ ካምፕ
13)ፈለገ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ሳሪስ 58
14) ፉሪ ደብረ ሰላም መድሃኔአለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ጀሞ 1 ኮንዶሚንየም
15) ምዕራፈ ቅዱሳን ፈልገ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም
ልዩ ስም፦አቃቂ ክ/ከ ሳሪስ
16) ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ ወ ገብረ ክርስቶስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቅ/ክ/ከ ወረዳ 1 ዘነበ ወርቅ
17) ፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ ፈጬ
18) ጃቴ መካነ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምህረት ካቴድራል
ልዩ ስም፦አቃቂ ክ/ከ 08
19) ቃሊቲ ደብረ መድሃኒት መድሃኔአለም እና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 12 ሰሪቲ
20) ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ካቴድራል
ልዩ ስም፦ክ/ከ ኮልፌ አጠናተራ
21) ላምበረት ደብረ ፀሀይ አቡነ አረጋዊ ወገብረ መንፈስ ቅዱስ ወቅድስት አርሴማ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ክ/ከ የካ ልዩ ቦታ ላምበረት
2 525
ጥቅምት 13
ዘርአ ቡሩክ
በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት
በደብረ መድሃኒት አቡነ ሐብተማርያም ወቅድስት ልደት ወቅድስት አርሴማ ገዳም
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አስኮ ካኦጄጄ ዱቄት ፋብሪካ ከፍ ብሎ ቃሌ ተራራ ላይ
ይከበራል።
🤲 አቡነ ዘርአ ቡሩክ ይጠብቁን 🤲
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ።
https://t.me/NIGSE6
በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
2 525
ጥቅምት 5
💚አቡነ 💛ገብረመንፈስ ቅዱስ❤
ዕረፍት እና ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት
በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት በነዚህ አብያተክርስትያናት
በአለ ንግሱ ይከበራል።
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ።
https://t.me/NIGSE6
በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
🤲 አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ይጠብቁን 🤲
1) ጀሞ ደብረኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጀሞ
2) አስኮ መካነ ህይወት ቅዱስ አማኑኤል እና አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አስኮ አዲስ ሰፈር
3) ድልበር መካነ ጎልጎታ መድሃኔአለምቤ/ክ
ልዩ ስም፦ጉለሌ ድልበር
4) የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም
ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ ልኳንዳ ፈጥኖ ደራሸ ካምፕ
5) ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሐይማኖት
ልዩ ስም፦ልደታ /ክ/ከ መርካቶ
6) አየር ጤና ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አየር ጤና
7)ብርሐናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ እና ገነተ ብርሐን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
ልዩ ስም፡- አዲስ ከተማ ክ/ከ ዊንጌት ት/ቤት
8) ቤተል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቅ/ክ/ከ ቤተል
9) መዝገበ ምህረት ቅዱስ ፋኑኤል
ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ ፋኑኤል ሰፈር
10) ቦሌ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ቦሌ እግዚአብሔር አብ
11) ኮተቤ ማህደረ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ሉቄ
12) መሪ አያት ምስራቀ ፀሐይ መካነ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ መሪ
13) ቱሉ አቦ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ፤ቅዱስ ዑራኤል እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ቱሉ አቦ
14) የረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጎሮ
15) ሲኤምሲ ደብረ ጽባህ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ሲኤምሲ
16) ደብረ ፅጌ ቅዱስ ኡራኤል
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ካዛንቺስ
17) ቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ፈረንሳይ ለጋስዮን
18) ጎፋ መብራት ኃይል ደብረ መዊዕ ቅዱስ መርቆሬዎስ እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጎፋ መብራት ኃይል
19) ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 1 ለቡ(ፉሪ)
20) መካኒሳ ምዕራፈ ፃድቃን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ መካኒሳ አቦ
21) ምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም
ልዩ ስም፦አቃቂ ክ/ከ ሳሪስ
22) ኮዬ መካነ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከኮዬ
23) ቀርሳ ፈለገ ብርሃን ቅድስት ልደታ ለማርያምና አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ቀርሳ
24) ደብረ ሠላም ቅዱስ በአለወልድ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦
25)ቃሊቲ መካነ ስብሀት ቅድስት ሥላሴ እና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ ክ ከተማ
ወረዳ 8 አረጋውያን ክብካቤ ጀርባ
26) የላምበረት ደብረ ፀሀይ አቡነ አረጋዊ ወገብረ መንፈስ ቅዱስ ወ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ
ልዩ ቦታ የካ ክ/ከ ላምበረት
27) አንቀፀ ብፁዓን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ ሐብተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን
ልዩ ስም፦ ኮ/ቀ ክፍለ ከተማ ወይራ የጋራ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ጀርባ
28) የቦሌ አራብሳ ዋሻ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፣ ቅድስት ልደታ ለማርያም ፣ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ፣ ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን
ልዩ ስም፦ አራብሳ ኮንዶሚኒየም አከባቢ
29) የካ አባዶ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን
ልዩ ስም፦ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም
30) ደብረ ሠላም ቅዱስ በአለወልድ ቤ/ክ
ልዩ ስም:- ገላን ከተማ መምህራን ሰፈር አለፍ ብሎ
2 525
ቅዱሳን ነገስታት ኢዛና ሳይዛና
ጥቅምት ፬ በዚህች ቀን የኢትዮጵያ ባለውለታዎች፤ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ እንድትሆን ትልቁን ድርሻ ያበረከቱ እጅግ የከበሩ ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ ዕረፍታቸው ነው፡፡
እነዚህ ቅዱሳን ነገስታት አብርሃና አጽብሐ በመላው ሀገሪቱ እየተዘዋወሩ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን ከመፈጸማቸው በተጨማሪ 154 አብያተ ክርስትያናትን ያሳነጹ ሲሆን ከእነዚህም 44ቱ አስደናቂ ናቸው፡፡ ባለ44 ምሰሶ ከፍልፍል ድንጋይ የተሰሩ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ በገልአርታ የሚገኘው ሰው የማይከፍተው ሰው የማይዘጋው የቀመር አርባዕቱ እንስሳ ቤተክርስትያን ይገኝበታል፡፡ እነዚህ ጻድቃን ነገሥታት ሀገሪቱን ተከፋፍለው በወሎ፣ በሸዋ የየካ ሚካኤል / አዲስ አበባ/ ፣ በከፋ የብሐ ጊዮርጊስን፣ በሰላሌ የዋሻ ሚካኤልን፣ በጎጃም የዲማ ጊዮርጊስን፣ መርጡለ ማርያም፥ በጎንደር ስማዳ የጃን ሚካኤል ቤተ ክርስትያንን አሳንጸው እየተዘዋወሩ እያገለገሉ እንደነበር ተመዝግቧል። ታላቁ አብርሃ በ374 ዓም ጥቅምት 4 ቀን በዕለተ እሑድ ዐረፈና ተቀበረ፡፡ ወንድሙ አጽብሐ ደግሞ ጥቅምት 4 ቀን 379 ዓም ዐረፈ፡፡ሁለቱም ነገሥታት ልደታቸውም ሆነ ሞታቸው አንድ ቀን ነበር፡፡ ዓመተ ምሕረቱ ግን ይለያያል፡፡ በሞቱም ጊዜ በመቃብራቸው ላይ ቀስተ ደመና ተተክሎ ታይቷል፡፡ እነዚህ ነገሥታት ለሀገራችን ብርሃንን የገለጹ ባለውለታዎቻችን ሲሆኑ የኦሪቱን ሥርዓት በሐዲስ ሥርዓት የለወጡ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ዓለም ዛሬም ድረስ የሚገረምባቸውን የአክሱም ሀውልቶች ያቆሙ ናቸው፤ 33 ሜትር ተኩል ድንጋይን ከየት አመጡት?! እንዴትስ ቀረጹት?! እንዴትስ ብለው አቆሙት?! ይህ የእግዚያብሔር ተአምር ነው እንጂ፤ እኛስ እጹብ ግሩም ብቻ ብለን እናልፋለን። በኢትዮጵያ ከነገሱ ከጥንት ነገስታት እንደ አብርሃና አጽብሃ በርካታ ታሪክን አኑሮልን ያለፈ ንጉስ የለም ብንል አልተሳሳትንም የሁሉም ቅዱሳን ነገስታት መሰረትና ምክንያት ናቸውና:: እነዚህ ቅዱሳን የኢትዮጵያን ድንበር አስፍተው ክርስትናን አጽንተው ያስረከቡን ዋኖቻችን ናቸው:: የቅዱሳኑን ክብር በእኛ ላይ ያድርግልን:: ጸሎታቸው: በረከታቸውና አማላጅነታቸው ይደርብን:: "የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል:: "መዝ 111/112/
2 525
ጥቅምት 4
💚አብርሃ 💛ወአፅብሃ❤
በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት
1) ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ ወ ገብረ ክርስቶስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቅ/ክ/ከ ወረዳ 1 ዘነበ ወርቅ
2) ዋሻ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖትና አብርሃ ወአፅብሃ ውቅር ቤተ ክርስቲያን
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አንቆርጫ ዋሻ ሚካኤል
3) መሪ ደብረታቦር ቅዱስ ፋኑኤል ፣ አብርሃ ወአጽብሐ ወቅድስት በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ።
ልዩ ስም ፦ አያት መሪ (ከመሪ ባቡር መውረጃ ፊት ለፊት ባጃጅ ተራ አለ ። ከዛ እስከ ቤተ ክርስቲያኑ የሚያደርስ ባጅጅ ያገኛሉ ።)
በአለ ንግሱ ይከበራል።
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ።
በቴሌግራም https://t.me/NIGSE6
በፌስቡክ https://www.facebook.com/በኢኦተቤክ-የአዲስ-አበባ-አብያተ-ክርስትያናት-109013113871986/
ይቀላቀሉን::
በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
🤲 አብርሃ ወአፅብሃ ይጠብቁን 🤲
2 525
ጥቅምት 5
💚አቡነ 💛ገብረመንፈስ ቅዱስ❤
ዕረፍት እና ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት
በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት በነዚህ አብያተክርስትያናት
በአለ ንግሱ ይከበራል።
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ።
https://t.me/NIGSE6
በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
🤲 አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ይጠብቁን 🤲
1) ጀሞ ደብረኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጀሞ
2) አስኮ መካነ ህይወት ቅዱስ አማኑኤል እና አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አስኮ አዲስ ሰፈር
3) ድልበር መካነ ጎልጎታ መድሃኔአለምቤ/ክ
ልዩ ስም፦ጉለሌ ድልበር
4) የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም
ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ ልኳንዳ ፈጥኖ ደራሸ ካምፕ
5) ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሐይማኖት
ልዩ ስም፦ልደታ /ክ/ከ መርካቶ
6) አየር ጤና ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አየር ጤና
7)ብርሐናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ እና ገነተ ብርሐን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
ልዩ ስም፡- አዲስ ከተማ ክ/ከ ዊንጌት ት/ቤት
8) ቤተል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቅ/ክ/ከ ቤተል
9) መዝገበ ምህረት ቅዱስ ፋኑኤል
ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ ፋኑኤል ሰፈር
10) ቦሌ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ቦሌ እግዚአብሔር አብ
11) ኮተቤ ማህደረ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ሉቄ
12) መሪ አያት ምስራቀ ፀሐይ መካነ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ መሪ
13) ቱሉ አቦ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ፤ቅዱስ ዑራኤል እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ቱሉ አቦ
14) የረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጎሮ
15) ሲኤምሲ ደብረ ጽባህ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ሲኤምሲ
16) ደብረ ፅጌ ቅዱስ ኡራኤል
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ካዛንቺስ
17) ቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ፈረንሳይ ለጋስዮን
18) ጎፋ መብራት ኃይል ደብረ መዊዕ ቅዱስ መርቆሬዎስ እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጎፋ መብራት ኃይል
19) ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 1 ለቡ(ፉሪ)
20) መካኒሳ ምዕራፈ ፃድቃን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ መካኒሳ አቦ
21) ምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም
ልዩ ስም፦አቃቂ ክ/ከ ሳሪስ
22) ኮዬ መካነ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከኮዬ
23) ቀርሳ ፈለገ ብርሃን ቅድስት ልደታ ለማርያምና አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ቀርሳ
24) ደብረ ሠላም ቅዱስ በአለወልድ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦
25)ቃሊቲ መካነ ስብሀት ቅድስት ሥላሴ እና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ ክ ከተማ
ወረዳ 8 አረጋውያን ክብካቤ ጀርባ
26) የላምበረት ደብረ ፀሀይ አቡነ አረጋዊ ወገብረ መንፈስ ቅዱስ ወ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ
ልዩ ቦታ የካ ክ/ከ ላምበረት
27) አንቀፀ ብፁዓን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ ሐብተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን
ልዩ ስም፦ ኮ/ቀ ክፍለ ከተማ ወይራ የጋራ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ጀርባ
28) የቦሌ አራብሳ ዋሻ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፣ ቅድስት ልደታ ለማርያም ፣ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ፣ ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን
ልዩ ስም፦ አራብሳ ኮንዶሚኒየም አከባቢ
29) የካ አባዶ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን
ልዩ ስም፦ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም
30) ደብረ ሠላም ቅዱስ በአለወልድ ቤ/ክ
ልዩ ስም:- ገላን ከተማ መምህራን ሰፈር አለፍ ብሎ
2 525
☞ጥቅምት 3 ቀን ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ ለተባሉ ለአባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የጽንሰታቸው አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
☞አባ ጊዮርጊስ የተወለዱት በአሁኑ ደቡብ ውሎ ሀገረ ስብከት በቦረና አውራጃ
በከለላ ወረዳ ልዩ ስሟ (ሰግላ) በተሰኘች አካባቢ ነው፡፡
☞የአባ ጊዮርጊስ አባታቸው ሕዝበ ጽዮን ከተከበሩ መምህራን ወገን የሆኑና
የቤተ መንግሥት ባለሟል፤መጻሐፍትን የሚያውቁ፤የሸግላ ሀገር ገዥ ነበሩ፡፡
☞እናታቸው ደግሞ በወለቃና በበቶ ወንዝ መካከል ከሚገኙ ሸማምንቶች
የተወለዱ እምነ ጽዮን የተባሉ ደግ እናት ነበሩ፡፡
☞እነዚህ የተመረጡ ባል እና ሚስት ልጅ ስላልነበራቸው አብዘተው ያዝኑ ነበር
በእመቤታችን በድንግል ማርያም እና በሊቀመላዕክት ቅድስ ዑራኤል ምስል ስር
ዘወትር ያለቅሱ ነበር፡፡
☞ጌታችን ልመናቸው እና ለቅሷቸውን ሰምቶ በወርሐ መስከረም የመላእክት
አለቃ ዑራኤል ተልኮ ልጅ እንደሚወልዱ ስሙንም በሰማዕታት አለቃ በቅዱስ
ጊዮርጊስ ስም እንደሚሰይመው ነገራቸው፡፡
☞እነሱም የደስታ ምስጋና ለፈጣሪያቸው ምስጋና ካቀረቀብ በኀላ ቅዱስ
አባታቸው ጥቅምት 3 ተጸንሰው በሐምሌ 7 ቀን ዕለተ ማክሰኞ ተወለዱ፡፡
☞አባ ጊዮርጊስ እድሜአቸው ለትምህርት እስኪደርስ ድረስ እናታቸው ቤት
ውስጥ በፈሪያ እግዚአብሔር አደጉ፡፡
☞እናታቸው ጽዮን ልጃቸው በዘመኑ ከነበሩት ጳጳስ ዘንድ በመውሰድ ዲቁና
ካሾሟቸው በኃላ በጊዜው በኢትያጵያ ታላቅ የትምህርት ማእከል በነበረች ሐይቅ
ደብረ ነጎድጎድ ገዳም ወደምትገኘው ትምህርት ቤት ከታላቁ ሊቅ ዐቃቤ ሰዓት
ሠረቀ ብርሃን እንዲማሩላቸው አድርሰዋቸው መጡ፡፡
☞በዚያ ገዳም ያለ ዕረፍት የጉልበት ሥራ በመሥራት ገዳሙን ያገለግሉ
አባቶችን ይረዱ ነበር፡፡ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል
ሥር አብዝተው በመስገድ ፈጣሪያቸውን ይማፀኑ ነበር፡፡
☞ይሁን እንጂ አባታቸው እንደተመኙት ትምህርት ለአባ ጊዮርጊስ በቀላሉ
ሊገባቸው አልቻለም፡፡ ይህን የተረዱት አባ ሠረቀ ብርሃን እንዳይወቀሱ ወደ
አባታቸው ላኳቸው፡፡
☞አባታቸውም መልሰው በማምጣት ልጁን የወለድኩት በስእለት ነውና ከዚሁ
ገዳሙን እያገለግሉ አባቶችን እየረዱ ይኑር ብለው ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም
አድርሰዋቸው ተመለሱ፡፡
☞በዚያም ትምህርታቸውን እየተማሩ በቀን ዘጠኝ ዘጠኝ ቅርጫት እየፈጩ
ማገልገል ቢጅምሩም ቅን አገልግሎት የሚያበረክቱላቸው መነኮሳት
ከማመስገን ይልቅ ትምህርት የማይገባው እያሉ ይሰድቧቸውና ይነቅፏቸው
ጀመረ፡፡
☞አባ ጊዮርጊስም ግን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው ደግ ሰው ናቸውና እንደ
ሰደብኝ ልሰደብ እንደ ናቁኝ ልናቅ ሳይሉ የተለመደ አገልግሎታቸውን ሳያቋርጡ
ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ሥር በግንባራቸው ተደፍተው፤
እመቤቴ ሆይ መነኮሳት በእኔ ላይ እየፈጸሙብኝ ያለውን ነቀፋ ዘለፋ ተመልከተሽ
ትምህርቴን እንዲገልፅልኝል ከልጅሽ ከጌታችን አማልጂኝ እያሉ ያለቅሳሉ፡፡
☞እመቤታችንም ድንግል ማርያም በገሀድ ተገልጻ አይዞህ አታልቅስ ትምህርት
ተከልክሎብህ ሳይሆን የምትጠቀምበት ጊዜ እስኪደርስ ነበር፤ አሁን ግን ጊዜው
ደርሷልና እስከ 7ቀን በዚሁ በሱባኤው እንዳለህ ሆነህ ጠብቀኝ ብላቸው
ተሰወረች፡፡
☞እሳቸውም ተስፋውን ተቀብለው በሱባኤው እንዳሉ እመቤታችን ድንግል
ማርያም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዑራኤል አሰከትላ ጽዋዓ እሳት አስይዛ መጥታ
የሕይወት ጽዋዕ አጠጣቻቸው፡፡
☞አባ ጊዮርጊስም የሕይወት ጽዋዕን ከጠጡ በኃላ የሰማይና የምድር ምስጢር
ሁሉ ተገልጸላቸው፡፡
☞በእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ተመልተው እግዚአብሔር በመዓልትና በሌሊት
በዜማ የሚመሰገንባቸውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፀሎት
የምትመሰገንበትና ሌሎችንም የምስጋና የጸሎት መጻሕፍትን ደርሰዋል፡፡
☞አባ ጊዮርጊስ እንደ ሐዋርያት በሀብተ መንፈስ ቅዱስ የተመሉ አባት ስለነበሩ
ዕውቀት ሳይወስናቸው ከቅዱስ ያሬድ የዜማ ትምህርት ሊቃውንት መካከል
የዜማ መምህር ናቸው፡፡
☞በዚህም የቅዱስ ያሬድን ዜማ በተለይም ድጓውን በዘመናት ከፋፍለውና
በየበዓላቱ አደራጅተው ቅርፅ በማስያዝ ለቅዱሳኑ ሁሉ በየበዓላቶቻቸው
የሚዜመውን አዘጋጅተው ለደቀ መዛሙርቶቻቸው በማስተማር እንዲስፋፋ
አድርገዋል፡፡
☞አባ ጊወርጊስ ድጓውን በደብረ ነጓድጓድ ሐይቅ ለ7 ዓመት፤ በርእስ አድባራት
ተድባበ ማረርያም ደግሞ 7 አመት ካስተማሩ በኃላ ከእሳቸው ደቀ መዛሙርት
መካከል እነ ልሳነ ዕፍረት ድጓውን ቤተልሔም ይዘውት በመሔድ ከግራኝ
አህመድ ጥፋት በኃላ እዚያው በመገኘቱ ቤተልሔም የድጓ ምስክር ሆኖ ቀርቷል፡፡
☞በዚህም በዜማው በኩል አባ ጊዮርጊስ ከያሬድ በኀላ የተነሡ ዳግማዊ ያሬድ
ሲባሉ በዘመኑ የነበሩትን መናፍቃን በመከራከር በመርታታቸው ኢትዮጵያዊ
ቄርሎስ የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል፡፡
☞አባ ጊዮርጊስ ይማሩበት በኃላም ያስተማሩበት ብዙ ደቀ መዛሙርትን
ያወጡበት የነበረው ቦታ ደብረ እግዚአብሔር ይባላል፡፡
☞አባ ጊዮርጊስ አሰተምረው ለንግሥና ከበቁት መካከል አፄ ዘርዓይቆብ
ከንግሥናቸው በተጨማሪ በደረሷቸው ድርሰቶች ለእመቤታችን ባለቸው ፍቅር
በሳቸው ውሰጥ አባ ጊወርጊስ ትምህርታቸው ጎልተው ሰለሚታዩ ከሊቃውንቱ
የሚቆጠሩ ናቸው፡፡
☞አባ ጊዮርጊስ የራሳቸውን ቤተመቅደስ ፈልፍለው ያነጹ ሲሆን በዚም ቅነኔ
ማኅሌት፤ ቅድስትና መቅደስን የያዘ በምሰሶም የተከፈለ ነው፡፡
☞ይህ ቤተ መቅደስ አስገራሚ የሚሆኑ የብርሃን መስኮቶች ያሉትና አባ
ጊዮርጊስ ድርሰት የደረሱባቸው ዋሻዎች፤ የክርስትና ቤትና የቅዱሳን መካነ
ዓፅም ከዐለት ተፈልፍለው ተሠረተዋል፡፡
☞የአባ ጊወርጊስ የድርሰት ስራወች መካከል መጽሐፈ ምስጢር፤ መዓዛ ቅዳሴ፤
ቅዳሴ እግዚእ ካልእ ፤ አርጋኖ፤ ኆኅተ በብርሃን፤ ሕይወተ ማርያም ፤ ውዳሴ
ሰብሐት ፤ ፍካሬ ይማኖት ከብዙ በጥቂቱ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
☞አባ ጊወርጊስ ከብዙ ተጋድሎ እና ድንቅ ስራ በኅላ በ ሐምሌ 7ቀን
በ1417 ዓ/ም በ60 ዓመታቸው ዐርፈዋል፡፡
☞ለአባጊወርጊስ የተለመነች ድንግል ማርያም ለእኛም ትለመነን ማስተዋሉን
ታድለን፡፡
☞የአባ ጊወርጊስ የፀሎቱ በረከት አይለየን፡፡
☞(ገድለ አባ ጊዮርጊ ዘጋስጫ እና ገድለ አቡነ በፀሎተ ሚካኤል)
2 525
💚ጥቅምት💛 3❤
ጽንሰት
💚አባ ፡ ጊዮርጊስ ፡ ዘጋስጫ💛❤
በአዲስ አበባበ አህጉረ ስብከት
በ ርእሰ አድባራት እንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ
ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ እንጦጦ በአለ ንግሱ ይከበራል።
ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
ሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ እንዲያገኘው #share በማድረግ አብያተ ክርስትያናትን ያስተዋውቁ።
https://t.me/NIGSE6
በፌስቡክ https://www.facebook.com/በኢኦተቤክ-የአዲስ-አበባ-አብያተ-ክርስትያናት-109013113871986/
ይቀላቀሉን::
በዚህ ቻናል ላይ አስተያየት ካሎት በ https://t.me/DAN_TRADING_PLC ቴሌግራም ላይ መልእክት ይላኩ።
🤲አባ ፡ ጊዮርጊስ ፡ ዘጋስጫ ይጠብቁን 🤲
2 525
❖ መስከረም 29 በክርስቶስ ስም አንገቷን ለሰይፍ የሰጠችው የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ በቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ❖
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖✔💥 ስለ ቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ቀደምት ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕሏን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች።
💥 እጅግ መልከ መልካም ነበረች። ቅዱስ ጳውሎስ “ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥34) ያለውን አስባ ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር። ከ284- 305 በሮም የነገሠው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡
❖✔💥 እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡
❖✔💥 ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ጌታችን በወንጌል “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” (ማቴዎስ 10፥23) ያለውን አስበው ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡
💥 ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና
አምላካችን ክርስቶስ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ 10:32-33) ያለውን በማሰብ “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡
❖✔💥 የመልኳን ደም ግባትም በማየት ንጉሥ ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው፣ ክርስቶስን እንድትክድ በብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው ነቢዩ ዳንኤል እንዳደረገው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡
❖✔💥 ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በግድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡
❖✔💥 ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ኃይል እእንዳሸነፈ ቅድስት አርሴማም እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው፤ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ።
💥 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" (ሮሜ 8:35-36) እንዳለ ያደረሱባት መከራ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያት አልቻለም።
💥 ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስከትሎ ተገለጸላት። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤” (ዘዳግም 7፥9) እንደሚል
ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም 29 በ290 ዓ.ም. አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለች።
💥 አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" (ኢሳ 56:4-5) ብሎ እንደተናገረ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በአርመን አለ፡፡
❖✔💥 በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው አማናዊ ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ ታቦቷ ካለባቸው እጅግ ብዙ በረከት ካላቸው የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ እና በአውሮፓ ስኮትላንድ ግላስኮ ይገኛሉ፨
❖✔💥 ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦
❖✔💥 ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡-
✍️ “በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ
እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ
ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ
ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ
ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ”
(በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡
❖✔💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦
✍️“ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ
ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ
ዘፈጸመት ገድላ በጻማ
ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡
(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨
❖✔💥 እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨
❖✔💥 “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ
በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ
አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ
አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ
ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ”
(በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች
