es
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Ir al canal en Telegram

EEP Communication

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram EEP Communication

El canal EEP Communication (@eepcommuication) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 698 suscriptores, ocupando la posición 8 062 en la categoría Tecnologías y Aplicaciones y el puesto 2 174 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 698 suscriptores.

Según los últimos datos del 01 septiembre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 139, y en las últimas 24 horas de 1, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 28.75%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 16.42% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 513 visualizaciones. En el primer día suele acumular 2 578 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 10.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
EEP Communication

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 02 septiembre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Tecnologías y Aplicaciones.

15 698
Suscriptores
+124 horas
+277 días
+13930 días
Archivo de publicaciones
የውስጣዊ ፍስሃ፥ ደስታ፣ እንባ–ሲቃ፣ ሳቅ፣ ብርሃን የዘመናት የቁጭት ስሜት፣ የስኬት ተድላ፤ አሁናዊ የሚሰማኝ ስሜት!! በቅድሚያ፥ የሀገሬ ኢትዮጵያ የኔ ትውልድ ዓድዋ፣ የላቀ የታሪክ ምዕራፍ–ታሪክ ቀያሪ  ጉዞ አካል ላደረገኝ  ፈጣሪ ተመስገን! 🙏🏾 የዓመታት ምኞት፥ የዘመናት ፅኑ ሕልም፣ የመጪው ትውልድ ደማቅ ብርሃን እውን ሆኖ በአዲስ ዓመት መባቻ ከላቀ ገፀ-በረከት ጋር አዲስ ዓመቱን ስንቀበል፥ ድርብ ደስታ ነው። እንኳን ደስ አለን፥ እንኳን አደረሰን። ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ፥  እንኳን ደስ አለን፥ እንኳን ደስ አላችሁ።  እንኳን በደስታ ሲቃ ለምንቀበለው አዲስ ዓመት አደረሳችሁ። እኛ የዚህ ዘመን ትውልድ፥ ለትውልድ የምናወርሰው መቻልን፣ ብርታትን እና የልማት አርበኝነትን ነው። የተጣመመ ትርክት አቃንተን፥ በዕዳ  የተረከብነውን ለውጠን ወረት እና ምንዳን እናስረክባለን:: እንኳን ደስ አለን! አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዋዜማ መርሐ ግብር በልዩ ድምቀት ተከናውኗል .......///......... ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት የዋዜማ መርሃግብር በድሮን ትርኢት እና በርችት ዝግጅቶች በደመቀ ድባብ ተከናውኗል። የዋዜማ መርሀግብሩ የተለያዩ ህብረ ቀለማዊ ትርኢቶች ቀርበውበታል። በመርሃ ግብሩ ላይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የቀድሞው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል። ዛሬ የሀገራት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የግድቡ ምርቃት በይፋ የሚከናወን ይሆናል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

ጳጉሜን -3 የእመርታ ቀን እመርታ ለዘላቂ ከፍታ የወረስነው ዕዳ ብዙ፤ የምንጓዝበት መንገድ ረዥም፤ የሕዝባችንም ፍላጎት ሰፊ ነው፡፡ ቀስ በቀስ በሚደረግ የተለምዶ ጉዞ ወደምንፈልገው የብልጽግና ምዕራ
ጳጉሜን -3 የእመርታ ቀን እመርታ ለዘላቂ ከፍታ የወረስነው ዕዳ ብዙ፤ የምንጓዝበት መንገድ ረዥም፤ የሕዝባችንም ፍላጎት ሰፊ ነው፡፡ ቀስ በቀስ በሚደረግ የተለምዶ ጉዞ ወደምንፈልገው የብልጽግና ምዕራፍ አንደርስም፡፡ ያለን አማራጭ አንዳንድ እርከኖችን መዝለል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ፈጠራና ፍጥነት ወሳኞች ናቸው፡፡ ከተለመደው መንገድ ወጣ ማለት፣ ከተለመደው ጊዜ በላይ መሥራት፣ ከተለመደው ዋጋ በላይ መክፈል ያስፈልገናል፡፡ ዓላማችን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር አይደለም፡፡ ከትናንት ዘለን ወደ ነገ መድረስ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 3 ቀን 2017 ዓ.ም

ጳጉሜን -2 የኅብር ቀን ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ ኢትዮጵያ በብዙ ጸጋዎች የተሞላች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ጸጋዎቿ የተለያዩ ሳይሆኑ ልዩ ልዩ ናቸው፡፡ የባህል፣ የቋንቋ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔ፣ የእምነት
ጳጉሜን -2 የኅብር ቀን ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ ኢትዮጵያ በብዙ ጸጋዎች የተሞላች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ጸጋዎቿ የተለያዩ ሳይሆኑ ልዩ ልዩ ናቸው፡፡ የባህል፣ የቋንቋ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔ፣ የእምነት፣ የጾታ፣ የአመለካከት፣ ወዘተ ብዝኃነት ያለንን የጸጋ ብዛት የሚያመለክት ነው፡፡ ብዝኃነት የኢትዮጵያ ታሪኳ እና መልኳ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም

በከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ሥር ግንባታ ማከናወን አደገኛ መሆኑን ምን ያህል ያውቃሉ? ከአዲስ ዌስት ወይም ከኮልፌ ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ጥቁር አንበሳ ማከፋፈያ ጣቢያ በሚሄደው መስመር ሥር አደገኛ የህንፃ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ተመልክተናል፡፡  ግንባታው ከአደገኛነቱ ባሻገር በቸልተኝነት የተከናወነ ተግባር ለመሆኑ የምትመለከቱት ምስል አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ግንባታው ከከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ ሥር መከናወኑ እንደ ፈሮ ብረት እና ቆርቆሮ ያሉ ኤሌክትሪክን የመሳብ አቅም ያላቸው የግንባታ ግብዓቶች ኤሌክትሪክን በመሳብ በቀጥታ በሰዎች አካል እና ህይወት ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ይህ ግንባታ ትናንት በልደታ፣ በቂርቆስ እና በአራዳ ክፍለከተማ የተወሰኑ አካባቢዎች በተለይም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና በሜክሲኮ አካባቢ የኃይል መቋረጥ እንዲከሰት ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡ አሁን ላይ ግንባታው በሰው ህይወትም ሆነ አካል ላይ ጉዳት ባያደርስም መስመሩ ከሚያሰተላልፈው ከፍተኛ ቮልቴጅ አንፃር አደጋ መድረሱ የሚቀር እንዳልሆነ እናምናለን፡፡ በቀጣይም ከዚህ መስመር ኃይል የሚያገኙ አካባቢዎች በተደጋጋሚ ኃይል እንዲቋረጥባቸው፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳይችሉ የሚያደርግ እና ህብረተሰብን ለእግልት የሚዳርግ በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ “በቡሃ ላይ ቆሮቆር” እንዲሉ አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት በቸልተኝነት የሚከናወኑ አደገኛ ግንባታዎች በበዓል ወቅት ህብረተሰቡን ኃይል በማሳጣት የበዓል ድባብን ሊረብሹ ስለሚችሉ የግንባታ ፍቃድ የሰጡ አካላት ውሳኔያቸውን በማጤን ግንባታውን ሊያስቆሙ ይገባል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ በዚሁ መስመር ሥር የሚከናወኑት የድንጋይ ማውጣት ሥራዎች የአፈር መንሸራተት እያስከተሉ ስለሆነ እንቅስቃሴዎቹ ተገተው የእርምት እርምጃ ካልተወሰደ የኃይል መቋረጥ ሊያመጣ ስለሚችል የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡት እንጠይቃለን፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል! 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1

ተቋሙ በደሴ ከተማ የአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ አስጀመረ ‎……...///…….... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በደሴ ከተማ የአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ አስጀመረ። በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የደሴ ከተማ አስተዳደር ተወካይ ከንቲባ ኮማንደር ሰዒድ ዓሊ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የከተማዋን ዕድገትና የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል  እያከናወነ ላለው በጎ ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አንዱዓለም ሲዓ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከ128 ዓመታት በላይ የተለያዩ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየ የህዝብ ተቋም ነው። ተቋሙ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ከመላው ህዝብ ጋር በመሆን ከተስፋ ወደሚጨበጥ ብርሃን የቀየረ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያውያን በላባቸው፣ በደማቸውና ባላቸው አቅም ሁሉ ላደረጉት አበርክቶ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ተቋሙ ከሚያከናውናቸው በርካታ የኃይል መሠረተ ልማቶች ጎን ለጎን በልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝም ነው ያብራሩት። እንደ ኢንጂነር አንዱዓለም ገለፃ ከደሴ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የተጀመረው የአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተቋሙ በመላ ሀገሪቱ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያከናውነው አካል ነው። የተቋሙ ባለሙያዎች መሟላት የሚገባቸውን የዲዛይን እና መሰል ጉዳዮች ለሥራ አመራሩ እንዳቀረቡ የቤቱን ግንባታ በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለማስረከብ እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል። በተቋሙ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝ በበኩላቸው ተቋሙ በአማራ ክልል ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ግንባታዎችን እያከናወነ ይገኛል። ተቋሙ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ አካባቢዎች የህብረተሰቡን ፍላጎት ያማከሉ ውጤታማ የማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎች ሲያከናውን መቆየቱንም አስታውሰዋል። የደሴ ከተማን የኃይል አቅርቦት ለማሻሻል የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እየተገነባ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሙላት ከዚሁ ጎን ለጎን በከተማዋ ለሚኖሩ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ኑሮ መሻሻል የቤት ግንባታ መጀመሩ ትልቅ ዕድል ነው ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተቋሙ የሥራ አመራሮች እና የደሴ ከተማ አስተዳደር ተወካይ ከንቲባ ኮማንደር ሰዒድ አሊ በደሴ ከተማ ‎የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናውነዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ የተከናወነው በከተማዋ በሚገኘው የቅዳሜ ገበያ አጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በደሴ ባለ 230 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ቅጥር  ግቢ ውስጥ ነው። የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራሙ ፅዱና አረንጓዴ አካባቢን ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት አንድ አካል በመሆኑ በዕለቱ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ዛፎች ተተክለዋል፡፡ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የከተማው የግብርና ቢሮ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ በተቋሙ የሰሜን ምስራቅ ሪጅን እና የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ተሳትፈዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

photo content
+9

ጳጉሜ 1፣ የጽናት ቀን ይህ ቀን የሀገራችን ሁሉን አቀፍ ስኬት ለማረጋገጥ በማያቋርጥ ጽናትና ብርታት ለተፋለሙ ጀግኖች ክብር የምንሰጥበት ቀን ነው። በዚህም በቅርቡ በሚመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳ
+1
ጳጉሜ 1፣ የጽናት ቀን ይህ ቀን የሀገራችን ሁሉን አቀፍ ስኬት ለማረጋገጥ በማያቋርጥ ጽናትና ብርታት ለተፋለሙ ጀግኖች ክብር የምንሰጥበት ቀን ነው። በዚህም በቅርቡ በሚመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ኃይል ማመንጫ ግድብን ጨምሮ ተቋሙ በሚያከናውናቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ በጽናት ለተሳተፉ የተቋማችን ሠራተኞች እና መሐንዲሶች ክብር እንሰጣለን። የእነርሱ ጽናት እና የማይናወጥ ቁርጠኝነት ሁሉንም ፈተናዎች ተቋቁሞ ታላቅ ህልምን ወደ ተጨባጭ እውነታ ቀይሯል። እነሱ የጽናት ሕያው ምሳሌዎች ናቸው 💧💡 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ ማብሰሪያ ነው ….///….. የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ኃይል ማመንጫ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ ማብሰሪያ ነው አሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ሞገስ መኮንን የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅንና ለምርቃት ዝግጁ መሆንን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት ኃይል ከማመንጨት ባሻገር ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው የህዳሴ ግድብ ብዙ ጫናዎችን ተቋቁሞ በቆራጥ የአመራር ውሳኔ ተጠናቋል፡፡ የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ 54 በመቶ ላይ የሚገኘውን የኃይል ተደራሽነት ሽፋን ለማሳደግና የጎረቤት ሀገራትን በኃይል ለማስተሳሰር የጎላ ሚና እንዳለውም አብራርተዋል፡፡ ለረጅም ዘመናት በውጫዊ ጫናዎች እና በነበረብን ድህነትና ኋላ ቀርነት ምክንያት ዐባይን መሰል ድንበር ተሻጋሪ የተፈጥሮ ሀብታችንን ተጠቅመን የኃይል ፍላጎታችንን ለማሟላት ሳንችል ቆይተናል ብለዋል፡፡ ይህን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመቅረፍ በተፈጥሮ ሀብቷ ተጠቅማ ከድህነት ተላቃ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በራስ አቅም፣ ዕውቀትና ገንዘብ ገንብታ ማጠናቀቋን አንስተዋል፡፡ ግድቡ ኃይል ከማመንጨት ባሻገር በዓሳ ምርት፣ በቱሪዝም፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በኢንዱስትሪ ልማት እና ቀጣናዊ ትስስርንና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ በኩል ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች በማድረግ የኢትዮጵያን የመልማት አቅሟን መገደብ እንደማይቻል ዐቢይ ማሳያ መሆኑን ያነሱት አቶ ሞገስ የግድብ ግንባታው መጠናቀቅ ኢትዮጵያ ስታራምድ የቆየችውን የጋራ ተጠቃሚነት መርህ በተግባር በማረጋገጥ ዓለም አቀፍ ተሰሚነቷን እና የመደራደር አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ እንደ አቶ ሞገስ ገለፃ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የላብና የደም ጠብታ ያረፈበት የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ ማብሰሪያ ነው፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1

ግድቡ ኢትዮጵያ በጽናት ማደግ እንደምትችል ያሳየ ነው ......///........ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን ያሰቡትን እና ያቀዱትን ከግብ ማድረስ እንደሚችሉ ያሳየ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ተናግረዋል። አቶ ሞገስ እንደገለፁት የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዐባይ ግድብ ላይ ለመጠቀም የነበራት የዘመናት ህልም እውን የሆነበት እና የአይቻልም መንፈስ የተሰበረበት ታሪካዊ ድል ነው። ይህ ግድብ ኢትዮጵያ የራሷን ሀብት በአግባቡ የመጠቀም መብቷን እውን ያደረገችበት የሉዓላዊነት መገለጫ መሆኑንም ነው ዳይሬክተሩ የገለፁት። ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ የሚገጥሙ ጫናዎችን ተቋቁማ ለስኬት እንደምትበቃ ያረጋገጠ ነውም ብለዋል። መላው ኢትዮጵያዊያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በጉልበት፣ በዲፕሎማሲ እና በመስዋዕትነት ያፀኑት ታሪካዊ ግድብ ነው መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን ከጎረቤት ሀገራት ጋር በፍትሐዊነት መጠቀምን መርህ  አድርጋ እየሰራች መሆኑን የገለፁት አቶ ሞገስ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትም ይህን በመረዳት ተባባሪ ሊሆኑ እንደሚገባ ተናግረዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

‎ግድቡ በራስ አቅም የመልማት አቅማችን ዐቢይ ማሳያ ነው‎ .....///..... ‎ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ በራስ አቅም የመልማት አቅማችን ዐቢይ ማሳያ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። ‎ ‎ተቋሙ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅንና ለምርቃት መዘጋጀትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን በስካይ ላይት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ‎ ‎መግለጫውን የሰጡት የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ዳግማዊ ዓድዋ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ለምርቃት ዝግጁ ሆኗል። ‎ ‎ግድቡ ከፋይናንስ ምንጩ፣ በሚይዘው የውሃ መጠን፣ በሚሰጠው ትርጉም ከሌሎች የኃይል ማመንጫዎች ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል። ‎ እስካሁን ያለው ‎የግድቡ ግንባታ ወጪ ከ233 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑንና ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት መሸፈኑን የጠቆሙት አቶ ሞገስ ከዚህ ውስጥ 91 በመቶው ከንግድ ባንክ እንዲሁም ቀሪው 23 ቢሊዮን ብሩ ወይም 9 በመቶው በሕብረተሰብ ተሳትፎ የተገኘ መሆኑን ተናግረዋል። ከፋይናንስ ተሳትፎ በተጨማሪ ሕብረተሰቡ በዕውቀት፣ በዲፕሎማሲ፣ በጉልበት እና በሀሳብ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደነበረው አብራርተዋል። ይህም ግድቡ በጫናዎች ሳንበገር በፍትሐዊነት በራሳችን አቅም የመልማትና ብሔራዊ ጥቅማችንን የማስጠበቅ ጽኑ ፍላጎታችንን ለዓለም ያሳየ ነው ብለዋል። አሁን ላይ የግድቡ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለምርቃ ዝግጁ መሆኑን ያወሱት አቶ ሞገስ በህዳሴ ደዴሳ ሆለታ እና በበለስ መስመር በኩል ኃይሉ ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት እየገባ መሆኑን አብራርተዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

‎ተቋሙ ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ነው ‎....///.... ‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅንና ለምርቃት መዘጋጀትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን በስካይ ላይት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል። ‎ ‎መግለጫውን የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በመስጠት ላይ ናቸው። ‎ ‎ጋዜጣዊ መግለጫው በግድቡ ታሪካዊና ብሔራዊ ጠቀሜታ፣ የግድቡ የቴክኒክ እና የኦፕሬሽን ስኬት፣ ለሀገር ኢኮኖሚና ልማት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ እንዲሁም ተግዳሮቶች እና የወደፊት ዕቅዶች ዙሪያ ትኩረት ያደርጋል። ‎ ‎እኛም በጋዜጣዊ መግለጫው የሚነሱ ኃሳቦችን እየተከታተልን በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን የምናደርሳችሁ ይሆናል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content