የተሰባበሩ ፊደላት
Canal cerrado
798
Suscriptores
Sin datos24 horas
-27 días
-1030 días
Archivo de publicaciones
798
ንጉሡ ተሰማ (ጢያ)
******
አትደውዪ
አታናግሪኝ
ከዚህ ይብቃን : መነጋገር ፣
ከውሸቱ
ከማታለል
አሁን በቃን : መከራከር ።
አትደውይ
አልደውልም
ስሜን ብቻ : ለአፍታ አንሺው ፣
ከሞገስ ጋር
ከፍቅር ጋር
እደርሳለሁ : ትዝታሽን : ላስታግሰው ።
798
ተርቤ ነበረ ... ዓይኗን ስታርቀው ፣
ጠምቶኝም ነበረ ... ሳቋን ስትሸሽገው ፣
ምላሼን ትሻለች ... ወዳ አታውቅም ሰው ።
ልውረድላት እኔ : ከልቧ ዙፋን ላይ ፣
ሰው ለምኜ አላውቅም ... እንኳን ለንግስና : ለ'አንድ' አፍታ ልታይ ።
798
(ቡና 40 ብር /ርዕስ ነው 🤔 አትበሉ 😀)
✍️ በንጉሡ ተሰማ(ጢያ)
አይዘልቁም ይሉናል : ከመቼው ታያቸው?
አንቺን አግዝፈውሽ : እኔን አሳንሰው።
ማነሱንስ ልነስ : አንቺን ግን በደሉሽ፣
እኔን አፅድቀውኝ : #ከፍ_አርገው_ኮነኑሽ
ምክንያት...
ከፍ ያለ በአፉ : ከገነቱ ደርሶ፣
እንዳይተርፍ ይወድቃል : ዝቅ ካለው አንሶ።
798
ግጥም :- ንጉሡ ተሰማ_____ ደገፉሽ ይሉኛል : ወጥተው ባደባባይ ሁሉም እያወቁ : እንደሌለሽ ፀባይ ። *** ዓይንህ ያምራል ብሎ : ሰው ነግሮኝ ነበረ ፣ አንቺን በማለቴ : ሳይቆይም ታወረ ። *** ነግረውኝ ነበረ : ጥርስህ ያምራል ብለው : አንቺን ከመስማቴ : ሳቄ ከኔ የራቀው ። *** ሁለመናህ ጥዑም : የተንቆጠቆጠ ፍቅርህ ... ወዳጅ ብቻ : ጠላትን የላጠ ብሎኝም ነበረ : ዛሬ ካንቺ ደርባ : በውሸት ያጌጠ። *** ይሁን ምን ያደርጋል !? አንድ ያንቺን ገላ እንጂ : እንዲቃጠል 'ምሻው ፣ ተከታይሽ እንኳን : 'ቆንጆ' 'ውብ' እንዳለሽ : መስገድ አያቆምም ገና ለሚመጣው።
798
ልክ 12 ሰዓት ሲሆን ይለቀቃል
በውስጡ ሁለት ትልልቅ የሞባይል ካርዶችን ይዟል (ቀድሞ የሞላ ይወስደዋል)
ከታች ባለው link ተጠቀሙ !!!
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/0KQXM7Oxt_0
798
( ✍️ንጉሡ ተሰማ (ጢያ)) / t.me/Nigusu_Tesema
****
ይዘረፋል ሁሉም : ከ'ቅኔ ጀምሮ : እስከ ንብረት ድረስ ፣
እኔን እንዳሰርሽኝ : እንዳፈናቀልሽኝ : እንደዘረፍሽኝ ውርስ ።
***
ታድሪ ትኖሪያለሽ : እኔ ተቸግሬ : አንቺ ተንደላቀሽ፣
ዘር አታስቆጥሪኝ : ሽለላ ፉከራ : እያልኩ እንዳስንቅሽ ፥
በይ ውረጅ ከልቤ : ወይ ነይልኝ ፈጥነሽ ፥
የፍቅር ጥለቱን : በእሳት ሳልስልልሽ ።
***
በጠራራው ፀሐይ : ልቤን አስከትለሽ : እንደነጎድሽ ወዲያ ፣
ነግሬያቸው ነበር ...እንዲመረምሩ : ካላታለልሻቸው ... የበደሌን ዝርፊያ ፣
ወይ ልቤን መልሺ ... ወይም ቅሪ ወዲያ ።
798
ተማሪ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ፣ ዘመድ እና የቅርብ ሰው ካሏችሁ አጋሩልኝ !!!! 🙏🙏🙏
https://youtu.be/xNFnuUydW28?si=XDkhM5OYHcfX_0VI
798
ከመናገር ቀርቷል : ደጅ አዝማችነቱ ፣
አንቺ ብቻ ሁኚ ... የልቤ ንግስቱ ።
Inspired by #Sunday (ልመና እና ዝገት)
@Nigusu_Tesema
798
የተፈናቀለ
የተጎሳቆለ ...
የተጨቆነ ህዝብ : በበዛበት ሀገር ፣
እንዴት ቢታሰብ ነው ?
ሰውነት ተሸሽቶ : መታበይ በ በርገር ።
ለሆድ ሆኖ ትግሉ : ለእንጀራ ለቁራሽ ፣
ሰውነት ረገፈ : እንደሚቦን አመድ : እንደቤት ፍርስራሽ ።
👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/AgBjDz-EWHs?si=qeOu_WX8fS55nJBW
¡Ya disponible! Investigación de Telegram 2025 — los principales insights del año 
