ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

የተሰባበሩ ፊደላት

የተሰባበሩ ፊደላት

الذهاب إلى القناة على Telegram
793
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+17 أيام
+130 أيام
أرشيف المشاركات
ውልብታ (በእውቀቱ ስዩም)
በደራው ጎዳና፤ ብቅ ብትይ ደንገት ተበደርኩኝና የሎጥን ሚስት አንገት ዞሬ ባስተውልሽ ፤ ድፍርስ አይኔ ጠራ፤ ማየት ፍዳን ሳይሆን፤ ጽድቅን እየጠራ፤ ፈገግታሽ አንደ ህልም የሁዋሊት ያስኬዳል፤ በዚህ መጠን ማማር፤ በህግ ይፈቀዳል ?

photo content

ኩል እና ዙፋኑ
ተኩ'ላ ታይታለች : ከታችኛው መንደር፣ ውሾቹ ጮኸዋል : መምጣትሽን ለማብሰር ። ይደምቃል መንደሩ : በእሷ መኳኳል ውስጥ ፣ ናፍቆት እና እሳት : በአንዴ ደርሶ ሲረግጥ። ተኩ'ላ ኩሉን : ሠው'ን አስፈጀችው ፣ አንበሳ እና ነብር : ነኝ ማለት ጀምሯል ፡ በጉ በየቦታው ፣ አንድ የአደን ዝና አንድ እንኳን 'ሚያፀድቀው : ሥራ እጁ ሳይነካው ፣ ለሹመት ይሮጣል : ኩልሽ'ን ለማጥፋት : ህሊና ሳይኖረው። ✍️ @Nigusu_Tesema

photo content

(በላይ በቀለ ወያ ) ነግሬሽ ነበረ... ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!! ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ነግሬሽ ነበረ.... ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ የወንድ ልጅን ዐይን.. ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ ነግሬሽ ነበረ... ትንሽ ስትዘነጊኝ ፣ ብዙ እንደማስብ!!! ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ ሳሙና ነው ብዬ ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ እድፋም ስሜቶችን... አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!! ።።፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።።።። ነግሬሽ ነበረ... ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት በክብር ነው እንጂ... በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡ ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም ነግሬሽ ነበረ እናትነት ስሟ ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ። ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ነግሬሽ ነበረ... ሴት ክብሯን ስትጥል ፣ እድሜዋ ይሔዳል የወንድ ልጅ ቤቱ... የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ነግሬሽ ነበረ... ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው ቁንጅናም ይረክሳል! ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው! ።።።። ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ "ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ ልክ ነሽ አንዳንዴ እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ። ።።። ሞኝ ሰው ሲመክሩት ሞኝ ሰው ሲነግሩት የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ ግን እነግርሻለሁ! ነግሪያት ነበር ስል ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ። ።።። ግን እነግርሻለሁ ግን እመክርሻለሁ ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም ሁሉም ይመኟታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!!

Story

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ !!! መልካም አዲስ አመት !!!! @Nigusu_Tesema
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ !!! መልካም አዲስ አመት !!!! @Nigusu_Tesema

✍️ ንጉሡ ተሰማ (ጢያ) ከባህል እናምልጥ ? ተብትቦ ካስቀረሽ ? ኃላፊነት ነፍጎ : አባክኖ ካስቀረሽ ። ነይ አብረን እናምልጥ ! ሁሉም ቀላል አ'ርገው : እንዳልችል ካ'ረጉኝ፣ ወንድነቴን ነፍገው
✍️ ንጉሡ ተሰማ (ጢያ) ከባህል እናምልጥ ? ተብትቦ ካስቀረሽ ? ኃላፊነት ነፍጎ : አባክኖ ካስቀረሽ ። ነይ አብረን እናምልጥ ! ሁሉም ቀላል አ'ርገው : እንዳልችል ካ'ረጉኝ፣ ወንድነቴን ነፍገው : 'ኩራተኛ ብቻ' : ሥም ከለጠፉልኝ ፣ እናምልጥ ከእነኚህ : እኔነት ፍለጋ ፣ ለብቻ መቆሙን : እንልመደው እስቲ : ሸሽተን ከዚያ መንጋ ። @Nigusu_Tesema

Story

አሁን ከአሁን ካወቀችው ብዬ : የወንድን ፈተና : ችግሬን ሳልነግራት ፣ ዓይኔ ብርሃናማ : ብርሃን ሲበትን : ቃላት ሲዘራላት ፣ እሷ ልቧን እጓጂ : የፍቅሬን ከፍታ : ደርሳ ለመመልከት : እሷን መ
አሁን ከአሁን ካወቀችው ብዬ : የወንድን ፈተና : ችግሬን ሳልነግራት ፣ ዓይኔ ብርሃናማ : ብርሃን ሲበትን : ቃላት ሲዘራላት ፣ እሷ ልቧን እጓጂ : የፍቅሬን ከፍታ : ደርሳ ለመመልከት : እሷን መች አደላት !? *** የሰከነ ልቤ : ይናጣል በሷው ክንድ ፣ መረጋጋት የለም : አንድ ቦታ መልመድ ፣ ስትመጣ ደስ ብሎኝ : እሸኛለሁ ስትሄድ ። *** ስጋት አለኝ... የወሰደ መጓገድ : ሁሉ አይ'መልስም ፣ ቀርታ እንዳይሆን ብቻ : በቅርብ አልታየችም፡፡ ✍️_ @Nigusu_Tesema

photo content

አውቄ ነው እንጂ : ዝም እና ሄድ ያልኩት ፣ ትንሽ ሰነባብቷል : ዓለም'ን ከተውኩት ። *** ሄድኩኝ : መጥቻለሁ መጣሁ : ቀርቻለሁ : እያለ ላይሞላ ፣ ስንቱን ወጣት ንቆ : ስንቱንስ አጉላላ ።
አውቄ ነው እንጂ : ዝም እና ሄድ ያልኩት ፣ ትንሽ ሰነባብቷል : ዓለም'ን ከተውኩት ። *** ሄድኩኝ : መጥቻለሁ መጣሁ : ቀርቻለሁ : እያለ ላይሞላ ፣ ስንቱን ወጣት ንቆ : ስንቱንስ አጉላላ ። *** በከንፈሩ ብቻ : ሀገር እየሰራ : እየሸጠ ደርሶ ፣ ስንት ስጋ ቆርሶ : የስንቱ ደ'ም ፈሶ ፣ መዝቀጥ መንኮታኮት : መውደም መጥፋታችን ፡ በማር ተለውሶ ፣ ደስታ ሳቅ ብልጭታ : ብቻ ያሳዩናል : ህሊናቸው ፈርሶ። *** አውቄ ነው እንጂ : ዝም እና ሄድ ያልኩት ፣ ትንሽ ሰነባብቷል : ዓለም'ን ከተውኩት ። ✍️ @Nigusu_Tesema

photo content

ማንነት ቀይሬ ላኑር ባልኩኝ ፍቅሬ'ን ፣ ከ ቀስታ ጉዞ : መርጬ መፍጠንን ፣ ዘራፍ ወንዱ... አጣሁ በሜዳዬ : ሰጋሪ ፈረሴን ። *** ጀግንነት ወርሼ : ከአባት ከ ሀያቴ ፣ ለካ... ሚቀየር አይደ
ማንነት ቀይሬ ላኑር ባልኩኝ ፍቅሬ'ን ፣ ከ ቀስታ ጉዞ : መርጬ መፍጠንን ፣ ዘራፍ ወንዱ... አጣሁ በሜዳዬ : ሰጋሪ ፈረሴን ። *** ጀግንነት ወርሼ : ከአባት ከ ሀያቴ ፣ ለካ... ሚቀየር አይደለም : ጠይም እኔነቴ ። ሜዳ እና ፈረሱ : ጀግኖችን ይመርጣል ... ፣ ለሚመጣው ፍቅርን : ሂያጆችን ይሸኛል ። ምርጫ ትቶልሻል... የቱ ይሻልሻል ? (ለተጓዥ) ✍️ @Nigusu_Tesema

Inbox for any inquiries you wish to submit. @Nigusu_Tesema
Inbox for any inquiries you wish to submit. @Nigusu_Tesema