cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

🔥𝑺𝒆𝒏𝒋𝒐 𝑫𝒂𝒊𝒍𝒚 𝑵𝒆𝒘𝒔 𝑶𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍 💯

👉የቀኑ አዳዲስ ቀናዊ ውሎዎች ዜናዎች እንደደረሱ እናቀርብሎታለን 👉የደረሱንን ዜናዎች አጠናክረን እናቀርባለን 👉ስለ ሴንጆ ፕሪምየር ሊግ ውጤቶች እናወራለን 👉ትኩስ ዜና ካሎት ለቦቱ ይላኩ ቢቻል ከፎቶ እና ከነ ሙሉ መረጃው ብትልኩልን ምርጥዬ ነው ብቻ እርሶ ቻናላችንን ሼር ያርጉ ሀሳብ አስተያየቶን @senjonewsgp ያድርሱን @senjonewssbot

Mostrar mĂĄs
Publicaciones publicitarias
2 381
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የcallids batch መፅሄት ብልሽት የ2015E.C የCallidus batch መፅሄት ከወራት ጥበቃ እና እንግልት በኋላ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ ተጠናቆ መምጣቱን ገልፀን ነበር እናም አልቆ የመጣው መፅሄት እንደተመለከትነው እጅግ በጣም አሳፋሪ ሆኖ አጊኝተነዋል። ጉድለቶቹ እና ጥፋቶቹ ከመፅሄቱ መጀመርያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ በጉልህ ሰፍሮ የሚታይ ሲሆን ጥፋቶቹ ተቆጥረው የማያልቁ እጅግ አሳፋሪ ስራ ነው። ከጥፋቶቹ ውስጥ ጥቂቶቹን ለመግለፅ ያክል ብራቸውን ከፍለው መፅሄት እንዲታተምላቸዉ ያዘዙ ተማሪዎች ከነአካቴዉ በመፅሄቱ ላይ ያለመካተታቸዉ፣የመፅሄት ፅሁፍ አስገብተው በመፅሄቱ ላይ ያልተፃፈላቸው እንዲሁም የተሳሳቱ መግባት የሌለባቸው ፎቶዎች እንዲሁም የተበላሹ ምስል አገባቦች ከታዩ ጥፋቶች በጥቂቱ ሲሆኑ የተቀሩትን ጥፋቶች እዛዉ መፅሄቱ ላይ በግላጭ መመልከት የምትችሉት ሀቅ ነው። የምረቃ ኮሚቴው እነዚህን ጥፋት እና ጉድለቶች ለማስቀረት እናም በጥሩ ህትመት ቤቶች ስራውን ለማከናወን የሞከረ እና የጣረ ቢሆንም ከላይ በነበሩት አካላት (በምረቃ ኮሚቴው መሪ በነበረው አካል )እንቢተኝነት ለግል ጥቅም በተደረገ ሴራ ምክንያት የምረቃ ኮሚቴው ጥረት ሳይሳካ አሁን ለደረሰው ጥፋት መንስኤ ሆኗል። መፅሄቱን ለመቀበል የሄዱ ተማሪች የደረሰውን ጥፋት ለመጠየቅ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ወደተባሉት አካላት ቅሬታው ለማቅረብ ቢሄዱም በ"ምን አገባኝ" ምላሽ ከቢሮ የተሰናበቱበት ሁኔታም ነበር። ከላይ ለተጠቀሱት ሁሉ ጥፋቶች እና ጉድለቶች የምረቃ ኮሚቴ "መሪ" የነበረው አካል ሙሉ ሀላፊነቱን የሚወስድ ይሆናል። ለደረሱት ጉድለቶች እና ጥፋቶች በተማሪዎች ተወክለው የነበሩ የምረቃ ኮሚቴ አባላቶች ስም ታላቅ ይቅርታ ለወከሉን ተማሪዎች እንጠይቃለን። ከላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች ቀጣይ ለሚመጡ ተመራቂ ተማሪዎች የማንቂያ ደውል ሆኖ ሊጠቀስ ይገባል። Big love & Big respect All of Callidus batch students❤️‍🩹 [የምረቃ ኮሚቴው] @senjonews @senjonewsgp
Mostrar todo...
👍 17
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
የፌስቡክ አገልግሎት ተመለሰ። ለሰዓታት ተቋረጠው ከነበሩት በሜታ ስር ከሚገኙት አገልግሎቶች አንዱ ፌስቡክ ዳግም መስራት ጀምሯል። እዚህ ኢትዮጵያ ኢንስታግራም እና ትሬድ አሁንም እየሰሩ እንዳልሆነ ለመረዳት ተችሏል። የሜታ አገልግሎቶች በምን ምክንያት እንደተቋረጡ እስካሁን በኩባንያው በኩል በይፋ የተባለ ነገር የለም። @tikvahethiopua
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🚨 ከስፖርት ውጭ | ፌስቡክ፣ ኢንንስታግራም እና ሜሴንጀር በመላው ዓለም ተቋረጡ በሜታ ኩባንያ ስር የሚንቀሳቀሱት ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር በመላው ዓለም በድንገት መቋረጣቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ነው። እነዚህ የማህበራዊ ትስስር አይነቶች መቋረጣቸው በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ሰበር ዜና ሆኖ እየወጣ ይገኛል።[EBC] @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
Mostrar todo...
🚨ለ2015 የቅዱስ ዮሴፍ አዳማ Callidus batch ለነበራቹ በሙሉ🚨 ከወራት በፊት ትዕዛዝ ላይ የነበረው መፅሄት በመጠናቁ ከነገ 27/2016 ጀምሮ ትምህርት ቤት በመሄድ ከስቶር የትናየት ጋር በመሄድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን። ራቅ ያለ ዩንቨርስቲ የምትገኙ ወላጆቻቹ እንዲቀበሉላቹ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን አያይዘን እንገልፃለን። @senjonews @senjonewsgp
Mostrar todo...
👍 5❤‍🔥 2❤ 2
🚨ሰኞ እለት ወደ መደበኛው የትምህርት ጊዜ የምትመለሱ ይሆናል።
Mostrar todo...
👍 44🤝 5🔥 3🎉 2
Photo unavailableShow in Telegram
🚨Breaking🚨 ለቅዱስ ዮሴፍ አዳማ ተማሪዎች በሙሉ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ነገ የካቲት 22/2016 ዓ.ም እንደ ኦሮሚያ ክልል በወጣ ትእዛዝ ከነገ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የመምህራን ስልጠና በመኖሩ ነገ የመደበኛ ትምህርት እንደማይኖር ልናሳውቅ እንወዳለን። እንዲሁም በዕለተ እሁድ ሊከናወን ታቅዶ የነበረው የወላጆች ቀን በአልም በዚሁ ምክንያት ለሌላ ቀን መዘዋወሩንም ለመግለፅ እንወዳለን። [ወ/ም አማኑኤል ሰይፉ] #Share_Share📱📲 @senjonews @senionewsgp
Mostrar todo...
👌 48🎉 11👍 8😍 8🙏 5❤ 4❤‍🔥 3🔥 3🫡 1
Repost from Tikvah-University
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ እየተካሔደ ነው።
ተፈታኝ ተማሪዎችን የመመዝገብ ሥራ ከየካቲት 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል። ምዝገባ የጀመሩ አካባቢዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ምዝገባ ያልተጀመረባቸው አካባቢዎች በቀጣይ ምዝገባውን እንደሚያካሒዱ የአገልግሎቱ ም/ዋ/ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ገልጸዋል። በመደበኛ እና በማታ መርሐግብር የመልቀቂያ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች ይከናወናል የተባለ ሲሆን በግል፣ በርቀት እና በበይነ መረብ ተምረው የሚፈተኑ ተማሪዎች ምዝገባ በክ/ከተማ፣ በልዩ ወረዳ እና በወረዳ የትምህርት ጽ/ቤቶች እንደሚካሔድ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከ870 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ይጠበቃል። @tikvahuniversity
Mostrar todo...
🔥 2👍 1
Repost from Tikvah-University
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡ የተፈጥሮ ሣይንስ፦ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት የማኅበራዊ ሣይንስ፦ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል። በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል። ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል። የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። @tikvahuniversity
Mostrar todo...