cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Injibara University👩🏻‍🎓🧑🏻‍🎓👨‍🎓

- Hello Injibara university students. - technology , news etc -Sport News ♦️ ለአስተያየት ፣ጥያቄ ፣ጥቆማ ፣ ለማስታወቂያ ፣ @injibara_Uni_bot

Mostrar mĂĄs
EtiopĂ­a10 250AmĂĄrico8 900La categorĂ­a no estĂĄ especificada
Advertising posts
291Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Repost from Tikvah-University
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለ153 ተማሪዎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ/STEM ስልጠና መስጠት ጀምሯል። ሰልጣኝ ተማሪዎቹ ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚገኙ ሲሆን በጉራጌ ዞን የተውጣጡና የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸው ተገልጿል። የክረምት መርሃ ግብር ስቴም/STEM ፕሮግራም ሰልጣኞቹ በቆይታቸው ተገቢው ተግባር ተኮር ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተመላክቷል። በተጨማሪም የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት በዩኒቨርሲቲው እንደሚቀርብላቸው የዩኒቨርሲቲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ዳይሬክቶሬት መረጃ ያሳያል። @tikvahuniversity
Mostrar todo...
Repost from Tikvah-University
በጎንደር ሁሉም ዞኖች ለሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ሊሰጥ ነው። የጎንደር ሰላምና እድገት ማኅበር የተባለ የሲቪክ ተቋም በጎንደር ሁሉም ዞኖች በሚገኙ 80 ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመጪው መስከረም ለሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል የኦሪንቴሽን መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ በማጠናከሪያ ትምህርት ፕሮግራሙ 400 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና 80 የዩኒቨርሲቲ መምህራን እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡ የማጠናከሪያ ትምህርቱ ባለፈው ዓመት የታየውን የ12ኛ ክፍል ፈተና የውጤት ማሽቆልቆል ለመቀልበስ እንደሚያግዝ የገለጹት የማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሪሁን ካሳው፤ የትምህርት ይዘቶችና ግብዓቶች ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። @tikvahuniversity
Mostrar todo...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#MadingoAfework ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
ጎንደር ጎንደር… "…የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድምጻቸውን ማሰማት ጀመሩ። ያኔ የወያኔ መንግሥት በመውደቂያው ዋዜማ ወያኔ በኦሮሚያ ለምትጨፈጭፋቸው ኦሮሞዎች የፍርሃት ወጥመድን ሰባብሮ በመጣል አደባባይ ወጥቶ ለኦሮሞ ወንድሞቹ ድምጹን ያሰማው ጎንደር ነው። "በኦሮሚያ የሚፈሰው ደም የእኔ ደም ነው" በማለት ድምፁን ያሰማና በእለቱም የወያኔ አግአዚ ጦር በስናይፐር ብዙ ጎንደሬዎችን የፈጀበትን ጊዜ እናስታውሳለን። ስብሃት ነጋና ማፍያ ቡድኑ እንደሚበተኑ፣ ኢትዮጵያ ግን እንደምትቀጥል ጎንደር ነበር በፖለቲካ ነቢያቶቿ በኩል ያወጀችው። "…ለኦሮሞ ብላ በወያኔ የሞተችው ጎንደር ዛሬም ኦሮሞ ለወያኔ መደረቡ ሳያንስ ወያኔም ሄዳ በኦሮሞ መገደል፣ መጨፍጨፉ በዛበት። እናም ዛሬ ጎንደር እምቢ አልታረድም ብላ ድምጿን ሀ ብላ ማሰማት ጀምራለች። ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምኦንም "እኛን የኦሮሞ ተቃውሞ አላሰጋንም፣ እኛን አንኮታክቶ የጣለን የዐማራ ተቃውሞ ነው፣ ጎንደር ላይ የተነሣውን ተቃውሞ ነው መመከት ያልቻልነው" ነበር ያሉት። ጌታቸው ረዳ እና ሙፈሪያት ካሚልም ያኔ በፋና ቴሌቭዥን ቀርበው "እንዴት የጎንደር ዐማራ የኦሮሞ ወንድሜ ብሎ ሰልፍ ይወጣል? በማለት ነበር ኮሬንቲ ለመጨበጥ ሲንጨረጨር የነበረው። "…ጎንደር በዐብይ አሕመድ አማችነት ከተያዘች በኋላ ዝምታ አብዝታ ነበር። የጎንደር አክቲቪስቶች እነ ቶማስ ጃጀው፣ ሙሉአለም ገብረመድህን ወዘተም ድምፃቸውን ካጠፉ ቆይተዋል። ዛሬ ሃይለማርያም ደሳለኝና ሙላቱ ተሾመ ጎንደር ሄደው ችግኝ ትከሉ ቢሉም ጎንደር ዛሬ በወለጋ ለታረዱት ከ2ሺ በላይ ለሆኑት ዐማሮች ድምጿን ማሰማት ጀምራለች። አትነሣም ወይ፣ አትነሣም ወይ የፈሰሰው ደም ያንተ አይደለም ወይ ⛔ በቃ‼️ ⛔ ቀይ አሻራ ⛔ ብሔራዊ የዜግነት ክብር #Stop_amhara_genocide
Mostrar todo...
Repost from Injibara University
Academics without Borders (AWB) volunteer, Prof. Margaret Osborne, from the School of Business at Seneca College, attended a first-year entrepreneurship class as a guest lecturer this week.    Prof. Osborne and fellow AWB volunteer and Seneca faculty member, Dr. Hemant Sangwan, are working with the faculty of the College of Business and Economics at Injibara University to supplement the freshman entrepreneurship course with pedagogical techniques and case studies, providing practical examples for students on entrepreneurship opportunities.    Mr. Lingerew Atinkut, the Dean of the College of Business and Economics, indicates that the support provided by the AWB volunteers has the potential to enhance the entrepreneurship course for the benefit of current and future students.  It is worth mentioning that Injibara University has been providing training to various departements of our university through the project Academic without Border (AWB). Jun
Mostrar todo...
Repost from Injibara University
ማስታወቂያ ******** ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ አመልካቾች እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባወጣው ማስታወቂያ ተመዝግባችሁ ለፈተና የተመለመላችሁ ስለሆነ ሰኔ 8/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በዩኒቨርሲቲው ሰው ኃብት ሥራ አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳውቃለን፡፡ ሰኔ 1/2014 ዓ.ም፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
Mostrar todo...
Repost from Injibara University
ማስታወቂያ *** ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ፦
Mostrar todo...
Repost from Injibara University
ማስታወቂያ *** ለመጀመሪያ ዲግሪ ክረምት ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
Mostrar todo...
Repost from Injibara University
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የክህሎት ስልጠና ተሰጠ፡፡ ***** የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከእንጅባራ ከተማ የከተሞች ምግብ ዋስትና ሴፍትኔት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ከእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ 567 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ሲሰጥ የነበው የክህሎት ስልጠና ተጠናቋል፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ የተገኙት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር መልካም አባተ የዚህ ስልጠና ዓላማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ከድህነት እንዲወጡ የክህሎት ስልጠና መስጠት እና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ዶ/ር መልካም አያይዘውም ስለ ህይወት ክህሎት፣ በገንዘብ አያያዝ፣ በጊዜ አጠቃቀም፣ ግጭት የመፍታት እና መቻቻልን የማዳበር ክህሎት ላይ አተኩሮ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ የእንጅባራ ከተማ የከተሞች ምግብ ዋስትና ሴፍትኔት ፕሮግራም አስተባበሪ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ምህረት በበኩላቸው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከከተማዋ ለተውጣጡ እና በ5ቱ ፓኬጆች ለተቃፉ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ዋስትናቸውን ለማረገገጥ ለሚደረገው እንቅስቃሴ አጋዥ የሆነ የክህሎት ስልጠና በመስጠቱ አመስግነው በቀጣይ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በትብብር ለመስራት ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የትምህርት እና ስነ- ባህሪ ኮሌጅ የሳይኮሎጅ መምህራን የሆኑት መ/ር እርቅይሁን አላምነህ፣ መ/ር ሙላት አራጋው፣ መ/ር አድምጠው አበበ እና መ/ር ፈንታሁን እንዳሌ ሲሆኑ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል። ሰልጣኞችም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው ባገኙት የህይወት ክህሎት ስልጠና መደሰታቸውን ገልፀዋል። ግንቦት 29/2014 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
Mostrar todo...
Repost from Injibara University
Academic Without Border የተሰኘ የፕሮጀክት ተቋም ለ1ኛ አመት ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሥራ ፈጠራ ክህሎት ገለፃ አደረገ፡፡ **** ከናዳ ሀገር የሚገኘው Academic Without Border (AWB) የተሰኘ የፕሮጀክት ተቋም ለአንደኛ ዓመት የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በሥራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ተጋባዥ መምህር በሆኑት የ AWB volnter and School of Business at Seneca Colleage Prof. Margaret D. Osborne እንዲሁም የAWB በጎ ፈቃደኛ እና seneca facality member, Dr. Hemanet Sangwan አማካኝነት ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ጋር በመሆን በምሳሌ የታገዘ ገለፃ አድርገዋል። በተጨማሪም ለመምህራን የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት፣ የሥራ ፈጠራ ማስተማሪያ (ሞጁል) ዝግጅትና የመማር ማስተማር ስራን ለዚሁ የትምህርት ዓይነት አጋዥ ማድረግ፣ የሥራ ፈጠራ ክለብ እና ኢንኩቤሽን ሴንተር ማቋቋም ወደ ፊት የሚሰራባቸው ዘርፎች እንደሆኑ ፕሮግራሙን ያስተባበሩት የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን አቶ ልንገረው አትንኩት ተናግረዋል፡፡ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ Academic without Border (AWB) በተሰኘ ፕሮጀክት አማካኝነት ለዩኒቨርሲቲያችን የተለያዩ ሥራ ክፍሎች ሥልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ ግንቦት 30/2014 ዓ.ም፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
Mostrar todo...