Eshet Academy General Secondary School
Ir al canal en Telegram
Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
2 215
Suscriptores
-224 horas
+27 días
+230 días
Archivo de publicaciones
ለእሸት አካዳሚ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪና ወላጆች በሙሉ
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ቤት ወርሃዊ ክፍያ በፊት እንደነበረው በወጋገን ባንክ የሚቀጥል ሲሆን ከጥቅምት /2019 ጀምሮ ወርሃዊ ክፍያችሁን በአዲስ መክፈያ ኮድ የሚከፈል መሆኑን እየገለፅን ኮዱንም ከታች ባስቀመጥንላችሁ ኤክሴል ላይ ከስማችሁ ትይዩ ያለውን ESST ብሎ የሚጀምረውን User ID ቁጥር በመጠቀም መክፈል የምትችሉ መሆኑን እያሳሰብን የጥቅምት ወር ክፍያ የሚከፈለው ከጥቅምት 25 እስከ ህዳር 10 ነው።
Repost from Ministry of Education Ethiopia
📢 ማስታወቂያ
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
1. በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement
ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ።
2. በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement
3. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሁን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት የምትችሉ መሆናችሁን እንገልጻለን።
ትምህርት ሚኒስቴር
ማስታወቂያ
በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7/ 2019 ዓ.ም. እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ እንድትሞሉ እንገልጻለን።
የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences
05/01/2019
ሰላም የተከበራችሁ ተማሪዎችና ወላጆች ዛሬ የትምህርት አጀማመር ላይ የተገኘው ተማሪ ቁጥር ከሚጠበቀው አንፃር ዝቅተኛ ነው። ስለዚህ ከነገ ጀምሮ መደበኛ መማር ማስተማር ስራው ተጠናክሮ ስለሚቀጥል ማንኛውም ተማሪ የትምህርት ቁሳቁሶችን አሟልታችሁ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን ።
የአንድ ቀን ትምህርት መባከን ወይም አለመማር ጉዳቱ ከፍተኛ ነው።
የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።
ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%)
2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%)
በልዩ ድጋፍ የሚታይ የተማሪ ምድብ
1. ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)
2. ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)
3. በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውር ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%)
4. በተፈጥሮ ወይም በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
03/01/2019
በቅድሚያ ለትምህርት ቤታችን ተማሪዎች እና ወላጆች እንኳን ለ2019 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ እያልን የ2019 ዓ.ም ትምህርት የሚጀምረው ማክሰኞ መስከረም 5/2019 መሆኑን እየገለፅን በዕለቱ ሁሉም ተማሪዎች ዩኒፎርማችሁን ለብሳችሁ እንዲሀም አስፈላጊ የትምህርት መሳሪያዎችን አሟልታችሁ እንድትገኙ ።በዕለቱ ትምህርት ቤት የምትቆዩት እስከ 6:00 ሰአት መሆኑን እንገልፃለን።
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE
የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ወስደው በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲያስገቡ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ተማሪዎች ምርጫቸውን ትምህርት ቤት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው በኦንላይን ማስገባት ይችላሉ።
የምርጫ ማስገቢያ ድረ-ገጹ፦ student.ethernet.edu.et ነው።
- በሕክምና ምክንያት ልዩ ሁኔታ ያላቸው፣
- የአካል ጉዳተኛ የሆኑ፣
- ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች
- ከ6 ወር በታች ሕፃን የሚያጠቡ እናቶች ተገቢውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ እንደሚጠበቅባቸውም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
#MoE
ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።
በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
Repost from እሸት አካዳሚ ከ1-8ኛ ክፍል
30/11/2018
በ2018 የትምህርት ዘመን በእሸት አካዳሚ 8ኛ ክፍል ለተፈተናችሁና ክልላዊ የሚኒስትሪ አማካይ ውጤት 50እና በላይ ላመጣችሁ በመሉ
ከዚህ በፊት ባስተላለፍነው መልዕክት መሰረት የ2019 የትምህርት ዘመን የ9ኛ ክፍል የመጨረሻ ምዝገባ ነገ ማለትም ነሐሴ 01/2018 መሆኑን እየገለፅን ከዚህ ቀን በኋላ ለሚመጣ ተመዝጋቢ ቦታ ባይኖር ሃላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን ።
እሸት አካዳሚ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
16/11/2018
ለአዲስ አመልካች ተፈታኝ ተማሪዎች
ነገ ሊሰጥ የነበረው መግቢያ ፈተና ለሰኞ 3:00 የተራዘመ መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ
1.ማንኛውም ነባር ተማሪ ለምዝገባ ሲመጣ የተማሪ ሪፖርት ካርድ ካልያዘ አይመዘገብም
2. ክፍያ ከፍሎ ለመመዝገብ የግድ ከትምህርት ቤት መጥቶ የባንክ መክፈያ ወረቀት መውሰድ አለባችሁ።
13/11/2018
ለእሸት አካዳሚ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ነባር ተማሪዎች በሙሉ
የ2019 ዓ/ም የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 15 /2018 ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ማለትም እስከ ሐምሌ 21/2018 ድረስ ብቻ መሆኑን እየገለፅን ከዚህ ቀን ውጭ የሚመጣን ነባር ተማሪ ቦታ ከሞላ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እየገለፅን
የምዝገባ ሰአት
ከጥዋት 2:30--6:00
ከሰአት 8:00-- 10:00 ሰአት መሆኑን እና የክፍያ አይነቶችና መጠኖችን ከዚህ በታች ባለው ምስል ልከናል።
