HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
Ir al canal en Telegram
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
Mostrar más2 277
Suscriptores
Sin datos24 horas
+47 días
+2930 días
Archivo de publicaciones
መተትንና ሥራይን በገንዘብ ማስፈታትና ያልገቡን ከባባድ እውነቶች!! ማህበረ ቅዱሳን ለመጀመሪያ ጊዜ ያጋለጠው ከባድ እውነት!! https://youtu.be/q1FBgB80UY4
#አሜሪካን_ያላችሁ_ተዘጋጅታችኋል!!
ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎት በአሜሪካን
=> በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት እና በአካባቢው የሚገኙ ማህበረ ምዕመናን ባደረጉት መንፈሳዊ አገልግሎት ጥሪ መሠረት እሑድ ከሚያዝያ 11 እስከ ሚያዝያ 13 April 19th To Tuesday April 21st ሰዓት 10am to 5:30pm የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ የወንጌል ትምህርትና የፈውስ የጠበል አገልግሎት ይከናወናል! ይህንን መንፈሳዊ አገልግሎት ከመላው አህጉራት እና ከተማ ለመሳተፍ የምትመጡ ምዕመናን አገልግሎት የሚከናወንበት የቦታ አድራሻ location ሜሪላንድ Patuxent River Park Pavilion 16000 Croom Airport Road Upper Marlboro, MD 20772 መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።
አዘጋጅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማህበረ ምዕመናን ኮሚቴ Beth Saida Orthodox group of Maryland 📞 240 605 4111
እኔ መምህር ግርማ ሲያስተምሩ ሆድ ይብሰኛል ችግራችን ፈተናችን የገባቸው አባት!! መምህር ተስፋዬ ላይ የተፈበረኩ የውሸት ዜናዎች!! #ፈውስ #ጸሎት #ስግደት https://youtu.be/KcpdCNo6qJM
=> እንኳን አደረሳችሁ የጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም ረድኤትና በረከት በሁላችንም ላይ ይደር። የቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎትና ምልጃ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅልን። እንደዚሁም ለልጆቻቸውና ለሀገራችን ኢትዮጵያ የለመንከው ልመና ሁሉ ይፈጸም፤ አሜን።
እግዚአብሔር ያክብርልኝ ከመሸ በኋላ ለላው ወንድማችን ደግሞ ተዓምረ ማሪያም ይገዛበት ብሎ ይኼንን አስገብቷል። በእውነት ዛሬ ቤተሰቦቼ አኮራችሁኝ። እግዚአብሔር በወጣ ይተካላችሁ። 🙏🙏
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን በእውነት! በድጋሚ አንዱ ወንድማችን ደግሞ ይኼው ይኼንን አስገብቷል። ቅዱስ ሚካኤል ይስጥልኝ።
ተመስገን ነው! ይኼው ለላኛው ወንድማችን ደግሞ ሙሉ የመጽሀፍቶቹን ወጪ ሸፍኖልናል! በወጣ ይተካ ብለናል። እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን።
መምህር ተስፋዬን ያናደደው የዲያቆን ዮርዳኖስ አሳፋርና የማይገባ ንግግር!! በዚህ ደረጃ አባቶችን መሳደብና መንቀፍ ለምን አስፈለገ!? #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ https://youtu.be/75OJJCwTv9o
ምስጥረን ሳታወጣ ግደላት አጥፋት ተብዬ በሽታ ሆኜ ገባሁባት አዋረደችኝ!! ሞገስ ሁኔኝ እያላችሁ ስገዱ ያልነው ለዚህ ነው!! በቅዱስ ቁርባን የታሰረ መንፈስ!! https://youtu.be/lwR4i4V6lds
#የበረከት_ጥሪ!
=> በቀን 21 ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ሙሉ በሙሉ የወደመው በጎፋ ዞን የሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን እና ነዋዬተ ቅዱሳትን የመተካት ዘመቻ ጀምረናል። ተሳተፉልን። ከታች ያሉት ነዋዬተ ቅዱሳት እና ቅዱሳት መጽሐፍት ስላልተያዙ ሸፍኑልን። ስለ ቅዱስ ሚካኤል ብላችሁ ዛሬ ሙሉ በሙሉ ከታች ያለውን ነዋዬተ ቅዱሳት እንድንችላቸው ዘንድ በዘመቻ እንሳተፍ።
6. ጽና /ብዛት 1/ ዋጋ :- 4,000.00
7. ኩስኩስት /ብዛት 1/ ዋጋ :- 4,700.00
8. ድርገት መውረጃ (አጎበር) /ብዛት 1/ ዋጋ :- 5,000.00
9. ከበሮ በቁጥር /ብዛት 2/ ዋጋ :- 9,000.00
10. ጽናጽል /ብዛት 10/ ዋጋ :- 4,000.00
11. መቋሚያ /ብዛት 10/ ዋጋ :- 2,000.00
12. ዣንጥላ ድባብ /ብዛት 2/ ዋጋ :- 5,600.00
13. ትልቁ ዣንጥላ /ብዛት 1/ ዋጋ :- 5,500.00
14. ደወል /ብዛት 1/ ዋጋ :- 22,000.00
15. ልብስ ተክኖ /ብዛት 1/ ዋጋ :- 18,000.00
16. ምንጣፍ በካሬ 87 ;- 27,840.00
17 መንበር .....50,000
የመጽሐፍት ዝርዝር
1. መጽሐፈ ቅዳሴ በቁጥር 1 - 3,000.00
3.ሃይማኖተ አበው በቁጥር 1 - 2,000.00
4.መጽሐፈ ግጻዌ በቁጥር 1 - 600
5.መጽሐፈ ክርስትና በቁጥር 1 -500
6.ታምረ ማርያም በቁጥር 1 -4,500.00
7.መጽሐፈ ሰዓታት በቁጥር 1-900
8.መልከእ ጉባኤ በቁጥር 1 - 900
9.ስንክሳር የዓመት በቁጥር 1 -5,500.00
10.ተአምረ ኢየሱስ በቁጥር 1 - 1,800.00
11.ግብረ ህመማት በቁጥር 1 - 4,400.00
12.መጽሐፈ እጣን በቁጥር 1-600
13.መጽሀፈ ግንዘት በቁጥር 1-500
**
ህጋዊ የቤተክርስቲያን አካውንት ቁጥእ
ማቼ ፃንጋ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
1000349219216
***
ያስገባችሁበትን የባንክ ስሊፕ ወይም ደረሰኝ በውስጥ መስመር ላኩልን። የምትሸፍኑትን ነዋዬተ ቅዱሳት መርጣችሁ ገንዘቡን በናስገባት ስሊፑን ላኩልን። ስለቅድስት ማርያም ብላችሁ🙏
መናፍስት በቶሎ እንድታሰሩ ይኼንን ሦስት መንገድ ዘወትር ተግብሩ!! የቤተሰብን መንፈስ በጭራሽ ወደራሳችሁ አትሳቡ!! 3ቱ ርኩሳን መናፍስትን ማሠሪያ መንገዶች! https://youtu.be/MoL9CmdkO9w
መምህር ግርማ ደብተራ ናቸው እያልኩ እንዳትኼድ እከለክላትና አጠራጥራት ነበር!! በወገብ ህመምና በዲስክ መንሸራተት የምትሰቃዬ ሰዎች ይኼንን አዳምጡ!! #ጸሎት https://youtu.be/y84_aKUv3O0
=> የእህታችን ጥያቄ! በህይወቴ በጣም የተወሳሰበ ነገር አለ እባክህን አማክረኝ፡፡ አንዳንዴ ግራ ይገባኛል እና የምትችል ከሆነ በመፍትሄ ሀሳብ እርዳኝ፡፡ ባለቤቴ በጣም እየረበሸኝ ነው። ለምን ትጸልያለሽ ይለኛል፡፡ ለምን ትቆርቢያለሽ ይለኛል፡፡ እኔን መስማት ያመዋል፡፡ ብቻ ምኑ ቅጡ ግራ ገባኝ አሁን። ምን ላድርግ?
=> እህታችን እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ፈታኝ ወቅት ብርታቱንና ትዕግሥቱን ይስጥሽ። ባለቤትሽ በጸሎትሽና በቍርባንሽ ላይ የሚያሳየው ተቃውሞ በመንፈሳዊው ዓለም "የፈተና ውጊያ" ተብሎ ይታወቃል። ሰይጣን አንቺ ወደ ፈጣሪሽ ስትቀርቢና ስትቀደሺ ስለሚቀና፣ የሚወጂውን ሰው በመጠቀም ሰላምሽን ሊነጥቅሽና ከመንፈሳዊ መንገድሽ ሊያስቆምሽ ይጥራል። ከዚህ በታች ያሉትን 5 ነጥቦች በጸሎትና በጥበብ ተግብሪያቸው፦
፩. ውጊያው ከመንፈስ ጋር መሆኑን ተረጂ፦ ባለቤትሽ እንዲህ የሚያደርገው በውስጡ ባለ ድካም ወይም በጠላት ውጊያ እንጂ እርሱ ክፉ ስለሆነ አይደለም። ስለዚህ በእርሱ ላይ አትቆጪ፣ አትጣዪውም፤ ይልቁንም በውስጡ ያለውን ያንን አስቸጋሪ መንፈስ በጸሎት ተዋጊው። ቅዱስ ጳውሎስ "መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለም" (ኤፌ ፮:፲፪) እንዳለው አስቢ።
፪. በምስጢርና በጥበብ ጸልዪ፦ ጸሎትሽ በእርሱ ፊት ጠብ የሚያጭር ከሆነ፣ ጌታችን በወንጌል እንዳዘዘን "ወደ እልፍኝሽ ግቢና መዝጊያሽን ዝጊ" (ማቴ ፮:፮)። እርሱ በሌለበት፣ ተኝቶ እያለ ወይም በልብሽ በስውር ጸልዪ። አምላክ በስውር የምታደርጊውን ጸሎት ይሰማል፤ በመካከላችሁ ያለውንም ግድግዳ ያፈርሰዋል።
፫. በምግባርሽ መስክሪለት፦ ጸሎትና ቍርባን በውስጥሽ ሰላምን፣ ትሕትናንና ፍቅርን ሊያሳድጉ ይገባል። እርሱ ሲቆጣሽ አንቺ በትሕትና ዝም ስትዪ፣ ይበልጥ ስትንከባከቢውና ፍቅር ስታሳዪው "ይህቺ ሴት የምትጸልየው ጸሎት ለውጥ አምጥቶባታል" ብሎ እንዲያምን ያደርገዋል። ቅዱስ ጴጥሮስ "ያለ ቃል በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲረቱ" (፩ኛ ጴጥ ፫:፩) እንዳለው፣ ያንቺ ዝምታና ትዕግሥት ትልቁ ስብከት ነው።
፬. የንስሐ አባትሽን አማክሪ፦ ይህንን ሁኔታ ለንስሐ አባትሽ በግልጽ ንገሪያቸው። አባቶች ምስጢራዊ በሆነ መንገድ (በጸሎትና በምክር) የሚረዱበት መንገድ ይኖራል። ምናልባትም በመካከላችሁ ያለውን የጠላት ውጊያ የሚሰብር ልዩ ጸሎት ሊያደርጉላችሁ ይችላሉ።
፭. ስሙን በመቁጠሪያ ጥሪ፦ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ለባለቤቴ ልቦና ስጠው፣ ቤታችንን በሰላም አብራልን" እያልሽ በመቁጠሪያሽ ለምኚ። የፈጣሪ እጅ የሰውን ልብ የማለስለስ ኃይል አለው።
በመጨረሻም እህቴ ሆይ፤ አትሸበሪ፣ ተስፋም አትቁረጪ። ቅዱስ ቍርባን የሕይወት መድኃኒት ነውና ከንስሐ አባትሽ ጋር በመመካከር በንጽሕና መቀበልሽን አታቋርጪ። ጠላት አንቺን ለማስቆም ቢሞክርም፣ አንቺ ግን በትዕግሥት ከጸናሽ ባለቤትሽንም ጭምር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይዘሽው ትገባለሽ።
"ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል።" (ያዕቆብ ፬:፯)
እግዚአብሔር ሰላሙን በቤትሽ ያውርድ! አሜን።
=> የአባታችን መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ መንፈሳዊ አገልግሎት ቀጥሏል!! ጉባኤው በቀጣይ ቅዳሜና እሁድ በ26 እና በ27 /07/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አያት ቅዱስ ፋኑኤልና መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን የወንጌል ትምህርት እና የፀበል አገልግሎት ይከናወናል ሥለ አገልግሎቱ ፈጣን መረጃዎችና አዳዲስ ትምህርቶች እንዲደርሳችሁ ቻናሉን አሁኑኑ #የዩቱብ ቻናላችንን #ሰብስክራይና #ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ። ለሁሉም እንዲዳረስ #ሸር ማድረጋችሁን እንዳትረሱ!!
ይኼንን ጉዳይ እንደቀልድ የምታስቡ ሰዎች እራሳችሁን በደንብ ፈትሹ!! በዕዳ የተያዘ ትውልድ መከራው ብዙ ነው!! ለዘላለሙ ሰዓት የምትዘጋጀው ቤተክርስቲያን!! https://youtu.be/XxQh4ZSkneM
