es
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 470 suscriptores, ocupando la posición 5 536 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 193 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 470 suscriptores.

Según los últimos datos del 29 julio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 70, y en las últimas 24 horas de -1, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 26.77%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 8.00% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 141 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 237 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 22.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 30 julio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 470
Suscriptores
-124 horas
+837 días
+7030 días
Archivo de publicaciones
ገብርኄር፤ ስድስተኛው ሳምንት #ገብር ኄር፥ ገብር ምዕመን ፥ ገብር ሀካይ ስድስተኛ ሳምንት ገብርኄር ይባላል፡፡ ገብርኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት ስለ ስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኄር /ስለታማኝ/ አገልጋይ ያስተማረውን ትምህርት ይነገራል ይህንንም የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡ ይኸውም ማቴ 25፥14-30 ላይ ይገኛል፡፡ (ይህም ክፍል ጌታችን በማቴዎስ ወንጌል በምሳሌ ካስተማራቸው ትምህርቶች አንዱ ነው)፡፡ ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ዐቅሙ፡ ለአንዱ አምስት መክሊት፥ ለአንዱ ሁለት፥ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ፡፡ መክሊት የወርቅ መለኪያ /መስፈሪያ/ ነው፡፡ አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፡፡ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ ፡፡ አንድ ተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቆፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ፡፡ ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቈጣጠራቸው፡፡ *አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክ፤ ‹‹ ጌታ ሆይ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት›› አለ፡፡ ጌታውም፦ ‹‹መልካም አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ (ገብር ኄር)፤ በጥቂቱ ታምነሃል በቡዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፡፡›› አለው፡፡ *ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት፡፡›› አለ፡፡ ጌታውም፡፡ መልካም፡ ‹‹ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ (ገብር ምዕመን) በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ *አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ካልዘራህባት የምታጭድ፥ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ሌቦች እንዳይሠርቁኝ አታላዮች እንዳይቀሙኝ ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ መክሊትህ እነሆ›› አለው፡፡ ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፡- ‹‹አንተ ክፋና ሃኬተኛ ባሪያ (ገብር ሀካይ) ካልዘራሁበት እንደማጭድ ፥ ካልበተንሁበትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፤ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር፡፡ ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አስር መክሊትም ላለው ስጡት፤ እሱን ደግሞ ወደ ዘለዓለም ሐዘንና መከራ ወዳለብት ወደ ጨለማው አውጥታችሁ ጣሉት›› አላቸው፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወስድበታል፡፡  አገልጋዮችም ይህንን ክፉ አገልጋይ ወደ ጨለማው አውጥተው ጣሉት፡፡ በዚህ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡ † መክሊት የተባለ ጸጋ ስጦታ ሲሆን፤ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታ ተሰጥቶናል በተሰጠንም ስጦታ ልናገለግልበት ያስፈልጋል፡፡ † በተጨማሪ መክሊት ቃለ እግዚአብሔር ነው፤ የሰማነውን ቃለ እግዚአብሔር ለመተግበር እየበረታን ለሌላው ማሰማት ይገባናል፤ ከእኛ የሚጠበቀው ማሰማቱ ብቻ ነው፤ በልቦናው አድሮ ሥራ የሚያሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ እኛም በሃይማኖት ጠንክረን በምግባር በርትተን ታማኝ ባርያ ልንሆን ይገባል፡፡ ፠፨፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠፨፠ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

እንኳን ለመስቀለ ኢየሱስ መጋቢት 10 በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ (ይህንን ያውቃሉ? በአዲስ አበባ በብቸኝነት ከቀድሞ ጀምሮ የመስቀለ ኢየሱስ በዓል በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያን ክብረ በዓሉ እንደሚከበር፡፡) ፨ በዚሁ ደብር በቀደሙት ዘመናት አገልጋዮች የመድኀኔዓለምና የመስቀል አገልጋዮች ተብለው በሁለት ምድብ የሚያገለግሉ አገልጋዮች የነበሩ መኾኑን ፤ ፨ የመስቀል አገልጋይ ካህናት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደመወዛቸው ከቤተ መንግሥት እንደሚከፈላቸው፤ ….) ፨ በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀል ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት፡፡ (የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም የቤቱ የመስቀል ወረብ)  ፨ በሃገራችን ኢትዮጵያ መስቀልን በሚመለከት ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የደመራ መስቀል በዓል /መስከረም 16 እና 17/ እንዲሁም መጋቢት 10 የመስቀለ ኢየሱስ በዓል ተያያዥነት ያላቸውና ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከጌታችን ሞትና ትንሣኤ በኋላ በቀራንዮ አደባባይ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ጌታችንን የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከቀራንዮ ወደ ጎልጎታ (ጌታችን ተቀብሮባት ወደነበረው መካነ መቃብር) ወስደው አኑረውታል፡፡ አበው ሐዋርያት ወደየሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱ የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገዋል፤ ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱም በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ጠዋትና ማታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተዓምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ ተፈውሰዋል፡፡ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ስቧቸዋል፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው ሕይወት የሆነውን የጌታ መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ቀብረውት ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየጣሉበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆይቷል ‹‹በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀልከ ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት›› እንዲል፡፡ ሆኖም በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጉዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንተ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ (በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ)›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት ድል በማድረጉ ነው፡፡ የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት፥ ታሪኩ በውስጧ የሰረጸባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው ሆኖም ሊተባበራት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ረሃብና ጽም ስታበዛበት ግን የረሃብና የጽሙን መጽናት ተመልክቶ ከእነዚህ ከሦስት ተራሮች አንዱ እንደሆነ ነገራት፤ ከሦስቱ ተራራ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ፥ ደመራ አስደምረሽ፥ በእሣት አያይዘሽ፥ በፍሕሙ ላይ ዕጣን አፍስሽ፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጢሱ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው መስከረም 16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡ ፨ መስከረም 17 ቀን ማለትም የደመራ በዓል ማግስት የምናከብረው የመስቀል በዓል ደግሞ ንግሥት እሌኒ ደመራ አስደምራ እጣን አጢሳ (አስጢሳ) የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት ቁፋሮ በተጀምረ ከ5 ወር ከ23 ቀን በኋላ መስቀሉ መጋቢት 10 ተገኝቷል፤ ከ10 ዓመት በኋላም ቤተ መቅደሱ ታንጾ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡ መስቀሉም እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽባዎችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ ይህ የጌታ ዕፀ መስቀልም በዓፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በለያዩ ቅዱሳት መካናት (እንጦጦ ማርያም፣ ጋራ መድኃኔዓለም፣…..) ሲያርፍ ቆይቶ በስተመጨረሻው ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል›› ተብሎ ለዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ በተነገረው መሠረት በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም በክብር አርፏል፡፡ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡ * "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" /ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ * ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።›› /ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ገላ.6፥14፣ 1ኛቆሮ.1፥18/ * እንደተለመደው ሥርዐተ ማኅሌቱንም አቅርበንላችኋል፡፡ እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ በዋይዜማ፣ በሰርክ ጕባኤ፣ በሰዐታቱ በኪዳኑ፣ በዑደተ ታቦተ ሕጉና በቅዳሴው እንገናኝ፡፡  ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

፨ #ደብረ_ዘይት ፨ የዐቢይ ጾም 5ኛ ሳምንት ※※※ ከዳግም ምጽአት በፊት የሚከሰቱት ድርጊቶች ※※※ ፨ ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት ነው፡፡ ይህም ቦታ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ካለው ከቄድሮስ ሸለቆ ራቅ ብሎ የሚገኝ፣ ርዝመቱ ፪ ኪሎ ሜትር፥ ከፍታው ደግሞ ከኢየሩሳሌም ከተማ በላይ 62 ሜትር ያህል ከፍታ ያለው ነው፤ቢታንያና ቤተ ፋጌ ከደ/ዘይት ተራራ ሥር የሚገኙ ቦታዎች ናቸው፡፡ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ የተፈጸሙ ዋና ዋና ድጊቶች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፡- ⊚ በደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነበር። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥፩፡፡ ⊚ የጌታችን በዳግም ምጽአት እንደሚመጣ አስተማሮበታል /ማቴ.24፥1-36/ ⊚ 33 ዓመት ከ3 ወር በዚህ ምድር ተመላልሶ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ያረገበት ተራራ ነው፤ ‹‹ሁለት ሰዎች ነጫጭ ልብስ ለብሰው በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው ‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እያያችሁት ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ፥ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል› አሏቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤›› ሐዋ.1፥11-12፣ ሉቃ.24፥51-52/፡፡ ⊚ ዳዊት ከልጁ ከአቤሴሎም በሸሸ ጊዜ ወደ ደብረ ዘይት አቀበት ወጥሮ ነበር /2ኛ ሳሙ.15፥30/፣ ⊚ ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ሆሳዕና ከደብረ ዘይት ወደ ኢየሩሳሌም ሒዷል /ማር.11፥1/ ⊚ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ግርጌ በምትገኘው ለምለም ስፍራ በጌቴ ሴማኒ በአይሁድ ጭፍሮች ተያዘ፡፡ ማር.26፥30-36፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተቀበረችበት ቦታም በጌቴሴማኒ ነበር፡፡ ⊚ በደብረ ዘይት ተራራ ወገብ ላይ በሰፊው ተንጣሎ የሚታይ የአይሁድ መቃብር አለ። ይህን ስፍራ ለመቃብርነት የመረጡበት ምክንያት ወደፊት መሢሑ መጥቶ እስራኤልን ነፃ አውጥቶ ወደ አባቱ ያርጋልና ኋላ ለፍርድ ሲመጣ በመጀመሪያ የሚፈርድበት ስፍራና ሙታንም የሚነሱበትና የሚሰበሰቡበት ስፍራ ይህ በመሆኑ እኛ መሢሐችንን ለማግኘትና ከሙታንም ለመነሳት የመጀመሪያዎቹ እንሆናለን ብለው በማመናቸው ነው። አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መሢሕ እርሱ ነው ብለው አያምኑም። በመሆኑም እስራኤል ወደፊት አንድ ታላቅ መሢሕ እግዚአብሔር እንደሚልክላቸው ባላቸው ተስፋ መሠረት ገና አሁንም ድረስ መሢሐችንን እንጠብቃለን ይላሉ፤ ነገር ግን አይሁድ በዚህ በትልቁ ነገር ላይ ወደኋላ ቀርተው ተበድለዋል። ቀመረ አዝማናትን ቀንሰዋል፥ ቈነጻጸለዋል፤ የኦሪት መጽሐፋቸው ኦሪተ ብጡል ተብላለች፤ ይመጣል ያሉበትም ዘመን ሳይመጣ ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ 8ኛ ሺህ ላይ ደርሰናል፡፡ ይሁንና እግዚአብሔር እስራኤልን ብቻ ሳይሆን ዓለሙን ሁሉ እንዲያድን  አንድ  ልጁን  ጌታችን  መድኃኒታችን  ኢየሱስ  ክርስቶስን ልኮልን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶልን በእርሱ ቁስል እኛ ተፈውሰናል፣ በእርሱ ሞት እኛ ሕይወትን አግኝተና/ኢሳ.፶፫፥፬-፮/። ከዚህ በኋላ ሌላ መሢሕ ሌላ አዳኝ ፈጽሞ የለም፡፡ ※ ከዳግም ምጽአት በፊት የሚከሰቱት ድርጊቶች /ማቴ. ፳፬፥ ፫-፴፮/ እንደተገለጸው፡- ⊚ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ ⊚ ጦርነትን የጦርነትንም ወሬ ትሰማላችሁ ⊚ ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣሉ ⊚ በየሀገሩም ረኃብ፣ ቸነፈርም፣ የምድር መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል ⊚ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል፤ ስለ ስሜም በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ⊚ በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በእርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፣ እርስ በእርሳቸውም ይጣላሉ ⊚ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ ⊚ ከዐመፅም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች ⊚  የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰችው ሥፍራ ቆሞ ታያላችሁ ⊚ በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል ካለ በኋላ እስከመጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል በማለት ገልጾላቸዋል። ※የዐቢይ ጾም 5ኛ ሳምንት ደብረ ዘይት በመባል የሚታወቀው የደብረ ዘይት ሰንበት ምጽአት የተነገረበት ከመሆኑም በስተጀርባ በዚህ ዕለት ምጽአት እንደሚሆን ይታመናል፡፡ ከዐቢይ ጾም በ5ኛ ሳምንት መከበሩ በ5,500 ዓመተ ዓለም የመጣው ጌታ ከዚህም በኋለ በዚሁ ዕለት የሚመጣ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958