es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 16 044 suscriptores, ocupando la posición 5 280 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 239 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 16 044 suscriptores.

Según los últimos datos del 27 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 518, y en las últimas 24 horas de 0, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 24.70%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.29% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 963 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 651 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 29.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 28 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

16 044
Suscriptores
Sin datos24 horas
+987 días
+51830 días
Archivo de publicaciones
#ጥር_7_በዓለ_ሥላሴ_የሰናዖርን_ግንብ_ያፈራረሱበትና_ቋንቋ_የደባለቁበት_ዕለት_ነው፡፡ ለጥር 7 ከዋይዜማው ጀምሮ የሚባለውን ሥርዐተ ማኅሌት ከወረብ ድምፅ ጋር አብረን አዘጋጅተነዋል፤ መልካም ሥርዐተ
+4
#ጥር_7_በዓለ_ሥላሴ_የሰናዖርን_ግንብ_ያፈራረሱበትና_ቋንቋ_የደባለቁበት_ዕለት_ነው፡፡ ለጥር 7 ከዋይዜማው ጀምሮ የሚባለውን ሥርዐተ ማኅሌት ከወረብ ድምፅ ጋር አብረን አዘጋጅተነዋል፤ መልካም ሥርዐተ ማኅሌት፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem ወረቦቹን በድምፅ ማጋኘት ከፈለጉ በቴልግራም ገጻችን (https://t.me/medihanaelem) ያገኛሉ፡፡

በቅድስት ሥላሴ የተሰየሙ ብዙ አድባራትና ገዳማት ቢኖሩም፤ የታሪክ ሙዳይ የኾኑ፥ ከዕድሜያቸው ብዛትና ከአመሠራረታቸው አንጻር በታሪክ አሻራ ላይ ያላቸው አስተዋጽዖ ከፍተኛ የኾኑ ፥ የታሪክ አሻራቸው ያንጸባረቀ፥ አሻራቸው የላቀ፥ እድሜያቸው የጎላ፤ 8ቱ ዐበይት ገዳማት (ቤ.ክ)፤ እንዲሁም በአ.አ. ክብረ በዓሉ የሚከበርባቸው አብያተ ክርስቲያናት፡፡ 1ኛ) #ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም፤ ከ2000ዓመታት በላይ ያስቈጠረ፤ የብዙ ቅዱሳን (የአባ ዓምደ ሥላሴ፣ የአባ ክፍለ ማርያም፣ የ7ቱ ዘሥላሴ፣ የአባ አርከ ሥሉስ ቅዱስ /የአርኬና የመልክዓ ቊርባን ደራሲ/፣ …….. ) መፍለቂያ፡፡ 2ኛ) #አሰቦት_ቅድስት_ሥላሴ፣ በ13ኛው ክ/ዘመን በታላቁ ጻድቅ በአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የተመሠረተ፡፡ 3ኛ) #ደብረ_ብርሃን_ሥላሴ_ሰሜን_ሸዋ_ደብረ_ብርሃን_ከተማ፤ በ14ኛው ክፍለ ዘመን በዓፄ ዘርዓያዕቆብ ዘመን የተመሠረተ፡፡ 4ኛ) #መካነ_ሥላሴ_ደቡብ_ወሎ_ወረኢሉ፤ በ1500ዓ.ም. በዓፄ ናዖድ የተመሠረተና በልጁ በዓፄ ልብነ ድንግል ሥራው የተጠናቀቀ፤ ባለ 16 መንበር በዕንቊና በወርቅ የታነጸ የነበረ፤ (ኋላ በግራኝ የፈረሰ፤ ጽላቱ በዓፄ ምኒልክ ወደ አዲስ አበባ የመጣ ቀድሞ መካነ ሥላሴ አሁን 4 ኪሎ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ በመባል የሚጠራው)፤ ደቡብ ወሎ ያለው መካነ ሥላሴ ግን ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ነውና በቀድሞው ቅርጹ በባለ 16 መንበር ተደርጎ ካች አምና የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ በመገንባት ላይ ይገኛል፤ (ለሕንፀታ ቤቱ ኹላችንንም ያብቃን)፡፡ 5ኛ) #ደብረ_ብርሃን_ሥላሴ_ጎንደር_ከተማ፤ በጥር 26 ቀን 1683 ዓ.ም. በዓፄ አድያም ሰገድ የታነጸ፤ በጎንደር ከተማና ዙሪያ ከሚገኙ 44ቱ ታቦታተ ጎንደር በአሠራሩ ልዩ የኾነ፤ በ1880ዎቹ ድርቡሽ ጎንደር ከተማን ሲያጠፋ አብረው ከጠፉት 44ት አብያተ ክርስቲያናት በተዓምራት ሳይቃጣል የቀረ፤ የታላላቅ ሊቃወንት (የእነ ሊቁ ክፍለ ማርያም) መፍለቂያ፡፡ 6ኛ) #ናርጋ_ሥላሴ_ከጣና_ላይ_ገዳማት_አንዱና_ዋነኛው፡፡ 7ኛ) #ጨለቆት_ሥላሴ_ትግራይ፤ መቀለ አጠገብ፡፡ 8ኛ) #አዲስ_አበባ_መካነ_ሥላሴ_ ( #መንረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ በመባል እየተጠራ ያለ) (4 ኪሎ)፡፡ #በአዲስ_አበባ_የሚገኙ_የቅድስት_ሥላሴ_አብያተ_ክርስቲያናት (ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ ጨምሩበት) 1ኛ. መካነ ሥላሴ (መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤ.ክ.)፤ (4 ኪሎ) 2ኛ. መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ (ሽሮሜዳ) 3ኛ. መሪ ምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ሥላሴ (አያት መሪ) 4ኛ. ካራ አሎ ቅድስት ሥላሴ (ካራ አሎ ፥ አባዶ አጠገብ) 5ኛ. ጠሮ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ፤ (ኮልፌ ቀራንዮ) 6ኛ. ጀሞ ፈለገ ኮሬብ ቅድስት ሥላሴና ቅድስት ማርያም (ጀሞ) 7ኛ. ሰፈረ ገነት ቅድስት ሥላሴ (ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፥ ወረዳ 4) 8ኛ. ፈለገ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ (ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ) 9ኛ. ቂሊንጦ ቅድስት ሥላሴ (አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፥ ወረዳ 9) 10ኛ. ኤረር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ (ጎሮ ሰፈር፥ ወረዳ 9) 11ኛ. መሪ ቅድስት ሥላሴ (መሪ አያት፥ ወረዳ 13) እንዲሁም በድርብነት 12ኛ. ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (የሥላሴ ታቦት በድርብነት ይከበራል) (አዲሱ ገበያ) #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ጥር 6 በዓለ ግዝረት፥ ዕረገተ ኤልያስ ዕረፍተ ኖኅ፥ ልደተ ቅድስት አርሴማ፥ ዕረፍተ ዐቢይ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ፥ አቡነ ኖኅኖኅ አባ ሙሴ ገዳማዊ፥ አባ ወርክያኖስ፥ ወአባ ሙሴ፡፡ ክብረ በዓሉ የሚከበርባቸው ቦታዎች፤ (ተጨማሪ ካሉ ከነፎቷቸው ጨምሩበት) #ለብቃ_ኢየሱስ/ሰሜን ሸዋ/፣ #በለስ_ዋሻ_ኢየሱስ /ተጉለትና ቡልጋ/፥ #በአ.አ. #ገነተ_ኢየሱስና_ገነተ_ማርያም ቤ/ክ፤ (ፈረንሳይ) #በአ.አ #ገዳመ_ኢየሱስ (ኮልፌ 18) #በአ.አ #እንጦጦ_ደብረ_ኀይል_ቅዱስ_ራጕኤልና_ኤልያስ (የኤልያስ ዕርገቱ) #በጎጃም_ደብረ_ኤልያስ ይከበራል፡፡ #ግዝረተ_እግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ፠ ጌታችን በተወለደ በ8ኛ ቀኑ ዕጉለ ማዕነቅ ይዞ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ የፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ ፠ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋ ግዝረትን ተቀበለ፣ ለአባቶች የተሰጠውን ቃልኪዳን ይፈጽም ዘንድ›› /ሮሜ.፲፭፥፰/፡፡ ፠ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ በስምንተኛው ቀን እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ግዝረት ይፈጸምለት ዘንድ ሕፃኑ ጌታችንን ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ሲገረዝ የሊቀ ካህን ልጅ ነው ብለው ሊገርዙት ወደ እርሱ መጡ፡፡ ጌታችን ግን ወደ ምድር የመጣው፡፡ ለትሕትና ነው እንጂ ለልዕልና አይደለምና ወሰዱት አለ /ትርጓሜ ወንጌለ ሉቃስ/፡፡ ፠ የእመቤታችን ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማኅፀን እንደመውጣቱ የጌታችን ግዝረቱም የማይመረመር ሆነ፡፡ እንዲሁ በተዘጋ ቤት መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር እነዲሁ እንደፈቀደ ከረቀቀ ጥበቡ ችሎታውን በመገረዝ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ ገለጠ፡፡ #ቅዱስ_ኤልያስ_በእሳት_ሰረገላ_ወደ_ብሔረ_ብፁዓን_ያረገበት_ዕለት_ነው፡፡ (የዚህን ቅዱስ ነቢይ ታሪክ በደንብ ያንቡብት ብዙ ትምህርት ይቀስሙበታል) **በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ ነው፡፡ ✤ የሰማርያው ነቢይ ቴስቢያዊው ኤልያስ ከቅዱሳን አበው ነቢያት አንዱ ሲኾን አባቱ ኢያሴዩ እናቱ ደግሞ ቶናህ(ቶና) ሲባሉ ሲወለድ መላእክት በእሳት ሰፋድል (መጠቅለያ መጐናጸፊያ) ጠቅልለውት ነው፡፡ የስሙ ትርጉምም ‹‹እግዚአብሔር አምላክ ነው›› ማለት ነው፡፡ ** ኤልያስ ብዙ ነገር ስለሚያስተምር የቀና እምነቱን ውጤት ጥቂት መመልከት እኔ ማነኝ? ለሚሉት እጅ ይዞ ይመራል፡፡ ✤ 1. ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማይ ዝናም ለዘር፥ ጠል ለመከር ከመስጠት እንዲከለከል ምድርም የተከሉባትን ✤ 2. አመጸኞች አክአብንና ኤልዛቤልን ምንነታቸውን ካሳወቀ በኋላ የዘጋውን ለመክፈት ወደ ፈጣሪው በመጸለይ ዝናም አዝንሟል፡፡ ✤ 3. በተፈጥሮ የማይመስላቸው በቋንቋም የማይግባባቸው እንኳን ለሰው ሥጋ ሊያመጡ ከሰው ሥጋ የሚነጥቁ አሞራዎች እንጀራና ሥጋ ለምግብ እንዲያመላልሱለት አደረገ 1ኛ ነገሥ. 17፥6-7፡፡ እነዚህ አሞራዎች ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ በጋ ከክረምት የለምንም እረፍት ኤልያስን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ እምነት ካለ ተአምር መሥራት አይገድም ይህንም ከኤልያስ ይማሯል፡፡ ✤ 4. ለአንዲት መበለት ዱቄትና ዘይት አበረከተ፤ ኤልያስ ቁራሽ እየለመነ ያደረገውን ተአምር ልብ ይሏል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 17፥16-24፡፡ ✤ 5. ዱቄትና ዘይት ያበረከተላት የሰራፕታዋ ሴት ልጇ /ኋላ ዮናስ ነቢይ የሆነው/ ቢሞት ከሞት አስነሳው 1ኛ ነገሥ. 17፥20-23 ✤ 6. ለብዙ ጊዜ በቤተ መንግሥት ተሰግስገው አክአብና ኤልዛቤልን በሐሰት ሲደልሉ፥ ግብዝ ሕብረተሰቡን ሲያታልሉ፥ ለፍቶ ያገኘው ገንዘቡን ሲሸልጉ፥ በኀጢአት ሊያስወጉ የነበሩ ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖትን በሕብረተሰቡ ፊት እስከ መምህራቸው ሰይጣን በቅሌት አከናንቦ ሲያስቅባቸው ውሏል፤ ሐሰቶች የነበሩትን 850 የሚጠጉ የጣዖት ካህናትንም ወደ ቂሶን ወንዝ አውርዶ ፈጅቷቸዋል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 18 20 -29 ✤ 7. ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት ያቀረበው ንጹሕ መሥዋዕቱን ከሰማይ እሳት ወርዶ በሰው ፊት በላለት (ተቀበለለት) 1ኛ ነገሥ. 18፥30-40፡፡ በዚህም ማንነቱን በሰይጣንና በሰይጣን አቀንቃኞች ፊት አስመስክሯል፡፡ ✤ 8. እሳት ከሰማይ በማዝነም ሊጣሉት የመጡትን መምለኪያነ ጣኦት፥ ምሉአነ ኀጢአት፤ የሰይጣን ሠራዊት በሰው ደም የሰከሩ፥ በዲያብሎስ የሚመሩ ጠላቶቹን አጋይቷል 2ኛ ነገሥ 1 9-13 ✤ 9. ምግብና መጠጥ መልአክ ከሰማይ አመጣለት ያንን ተመግቦ ለአርባ ቀን ያለምንም ምግብና መጠጥ እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ተጉዟል 1ኛ ነገሥ. 19፥5-7፡፡ ✤ 10. በመጎናጸፊያው የዮርዳኖስን ባሕር ከፍሎ ከነ ደቀመዝሙሩ በደረቅ ተሻግሯል 2ኛ ነገሥ. 2፥11፡፡ ለደቀመዝሙሩም ሀብተ መንገፈስ ቅዱስን አድሎታል፡፡ ✤ 11. በትህትናው ‹‹ይበቃኛል፤ አሁንም አቤቱ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ›› ብሎ እንዲሞት ለመነ፡፡ እግዚአብሔር ግን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ918 ዓመተ ዓለም ሳይሞት በሕይወቱ መራራውን ሞት ዕያየው በብርሃን ሠረገላ ወደሰማይ አሳርጎታል፡፡ 2ኛ ነገሥ. 2፥6-9 ✤ 12. እንደ አስፈላጊነቱ ከፈጣሪው ጋር ለብዙ ጊዜ ተነጋግሯል፡፡ ✤✤#ከአንድ እስከ አስራ አንድ ያደረጋቸውን ተአምራት የፈጸመለት ታማኝ ፈጣሪው ሰው በሆነበት ወራት በተራራ ከጓደኞቹ ጋር ብርሃነ መለኮቱን ገለጠለት ማቴ 17፥3፡፡ #ደመና_ደመና ….. #በሠረገላ_፤ ኤልያስ ኤልያስ ….. በሠረገላ፤ በእሳት ሠረገላ ….. በሠረገላ፤… ሰወረው ደመና ….. በሠረገላ፤ ኤልያስ ያረገው… በሠረገላ፤ በእሳት ሠረገላ…. በሠረገላ፤ በጾም በጸሎት ነው …. በሠረገላ፤ አይደለም በሌላ …. በሠረገላ፡፡ #ዳግመኛም ዛሬ የአባቶችን ኖኅ መታሰቢው ነው፡፡ ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ …ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ፥ ፍጹምም ሰው ነበር፡፡ ኖኅ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፡፡ /ዘፍ. 6፥7/ #ዳግመኛም በዚህች ዕለት በበረሃ ስልሳ ዘመናት የኖረ የቅዱሳንን ልቡና ከማየቱ የተነሣ ያደነቀ፤ ፊቱም ተለውጦ እንደእሳት ፍሕም ሆነ አባ ሙሴ በዓለ ዕረፍቱ ነው፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

እንኳን አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ እናስተዋውቃችሁ ክፍል ፩፤ ጥምቀትን በጎንደር ለምታከብሩ፤ #ከ44ቱ_ #ታቦታተ_ጎንደር_መካከል_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_የሚወርዱት_የሚከተሉት_ናቸው፡፡ /ታቦታቱ የሚወጡት
+4
እንኳን አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ እናስተዋውቃችሁ ክፍል ፩፤ ጥምቀትን በጎንደር ለምታከብሩ፤ #ከ44ቱ_ #ታቦታተ_ጎንደር_መካከል_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_የሚወርዱት_የሚከተሉት_ናቸው፡፡ /ታቦታቱ የሚወጡት በጥር 10፣ 11፣ 12፣ 18 (ስባረ ዓፅሙ)፣ 21 (አስተርዕዮ)፣ 22 (ዑርኤል)፡፡) #፩ኛ) #በጥር_10፣ 11ና 12 #በጎንደር_ፋሲለደስ_መዋኛ_ገንዳ (#ቀድሞ_የሰማዕቱ_ቅዱስ_ፋሲለደስ_ቤተ_ክርስቲያን_በነበረበት ቦታ ላይ የሚወጡ ታቦታት) 1ኛ. ቀሃ ኢየሱስ 2ኛ. ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ 3ኛ. ዕልፍኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ 4ኛ. ሰማዕቱ ቅዱስ ፋሲለደስ (አብሮ ከቀሃ ኢየሱስ ጋር ይወጣል) 5ኛ. መንበረ መንግሥት መድኀኔ ዓለም (መ.መ.መ) 6ኛ. አባ ጃሌ ተክለ ሃይማኖት 7ኛ. ፊት ሚካኤል 8ኛ. አጣጣሚ ሚካኤል፡፡ ናቸው #፪ኛ) #በጥር 10፣ 11 #በልደታ_ሜዳ_(ኮሌጅ አጠገብ) (ከአፄ ፋሲል መዋኛ ገንዳ በፊት በጥንቱ የታቦታት ማደርያ) ፠ መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም #፫ኛ) #በጥር_18 #ጎንደር_የመምህራን_ኮሌጅ_ወደ_መስጊድ_ጊዮርጊስ_መሄጃ_ጋር (የጥር 18 ስባረ ዓፅሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት) ፠ ርዕሰ አድባራት አበራ ጊዮርጊስ #፬ኛ) #በጥር_21 #በአዘዞ_ድማዛ_ወንዝ_አጠገብ_ (የጥር 21 የአስተርዕዮ ዕለት) አዘዞ ሎዛ ማርያም (ድፍን ጎንደር ተሰባስቦ የአስተርእዮ ዕልት የሚያከብርበት) #፭ኛ) #በጥር_22 #በበዓታ_ጠበል_ቤት (ጥር 22 የቅዱስ ዑርኤል ዕለት) ደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ ዑር(ራ)ኤልና በዐታ፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/med

‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በጥር ፫/፳፻፲፪ ዓ.ም. ጋብ
+2
‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በጥር ፫/፳፻፲፪ ዓ.ም. ጋብቻሽን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ የፈጸምሽው የሰ/ት/ቤታችን አባል እኅታችን፤ #ስንታየሁ_መላኩ_ከቢልልኝ_ገረመው ጋር የፈጸማችሁትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ፥ ያጣምራችሁ፥ ያዋሕዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ ✤ ‹‹ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንዲሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡›› ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፖሊካርፐስ በላከው መልእክቱ ✤ ከተጋባችሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርአያዕቆብ፡፡ /ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

#ለ1512 #ዓመታት_ባለውለታዋን_ዘንግታ_የቆየችው_እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም_ጥር_3/2012 ዓ.ም. #ባለውለታዋን_አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕን_ፎቶ_ላይ_በምታዩት_ሁኔታ_ዘክራለች_፡፡ ፠ እንጦ
+6
#ለ1512 #ዓመታት_ባለውለታዋን_ዘንግታ_የቆየችው_እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም_ጥር_3/2012 ዓ.ም. #ባለውለታዋን_አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕን_ፎቶ_ላይ_በምታዩት_ሁኔታ_ዘክራለች_፡፡ ፠ እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት በ485 ዓ.ም. የሸዋ አባቶች የዐብዩ መድኀኔ ዓለምንና የበረከት ኪዳነ ምሕረት ታቦትን ይዘው ለ3 ወራት የተሰባሰቡባት ስትሆን፤ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እንጦጦ ላይ አስቀምጠውና ገዳሟን መሥርተው፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ይዘው ወደ ዋልድባ በመሄድ ቀድሞ ጌታችን የገደመውን ገዳም ለ2ኛ ጊዜ አስፋፍተውታል፡፡ ፠ ከ16 ዓመታትት በኋላ በ500 ዓ.ም. ደግሞ አቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ከአኵሱም ወደ ሸዋ ሲመጡ ሐመረ ኖኅን በገዳምነት ገድመው ጠበሏን አፍልቀው ሕሙማንን ፈውሰው ተመልሰዋል፡፡ ፠ በ197 ዓ.ም. አንድ ምዕመን ለአቡነ ተክለሃይማኖት አስፈቅደው፤ ገድላቸውን ከአኵሱም አጽፈው በማምጣት ማኅሌቱ እንዲቆም፣ ገድላቸው እንዲበብ፤ 50 ብር እየከፈሉ የጻድቁን ዝክር በዳቦና በለስላስ እንዲገለገል አስደርገዋል፡፡ ፠ ዘንድሮ በ2012 ዓ.ም. ደግሞ ታቦተ ሕጋቸው ወጥቶ ተከብሯል፤ በክብረ በዓሉም ላይ መናኙ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ስምዖን (የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የበላይ ኃላፊና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል) ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬን ሰጥተዋል፡፡ ፠ የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ይመስገን፨ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ጥር 4 #የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው፡፡ (የአባ ናርዶስ ዘደብረ ቢዘን እረፍቱ ነው፡፡ የጊዮርጊስ፤ የሊቀ ጳጳሳት ማርቴና፤ የሰማዕት ታኦድራ፤ የአባ ሊቃኖስ፤ የቀውስጦስ መታሰቢያቸውም ነው፡፡) ፨ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ፤ #በተለያዩ_ቅጽል_ስሞች_የሚጠራ፤ (100 አካባቢ ከሚጠጉ ስሞቹ ጥቂቶቹን /21ዱን ስሞች ከጽሑፍ በስተመጨረሻ ይመልከቱ) #ሰዓሊ_የኾነ፤ የጌታችንን ስነ ስቅለት የሳለ፡፡ #ከ81ዱ_የመጽሐፍ_ቅዱስ_ክፍሎች_5ቱንና_ሌሎች_መጻሕፍትንም_(ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤ #ብዙ_ደቀ_መዛሙርትን_ያስተማረ፤ ✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤ ✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤ ✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤) ✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤ ✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /እመጽሐፈ ሰዐታት/ ፨ ‹‹ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፤ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ›› /መልክአ ኢየሱስ/ ፨ ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ ዘሰዓሞ፤ ዮሐንስ ርኄ ዮሐንስ ቀናንሞ፤ ለዝ ወልድኪ መሐሪ ኅሩመ በቀል ወተቀይሞ፤ ማርያም ሀብኒ በእዴኪ እንዘ ትጼውዒ ስሞ፤ ሥጋሁ ቅዱሰ ወክቡረ ደሞ፡፡ /መልክአ ሥዕል/ ፨#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ፤ ዮሐንስፍቁረ እግዚእ፥ ወልደ ዘብድዮስ ፥ ዮሐንስ ነባቤ መለኮት ፥ ዮሐንስ ቦኦርኔጌስ ፥ ዮሐንስ አብቀለምሲስ ፥ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፥ ዮሐንስ ድንግል 1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ) 2. ዮሐንስ ድንግል 3. #ዮሐንስ_ፍንው 4. #ዮሐንስ_ካህን 5. #ዮሐንስ_ኅሩይ 6. ዮሐንስ ሥርግው 7. #ዮሐንስ_ምዑዝ 8. ዮሐንስ ቅኑይ 9. #ዮሐንስ_ማኅቶት 10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ 11. #ዮሐንስ_ክቡር 12. ዮሐንስ ጻድቅ 13. #ዮሐንስ_ረድእ 14. ዮሐንስ ማኅቶት 15. #ዮሐንስ_ድንግል 16. ዮሐንስ ንጹሕ 17. #ዮሐንስ_ለባዊ 18. ዮሐንስ መረግድ 19. #ዮሐንስ_ዕንቈ 20. ዮሐንስ መልአክ 21. #ዮሐንስ_ኪሩብ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#በሃገራችን_በኢትዮጵያ_ጥር_4_የቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸውን_ #13ቱ_ቦታዎች_እንጠቁማችሁ_፤ (ያልጠቀስነው ካለ ከነፎቱ ላኩልን) /ከዋይዜማው ጀምሮ በማኅሌቱ፥ በሰዐታቱ፥ በኪዳኑ፥ በቅዳሴው፥ በዑደተ ታቦተ ሕጉና በሠርክ ጕባኤ እንድንገናኝ ይሁን/፡፡ 1ኛ) #ደቡብ_ወሎ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ /ጥንታዊው ደብር፤ ከመካነ ሥላሴ አጠገብ የሚገኝ/፤ (መላው ወሎ በዚሁ ደብር እንገናኝ/ 2ኛ) #ሐይቅ_ደብረ_ነጎድጓድ_ቅዱስ_ዮሐንስ_ (የሐይቅና የደሴ ነዋሪ በዚህ ታላቅ ደብር እንገናኝ) 3ኛ) #ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ /#ከታላቁ_ደብር_ከደብረ_በንኰል_ገዳም_አጠገብ/ (ሰለኽላኻ ሽሬና አካባቢዋ ያላችሁ በዚሁ ደብር እንገናኝ) 4ኛ) #አደቁዋረክ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ /ማኅበረ ዴጎ አጠገብ/፤ (አኵስምና በአካባቢው ያላችሁ በዚሁ ደብር እንገናኝ) 5ኛ) #ገደፈና_ዮሐንስ /ማይጨው አጠገብ/፤ (ማይጨው ራያና መቀለ ያላችሁ በዚሁ ደብር እንገናኝ) 6ኛ) #ዣት_ደብረ_ፀሐይ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ /ሰሜን ሸዋ፥ ጅሩ/ (ሙሉ ሸዋ በዚሁ ደብር እንገናኝ) 7ኛ) #ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ /ደምበጫ አጠገብ/፤ (ጎጃም በሙሉ በዚሁ ደብር እንገናኝ) 8ኛ) #ዘንስር_ደብረ_ተድላ_ዮሐንስ_ማዕከላ_ለጐንደር፤ /ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱና ዋነኛው፤ በጎንደር ከተማ የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ወደ ግምጃ ቤት ማርያም ከመዛወሩ በፊት በብቸኝነት የጎንደርና የመላው ኢትዮጵያ ሊቃውንት የማኅሌተ ጽጌን ቁመት ለመቆም የሚተሙት ታላቅ ደብር/፤ (ጎንደርና አካባቢዋ ያላችሁ በዚሁ ደብር እንገናኝ) 9.1ኛ) #ደብረ_ነጐድጓድ_ቅዱስ_ዮሐንስና_መካነ_ጎልጎታ_ማርያም_ቤ_ክ_ማዕከላ_ለአዲስ_አበባ /መሐል አዲስ አበባ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አጠገብ የሚገኝ፤ ታቦተ ሕጉ ከኢየሩሳሌም የመጣና በአዲስ አበባ ብቸኛው የወልደ ነጐጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ./፤ (አዲስ አበባና በአካባቢዋ ያላችሁ በዚሁ ደብር እንድንገናኝ ይሁን) ፠፠ በአ.አ. በብቸኝነት ወደሚገኘው ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ማዕከላ ለአዲስ አበባ ለማኅሌት ከመላው ዓለም ስትመጡ ጋቢና ምንጣፍ መያዛችሁን አትርሱ፤ ከሰዉ ብዛት የተነሣ ቤተ ክርስቲያኑ እጅጉን ስለሚሞላ፡፡ 9.2ኛ) #ምስካየ_ኅዙናን_መድኀኔ_ዓለም_ገዳም (ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ባይከብርም ከጥንት ጀምሮ በውዳሴ በቅዳሴ ይከበራል፡፡) 10ኛ) #ቦኮሙራ_ወልደ_ነጐድጓድ_ቅዱስ_ዮሐንስ_ ቤ.ክን /ሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሚሻ ወረዳ ቦኮሙራ ቀበሌ/፤ (በሀድያ፣ በስልጤ፣ በጉራጌና በደቡብ የምትገኙ ሁሉ በዚሁ ደብር እንድንገናኝ ይሁን፡፡) 11) #ናዝሬት_ደብረ_ፍስሐ_ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ_ቤ/ክ 12) #ደሴ_ዩኒቨርሲቲ_ደብረ_ነጎድጓድ_ቤ/ክ 13) #መቱ_ደብረ_ሳሌም_ሐይቅ_ደብረ_ነጎድጓድ_ #በሠረገላ_ተመሠለት_ቤተ_ክርስቲያን_ደብረ_ተድላ(#ደብረ_ነጐድጓድ_/#_ዮሐንስ_/)፤/፪/ #እንተ_፬ቱ #_ገበዋቲሃ_፬ቱ_ወንጌላውያን፡፡/፪/ ፨ #ሰላም ለከ ዮሐንስ አቡቀለምሲስ፤ ሰላም ለከ ዮሐንስ ታዎጎሎስ፡፡ ሰላም ለከ ዮሐንስ ፍቊረ እግዚእ፤ ሰላም ለከ ዮሐንስ ድንግል፤ ሰላም ለከ ዮሐንስ ዘረፈቀ ውስተ ሕፅኑ ለኢየሱስ፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ኄር፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ፡፡ ፠ መደበኛ መዝሙር ጥናት አጥኚዎች፤ ፠ ለመደበኛ ክፍል አገልጋዮች፤ ፠ ለባለትዳር ጕባኤ አባላት ፠ ለወላጅ ኮሚቴ አባላት፤ ፠ ለቀደምት አባ
+1
ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ኄር፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ፡፡ ፠ መደበኛ መዝሙር ጥናት አጥኚዎች፤ ፠ ለመደበኛ ክፍል አገልጋዮች፤ ፠ ለባለትዳር ጕባኤ አባላት ፠ ለወላጅ ኮሚቴ አባላት፤ ፠ ለቀደምት አባላት በሙሉ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱ ገብርኤል ቤ/ክ የፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት እንኳን ለ2012 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ እያልን፤ የጥምቀት በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እያደረገ ነው፤ በመሆኑም ከመደበኛ አባላት ጋር የባለትዳር ጕባኤ፣ የወላጅ ኮሚቴ አባላት፤ ቀደምት የሰ/ት/ቤታችን አባላት በሙሉ በአንድ ላይ የመዝሙር ጥናታችን የሚጀምረው #ከጥር 1 - 9 ፤ ማታ ማታ ከ12:00-2:00 በመሆኑ በሰዐቱ ተገኝታችሁ የመዝሙር ክለሳውን እንድታጠኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ (ላልሰሙት ጥሪውን ያሰሙ)፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#አዋጅ_አዋጅ_አዋጅ_፤ #በአ.አ. #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት ቀድሞ በቅዳሴና በውዳሴ ታቦተ ሕጋቸው ሲከበር የቆየው የአቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ታቦተ ሕጋቸው #እሑድ_ጥር 3/2012 ዓ.ም. #ለመጀመሪያ_ጊዜ_ታቦተ_ሕጋቸው_ወጥቶ_ከብራል፡፡ (ሁላችሁም እንድትገኙ ገዳሟ ጥሪዋን አስተላልፋላች)፡፡ #ጥር_3 #አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ_ዕረፍታቸው_ነው_፡፡ ፠ #የደብረ_ሊባኖስ_ገዳምን_የመሠረቱና_በስማቸው_የተሠየመላቸው፤ ፠ ቅዱስ ላሊበላ ከ11ዱ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱን በስማቸው ያነፀላቸው፡፡ ፠ #ከደረቅ_ዐለት_ላይ_ውኃ_እያፈለቁ_ድውያንን_የሚፈውሱ_ተአምረኛ_አባት ፠ በኤርትራ አካለ ጉዛይ ገዳመ መጣዕ፣ በአኵሱም ከተማ አጠገብ፣ በላስታ ላሊበላ፣ ደብረ ወርቅ አቡነ ሊባኖስ ገዳም፣ እንዲሁም ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ በአ.አ. እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ገዳም ክብረ በዓል የሚከበርላቸው፡፡ (ሌሎቹን የምታውቋቸውን ከነፎቷቸው ላኩልን) (***** እኛም ለክብረ በዓሉ የሚሆነውን ከዋይዜማው ጀምሮ ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት እነሆ ብለናል፡፡ ወረቦቹን በድምፅ ከፈለጉ በቴሌግራማችን https://t.me/medihanaelem ላይ ያገኛሉ፡፡) ፠ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ሊድሯቸው ሲሉ መመነን በመፈለጋቸው መልአክ በሌሊት መጥቶ ወደ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡ ፠ አባ ጳኩሚስም ሥርዐተ ገዳምን፥ አስኬማ መላእክትን፥ ቅናተ ዮሐንስን አስተማሯቸው፤ አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡ ፠ ቀድሞ የመራቸው መልአክ ከአባ ጳኩሚስ ‹‹ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድሎህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ›› አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአኵሱም ተቀመጡ፡፡ ፠ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው (ቀድሞ የዋልድባን ገዳም ባስፋፉ አባቶች የተመሠረተችውን #የእንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳምን እስፋፍተው፡፡) ተመልሰው ወደ አኵሱም ሄዱ፡፡ ፠ በአኵሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ፥ ዕውራንን አበሩ፡፡ በዓታቸውንም ከአኵሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል ‹‹ተራ ውሃ ነው›› ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጥጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ ‹‹አምላከ አባ ሊባኖስ›› ብሎ አመሰገነ፡፡ (ስዕላቸው የሚገልጸው ይህንን ተአምር ነው፡፡) ፠ ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው ‹‹ምትሃት ነው የሚያሳየው›› ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡ ፠ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአኵሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ፤ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው ‹‹አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣ በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን›› ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡ አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡ ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡ ፠ ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ (የአሁኗ ደብረ ሊባኖስ) መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው ‹‹ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ (አቡነ ተክለ ሃይማኖት) ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኮሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል›› አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡ ፠ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አኵሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም ‹‹ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ›› አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹ሊባኖስ ዘመጣዕ›› የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው አፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡ ፠ ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ አፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡ ፠+፠ በመጨረሻም ጥቅምት 2 ቀን ተፀንሰው ፤ ፠+፠ ሐምሌ 3 ቀን ተወለደው፤ ፠+፠ በ140 ዓመታቸው ጥር 3 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ ፠+፠ ቅዳሴ ቤታቸው ደግሞ ሐምሌ 3 ነው፡፡ ይኸውም ለመጀመሪያ ጊዜ በዐፄ ገብረ መስቀል ጊዜ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ የተመረቀበት ዕለት ነው፡፡ ***** እኛም ለክብረ በዓሉ የሚሆነውን ከዋይዜማው ጀምሮ ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት እነሆ ብለናል፡፡ (ምንጭ፤ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ፣ 5ኛ መጽሐፍ የቅዱሳን ታሪክ) #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ #አጥቢያ_ለምትገኙ_የጽዋ_ማኅበራትና_ወጣቶች_በሙሉ፤ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሰን ፥ አደረሳችሁ እያልን፤ የጥምቀት ክብረ
+9
በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ #አጥቢያ_ለምትገኙ_የጽዋ_ማኅበራትና_ወጣቶች_በሙሉ፤ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሰን ፥ አደረሳችሁ እያልን፤ የጥምቀት ክብረ በዓልን እንደተለመደው በደማቅ ሥነ ሥርዐት እንድናከብር፤ በአጥቢያችን የምትገኙ፤ ፠ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያንንና የታቦት መተላለፊያ መንገዶችን የምታጸዱ፤ ፠ ምንጣፍ በማንጠፍ፣ በመጥረግና ከቦታ ቦታ በማጓጓዝ የምታገለግሉ፤ ፠ ከሰ/ት/ቤቱ ጋር ለበዓለ ጥምቀት በዝማሬ የምታገለግሉ የጽዋ ማኅበራት፤ ፠ ባንዴራ በመስቀል የምታገለግሉ፤ ፠ ሠረገላውን የምታጓጕዙ፤ ፠ ድንኳን በመጣል፣ ቄጠማ በመጐዝጎዝ የምታገለግሉ፤ ….. ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን በሙሉ በበዓሉ ዙሪያ ውይይት ስለሚኖረን #ሰኞ_ጥር_4፤ ከቀኑ #በ12_ሰዐት በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ (ጥሪውን ላልሰሙ በማሰማት ይተባበሩ) ‹‹ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው ፥ እነሆም ያማረ ነው፡፡›› #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem