es
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 531 suscriptores, ocupando la posición 5 401 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 211 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 531 suscriptores.

Según los últimos datos del 01 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -20, y en las últimas 24 horas de -2, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 27.08%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 4.34% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 206 visualizaciones. En el primer día suele acumular 674 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 22.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 02 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 531
Suscriptores
-224 horas
-87 días
-2030 días
Archivo de publicaciones
"ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ ፡-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" ስምዖን አረጋዊ የካቲት 8  ፤ የጌታችን  ከከበርች ልደት በኋላ  ወደ ቤተመቅደስ የገባበት ዕለት ኾነ ፡፡ በዓሉ ከጌታችን ንዑስ በዓሎች መኻከል አንዱ ነው ፡፡ ++++ የካቲት 8 ፤ ልደተ ስምዖን አረጋዊው  ፣ ካህን ፣ ጻድቅ ፣ ነቢይ ፡፡ በዓሉ የመድኀኔዓለም ቢሆንም ስምዖን አረጋዊ አማናዊ ድኅነት አግኝቶበታልና ፣  በእርጅና ምክንያት ከአልጋ ላይ ተጣብቆ ሲኖር ታድሶበታልና እንደ 30 ዓመት ጎልማሳም ዘሏልና  በዓሉ ይከብራል ። ስምዖን ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ሁሉ የድኅነት ባለቤት ኾኖበታልና በዓሉ ይከብራል ። ++++ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በተወለደ በ40 ቀኑ የኦሪትን ሕግ ለመፈጸም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ ። ይህም ሕግን ሊፈጽም እንጂ ሊያፈርስ አለመምጣቱን በቃልም ፣ በግብርም የገለጠበት በዓል መኾኑን ያስረዳናል። ሥርዓቱን ለመፈጸም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ጌታቸውን ይዘው፣ የርግብ ግልገሎችና ዋኖስ ጨምረው ወደ ቤተ መቅደስ ሔዱ ። ++++ የስምዖን አረጋዊ ነገርም እንዲኽ ነው .. ዓለም በተፈጠረ በ5,200 ዓመታት በጥሊሞስ የተባለ ንጉሥ በግሪክ ነግሦ ነበር። ዓለሙን እንደ ሰም አቅልጦ፣ እንደ ገል ቀጥቅጦ የገዛው መሆኑን ገልጦ፣ የቀረው ነገር አለመኖሩን ሲናገር ባለሟሎቹ በእሥራኤል ጥበብ የመላባቸው 46 መጻሕፍት ስላሉ እነርሱን አላስተረጎምክም አሉት። እስራኤልን አስገብሮ ስለነበር 46ቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ72 የአይሁድ ሊቃውንት ጋር አስመጣ። አይሁድ ተንኮለኛ መኾናቸውን ስለሚያውቅ 36 ድንኳን እንዲዘጋጅ አድርጎ ኹለት ኹለቱን መድቦ፣ የየድንኳኑን ሊቃውንት የሚቆጣጠሯቸው አንዳንድ ጠባቂዎች ጨምሮ  እንዲተረጕሙ አዘዛቸው። በዚህ ምክንያት በ284 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት 46ቱ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ወደ ልሳነ ጽርዕ (ግሪክ) በ70ው ሊቃናት ተተረጐሙ። ከ70 ሊቃናት በመኻከል አንዱ የነበረው #ስምዖን ምሁረ ኦሪት ነበር። ይተረጕም ዘንድ መጽሐፈ ኢሳይያስ ደረሰው። ታዲያ ይህ ሊቅ የትንቢቱን መጽሐፍ እየተረጎመ ሳለ ምዕራፍ ፯ ላይ ሲደርስ የሕይወቱን አቅጣጫ ወደ ዘላለማዊ በረከት የሚያሳድግ ልዩ ገጸ ንባብ ገጠመው ። እርሱም “ ስለዚኽ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነኾ ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” ኢሳ 7፥14 የሚል ነበር። ስምዖንም "እንዴት ድንግል ትፀንሳለች?" ብሎ "ድንግል" የሚለውን "ሴት" ብሎ ቀይሮ " ሴት ትፀንሳለች " ብሎ ለማረም ይሞክርና አመሻሽ ላይ ስለነበር እንቅልፍ ሸለብ አድርጎት ሲነቃ የቀየረው ተቀይሮበት " ድንግል ትጸንሳለች" የሚል ሁኖ ያገኘዋል።  ተሳስቼ ነው ብሎ አሁንም ሊያበላሽ ሲሞክር መልአኩ ሦስት ጊዜ አርሞበት  በሦስተኛው መልአኩ ራሱ ተገልጦለት "ይህችን ድንግል ሳታይና ልጇንም ታቅፈህ ሳትባረክ አትሞትም" ( የተጠራጠርከውን ሳታይ አትሞትም ብሎ ብሎ ነግሮት )  ተሰወረ። አረጋዊ ስምዖንም ከዚያች ዕለት ጀምሮ መድኅን ክርስቶስ እስከሚወለድ ለ284 ዓመታት ከአልጋ ጋር ተጣብቆ ኖረ። አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በተወለደ በ40 ቀኑ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ወጡ ። በዕለቱም መልአከ እግዚአብሔር አረጋዊ ስምዖንን ቀስቅሶ ተስፋ የሚያደርገው አዳኝ ክርስቶስ መምጣቱን ነገረው። በዚህ ጊዜ አረጋዊ ስምዖን አካሉ ታድሶ፣ እንደ 30 ዓመት ወጣት እምር ብሎ ከአልጋው ተነሣ። በፍጥነትም ወደ መቅደስ ገባ። መድኀኔዓለምን ከድንግል ማርያም ተቀብሎ በመታቀፍ "ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ፡-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" (" ጌታ ሆይ፥ አን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤ ይኽም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ፳ኤል ክብር ነው።" (ሉቃ 2÷29-32)  ) በማለት ጸለየ።  አምላኩም ጸሎቱን ሰምቶት በዛሬው ዕለት ዐረፈ። ከበዓሉ በረከት ይክፈለን። አሜን!! የሊቁ ስምዖን  አረጋዊ በረከት እና ምልጃ አይለየን ! በዓለ ስምዖን በዐይቢይነት  ሜላት ደብረ ገነተ ኢየሱስ  ይከብራል  ፡፡ ጐንደር   -- › አንዳቤቴ ወረደ   -- › ገነተ ኢየሱስ   በ13ኛ መቶ ክፍለ  ዘመን በአጼ ሰይፈ አርዕድ ዘመነ መንግስት ልዕልት ሜላተ ወርቅ ያሰተከለችው ደብር ነው ፡፡ +++ በዓሉ በኢየሱስ ስም የተሰየሙ አድባራትና ገዳማት ላይ ይከበራል ! +++ አንዲት ቤተክርስቲያን ፣ አንድ ሲኖዶስ ፣ አንድ ፓትርያርክ ፡፡ +++ / በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት  ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ /    #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot      www.finotehiwotsundayschool.com

መንፈሳዊ የእጮኝነት ጊዜ በመጋቤ ሐዲስ እንዳልካቸው ንዋይ(ክፍል 1) ተከታታይ ትምህርት በዓርብ ጉባኤ

2ኛው የተማሪዎች ልዩ ጉባኤ ፥ የፎቶ ማስታወሻ ። የካቲት 30 ፥ 2016  ዓ.ም ፥ መዝገበ ጥበብ ልሳነ ወርቅ ዋሴ( የቅኔ ፣ የአቋቋም እና የመጻሕፍት መምህር ) ፥  መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ ፥ ዲ/ን ኢዮብ  ወንድወሰን ፥ መ/ር ኢዮብ በቀለ በተገኙበት  የተማሪዎች ልዩ ጉባኤ ተካሄዷል ። በጉባኤው ላይ በተደረገው ትምህርታዊ ውይይት ከተማሪዎች የተሰበሰቡ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል ።