es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 950 suscriptores, ocupando la posición 5 312 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 242 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 950 suscriptores.

Según los últimos datos del 23 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 397, y en las últimas 24 horas de -13, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 25.83%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 11.01% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 117 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 755 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 29.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 24 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 950
Suscriptores
-1324 horas
+1467 días
+39730 días
Archivo de publicaciones
ከፎቶ ማኅደራችን፤ በመስቀል አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል አቅራቢዎች፤ በ1995፣ 2004፣2006፣2012 2007ዓ.ም እንዲሁም 2012 የመስቀል በዓል አገልጋዮች

፠፠፠ #የመስቀል_ክብረ_በዓላት_ #መስከረም_16_የደመራ_በዓል_፤ #መስከረም_17_የመስቀል_በዓል_፤ #መስከረም_10_ተቀጸል_ጽጌ_፤ #መጋቢት_10_መስቀሉ_የተገኘበት_በዓል፤ #share #like በብቸኝነት (እስከ ቅርብ ጊዜያት) ከንግሥት ዘውዲቱ ጀምሮ በደብራችን የመስቀል ክብረ በዓል መስከረም 17ና መጋቢት 10 ይከብራል፤ ይምጡና ያክብሩ #ደመራ_፤ ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ያወቀችበት ዕለት ነው፡፡ ጥንተ ታሪኩም፤ ክርስቶስ በሞተ ጊዜ የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በጌታ መካነ መቃብር ጎልጎታ ወስደው አኑረውታል፡፡ አበው ሐዋርያት የኢየሩሳሌሙ ኤጲስ ቆጶስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገው እነርሱም ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱ በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጠዋትና ማታ በጎልጎታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተአምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ መፈወስ ጀመሩ፤ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ሳባቸው፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ በመውሰድ ቀብረውት ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየተጣለበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆየ፡፡ በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጕዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንቱ ትዕምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ /በዚህ ምልክት ድል ታደርጋለህ/›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት ድል በማድረጉ ነው፡፡ የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመኾኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው እርሱም ሦስት ተራሮችን ጠቆማትና ከሦስት ተራሮች የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ግን በእግዚብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ /አስደምረሽ/ ዕጣን አፍስሺበትና በእሳት አያይዥው የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጭሽ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው መስከረም 16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡ ደመራ ማለትም፤ ደመረ፣ ጨመረ፣ አንድ አደረገ፤ ከሚለው የግእዝ ቃል የተወረሰ ሲሆን መቀላቀልን፣ መገናኘትን፣ መሰብሰብን፣ መጣመርን፣ መዋሐድን በአጠቃላይ ሱታፌን፣ አንድነትን እና ኅብረትን ያመለክታል፡፡ በዚህችም ቀን የጌታችን መካነ መቃብር ላይም ቤተክርስቲያን የታነጸችበት ዕለት ይታሰባል #መስቀል_፤ መስከረም 17 ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት መስቀሉ እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽቦችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ ✤ #ተቀጸል_ጽጌ_(#መስከረም_10_/#አፄ_መስቀል_/)፤ መስቀሉ ወደ ሃገራችን የገባባት ዕለት ነው፡፡ ✤ #መስከረም_21_፤ መስቀሉ መስከረም 10 ቀን ቀን ወደ ሃገራችን ከገባ በኋላ ‹‹መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ›› በተባለው ቃል መሠረት ከብዙ ፍለጋ በኋላ መስከረም 21 በግሸን ደብር ከርቤ ያረፈበት ዕለት ነው /ዝርዝሩን መስከረም 21 ይጠብቁ/፡፡ ✤፠ንግስት እሌኒ በመስከረም 16 ቀን ደመራ አስደምራ፤ ፠፠✤✤መስከረም 17 ቁፋሮ አስጀምራ ፠፠፠✤✤✤በመጋቢት 10 ቀን ቁፋሮ ተጠናቅቆ መስቀሉ ተገኝቷል፡፡ (በደብራችን በአ.አ እስከ ቅርብ ጊዜያት በብቸኝነት ከንግሥት ዘውዲቱ ጀምሮ በደብራችን የመስቀል ክብረ በዓል መስከረም 17ና መጋቢት 10 ይከብራል፤ ላልሰማው ያሰሙ፡፡ እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ ሙሉ ሥርዐተ ማኅሌቱን (ዘመድኀኔዓለምና ዘአደባባይ ብለን) አቅርበንላችኋል፡፡) እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ፤ መስከረም 16ና 17፤ በደመራው (በርጥብ እንጨት ለሚደመረው ደመራ)፣ በዋይዜማው፣ በማኅሌቱ፣ በሰዐታቱ፣ በኪዳኑ፣ በቅዳሴው፣ በዑደተ ታቦተ ሕጉ፣ የመስቀሉን እምነት ግናባራችንን ለመቀባት በቀጨኔ ደብረ ሰላም እንገናኝ፡፡ ፠ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን፤ የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡ ፠ "በወንጌሉ ያመናችሁ፤ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ፡፡" ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ /ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ላይ ባጭሩ የተወሰደ፡፡/