የጥበብ ማዕድ
📈 Análisis del canal de Telegram የጥበብ ማዕድ
El canal የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 890 suscriptores, ocupando la posición 5 407 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 116 en la región Etiopía.
📊 Métricas de audiencia y dinámica
Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 890 suscriptores.
Según los últimos datos del 24 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 628, y en las últimas 24 horas de 31, conservando un alto alcance.
- Estado de verificación: No verificado
- Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 2.61%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 2.09% de reacciones respecto al total de suscriptores.
- Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 415 visualizaciones. En el primer día suele acumular 332 visualizaciones.
- Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 9.
📝 Descripción y política de contenido
El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 25 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.
<< ሰብሊ ለምንድነው ብቻሽን መቀመጥ የምትወጂ ? ለምን ከሰው አትቀላቀይም ? >>
<< ተወኝማ አቤላ የኔን ነገር እያወከው ... የትኛው ፈላስፋ ነው ግን " ሰዎችን አልጠላቸውም ግን አጠገቤ ሲርቁ ምቾት ይሰማኛል " ያለው ? የኔም ህይወት ከሱ ጋር ተዛማጅ ነው ። ምናልባት እኔ ያሳለፍኩትን ህይወት አሳልፎ ይሆን ?>>
<< እንዶም አገኘሁሽ ! ያሳለፍሺውን ህይወት ጥቂቱን አሁን ንገሪኛ,,,,,, ካልሺኝ ፈላስፋው ጋር ህይወትሽ ተዛማጅ መሆኑን እንድነግርሽ >>
<< ተው ዛሬ አይሆንም >>
<< ነገሩን ራስሽ ነሽ ያመጣሺው so ቀጥይ ...>>
<< ኡፍፍፍ አቤላ አንተ ደሞ ድርቅ ካልክ አትመለስም >>
<< እነግርሃለው ካልሺኝ ስንት ቀኑ ዛሬ ተይዘሻል >>
<< እሺ ይሁና ግን ለዕንባህ ሶፍት ያዝ " ሰው ጋ ከመኖር ለብቻ መሆን ምቾት ይሰጣል " ያልኩበት ምክኒያት የዛሬ አምስት አመት በ Acounting ትምህርቴን ለመማር አሰብኩና እናቴና አባቴ እኔን ለማስተማር አቅም ስለሌላቸው አብሮ አደግ ጓደኛዬ ቤት የቤት ሰራተኛ ሁኜ በ weekend program ለመማር ወስኜ ተመዘገብኩ ። መማር እና መስራት እንደጀመርኩ ሰሞን ሁሉ ነገር ተመችቶኝ ነበረ ግን ቀስ በቀስ ሁሉ ነገር መስመር እየለቀቀ መጣ ። አሰሪዬም ቅዳሜ ቅዳሜ የታክሲ ብር መከልከል ጀመረች እኔም ከጎረቤቶች ብር ተበድሬ የጀመርኩትን ትምህርት ከማቋርጥ ብየ ክላስ እሄዳለሁ
.... አንዳንዴም የመመለሻ ብር አጥቸ የሶስት ሰዓት መንገድ በእግሬ እመጣለሁ ። " አቤላ እኔ እኮ ሰዎችን እወዳለሁ ግን ባዳና የሩቅ ሰው ቢጎዳኝ ምንም አልልም እኔ ግን የምፈተነው በቅርብ ሰው ፣ በማውቀው ፣ በአብሮ አደጌ ፣ መጎዳቴ ነው የምያበሳጨኝ ።
......ቤት ወልውየ ፣ ምግብ ሰርቸ ፣ ልብስ አጥቤ ቁጭ ከማለቴ ድሮ ለወልወል ጦርነት የተለበሱትን የነተቡ ልብስና ጫማ እንዳጥብ ትሰጠኛለች ። እናቴን ለማየት ሄጄ የእማዬን ፍቅርና ጠረኗን ሳላጣጥም " ቶሎ ነይ " ብላ ትደውላለች ። አሁን ራሱ በህይወት የቆየሁት ለከርታታው አባቴ ነው አቤላዬ አባቴ እኮ እኔ የጠየኩትን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም። የለምን አያውቅም እና ለዚህ ጀግናው አባቴ የኔ ራስን ማጥፋት ሳይሆን የኔን ወግ ማዕረግ የኔን ስኬት ተንሰፍስፎ ለሚጠብቅ አባት እንዴት አድርጌ ተስፋ ልቁረጥ? እንዴት የወረደ ቦታ ተገኝቸ ክብሩን በኔ በልጁ ምክኒያት ላጉድፍ? እንዴት ራሴን ላጥፋ ?,,,, በረሃብ አንጀቱ እየታጠፈ እኔ ልጁ እንድጠግብለት ለሚኳትን አባት አስክሬኔን አላስታቅፈውም ብየ ቀኔ እስከሚመጣ ድረስ አንገቴን ደፍቸ ከሰው ተነጥየ ብቻዬን አለሁ ።>>
<< ሰብሊዬ ምን አይነት ጥንካሬ ነው ያለሽ ? >>
<< ይሄ'ኮ የኔ ብቻ ታሪክ አይደለም የአብዛኛው ሴቶች ታሪክ ነው ። ደሞ ምርጥ አድማጭ እንደሆንክ ነግሬካለሁ ?>>
<< ሰብልዬ እያንዳንዱ ቃላቶችሽን በፍቅር ነው ምሰማቸው ምንም እኮ ነው ማትሰለቺ ! ሰብልዋ ። " ልሳምሽ ? >>
<< Of course >>
<< እምምምምምጷ >>
✍ Henokበድሮ ጊዜ ንጉሳዊያን ሲደብራቸው እና ህዝቡ ኣእምሮው እንዲዝናና አንድ ጭዋታ ያዘጋጁ ነበረ ። ያንን ጨዋታ ለመጫወት ከጎረቤት - ሩቅ ሃገር ያሉ ሰውነታቸው ፈርጠም ያሉት ተፋላሚዎች ተሰብስበው ይመጣሉ ።
ያንን ፍልሚያ ካሸነፉ እስር ወርቅ ወይም የንጉሱን ቤተ መቅደስ የውስጥ አስተዳደርነት ማዕረግ ይሰጣል ። እናም ይህንን ድል ለመቀዳጀት የፍልሚያ ሜዳ ውስጥ መግባት ያስፈልጋል ።
ድልን ፣ ስኬትን ለመቀዳጀት መወዳደር ፣ መፋለም ያስፈልጋል ። የድሮውን ስርዓት እንተወውና የአሁኑን ፍልሚያ እንመልከት ...
ወጣት ሆይ :- የዚህን ዓለም የህይወት ዉጣውረድ ለማሸነፍ ከፈለክ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደሩን ትተህ አንተነትን ተቀበልና ወደ ፍልሚያው ሜዳ የሚያስፈልግህን ቁሳቁስ ይዘህ ግባ ።በዚህ ፍልሚያ ውስጥ መውደቅ አለ ፣ መጠማት አለ ፣ መራብ አለ ፣ መቁሰል አለ፣ መድማት አለ ፣ ግን አንተ የአሁኑን ህመም በቆራጥነትና በእችላለሁ መንፈስ አጥፍተህ ከፊትለፊትህ ያለውን ድል ለመቀዳጀት ተዋጋ ።
ዙርያህ ላይ ያሉትን ስኬታማ ሰዎችን አትመልከት <<እንደነሱ ለምን አልሆንኩም >> ብለህ ራስህን አትውቀስ አሁንም አረፈደም ... ተነስ ! ለፍልሚያህ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ይዘህ ወደ ሜዳው ግባ ደግሞም አንድ ነገር አስታውስ ድልን የሚቀዳጅ ያጨበጨበ ሳይሆን የተፋለመና የሞከረ ነው ።
✍ Henokተስፋ ላለመቁረጥ ትልቁ ምክንያት የፈጠረህ አካል እና የተፈጠርክለት ትርጉም ሲሆን ፥
ከዚህ በመቀጠል ዋናው ነገር ግን አንተ የዓለማችን ምርጡ እና ድንቅ ሰው ስለሆንክ አለም አንዳች ጎኗን (ድክመቷን) እንድታሳርፍላት አብዝታ ትፈልግሀለች። ታዲያ እንዲህ በጉጉት የሚጠበቅ ሰው ከሆንክ ለየትኛውም ችግር ይህን ጉጉት እንዲያመክነው አትፍቀድ። ቢያረፍድም መድረስ ይቻላል .. ነገር ግን በጣም አስገራሚው እና ይህን እንድናምን የሚረዳን እውነታ ምንድነው ?? ውድቀትህ ሊያሸማቅቅህ አይገባም። ምክንያቱም አለም ትፈልግሀለች እንጂ አታውቅህም ፣ ስለዚህ ብትወድቅም ቀይ ካርድ ሰጥታ ከጨዋታ አታስወጣህም፡ አታቅህማ... የት ታቅሀለች🤷። ግን ትፈልግሀለች ... መልካም ምሽት ።
¡Ya disponible! Investigación de Telegram 2025 — los principales insights del año 
