የጥበብ ማዕድ
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览
频道 የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 890 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 407,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 116 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 890 名订阅者。
根据 24 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 628,过去 24 小时变化为 31,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.61%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.09% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 415 次浏览,首日通常累积 332 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 9。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
凭借高频更新(最新数据采集于 25 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 890
订阅者
+3124 小时
+1507 天
+62830 天
帖子存档
15 886
እወድሻለሁ አልኳት
<<አሁን ነው ትንሽ ያገገምኩት ፤ መሳቅ የጀመርኩት ፤ ብቻዬን መሆንን የለመድኩት ። አሁን ነው እንቅልፍ ሳልቸገር መተኛት የጀመርኩት ። አሁን ነው ሰበብ እያደረግኩ ፣ የሆነውን እያስታወስኩ መነፋረቅ ያቆምኩት ። >>
እኔ እኮ.. ..አቋረጠችኝ
ለቁምነገር ነው የምፈልግሽ ...አከብርሻለሁ ... እወድሻለሁ ...እታመንሻለሁ... አልከዳሽም ....ልትለኝ ነው አይደል ? ሁሉንም ተብያለሁ
ተወኝ ትንሽ ብቻዬን መሆንን ላጣጥመው ፤ ትንሽ ማገገሜ ይታወቀኝ ...ተወኝ >>
እሺ ...ግን
እውነቴን ነው ብሎ እውነተኛም አለ ፣
ኋላ ማየት ኋላ ያስቀርሻል ፣ ህይወት ወደፊትም ነው .....አሁንም አቋረጠቺኝ
<እሱንም ተብያለሁ......>>
እሺ ..አልኳት
ከትላንቱ ጋ የተጣበቀን ሰው ነገን ማሳየት ከባድ ነው
© Adhanom Mitiku
15 886
<< ሰብሊ ለምንድነው ብቻሽን መቀመጥ የምትወጂ ? ለምን ከሰው አትቀላቀይም ? >>
<< ተወኝማ አቤላ የኔን ነገር እያወከው ... የትኛው ፈላስፋ ነው ግን " ሰዎችን አልጠላቸውም ግን አጠገቤ ሲርቁ ምቾት ይሰማኛል " ያለው ? የኔም ህይወት ከሱ ጋር ተዛማጅ ነው ። ምናልባት እኔ ያሳለፍኩትን ህይወት አሳልፎ ይሆን ?>>
<< እንዶም አገኘሁሽ ! ያሳለፍሺውን ህይወት ጥቂቱን አሁን ንገሪኛ,,,,,, ካልሺኝ ፈላስፋው ጋር ህይወትሽ ተዛማጅ መሆኑን እንድነግርሽ >>
<< ተው ዛሬ አይሆንም >>
<< ነገሩን ራስሽ ነሽ ያመጣሺው so ቀጥይ ...>>
<< ኡፍፍፍ አቤላ አንተ ደሞ ድርቅ ካልክ አትመለስም >>
<< እነግርሃለው ካልሺኝ ስንት ቀኑ ዛሬ ተይዘሻል >>
<< እሺ ይሁና ግን ለዕንባህ ሶፍት ያዝ " ሰው ጋ ከመኖር ለብቻ መሆን ምቾት ይሰጣል " ያልኩበት ምክኒያት የዛሬ አምስት አመት በ Acounting ትምህርቴን ለመማር አሰብኩና እናቴና አባቴ እኔን ለማስተማር አቅም ስለሌላቸው አብሮ አደግ ጓደኛዬ ቤት የቤት ሰራተኛ ሁኜ በ weekend program ለመማር ወስኜ ተመዘገብኩ ። መማር እና መስራት እንደጀመርኩ ሰሞን ሁሉ ነገር ተመችቶኝ ነበረ ግን ቀስ በቀስ ሁሉ ነገር መስመር እየለቀቀ መጣ ። አሰሪዬም ቅዳሜ ቅዳሜ የታክሲ ብር መከልከል ጀመረች እኔም ከጎረቤቶች ብር ተበድሬ የጀመርኩትን ትምህርት ከማቋርጥ ብየ ክላስ እሄዳለሁ
.... አንዳንዴም የመመለሻ ብር አጥቸ የሶስት ሰዓት መንገድ በእግሬ እመጣለሁ ። " አቤላ እኔ እኮ ሰዎችን እወዳለሁ ግን ባዳና የሩቅ ሰው ቢጎዳኝ ምንም አልልም እኔ ግን የምፈተነው በቅርብ ሰው ፣ በማውቀው ፣ በአብሮ አደጌ ፣ መጎዳቴ ነው የምያበሳጨኝ ።
......ቤት ወልውየ ፣ ምግብ ሰርቸ ፣ ልብስ አጥቤ ቁጭ ከማለቴ ድሮ ለወልወል ጦርነት የተለበሱትን የነተቡ ልብስና ጫማ እንዳጥብ ትሰጠኛለች ። እናቴን ለማየት ሄጄ የእማዬን ፍቅርና ጠረኗን ሳላጣጥም " ቶሎ ነይ " ብላ ትደውላለች ። አሁን ራሱ በህይወት የቆየሁት ለከርታታው አባቴ ነው አቤላዬ አባቴ እኮ እኔ የጠየኩትን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም። የለምን አያውቅም እና ለዚህ ጀግናው አባቴ የኔ ራስን ማጥፋት ሳይሆን የኔን ወግ ማዕረግ የኔን ስኬት ተንሰፍስፎ ለሚጠብቅ አባት እንዴት አድርጌ ተስፋ ልቁረጥ? እንዴት የወረደ ቦታ ተገኝቸ ክብሩን በኔ በልጁ ምክኒያት ላጉድፍ? እንዴት ራሴን ላጥፋ ?,,,, በረሃብ አንጀቱ እየታጠፈ እኔ ልጁ እንድጠግብለት ለሚኳትን አባት አስክሬኔን አላስታቅፈውም ብየ ቀኔ እስከሚመጣ ድረስ አንገቴን ደፍቸ ከሰው ተነጥየ ብቻዬን አለሁ ።>>
<< ሰብሊዬ ምን አይነት ጥንካሬ ነው ያለሽ ? >>
<< ይሄ'ኮ የኔ ብቻ ታሪክ አይደለም የአብዛኛው ሴቶች ታሪክ ነው ። ደሞ ምርጥ አድማጭ እንደሆንክ ነግሬካለሁ ?>>
<< ሰብልዬ እያንዳንዱ ቃላቶችሽን በፍቅር ነው ምሰማቸው ምንም እኮ ነው ማትሰለቺ ! ሰብልዋ ። " ልሳምሽ ? >>
<< Of course >>
<< እምምምምምጷ >>
✍ Henok15 886
ተፈፀመ! መድፈኞቹ የእንግሊዝ ንጉስ ሆኑ!
የ22 ዓመታት ረጅም የናፍቆት ጉዞ፣ የእልህ አስጨራሽ ትግል እና የመስዋዕትነት ውጤት! አርሰናል በመጨረሻም የ2025/2026 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ በመሆን የክብር ዋንጫውን በኩራት ተረክቧል!
ይህ ስኬት ለሁላችንም ትልቅ ትምህርት ነው፦
የፈለገውን ያህል ጊዜ ብትወድቅ፣ የፈለገውን ያህል ጊዜ ነገሮች ባይሳኩ... በራስህ ማመንህን ካላቆምክ እና በትጋት መስራትህን ከቀጠልክ፣ የድል ቀንህ መምጣቱ አይቀሬ ነው!
15 886
በድሮ ጊዜ ንጉሳዊያን ሲደብራቸው እና ህዝቡ ኣእምሮው እንዲዝናና አንድ ጭዋታ ያዘጋጁ ነበረ ። ያንን ጨዋታ ለመጫወት ከጎረቤት - ሩቅ ሃገር ያሉ ሰውነታቸው ፈርጠም ያሉት ተፋላሚዎች ተሰብስበው ይመጣሉ ።
ያንን ፍልሚያ ካሸነፉ እስር ወርቅ ወይም የንጉሱን ቤተ መቅደስ የውስጥ አስተዳደርነት ማዕረግ ይሰጣል ። እናም ይህንን ድል ለመቀዳጀት የፍልሚያ ሜዳ ውስጥ መግባት ያስፈልጋል ።
ድልን ፣ ስኬትን ለመቀዳጀት መወዳደር ፣ መፋለም ያስፈልጋል ። የድሮውን ስርዓት እንተወውና የአሁኑን ፍልሚያ እንመልከት ...
ወጣት ሆይ :- የዚህን ዓለም የህይወት ዉጣውረድ ለማሸነፍ ከፈለክ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደሩን ትተህ አንተነትን ተቀበልና ወደ ፍልሚያው ሜዳ የሚያስፈልግህን ቁሳቁስ ይዘህ ግባ ።በዚህ ፍልሚያ ውስጥ መውደቅ አለ ፣ መጠማት አለ ፣ መራብ አለ ፣ መቁሰል አለ፣ መድማት አለ ፣ ግን አንተ የአሁኑን ህመም በቆራጥነትና በእችላለሁ መንፈስ አጥፍተህ ከፊትለፊትህ ያለውን ድል ለመቀዳጀት ተዋጋ ።
ዙርያህ ላይ ያሉትን ስኬታማ ሰዎችን አትመልከት <<እንደነሱ ለምን አልሆንኩም >> ብለህ ራስህን አትውቀስ አሁንም አረፈደም ... ተነስ ! ለፍልሚያህ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ይዘህ ወደ ሜዳው ግባ ደግሞም አንድ ነገር አስታውስ ድልን የሚቀዳጅ ያጨበጨበ ሳይሆን የተፋለመና የሞከረ ነው ።
✍ Henok15 886
...
ፉክክር ውድድር በነውር በክፋት
ብቻ ላለመሆን ብቻ ላለመቅረት
ለመቆየት ሲባል
ያልሆኑትን መምሰል
እስቲ ምን ያደርጋል?
ታብዮ እንደቀረ እንደደነደነ
ኣልኖርም እንዳለ እንደተቃረነ
ያ ግትር ልባችን
እንደሸሸ እግዜርን
እንደፈራ ሞትን
ሲሸሽ ሲከተለው
እስትንፋስ እያለው
ሊኖር ያልደፈረው
ከወዲና ወዲያ እንዲ ሚላተመው
ለሌላኮ ኣደለም
ለመመሳሰል ነው፥
ለመሰንበት ለመቆየት..
ኗሪውን ቆሞ ለማየት
ለማስቆጠር ሌላ እለት
ቀን ይደራርባል
ግን መች ይኖረዋል
እንዲሁ እንዳማጠ
ለከንቱ እንደለፋ
ላይደርስ እንደሮጠ
ኣንድ ቀን...
ኣንድ ቀን...
ኣንድ ቀን...እንዳለ
እየወላወለ
ዘመኑን ጨረሰ
ኣይ የሰው ልጅ ህይወት
ለመሆን ኣደለም፡መስሎ ለመታየት
በግራና በቀኝ እንደተጎተተ
መኖርን ሳይኖረው እንደሞተ ሞተ፥
....meron
15 886
ትቀርያለሽ_ብየ...
[በእውቀቱ ስዩም]
ግድየለሽምና ፥ ከልብ ላፈቀረሽ
ሶስቴ ተቀጣጥረን፥ አራት ጊዜ ቀረሽ።
ዛሬም እንደ ወትሮው፥ ትቀርያለሽ ብየ
እድል የላከውን፥ እጣ የሚመስል፤ እጦት ተቀብየ፥
አበባ ሳልቀጥፍ
አልጋ ሳላነጥፍ
ሙታንታየን ሳልጥፍ
በትራስጌየ ላይ ፎቶሽን ሳለጥፍ፥
ትቀርያለሽ ብየ፥
በመስታውቴ ፊት
ከልብ አስቀይሜ
አንድ እፍኝ ነጭ ሽንኩርት
እንደ ተልባ ቅሜ
አየሩን መርዤ፥ ህዋሴን አክሜ፤
ትቀርያለሽ ብየ፥
ጥፍሬን ሳልከረክም
በመቀስ ሳልንደው፥ የጉያየን ሸክም
ትቀርያለሽ ብየ
ጀንበርን ቀድሜ፤ ቤቴ ተከትቼ
ግቤን ያለ ረዳት፥ በጊዜ መትቼ
የከሸፈ ትውልድ አንሶላ ላይ ትቼ
ልተኛ ስዘጋጅ፥ እፎይ ብየ አርፌ
ከወደ በራፌ
“ውዴ! ደርሻለሁ፥ የሚል ድምጽሽ መጣ”
ከመግባትሽ በፊት፥ እኔ በየት ልውጣ?
15 886
ተስፋ ላለመቁረጥ ትልቁ ምክንያት የፈጠረህ አካል እና የተፈጠርክለት ትርጉም ሲሆን ፥
ከዚህ በመቀጠል ዋናው ነገር ግን አንተ የዓለማችን ምርጡ እና ድንቅ ሰው ስለሆንክ አለም አንዳች ጎኗን (ድክመቷን) እንድታሳርፍላት አብዝታ ትፈልግሀለች። ታዲያ እንዲህ በጉጉት የሚጠበቅ ሰው ከሆንክ ለየትኛውም ችግር ይህን ጉጉት እንዲያመክነው አትፍቀድ። ቢያረፍድም መድረስ ይቻላል .. ነገር ግን በጣም አስገራሚው እና ይህን እንድናምን የሚረዳን እውነታ ምንድነው ?? ውድቀትህ ሊያሸማቅቅህ አይገባም። ምክንያቱም አለም ትፈልግሀለች እንጂ አታውቅህም ፣ ስለዚህ ብትወድቅም ቀይ ካርድ ሰጥታ ከጨዋታ አታስወጣህም፡ አታቅህማ... የት ታቅሀለች🤷። ግን ትፈልግሀለች ... መልካም ምሽት ።
15 886
አንድ ሰው "ፈጣሪ ለምን ለጸሎቴን ወዲያው አይመልስም?" ብሎ አምላኩን ይወቅስ ነበር።
....
አንድ ቀን በባህር ላይ ሲጓዝ መርከባቸው ተሰበረችና ብቻውን በአንድ ደሴት ላይ ቀረ።
ለብዙ ቀናት "ጌታ ሆይ አድነኝ!" እያለ ጸለየ።
...
ቀረብ ወዳለው ደሴት ተጠግቶ መጠለያ እንዲሆነውም ከደረቁ ቅጠሎችና ቅርንጫፎች ትንሽ ጎጆ ቀለሰ። አንድ ቀን ግን ምግብ ፍለጋ ሄዶ ሲመለስ ጎጆው በእሳት ተያይዞ አመድ ሆኖ አገኘው።
...
ሰውየው በጣም አለቀሰ፤ "ጌታ ሆይ! መጠለያዬንም አቃጠልከው? ለምን እንዲህ ታደርግብኛለህ?" ብሎ አማረረ።
ከሰዓታት በኋላ ግን አንድ ትልቅ መርከብ እሱን ለመርዳት መጣች። "እዚህ መሆኔን እንዴት አወቃችሁ?" ሲላቸው፣
"ከደሴቱ የሚወጣውን ጭስ አይተን ነው!" አሉት። ያ ያማረረው እሳት ለመዳኑ ምክንያት ሆነ።
...
ፈጣሪ የሚመልስልን እኛ በምንፈልገው መንገድ ሳይሆን እኛን በሚጠቅመን መንገድ ነው። በሕይወታችን ውስጥ "ጥፋት" የመሰሉን ነገሮች ትልቅ በረከት ይዘው ሊመጡ ይችላሉ። ማን ያውቃል?? የእግዜር ጊዜ ገና ቢሆንስ??
15 886
🚨Breaking News
የፕሪምየር ሊግ አሸናፊነት ሜዳሊያ ባሁኑ እሁድ ለአርሰናል ተጫዋቾች ተላልፎ አይሰጥም።
ምክንያቱ ደግሞ ተጫዋቾቹ
ፋይዳ መታወቂያ አላያያዙም😂
15 886
ይድረስ ለ Ethio telecom
"Unlimited Data" ገዝተን ኢንተርኔት በነፃነት የመጠቀም መብታችን በምን ህግ ነው የሚታገደው?
ብዙዎቻችን ተመሳሳይ ችግር እየገጠመን ነው። Unlimited ጥቅል (Package) ገዝተን ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ከሰራ በኋላ ጨርሶ አይሰራም። የሚገርመው ነገር፣ ጥቅሉ እያለ አልሰራም ስላለኝ ብቻ ሌላ ተጨማሪ ጥቅል ለመግዛት ተገድጄ በሌላኛው ጥቅል ግን በሰላም እጠቀማለሁ።
ይህ ማለት ችግሩ ከኔ ስልክ ሳይሆን ሆን ተብሎ Unlimited ጥቅሉ ላይ የሚደረግ ማገጃ (Restriction) እንዳለ በግልጽ ያሳያል።
የበለጠ የሚያናድደው ደግሞ ወደ ደንበኞች አገልግሎት ማዕከል (994) ደውለን ስንጠይቅ የሚሰጠን ምላሽ ነው።
እንደ ጀማሪ ኢንተርኔት ተጠቃሚ "ስልክህን አጥፍተህ አብራ"፣ "ይሄን አስተካክል" እያሉ ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ እና አቅጣጫ የሚያስለውጥ መልስ ይሰጡናል።
ይህ አሰራር ፍፁም ትክክል አይደለም! ከተጠቃሚው ህዝብ ላይ ያለ አግባብ ገንዘብ መውሰድ ካልተባለ ምን ሊባል ይችላል? ኢትዮ ቴሌኮም ለከፈልንበት አገልግሎት ተገቢውን ምላሽና ጥራት ሊሰጠን ይገባል! እዚ Post ስር የተሰጡትን አስተያየቶች ተመልክታችሁ ምላሽ ብትሰጡን
#EthioTelecom #Ethiopia #ConsumerRights #InternetQuality
ግንቦት 12 2018 - እሮብ
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
