es
Feedback
የጥበብ ማዕድ

የጥበብ ማዕድ

Ir al canal en Telegram

ዝም ብለህ ተቀላቀል!

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram የጥበብ ማዕድ

El canal የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 932 suscriptores, ocupando la posición 5 411 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 116 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 932 suscriptores.

Según los últimos datos del 25 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 604, y en las últimas 24 horas de -23, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 2.64%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 2.10% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 419 visualizaciones. En el primer día suele acumular 334 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 10.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
ዝም ብለህ ተቀላቀል!

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 26 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 932
Suscriptores
-2324 horas
+1447 días
+60430 días
Archivo de publicaciones
ባለ ሀሰቱ ሀቀኛ ሲሆን ሀቀኛው ግን ሀቁን ሲያጣ እንዴት ያናድዳል?!

Anyone here መፅሔት የሚያነብ?? እስቲ የናንተን ምርጥ recommend አድርጉን😇

እድሜህ ከፍ ሲል ራስህን የመውደዱ መጠን አብሮ ከፍ ይላል! ለማረጋገጫ ፦ ድሮ ትዘለው የነበረን ከፍታ አሁን ለመዝለል ሞክር?!

ፀሐይ እንደሚመታው ፊት ምስኪንም ፣ ኮስታራም ፡ አስቂኝም ሁሉን በአንዴ የሆነ የለም!!!

በጠዋቱ ስራ ለመግባት Taxi  ለ ሁለት / ለሶስት ሰዓት ትጠብቃለህ  ,,  ታክሲ ውስጥ ትገባለህ ። ትክዝ ብለው የተቀመጡትን ሰዎች እየታከክ ወደ መጨረሻው ወንበር ሂደህ ቁጭ ትላለህ ። ብዙ ዓይነት ሰው ዝም ብለህ ታያለህ ትሰማለህ :-  የተለያየ መልክ ፣ የተለያየ ቋንቋ ፣ የተለያየ የሰውነት ጠረን ፣ ጮክ ብሎ ስልክ የሚያወራ ሰው ፣ የስልክህ ግማሽ የታክሲ ታሪፍ  ...። አጠገብህ የተቀመጠው ሰውዬ  ስልኩን ከኪሱ ለማውጣት የግራ ኩላሊትህን በክርኑ ይጎስምሃል ፣ በሌላኛው ገጥ ያለችው ደሞ ፊትህ ላይ ታስላለች ፣ ስልክ ተደውሎልህ ለማውራት ስትል ጨቅላዎች እንደ ሲንጋፑር ሞንታርቦ ጩሀው አላስወራ ይሉሃል ..... " ወራጅ "   ረዳቱ አይሰማህም እእእእ ( እንደ ድምፃዊ ግሮሮህን ትጠርጋለህ ) "  አረ ወራጅ!" " አንተ ረዳት  ወራጅ አለ እያልኩህ እኮ ነው! "  ብለህ ከብዙ ልምምጥና ሙከራ በኋላ ይሰማሃል ። እንደወረድክ ጫማህን ታያለህ ( " ከጭቃ ውስጥ ነው ከታክሲ ውስጥ ነው የወረድኩ ብለህ ራስህን ትጠይቃለህ "! )  ወደ ሊስትሮ ...... ሌላ ወጪ         አይ እኛ !!!!!!!!!!!    ✍ Henok

እቃቃ
መቼም ልጅ ያልሆነ የለም። ልጅ ሁኖም ታላላቆች "ርካሽ" በሚሉት የዛፍ ቅጠል ፣አቧራ፣ ውሀ፣ እንጨት ቤት ያልሰራ እና ያልተገበያዬ አልነበረም። ወይኔ.....ያኔ አስታውሳለሁ አንዴ፡ ብዙ "ብሮች" በኪሴ፣የምታምር ቆንጆ ባለቤት እና ልጆች ኑረውኝ እንዲሁም ጎረቤቶች። አይይ የነበረን ደስታ .....አይጠገብም ነበር .. ። ታዲያ ሲመሽ አፈራርሰነው "ጨዋታው ፈረሰ አባይ ደፈረሰ" ብለን ቤተሰቦቻችን "ቤት" ወደሚሉት የእኛን ቤት ትተን እንሄዳለን። ለካስ ብሩ በቤተሰቦቻችን ዘንድ ርካሽ የዛፍ ቅጠል ነበር፣ ቤቱም እንዲሁ ከርካሽ ጭቃ የተሰራ። ሲነጋም በአዲስ እንዲሁ እናደርጋለን... እኛ ምን አገባን ... ሰላም ያለው ህይወት ...ብቻ ምንፈልገው እስኪመሽ ብር (ርካሽ የዛፍ ቅጠል) መቁጠር ነው። ህይወቱንም እቃቃ ብለን ሰይመነዋል አይይይይ ... ደስ ሲል ... እና ምን ገረመኝ መሰላቹ፡ አሁን ላይ እውነት ብለነው የምንኖረው ህይወት ወይም ያኔ ቤተሰቦቻችን የሚኖሩት ህይወት ከሆነ ነገር አንፃር እቃቃ መሆኑ ነው። እስኪመሽ (ፍፃሜ ህይወት) ሁሉም በገንዘብ ወይም በሆነ ነገር ራሱን ማስደሰት ይፈልጋል። ሲመሽ ግን ቤተሰቦቹ (አበው አያቶቻችን) ወደሚኖሩበት እውነተኛ ቤት ይሄዳል። የሚያሳዝነው 😢 በዚህኛው ህይወት እንደልጅነታትን ዳግም ወይም ሲነጋ ሌላ እቃቃ ወይም ህይወት አለመኖሩ ነው። ይህን እቃቃ ድሮ ጨዋታ እንለው ነበር። አሁን ግን ዳግም ስለማይገኝ ነው መሰል ጨዋታ አንለውም ይልቁንም ህይወት ብለነዋል። ምናለ ህይወት የልጅነታችን እቃቃ ብትሆን ፍፃሜ የለ፣ ጭንቀት የለ ሰላም ....ነበር
 አይዞን ዲግሪ፣ ማስተር፣ ዶክትሬት፣ ገበሬ፣ ነጋዴ፣ቄስ፣... እያልን እቃቃ ለምንጫወት። ጥንቃቄ🔔 ምናልባት በዚህኛው ዙር ነገ ሌላ ጨዋታ የለም፤ ይህንኑ ነው ምንቀጥል። ስለዚህ ምርጫ ላይ ጠንቀቅ። ጌታየ ሲከብድህ ጨዋታ አፈርሳለሁ አይሰራም።

የምሬን ችለህና አጊንተህ ስትገኝ ነው ብዙ ሰውን መመልከት! ስሙ በስምህ ቢጠራ ራሱ ግድ የለውም ብቻ በአንተ ወገን ሆኖ ይነሳለት!!!

በፍልስፍናም ሆነ በ psychology  ዕይታ ልክነቱ ያልተረጋገጠ ግን እኛ እስከ ዛሬ የምንጠቀመውና ወደ ድንቁርና ጎዳና የምንገሰግሰው ጉዳይ ነው ። ጉዳዩም :- ሰው ራሱን ንፁህ አድርጎ የሌላን ሰው ስህተት እየፈረፈረ ኃጢያቱንና ስህተቱን ያወጣል ። Socrates ይህንን ጉዳይ "  በቅድሚያ ራስህን እወቅ "  ይላል ። ራስህን ካወቅክ የሌላ ሰው ጉዳይ አታይም ራስህን ነው ምታየው ። አንድ ሰው ከተሳሳተ ስህተቱን ይዘህ social media  ላይ አታውጣ ። ቆም ብለህ ራስህን ፈልግ ራስህን እወቅ ። Immanuel Kant  ደግሞ ስለዚህ ጉዳይ ሲያወራ :-  " Moral law " ጽንሰ ሃሳቡን ያቀርባል ። አንድ ሰው ራሱን ንፁህ አድርጎ ሌላውን አጉድፎ ሲናገር በሰው ዘንድ ተቀባይነት ቢያገኝም ክብር አይኖረውም  ያ ማለት ደግሞ የ moral ዕይታውን ይነካዋል ። Freiderich Neitzscheም ስለዚህ ጉዳይ ያለውን እንመልከት :- Nietzsche ይህንን ጉዳይ " moral superiority "  ነው ይላል ። ይህም ማለት ሰዎች ራሳቸው ከፍ ለማድረግ የሌሎችን ደካማ ጎን ይጠቀማሉ ። ይህም ማለት የራሳቸውን ደካማ ጎን የሚሸፍኑት በሌላው ድክመትና ስህተት ነው ።  ስለዚህ ሌሎችን ከመኮነን ይልቅ ራሳችንን ብናውቅና ብንመረምር የተሻለ ነው ። 🙏🙏🙏    ✍ Henok

ማን እንደሚያስቀናኝ ታውቃለህ?? አንተ ...ነህ በዚህ ልክ መፈቀር መቻልህ ከማንም የምታስበልጥህ፤የምትሳሳልህ፤የኔ የምትልህ(የሷ እኮ ግን አደለህም) በዚህ ልክ የምታፈቅርህ እኔ ስላለችህ እቀናብሃለ
ማን እንደሚያስቀናኝ ታውቃለህ?? አንተ ...ነህ በዚህ ልክ መፈቀር መቻልህ ከማንም የምታስበልጥህ፤የምትሳሳልህ፤የኔ የምትልህ(የሷ እኮ ግን አደለህም) በዚህ ልክ የምታፈቅርህ እኔ ስላለችህ እቀናብሃለው 🥹 እናት ለልጇ የምትሳሳውን ያህል ስስት የምትልልህ አፍቃሪ ስላለውህ እቀናለው 🥺 ረስተኽኝም እንኳን ስለማስታውስህ ባንተ እቀናለው ። ሁሌም ባስለመድከኝ ሰዓት የስልኬን ጥሪ ጓጉቼ ስለምጠብቅ፤online በገባሁኝ ቁጥር መልዕክቶችህን የላክልኝ እዬመሰለኝ ስለምባባ፤ ቀን በምናብ ለሊት በህልም አብሬህ ስለምኳትን፤ምስልህን እያዬሁ እስቅ የነበርኩኝ ሰው ዛሬ ሳላስበው ጉንጮቼ በእንባ ስለሚታጠቡ፤ ድምፅህ ሁሌም ካሳቤ ስላልጠፋ .......በዚህ ልክ ስላፈቀርኩህ እቀናለው 😢 አውቃለሁ አልመጥንህም ሁሌም አንሼብህ ይሆናል ግን የእውነቴን አፈቅርሃለው። ትናንት ያወራውህ ቃላት ሁሉ የእውነት ነበሩ ዛሬም እውነት ናቸው .......አለሜ ስልህ ከርሜ ሳጣህ አለመሞቴን አትይ መተንፈስ ብቻ ነው ምችለው ምንም አቅም የለኝም 💔 በህይወትህ አደራን ትፈራ አደል? እኮ ስለምትፈራው አደራዬን ትተብቅልኛለህ .... የኔ አደራ ልቤ ነው አዎ የኔ ልብ ያንተን ልብ ብትነጥቀኝም እኔ ግን የመንጠቅ አቅም አጣሁ ...አእምሮዬ ታግሎ ሊቀማህ ሲሞክር ልቤ ግን ከእናቱ ጡት እንደተነጠቀ ህፃን ያላንተ አሻፈረኝ ብሎኛል ... እና አደራህ ልቤን ጠብቅልኝ ሌላ ምንም አልልህም እንደ እህት እንደ ታናሽናም ሰው ልምከራችሁ idk ምክሬ ፌዝ ይመስላችሁ ይሆናል ግን በቃ አታፍቅሩ ማርያምን በቃ እረፉ ላትድኑ ትታመማላችሁ ይቅር መቼም እንዳትጠገኑ ሆናችሁ ከመሰበር በቀር ምንም ትርፍ የለውም በቃ 🥺🙌

መቃብሩ የተከፈተው ለሱ መውጫ ሳይሆን ለኛ መግቢያ ነው ።እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ ።

አንዳንድ ተሳፋሪዎች ግን ወቅታዊ ችግሮችን ተረዱ ካለመሔድ መጣበብን ብንመርጥ መቅረትን የሚያስመኝ አቀማመጥ ባለመጠጋት አታስመኙን።

፡ በማርያም ያጸኑት     የእምነት ክህደት ቃል                  ሳል' ነበር ምሶሶ፤ እኔ ለስንኩሌ     ልሸነግል በእምነት            ማርያምን አጣቅሶ! ፡ ምንም ባቀለውም     እንደገፊዎቿ ስሟን ባንደበቴ፤ እናት አለም ታሪክ፡        እመቤቴ ኪዳን፡                    እናት ነች እናቴ!!!        #ማርያም!     አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)

እኔ በህይወቴ ላይ ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ ጓደኝነትን አይቻለሁ ። ግን እስከ ዛሬ ፍፁም የሆነ ጓደኝነትን በገሃዱም ሆነ በምናቡ አለም አላየሁም ። ይህንን ፍፁም የሆነ ጓደኝነትን ማየት ከፈለጋቹ ለም
እኔ በህይወቴ ላይ ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ ጓደኝነትን አይቻለሁ ። ግን እስከ ዛሬ ፍፁም የሆነ ጓደኝነትን በገሃዱም ሆነ በምናቡ አለም አላየሁም ። ይህንን ፍፁም የሆነ ጓደኝነትን ማየት ከፈለጋቹ ለምሳሌነት የምጠቅሰው merlin tv series ነው ። Merlin film በጣም የታወቀ የእንግሊዝ ምርጥ fantasy / አስማታዊ ፊልም ነው ። ፊልሙ ድሎትንና ምቾትን የያዘ ሳይሆን በ merlin እና Arthur ላይ የሚመጣውን ችግር መከራ ጭንቀት እንዴት እንደሚወጡ ያሳያል ። ጓደኝነታቸው selfish የሆነ አይደለም ፣ የጥቅም አይደለም ፣ ጓደኝነታቸው ለሃሜት ተፈላልገው የሚለያዩ አይደለም ። የ merlinን ፊልም theme ብዙ ማውጣት ይቻላል ግን ለኔ ገዝፎ የታየኝ ጓደኝነታቸው ነው ። ተመልከቱት 🙏🙏

አንዳንዴ የለኝምን ሚያስተምርህ አለኝ ያልከው ሰው ነው።

የኢራን ባለስልጣን መርከቦች የሆርሙዝን የባህር ወሽመጥ ለማለፍ አሁንም የክፍያ ክፍያ መክፈል እንደሚጠበቅባቸው አሳወቁ። እኛስ ዘግተን ምናስከፍልበት ምን ኖሮን ይሆን?! ገድበነውም ከእንግልት ካልገደ
የኢራን ባለስልጣን መርከቦች የሆርሙዝን የባህር ወሽመጥ ለማለፍ አሁንም የክፍያ ክፍያ መክፈል እንደሚጠበቅባቸው አሳወቁ። እኛስ ዘግተን ምናስከፍልበት ምን ኖሮን ይሆን?! ገድበነውም ከእንግልት ካልገደበን ዓባይ ሌላ!!!

ዝንጀሮ እንኳን ካቅሙ ካፋፍ ይዶልታል ውጣልኝ ከሆዴ ሰው ይገባበታል🥺💔
ዝንጀሮ እንኳን ካቅሙ ካፋፍ ይዶልታል ውጣልኝ ከሆዴ ሰው ይገባበታል🥺💔

ከፒያሳ ኮዬ ፈጬ
ከፒያሳ ኮዬ ፈጬ

" ይህንን ዓለም በተረዳህ ቁጥር ራስህን ታጠፋለህ ። ለዚህም ነው ሞኞች ደስተኛ የሚሆኑት ፤ብልህ ሰዎች ደግሞ በብቸኝነት የሚኖሩት " ። The more understand this world , the more you destroy your self . That's why fools  happy , and intelligent people are live in loneliness .     Fyodor Dyostoveski

ለደፈረሰ ውሃ ትዕ'ግስት ስጠው!

🌬...ከእያንዳንዱ የከረደደ እጅ ጀርባ የከረደደ ትናንት የገነነ ልብ አለ.........ዉሀ ቀጠነ ብሎ ባር ባር ከሚለዉ ሰዉ ጀርባ ሙሾ የሚያስወርድ ትናንት አለ........በቀላሉ ማጅራቱ ከሚጎብጥ
🌬...ከእያንዳንዱ የከረደደ እጅ ጀርባ የከረደደ ትናንት የገነነ ልብ አለ.........ዉሀ ቀጠነ ብሎ ባር ባር ከሚለዉ ሰዉ ጀርባ ሙሾ የሚያስወርድ ትናንት አለ........በቀላሉ ማጅራቱ ከሚጎብጥ ሰዉ ጀርባ ማጅራት ገትር የሚያስይዝ ትናንት ያልታወቀለት ቁስል አለ። ሁላችንም የምንፈርደዉ የደረስንበት ላይ አይደል?!......የሌላዉን ሸክም እንዳናቀል እኛም ሸክም የከበደን ነን.............✨💐 ✍️ ጽዮን 🌸