የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Ir al canal en Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Mostrar más2 623
Suscriptores
+124 horas
+227 días
+3830 días
Archivo de publicaciones
በዓለ ቃና ዘገሊላ 2017 ዓ.ም ደብራችን ጽ/ጽ/ጎላ ቅዱስ ሚካኤል እና ዳግሚት ደብረሊባኖስ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት
+9
በዓለ ቃና ዘገሊላ 2017 ዓ.ም ደብራችን ጽ/ጽ/ጎላ ቅዱስ ሚካኤል እና ዳግሚት ደብረሊባኖስ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት
ምስጋና ዘፍኖተ ብርሃን
የከተራ የጥምቀት እና የቃና ዘገሊላ በዓል በሰላም አክብረን አጠናቀናል !!! ተመስገን ከሁሉ አስቀድሞ ለአምላካችን ለቅዱስ እግዚአብሔር ምስጋና አምልኮ እና ውዳሴ ይድረስው እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አሳዳጊያችን እና ጠባቂያችን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እንዲሁም ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ምስጋና ይድረሳችሁ !!!
የሰንበት ት/ቤታችን አባላት በሙሉ
ሕፃናት አባላት (የሰንበት ት/ቤቱ የነገ ተስፋዎች) ማዕከላውያን አባላት ( የሰንበት ት/ቤቱ ተረካቢዎቻችን) ወጣቶች አባላት (የሰንበት ት/ቤቱ ጠበቃዎች) የባለ ትዳር ጉባኤ አባላት (የሰንበት ት/ቤቱ ጥላዎቻችን ) ልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍላት ላይ የተሳተፋችሁ አባላት የልብሰ ስብሐት እጥረት አጋጥሞን በዝማሬ ያላሳተፍናችሁ አባላት እንዲሁም ለእኅት ሰንበት ት/ት ቤታችን ለደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ምክሐ ደናግል ሰንበት ት/ቤት ለደብራችን አገልጋዪች በሙሉ በጠቅላላ ለልዪ ልዩ የጊቢያችን ማኅበራት ለምንወዳችሁ እና ለምናከብራችሁ ይልቁን ቤተክርስቲያን በስስት ለምታያችሁ እና ጠበቃዋ ለሆናችሁ በሦስቱም መውጫ በር ላይ ላላችሁ የአጥቢያችን ወጣቶች እና ምዕመናን እንዲሁም
* ለደብራችን የአስተዳደር አካላት
* ለልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር
* ለልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
* ለወረዳ 07 የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት
በሙሉ ጊዜያችሁን ጉልበታችሁን ገንዘባችሁን ሳትሰስቱ እና ሳትቆጥቡ ስትሰጡ ለበዓሉ ድምቀት ለሆናችሁ ምዕመናን እና ምዕመናት በሙሉ ዋጋ ከፋይ አስራት ተቀባይ የለመኑትን የማይነሳ የነገሩትን የማይረሳ ቸሩ መድኃኔዓለም አምላካችን ዋጋቹሁን ይክፈላችሁ!!! ከዓይን ጥቅሻ ይልቅ ፈጥና የምትደርስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሕይወታችሁ በቤታችሁ ትግባ ስሙ ሲጠራ ልባችን ወከክ እግራችን ሸብረክ የሚለው ጠባቂያችን አሳዳጊያችን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከልጅነታችን እስከ ሽምግልናችን በጥባቆቱ አይለየን ከቁጥር ሳያጎድለን አምና ብለን ለማውጋት ያጎደለውን ለመሙላት ያብቃን!!! እንዲህ ማማራችን እና መዋባችን በእርሷ ነውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥም ከውጭም ጠላት ይጠብቅልን!!! ሐገራችንን ኢትዮጵያን በሰላም እና በፍቅር በአንድነቷ አጽንቶ ያቆይልን የዓመት ሰው ይበለን!!! አሜን
ጥር 12/2017 ዓ.ም
ካሣሁን እሸቱ
የጽ/ጽ/ሐ/ጎላ /ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ
የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
ም/ሰብሳቢ
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
+9
በዓለ ጥምቀት ጥር 11 2017 ዓ.ም አከባበር በፎቶ
Picsart_25-01-19_22-43-36-480.jpg1.21 MB
Picsart_25-01-19_22-52-12-648.jpg1.47 MB
¡Ya disponible! Investigación de Telegram 2025 — los principales insights del año 
