es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

𝑳𝒆𝒎𝒍𝒆𝒎 𝑯𝑺

𝑳𝒆𝒎𝒍𝒆𝒎 𝑯𝑺

Ir al canal en Telegram

ከት/ቤቱ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ‼️

Mostrar más
2 856
Suscriptores
+124 horas
+87 días
+15130 días
Archivo de publicaciones
📢 የትምህርት ቤት ማስታወቂያቀን፡ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች (ስሟችሁ ከዚህ በታች ለተዘረዘረው) ጉዳዩ፡ በማጠናከሪያ ትምህርት የቀረችሁበትን አሳማኝ ማስረጃ ስለማቅረብ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም በነበረው ማጠናከሪያ ትምህርት ላይ ያልተገኛችሁ በመሆኑ፣ ነገ ረቡዕ ጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ስትመጡ የቀራችሁበትን አሳማኝ እና ህጋዊ ማስረጃ ይዛችሁ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን። 📋 የተማሪዎች ዝርዝር Grade 11 A 📌Abiy Ambachew 📌Adoniyas Tamene 📌Amen Solomon 📌Beamlak Sisay 📌Eyosiyas Mikiyas 📌Maranatha Desta 📌Misgana Tesfaye 📌Tsion Asmie Grade 11 B 📌Eyobliu Endrias Grade 11 C 📌Bethelhem Ali 📌Bezawit Isaac 📌Feris Aldoseri 📌Kalab Muna Grade 11 D 📌Dibora Getu 📌Eyoas Kebede

photo content

ዉድ ወላጆች ቅዳሜ፣ መስከረም 23፣ 2019ዓ.ም በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ምክንያት መንገድ ሰለሚዘጋጋ ነገ አርብ፣ መስከረም 22፣ 2019ዓ.ም ትምህርት ቤት ዝግ መሆኑን እንገልፃለን።

እንኳን አደረሳችሁ ለተከበራችሁ የክርስትና እምነት ተከታይ ተማሪዎቻችን እና ወላጆች፣ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ እና ለደመራ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ! መስቀል የፍቅር፣ የሰላም እና የመተሳሰብ ምልክት እንደመሆኑ መጠን፣ ይህ በዓል ሲከበር  የደመራው እሳት ሲበራ እንደሚያንጸባርቀው የእናንተም የትምህርት ጉዞ በዕውቀት ብርሃን የተሞላ፣ ስኬታማ እና ብሩህ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።        መልካም የደመራ እና የመስቀል በዓል!

ለ ተማሪዎቻችን በሙሉ ጉዳዩ፦ ከመስከረም 11/2019 ዓ.ም ጀምሮ ስለሚኖረው የተጠናከረ የመማር ማስተማር ሂደት እና ስለሚተገበሩ የትምህርት ቤታችን ህጎች :- የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ የተማሪዎቻችንን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ እና ስኬታማ የትምህርት ዘመን እንዲኖረን ለማድረግ በሙሉ አቅሙ እየሰራ ይገኛል። በዚህም መሰረት፣ ከሰኞ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ትምህርት በተጠናከረ መልኩ የሚጀምር መሆኑን እየገለጽን፤ ሁሉም ተማሪዎች የሚከተሉትን ህጎች በጥብቅ እንዲተገብሩ እናሳስባለን። ለትምህርት ስኬት ቁልፍ የሆኑ የትኩረት ነጥቦች፦ 1⃣ ሰዓት አክባሪነት፦ የጠዋት መግቢያ ሰዓት እስከ  ጠዋቱ 1:50  መሆኑን አውቃችሁ በሰዓቱ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን። 2⃣የትምህርት ቤቱ መለያ፦ እያንዳንዱ ተማሪ ትምህርት ቤታችንን የሚወክል የተሟላ የደንብ ልብስ ብቻ ለብሶ መገኘት ይጠበቅበታል። 3⃣ዝግጁነት፦ በየዕለቱ በሚወጣው የትምህርት ፕሮግራም መሰረት አስፈላጊ የሆኑትን የትምህርት ቁሳቁሶች (ደብተር፣ መጽሐፍ፣ እስክሪብቶ፣ ወዘተ) በሙሉ ይዛችሁ መገኘት አለባችሁ። 4⃣ፀጉር እና ስነ-ስርዓት፦ ወንድ ተማሪዎች ጸጉራችሁን ንጹህ እና ለተማሪ የሚገባ (Clean Cut) አድርጋችሁ እንድትቆረጡ እናሳስባለን። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተዘረዘሩትን አራቱንም ነጥቦች ሳያሟላ የሚገኝ ማንኛውም ተማሪ ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ መግባት የማይችል መሆኑን እና ወደ ቤቱ ለወላጅ/አሳዳጊ በመደወል መጥተዉ  እንዲወስዱት የሚደረግ  መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን። ስኬታማ እና ውጤታማ የትምህርት ዘመን ይሁንልን❗️                   የትምህርት ቤቱ ‼️

photo content

ማስታወቂያ ለ9ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ በወጣው  ፕሮግራም መሠረት ከነገ ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት ስትመጡ ማሟላት የሚገባችሁ :- የደንብ ልብስ: የትምህርት ቤቱን ሙሉ የደንብ ልብስ በትክክል በመልበስ መገኘት ይኖርባችኋል። የፀጉር አቆራረጥ (ለወንድ ተማሪዎች): ፀጉራችሁን ክሊን ከት ተስተካክላችሁ። የፎቶ ክፍያ:  የመታወቂያ ፎቶ(Soft copy) ስለምትነሱ 50 ብር (አምሳ ብር) ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን። (የፎቶ መነሻ ቦታ: ፎቶ ሌጀንድ)

ጥብቅ ማሳሰቢያ :-ሁሉም ተማሪ በወጣዉ ፕሮግራም መሠረት የመገኘት ግዴታ አለበት ከዚህ ዉጪ በተለያዩ ምክንያቶች የማይገኝ ተማሪ አስተዳደራዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳስባለን።

photo content

Grade 9 Telegram= https://t.me/LEM30ye Grade 10 Telegram =https://t.me/LEM30yers Grade 11 Telegram =https://t.me/LEM30year

2019 A.C Grade 9-12 Section Placement - .pdf4.51 MB

photo content

photo content
+1

photo content

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9