Addis መረጃ™
@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹 . ⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬ ⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬ መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot
Mostrar más📈 Análisis del canal de Telegram Addis መረጃ™
El canal Addis መረጃ™ (@addis_mereja) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 35 769 suscriptores, ocupando la posición 7 160 en la categoría Noticias y medios y el puesto 1 025 en la región Etiopía.
📊 Métricas de audiencia y dinámica
Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 35 769 suscriptores.
Según los últimos datos del 15 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -86, y en las últimas 24 horas de -26, conservando un alto alcance.
- Estado de verificación: No verificado
- Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 19.95%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 11.34% de reacciones respecto al total de suscriptores.
- Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 7 140 visualizaciones. En el primer día suele acumular 4 058 visualizaciones.
- Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 20.
📝 Descripción y política de contenido
El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬
መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot”
Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 16 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Noticias y medios.
Cargando datos
| Fecha | Crecimiento de Suscriptores | Menciones | Canales | |
| 16 octubre | 0 | |||
| 15 octubre | 0 | |||
| 14 octubre | 0 | |||
| 13 octubre | 0 |
| 2 | Sin texto... | 1 |
| 3 | የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል ራማ ከተማን መቆጣጠራቸው ተገለጸ‼️
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል ትናንት ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም. ራማ ከተማን መቆጣጠራቸው ተመላክቷል።
የድልድይ መጥፋትና የተኩስ ልውውጥ፦ ይህንን ወታደራዊ እርምጃ ተከትሎ የኤርትራ ሰራዊት ከራማ ወደ ኤርትራ አዲዃላ መስመር ያለውን የመረብ ወንዝ የሚያሻግረውን ድልድይ 3 ጊዜ በመድፍ በመተኮስ ጉዳት እንዳደረሰበት ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አሳይተዋል።
የመሣሪያ ዝውውር፦ ኢትዮጵያ ከባድ መሣሪያዎችን ወደ ድንበር እያስገሰገሰች መሆኑን አናዶሉ ዘግቧል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1 | 3 469 |
| 4 | የሚሳይልና የፀረ-አውሮፕላን ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ፍስሃ ፀሃየ (ወዲ ፀሃየ) በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተነገረ።
በዛሬው ዕለት፣ ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም፣ የህወሓት ታጣቂ ኃይል የሚሳይልና የፀረ-አውሮፕላን ክፍል አዛዥ ተብሎ የተጠቀሰው ብርጋዴር ጄኔራል ፍስሃ ፀሃየ፣ በቅጽል ስሙ ወዲ ፀሃየ፣ በተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ ለማምለጥ ሲሞክር በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) እና በትግራይ የሰላም ኃይል (TPF) በቁጥጥር ሥር መዋሉን ምንጮች ገልጸዋል።
@Yenetube @Fikerassefa | 4 422 |
| 5 | ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በስልክ ተወያዩ።
የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ መልዕክት!...
ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ትኩረትን በሚሹ ጉዳዮች ላይ እጅግ ፍሬያማ የሆነ የስልክ ውይይት አድርጌያለሁ።
ያካሄድነው ውይይት በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን እድሜ ጠገብ ወዳጅነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊና ተግባራዊ አጋርነት ለማሳደግ በሁለቱም አገራት በኩል ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በተመለከተ የሰጠችውን ማረጋገጫ እያደነቅኩ የሁለትዮሽ ትብብራችንን ለማጠናከር እንዲሁም በቀጣናዊና ባለብዙ ወገን መድረኮች ቅድሚያ በምንሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ አብረን ለመሥራት ያለንን ቁርጠኝነት አረጋግጣለሁ። | 4 497 |
| 6 | ❗️ሸራሮ ምን እየተካሄደ ነው!!?
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ከባድ የአየር ድብደባዎች እየተደረጉ ነው።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባለፉት 2 እና 3 ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አካባቢዎች ከባድ ድሮን እና የአየር ድብደባዎችን ሲያካሂድ ቆይቷል።
የኤርትራ ጦር እና የትግራይ ተዋጊዎች ከዋና ዋና ከተሞች ሲወጡ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደህንነታቸው ወደተጠበቁ ቦታዎች እንዳይሸሹ እና ጥቃቶችን እንዳይሰነዝሩ ለመከላከል ቀጣይነት ያለው የአየር ዘመቻዎችን እያደረገ ይገኛል።
ከአዲግራት እስከ ዛላምበሳ፣ ከአድዋ እስከ ራማ፣ እና ሺራሮ አካባቢዎች በኢትዮጵያ አየር ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል።
ይህንን ተከትሎ በኤርትራ አዋሳኝ ሽራሮ አካባቢ የእሳት አደጋ የተነሳ ሲሆን ባለፉት ሁለት ወይም ሶስት ቀናት ውስጥ ወደ ኤርትራ ድንበር እየተዛመተ መሆኑን ከሳታላይት ምስሎች ለማየት ተችሏል።
@Yenetube @Fikerassefa | 4 396 |
| 7 | “በአስመራ አገዛዝና ደጋፊዎቹ ላይ በጊዜ እርምጃ አለመውሰድ ከባድ መዘዝ ያስከትላል”- ጌታቸው ረዳ
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፣ ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድና የቀይ ባህር ቀጠና ልዩ መልዕክተኛ አኔት ወበር እና በኢትዮጵያ ከሚገኙት የህብረቱ አምባሳደር ሶፊ ጋር በቀጣናው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያዩ።
በውይይታቸው በትግራይ፣ በኤርትራና በሱዳን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ጨምሮ ለቀጣናው ሰላምና ዘላቂ መረጋጋት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግልጽ የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።
ጌታቸው ረዳ በተለይም በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚገኘው አገዛዝና ደጋፊዎቹ በቀጣናው ውስጥ ያላቸውን አደገኛ ሚና በማንሳት፣ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ለማስቆም አስፈላጊው እርምጃ ካልተወሰደ ከባድ መዘዝ ሊከተል እንደሚችል ለአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ማስረዳታቸውን አስታውቀዋል።
በመጨረሻም በቀጣናው ያለው ውጥረት እንዳይባባስ ለመከላከል፣ የመረጃ ልውውጥን ለማጠናከርና በቅንጅት ለመስራት መስማማታቸውን ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።
@Yenetube @Fikerassefa | 4 713 |
| 8 | ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት ሊገቡ መቃረባቸውን ኢንተርናሽናል ክራይሲስ ግሩፕ የተባለው ግብረሰናይ ድርጅት ዛሬ ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም ባወጣው መረጃ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ኤርትራ ድንበር መድረሱን ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት ወደ ሙሉ ጦርነት የሚገቡበት ሁኔታ መጨመሩን ገልጿል።
@Yenetube @Fikerassefa | 4 944 |
| 9 | በሞተር ብስክሌት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ አዲስ ፖሊስ
በከተማችን አዲስ አበባ ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም ወንጀል የመፈፀም፣ የተሰረቁ እቃዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወር፣ የመንገድ ትራፊክ ህጎችን የመጣስ ( በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም ወ.ዘ.ተ.) በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን በመግለፅ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር መከልከሉን ይታወቃል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ህግን የማስከበር ስልጣንና ኃላፊነቱን በመጠቀም ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ አሳስቦ የሞተር ሳይከል መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያላቸው እና መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያደሱ ሞተር ሳይከል አሽከርካሪዎች ከነገ ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ/ም ጠዋት 12:00 ሠዓት ጀምሮ የትራንስፓርትና የትራፊክ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የወጡ ህጎችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ የተፈቀደ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ዋና ጠቅላይ መምሪያው የመንቀሳቀሻ ፈቃድ የሌላቸው እና ፈቃድ ሳያድሱ በሚንቀሳቀሱ የሞተር አሽከርካሪዎች ላይ በህግ አግባብ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አሳስቧል፡፡
ዘገባ፦ ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
@Yenetube @Fikerassefa | 5 106 |
| 10 | ጄኔራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ የታሰሩ አራት አመራሮች ተፈቱ!
ጄኔራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች መኮንኖች መለቀቃቸው ተረጋግጧል።በአሁኑ ወቅት በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሲሆን፣ ደህንነታቸውም የተጠበቀ እንደሆነ ተገልጿል።
እነዚህ መኮንኖች በህወሓት ታስረው ከነበረ በኋላ ከመቐለ ወደ ሰሜናዊው የጦር ግንባር አካባቢ መወሰዳቸው፣ ለኤርትራው መንግስት አሳልፎ የመስጠት ስጋት ፈጥሮ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa | 5 660 |
| 11 | የሰሜኑ ግንባር ወደ መደምደሚያው እየተቃረበ ነው። የህወሓት የተበታተኑ ቡድኖች ያልተቀናጁ ጥቃቶችን ሊያደርሱ ቢችሉም፣ በተደራጀ ሁኔታ መልሰው ለማጥቃት ያላቸው አቅም ውስን ነው። የፕሮፖጋንዳ ጩኸት ብቻውን ወታደራዊ አቅም አይሆንም‼️
የኤርትራ ጉዳይ ግን በተለየ ስትራቴጂካዊ እይታ መታየት ይገባዋል። የድንበር ጂኦግራፊ፣ የመሬት አቀማመጥና የቀጠናዊ ኃይል ሚዛን በደህንነት ስሌት ውስጥ ወሳኝ ናቸው።
አሥመራ ከኢትዮጵያ ድንበር ከ80 ኪሜትሮች ባነሰ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። በዙርያዋ ያሉት ተራሮች ካልሆነ በቀር የሚከላከላት ብርቱ ኃይል የላትም። ቡሬ ግንባር ለጥ ያለ ሜዳ ነው !!…. 40 ኪሎሜትር ባልሞላ ርቀት ለጥ ያለ ባህር !!
@Addis_Mereja | 5 767 |
| 12 | ትግራይ መቀሌ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዛሬ ጀምሯል።
ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ለሁለት ሳምንት ያህል ተቋርጦ ዛሬ መልሶ በጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው በረራ፦
➠ አቶ ጌታቸው ረዳ
➠ አብርሃም በላይ (ዶ/ር)
➠ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
➠ የትግራይ የሰላም ኃይል አዛዥ ጀነራል ወዲ አንጥሩ
➠ የትግራይ ሰላም ኃይል አመራር ሜጀር ጃነራል ዘውዱ ኪሮስ
➠ ኮሎኔል ወዲ አባተ ... እንደነበሩበት ተነግሯል።
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በጫናና በኃይል ከኃላፊነታቸው እንዲነሱና ትግራይን ለቀው እንዲወጡ ከተደረጉ ከ19 ወራት በኋላ ነው መቐለ የተመለሱት።
ዛሬ ጥዋት ላይ መቐለ፣ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርሱ በከተማዋ ወጣቶች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ቡድኑ በዛሬ ቆይታው ከኤርትራ በ35 ኪ/ ሜ ርቀት በምትገኘው ዓዲግራት ከተማ ገብቶ ከነዋሪዎች ጋር ይነጋገራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተሰምቷል።
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!
@Addis_Mereja | 8 045 |
| 13 | የኤርትራ ቴሌቪዥን ዶክመንተሪ
የኤርትራ ቴሌቪዥን የጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ንግግርን ጨምሮ የኢትዮጵያ ጄኔራሎች በተለያየ ጊዜ ስለጦርነቱ የሰጡትን ንግግር እንደ ማጣቃሻ ተጠቅሞ ዶክመንተሪ አዘጋጅቶ የጦርነት አዘል መልዕክቶችን እያስተላለፈ መሆኑን ተመልክተናል።
ለአብነት በቴሌቪዥን ጣቢያው 'ጦርነቱ ከተጀመረ ውጤቱ ግልጽ ነው' የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ንግግር በዶክመንተሪው የተካተተ ሲሆን የቴሌቪዥን ጣቢያው በመጨረሻም 'ጦርነት ከተጀመረ የብልፅግና መንግስትን እንደ ደርግ መንግሥት እንቀብረዋለን' የሚል መልዕክት እያስተላለፈ ይገኛል።
ምንጭ:- አዩዘሀበሻ
@Addis_Mereja | 6 336 |
| 14 | አዲግራት ‼️
ዛሬ የመከላከያ ሠራዊቱ አዲግራት ከተማን ሲቆጣጠር የከተማው ነዋሪዎችና የአካባቢው ህብረተሰብ ለሠራዊቱ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያደረጉት አቀባበል በፎቶ።
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!
@Addis_Mereja | 7 108 |
| 15 | የትግራይ ክልል የሕዝብ መዝሙር በአዲስ መልክ ሊቀየር መሆኑ ተገለጸ።
በክልሉ አዲስ አስተዳደራዊ መዋቅር እየተዘረጋ ነው
በትግራይ ክልል መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ክልሉን ወደ ሙሉ ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ የሚደረጉ አጠቃላይ የመልሶ ግንባታና የአስተዳደር መዋቅር ዘረጋ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገለጸ።
ከስፍራው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፣ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የአካባቢ አስተዳደሮችን የማጠናከርና ክፍተቶችን የመድፈን ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
በዚህም መሰረት በከተሞች አዳዲስ ከንቲባዎች፣ በወረዳዎች አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የዞን አመራሮች እየተሰየሙና እየተመረጡ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል የብዙዎችን ትኩረት የሳበው አቢይ ዜና፣ ህውሃት ለክልሉ ላለፉት 30 ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውና በይዘቱ ግጭት ቀስቃሽ እንደነበር የሚነገረው የሕዝብ መዝሙር በአዲስ መልክ ሊቀየር መሆኑ መሰማቱ ነው።
እንደ መረጃው ከሆነ የመዝሙሩን ግጥም አስተካክሎና ዜማውን አሻሽሎ በአዲስ መልክ የማዘጋጀት ስራ መጀመሩ የተነገረ ሲሆን፣ ይህም ክልሉን ወደ አዲስ የሰላም፣ የእድገትና የመልካም አስተዳደር ምዕራፍ ለማሸጋገር እየተደረጉ ካሉ ዋና ዋና እርምጃዎች አንዱ እንደሆነ ተመልክቷል።
@Addis_Mereja | 6 880 |
| 16 | ትግራይ ፣ ሽሬ❗️
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ የሰላም ሃይል በመሆን ሽሬ ከተማን ተቆጣጥሯል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ የሰላም ሃይል በመሆን ሽሬ ከተማን የተቆጣጠረ ሲሆን ወደ ከተማው ሲገቡ በህዝቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!
@Addis_Mereja | 6 939 |
| 17 | ወደ መቐለ ጥቅምት 1 በረራ ይጀመራል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረው ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገው መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን አሳውቋል።
ክደንበኞቻችን በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በመሄድ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከሉ 6787 በመደወል የጉዞ ምዝገባ ማስያዝ እንደሚችሉ ገልጿል።
@Addis_Mereja | 6 541 |
| 18 | በመንግስትና በፋኖ ኃይሎች መካከል የተካሄደ ከባድ ውጊያ‼️
በአማራ ክልል በመንግሥት ወታደሮችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደዉ ውጊያ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ወረዳዎች (መሀል ሜዳ፣ ዘመሮ እና ሞላሌ)በደቡብ ወሎ ከለላ በመንግስትና በፋኖ ኃይሎች መካከል በተካሄደ ከባድ ውጊያ የፀጥታ አካላትን ጨምሮ የሰዎች ህይወት ማለፉንና በንፁሃን ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼቨለ ገለጹ።
ደቡብ ወሎ መካነ ሰላም ከተማ ትናንት ከተሰማ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በኋላ ዛሬ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩ ተጠቅሷል።
@Addis_Mereja | 6 245 |
| 19 | በውቅሮ ከተማ የተለያዩ ከባድ መሣሪያዎችና
ተተኳሾች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ
በውቅሮና አካባቢው ተከማችተው የነበሩ በርካታ ዓይነት መሣሪያዎችና ተተኳሾች በሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ። በቀረበው መረጃ መሠረት፣ ይህ የሆነው ከመቀሌ ወደ ዓዲግራት በሚወስደው መስመር የተካሄደውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው።
በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መሣሪያዎች መካከል 155 ሚሊ ሜትር፣ 130 ሚሊ ሜትር እና 122 ሚሊ ሜትር መድፎች፣ ቢኤም-21 ሮኬቶች፣ 100 ሚሊ ሜትር የታንክ መሣሪያዎች እና 37.5 ሚሊ ሜትር የአየር መቃወሚያ ጥይቶች ይገኙበታል።
በተጨማሪም ዙ-23 የአየር መቃወሚያ ጥይቶች፣ 12.7 ሚሊ ሜትር ድሽቃ ጥይቶች፣ 7.62 ሚሊ ሜትር ክላሽ ጥይቶች፣ የተለያዩ የእጅ ቦምቦች፣ ፀረ-ሰውና ፀረ-ተሽከርካሪ ፈንጂዎች እንዲሁም ቢ-10 ፀረ-ታንክ መሣሪያዎች በመከላከያ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። በቀረበው መረጃ መሠረት፣ 7.62 ሚሊ ሜትር ተተካይ ክላሽ እና ሌሎች የተለያዩ ቀላልና ከባድ መሣሪያዎችም ተይዘዋል።
@Addis_Mereja | 6 537 |
| 20 | ትግራይ ክልል አሁናዊ ትክክለኛ መረጃ‼️
በትግራይ ክልል በተለይ በሶስት አቅጣጫ ወጊያው ቀጥሏል።
📌ከመቀሌ-ሀገረ ሰላም-አብዪ አዲ(ተንቤን-አድዋ መስመር አንዱ የውጊያ መስመር ሲሆን በዚህ መስመር መከላከያ ሰራዊት የተንቤን ዋና ከተማ የሆነችውን አብዪ አዲን ተቆጣጥሯል፣አድዋ ከተማ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴ ቆሟል ብለዋል።
📌ከመቀሌ-ውቅሮ-ነጋሽ-አዲግራት-ዛላንበሳ---- ሌላኛው ውጊያ እየተደረገበት ያለ መስመር ሲሆን በዚህ የውጊያ መስመር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ መስከረም 28 ከሰዓት በኋላ ውቅሮን አልፎ ነጋሽ የምትባል ከተማን ተቆጣጥሯል።
በውቅሮ መከላከያ ሰራዊት ፓትሮል መጀመሩን የአዩዘሀበሻ ምንጮች በምስል አጋርተዋል።
📌ከማይፀብሪ-አዲ ገብሩ-እንዳ ባጉና-ሽሬ-አክሱም ---ሌላኛው የውጊያ መስመር ሲሆን የህወሓት ተዋጊዎች ከእንዳባጉና እና ሽሬ ለቀው ቢወጡም መከላከያ ሠራዊት ገና እንዳልገባ የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
📌አዲግራት በዛሬው ዕለት ተደጋጋሚ የጀት ድብደባ ተፈፅሟል፣ የደረሰው ጉዳት አልታወቀም።
@Addis_Mereja | 6 088 |
