الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
Ir al canal en Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
2 157
Suscriptores
-224 horas
+367 días
+41730 días
Archivo de publicaciones
🎀አይዞሽ እራሴ አንድቀን የቤት እመቤት ሆነሽ ከቤትሽ ሁነሽ እፎይ ትያለሽ ኢንሸአሏህ ትንሽ ብቻ صبر
🤍 ኢንሻ አሏህ! ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል! የትዕግሥት ፍሬዋ ጣፋጭ ነውና ትንሽ ትዕግሥት ብቻ አሁንም ታጠቂ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ሁሉ ድካም አልፎ በቤተሰብሽ መሀል በሰላም በድል እና በእፎይታ የምትቀመጪበት ቀን ይመጣል።إن شاءلله
🎀አይዞሽ እራሴ አንድቀን የቤት እመቤት ሆነሽ ከቤትሽ ሁነሽ እፎይ ትያለሽ ኢንሸአሏህ ትንሽ ብቻ صبر
🤍 ኢንሻ አሏህ! ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል! የትዕግሥት ፍሬዋ ጣፋጭ ነውና ትንሽ ትዕግሥት ብቻ አሁንም ታጠቂ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ሁሉ ድካም አልፎ በቤተሰብሽ መሀል በሰላም በድል እና በእፎይታ የምትቀመጪበት ቀን ይመጣል።إن شاءلله
+1
ወርቅ እና ሴቶች ያላቸው ትስስር ለምነው🫂?!✨ ወርቅ💎 ሴቶች ከወርቅ ጌጦች ጋር ያላቸው ፍቅር ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ከልባቸው ጋር የተሳሰረ ነው። ሴቶች ወርቅን የሚመርጡት አሏህ ችግርን አያስነካን እና ዛሬ ለውበት የሚለብሱት ጌጥ ነገ በችግር ጊዜ የሚደርስላቸው አስተማማኝ ሀብት ነው 🤝 በችግር ጊዜ የማይጥል ዋጋውን ጠብቆ የሚኖር የሀብት ማከማቻ ስለሆነ እንወድሀለን ወርቃችን
ሰበር ዜና ወርቅ ቀነሰ ብርያላቺሁ ግዙዛሬ ላይ የወርቅ ዋጋ ማሽቆለቆሉ ደግሞ ትልቅ ዕድል ነው!
Repost from 📌 قَنَاةُ النِّسَاءِ السَّلَفِيَّاتِ🎀
لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ
እረ ጎበዝ ህዝቡን እዳለ ተክፊር ሊያደርጉት ነው ሄዱ እኮ አላህ ቀልብ ይስጣቸዉ ሀቂቃ ሲነግሩ አቸዉ ቅናት ይመስላቸዋል የሚያሳዝኑ ወላጆቻችሁ ካፊር መባላቸው
አዳምጡት ጀዛኩሙላሁ ኸይራ በኡስታዝ አቡ ኢምራን ዑዙር ቢል ጀህል ክፍል 01) በሊንኩ ገብታቹህ በደንብ አዳምጡ በተለይ በአሏህ ያጋራ ሙሽሪክ ነው ለምትሉ ሰወችን ለማክፈር የምትሮጡ ስሙ መጀመሪያ አዳምጡ ተማሩ✅👇
https://t.me/abu_abdil_hayyi_channel/3053
አዕምሮህ ከፈቀደና ካመነበት ማንኛውንም ከባድ ፈተና ማለፍና ስኬትን ማግኘት ትችላለህ ማለት ነው። የስኬት መሰረቱ የአካል ጥንካሬ ሳይሆን የውስጥ እምነት ነው።
ሰውነታችን ወይም አካላዊ አቅማችን የሚገዛው ለአዕምሯችን ውሳኔ ነው። አዕምሮ "እችላለሁ" ብሎ ካመነ አካልም ያንን አቅም ያመነጫል።
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #ስድስት _⓺
✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ
.................. #እራቢያ ................
#ባለቤቱ_የሌለው_ስደት"
አፋሩ እራቢያን በጉልበት ሊወስዳት ሲሞክር፣ እኔ እጁን እንደያዝኩ በመካከላችን የቃላት ጦርነት ተፋፋመ። ደላላው በግርምት "ምንድነህ? ምንህ ናት?" ብሎ ሲጠይቅ፣ ያቺ ድፍረት የታደለች ልጅ በሰው ሁሉ ፊት "እወደዋለሁ! ከሱ መለዬት!"አልችልም፣ ብላ አውጃ እርፍ አለች። በዚያ በስደተኞች መዓት ፊት፣ በታዛቢዎችና በሥጋ ነጋዴዎች መሃል፣ እራቢያ ልክ እንደ ሕፃን ልጅ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።
ያቺ ቆንጆ ልጅ ለእኔ ብላ ስታለቅስ ስመለከት፣ የድንጋይ ልብ ቢኖረኝ እንኳ ሊቀልጥ ግድ ነበር። እንባዬ ከአይኔ ሞልቶ ፈሰሰ። በውስጤ እንዲህ አልኩ፦ ወይኔ የሙሐመድ ልጅ! በበረሃው ቃጠሎ አልተሸነፍክም ነበር፣ ዛሬ ግን በፍቅር ተንበረከክክ!"
ዓይናውጣነቴና "የአዋቂ አጥፊ" ማንነቴ አሸነፈኝና፣ አላህ ባልፈቀደልኝ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ፣ በዚያ ሁሉ ሰው ፊት ጥምጥም አድርጌ እቅፍ አደረኳት። ስሜቱ ልክ እንደ እሳት ውርር አደረገኝ።የቀራሁት ቂሪዓት አውቃለሁ ያልኩት ግን ያላከት ማንነቴ "ይህ ስህተት ነው" እያለ ቢወቅሰኝም፣ የሰውነት ስሜቴ ግን በእራቢያ እቅፍ ውስጥ ሰጥሞ ነበር። እንዲህ አልኩ፦
"ሕግና ስሜት - ልቤ ውስጥ ሲጋጩ፣
"ሐላልና ሐራም - ሆነው ሲፋተጉ፤
በበረሃው መሃል - እቅፍሽ ገደለኝ፣
የእምነት ዋልታዬን - ናጋው መሰለኝ።
አፋሮቹና በዙሪያችን የነበሩት ስደተኞች ሁሉ በትዕይንቱ አዘኑ። ደላላዬ ጠርቶ እንዲህ አለኝ፦ እዚህ ሦስት ቀን ትቆያላችሁ፤ እሷ ወደ ደላላዋ ትሂድና በሦስተኛው ቀን ትመለሳለች። ለሱማሌ ደላላ ስለምናስረክባችሁ እዚሁ ትገናኛላችሁ። አለኝ ይህ ቃል ለእኔ የትንሣኤ ያህል ነበር። "እራቢዬ ሂጂ፣ እንገናኛለን" አልኳት። እሷም ስልኬን ተቀብላ፣ አይኗ እንባ እያረገዘ መኪና ላይ ወጥታ ከአይኔ ተሰወረች።
እራቢያ ስትሄድ ግን፣ በረሃው በድንገት ባዶ ሆነብኝ። የሐዘን አገር ከበበኝ። ያቺ ኢትዮጵያ ውስጥ "አገባሻለሁ" ብዬ የቃል ኪዳን እስረኛ ያደረግኳት ልጅ ትዝታዋ በእራቢያ ምክኒያት ደብዝዞ ነበር፤ አሁን ግን በብቸኝነቱ ሰዓት መልሶ አገረሸብኝ።
ያ ሦስት ቀን.. ለኔ እንደ ሦስት ክፍለ ዘመን ረዘመብኝ። ፀሐዩ ሲወጣና ሲገባ፣ እኔ የምጠብቀው እራቢያን ብቻ ነበር። በሦስተኛው ቀን በዚያ በረሃ ላይ ከ600 በላይ ስደተኞች ተጠራቀሙ። አቧራው፣ ግርግሩና የሰው መዓት በሞላበት በዚያ ሜዳ ላይ አይኔ የራቢያን ጠረን ፍለጋ ይባዝን ነበር።
"ሦስት ቀን መከራ - ሦስት ቀን ሰቀቀን፣
የራቢያን ሽታ - ፍለጋ ስባዝን፤
ስድስት መቶ ነፍስ - ሜዳውን ቢሞላው፣
አይኔ ግን እሷን ነው - አሁንም ሚመኘው።"
የንፅህናው ድባብና የፍላጎት ማዕበል
በዚያ በስደተኞች መዓት መሃል፣ የናፍቆት ጥም የደረቀውን የራቢያን ልብ ፍለጋዋ እውን ሆነ። ጓደኞቿ በግርግር ውስጥ " የት ነው?" እያሉ ሲያጠያይቁ፣ እኔና እሷ በዓይን ተገናኘን። ያኔ... ዓለም በሰከንድ ውስጥ ቆመች። ራቢያ ልክ እንደ ንፋስ ተወርውራ መጥታ ደረቴ ላይ ስትለጠፍ፣ በሰውነቷ ሙቀትና በናፍቆት ድምጿ ውስጥ ተቀበርኩ።
ነገር ግን.. ያ ማቀፍ ብቻ ሆኖ አላበቃም። የሰው ልጅ ፍላጎት ልክ እንደ ሰደድ እሳት ነው፤ አንዴ ከተለኮሰ ድንበር አያውቅም። እራቢያ "ናፍቀኸኛል" እያለች በተቆራረጠ ትንፋሽ ከንፈሬን ስትስመኝ፣ የነፍሴ ዋልታ ተናጋ። በዚያ ሁሉ ሰው ፊት፣ በበረሃው አቧራ መሃል፣ እኔ.. ያ ከቤተሰቦቹ ጋር በእምነቱ ምክንያት የተለየው፣ ያ ከሼኹ ፊት ቁጭ ብሎ "ቃለ አላህ ቃለ ረሱል" እያለ ቁርኣን የሚያነበንበው የሱና ወጣት፣ዛሬ የመጨረሻ ዘቀጥኩ በማትገባኝ ሴት እቅፍ ውስጥ ወደቅኩ።
"በአንድ በኩል ቂርዓት - በአንድ በኩል ስሜት፣
መሃል ላይ ቆሜ - በፈተና ድርሰት፤
የከንፈርሽ ጣዕም - ቢመስልም ማሬ፣
ልቤ ግን ያለቅሳል - ስለ ኃጢአት ፍሬ።
ወይኔ የሙሐመድ ልጅ! በዚያች ሰከንድ ውስጥ አይኔ እንባ ያዝላል። "ልሙት ወይስ ልዳን?" ብዬ የምጠይቅበት፣ የእምነቴን ድንበር የጣስኩበት መራራ ወቅት ነበር። ራቢያ በውበቷ ልክ እንደ ጽጌረዳ አበባ ብታብብም፣ ለእኔ ግን ያ አበባ ውስጥ ያለው እሾህ ነፍሴን ይወጋት ነበር። ከእርሷ በኩል የሚመነጨው የሙቀት ስሜት ገላዬን ቢያቀልጠውም፣ ውስጤ ግን በታላቅ ፀጸት ይቃጠላል።
ውድ አንባቢያን ሆይ! እዚህ ጋር ልባችሁን ሰብሰብ አድርጉ። ይህንን የምነግራችሁ ስሜታችሁን ለመቀስቀስ ወይም "ጭምልቅናን" ለማውራት አይደለም። እኔ ራሴ "ዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ ምን አደረሰኝ?" ብዬ ራሴን የምታዘብበት የታሪኬ መራራ ገጽ ነው። ይህ ታሪክ የመጨረሻው ዓላማው ትልቅ ትምህርት መለገስ ነውና፣ በቅንነትና በትዕግሥት ተከተሉኝ።
የልጅነት ንፅህናዬ፣ የቀራሁት ዕውቀቴና ያሳለፍኩት መንፈሳዊ ሕይወቴ፣ በበረሃው ፈተና ውስጥ እንዴት እንደተፈተኑ ስታዩ፣ የሰው ልጅ ደካማነትና የአላህ ጥበቃ አስፈላጊነት ይገባችኋል። ታሪኩን መጨረሻውን ሳታዩ አትፍረዱ፤ የዚህ ጉዞ ማቆሚያ ሌላ ታሪክ አለው።
ያኔ... በዚያ በረሃ አቧራ መሃል፣ የራቢያ ከንፈሮች ከከንፈሮቼ ጋር ሲጋጠሙ፣ ነፍሴ በሁለት ተቃራኒ ዋልታዎች መሃል ትወዛወዝ ነበር። በአንድ በኩል የወጣትነት ስሜት እንደ ሰደድ እሳት ገላዬን ሲያቀልጠው፣ በሌላ በኩል ግን ያ የቀራሁት ዕውቀትና የተማርኩት ተውሂድ በሕሊናዬ ፊት ቆሞ ይሞግተኝ ነበር።
በዚያች ሰከንድ ውስጥ ታላላቅ የጥንት ገድሎች በአእምሮዬ መጋረጃ ላይ ብልጭ አሉ።
አዎን! ነቢዩሏህ ዩሱፍም (ዐለይሂ.አሰላም) እኮ ያኔ በቤተ መንግሥቱ ዝግ ጓዳ ውስጥ፣ ውቢቱ ዙሌይኻ "ሀይተ ለክ" (ና ወደ እኔ) ስትለው ወጣት ነበር። እርሱ ግን "መዓዘላህ" (አላህ ይጠብቀኝ) በማለት የንፅህናውን ካባ አጥብቆ ያዘ።
"መርየምም (ዐለይሃ አሰላም) በብቸኝነት ጎዳናዋ ውስጥ ያ ያማረ ወንድ (መላኢካ) ሆኖ ሲመጣላት፣ አላህን በመጥራት ራሷን ጠበቀች። የነቢዩ ኢብራሂም (ዐለይሂ.አሰላም) ባለቤት ሣራም፣ ያ ግፈኛ ንጉሥ እጁን ሊዘረጋባት ሲል፣ በዱዓው ኃይል አላህ ከለላ ሆናት።
እኔ ግን.. የነዚህን ጀግኖች ታሪክ የምደግመው፣ የሰለፎችን መንገድ የምከተል የምለው "የሙሐመድ ልጅ"፤ በዚያች ቅጽበት እንደነርሱ መሆንን ባለመቻል የሞት ሞትን ሞትኩኝ ። እነርሱ ለአላህ ብለው ስሜታቸውን ሲገቱ፣ እኔ ግን በራቢያ እቅፍ ውስጥ ሰጥሜ፣ የከንፈሯን ጥንብ ጣዕም ለመቅመስ ነፍሴን አረከስኩ። እንዲህ አልኩ፦
"ዩሱፍ በዝግ ጓዳ - አላህን ሲጣራ፣
እኔ ግን በሜዳ - ሰራሁት መከራ፤
መርየም የጸናችበት - ያ የእምነት ዋልታ፣
እኔ ዘንድ ዛሬ - ሆነብኝ ሽንፈታ።
የጥንቱ ጀግንነት - ታሪኩ ሲወራ፣
የኔ ግን ተጻፈ - በውርደት መዝገብ ላይ በበረሃው አጥራ።
ወይኔ ፀጸት! በዚያ ሁሉ ሰው ፊት እራቢያ ስትጥምብኝ፣ እኔም የስሜት እስረኛ ሆኜ ስንበረከክ፣ አይኔ እንባ ያዝላል። ውስጤ "አትበላሽ! አትጥፋ!" እያለ ቢጮኽም፣ የሰውነት ሙቀት ግን ሰጥሞኝ ነበር።
ውድ አንባቢያን ሆይ! ይህንን የምነግራችሁ የውድቀቴን ጥልቀት እንድትረዱ ነው። ሰው ዕውቀት ቢኖረውም አላህ ካልጠበቀው በስተቀር ምን ያህል አቅመ ቢስ እንደሆነ እንድታዩት ነው። ይህ የታሪኬ "ጥቁር ነጥብ" ወደፊት ለሚመጣው ትልቅ ለውጥ መነሻ ነውና፣ በትዕግሥት ተከተሉኝ።
የተራራው ግርማና የእራቢያ ቃል
የመጨረሻው ክፍል !!
Repost from N/a
🚨 ከታላቅ ቅናሽ ጋር! 🚨
🛍ማስተዋወቅ የሚፈልጉት ነገር አለ ?
⭕️ መልሶት አዎ ከሆነ ከእኛ ጋር በመስራት የፈለጉትን ማስታወቂያ አሪፍ በሆኑ ከ90 ቻናሎች በላይ በማስተዋወቅ ስኬታማ መሆን ይችላሉ ::
👇 ፈጥነው ያናግሩን 👐
አሁን ቀጥታ ስርጪት ቁረአን ተፍሲር ተጀምሯል ግቡ 👇👇
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris
ማን ልበለው??"👍#⃣#⃣
⬅⬅⬅⬅⬅⬅⬅
የሄደበትን የሰረዘ፣
የነገር ሸርን ያረገዘ፣
በዛ ካልከው በዚህ ገብቶ፣
ግራ አጋቢ ግራ ገብቶ፣
በሰው ጫንቃ ሰርቶ እውቅና፣
ተራ ሁኖ መሳይ ጀግና፣
ፈሪ ሁኖ የአፍ ጀግና፣
ወሬ ብቻ ለፍቶ መና።
በልቶ እረጋጭ፤
ቀምቶ ሰጭ፤
ሰብሮ ጠጋኝ፣
ጨክኖ አዛኝ፤
ማን ይመስልሀል ይሄ ሰው??፣
ስጠረጥርስ ማን አልከው?፣
ተሸፍኖ በውብ ልብሶች፣
ተመሳስሎ በደጋጎች፣
ሰብል መስሎ አንክርዳዲ፣
ዘሪ መስሎ የሚያጭዲ፣
እውነት ነቅሎ ውሸት ተካይ፣
ፋሲድ ሁኖ ሷሊህ መሳይ፣
ይህንን ሰው ማን ልበለው?፣
ስም ስጥልኝ የምታውቀው።
ደስ የሚለው ሲታጀብ፣
ግራ ቀኙን ሲከበብ፣
በሰው ደንደስ ሲወደስ፣
ያለ ድርሻው ስም ሲወርስ።
ጩኸት ቀሚ በጉልበት፣
ረግዶ ወዳጅ በሰው ቤት፣
የፈተለ የውሸት ለምድ፣
አለቃቅሶ የሚሸውድ፣
ክብር ፣የለው ለትልቅ፣
ደስ የሚለው መሳለቅ።
በለለው ላይ አለኝ ባይ፣
የሰው አውሬ ሰው መሳይ፣
ባልጠሩበት አቤት ባይ፣
የሰው እንባ የሚያነባ፣
የሚታወቅ በወከባ፣
አሊም የለ ከሱ በላይ፣
መስአላን ፈቶ የሚያይ፣
ሁሉን እኔ ልሁን የሚል፣
ነጋ ኡዙር የሚፈትል፣
መቶ አልቃሽ፣
ቀድሞ ከሳሽ፣
ከዚህ በላይ ስሙ ቀረኝ፣
እየገባህ አታሶራኝ።
ባድስ ፊክራ እግር ሰዶ
አበዱ አለ ለራሱ አብዶ
ማነው ካልከኝ ጦሳ ማዶ።
አይ ጦሳ ማዶ🖊
የረያን..............✍
https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1
አንዳድ ሰዎች ግን እሆነ ግሩፕ ቻይናል ላይ አድሚን ካልሆን አንቀመጥም መልካም ስራ አንሰራም አድሚን እሆንበት ብቻ ግሩፕ ላይ ነው ተሳትፎ አችን ይገርመኛል መልካም ስራ ለመስራት አድሚን መሆን ይጠበቅብን አይመስለኝም መስራት ካለብሽ ስሪ ለአላህ ብለሽ ለስልጣን ብለሽ አትስሪ ራስሽን አትሸዉጅ ሀቢብቲ በስህተት አድሚናችን ከተነሳ ሩጠን ሊፍት ምን ማለት ነው አይ ሚድያ የስራህን ይስጥህ
ወርቅ በቆሻሻ መሃል ቢቀመጥም ክብሩ አያንስም። አንቺም በስደት ዓለም ውስጥ ስላሉ ፈተናዎች ትልቅ ክብር አለሽ🌸። ነገር ግን ክብሩ የሚጠበቀው በምግባር ነው። እራስሽን በፋሽን እና በቪዲዮ መድረክ ላይ ማሳየት ለሰዎች መጫወቻ ያደርግሻል እንጂ ክብርሽን ከፍ አያደርገውም✅። ቆም በይ! ስደትሽ ወደጀነት የሚያመራሽ ሰበብ ይሁን እንጂ የዘላለም ፀፀት አይሁንብሽ
#ያረብ ከሚፀፀቱት እዳታደርገኝ
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አምስት_⓹ ፣
✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ
.................. #እራቢያ ................
#ባለቤቱ_የሌለው_ስደት"
ደላላው በተርታ ሲያሰልፈን፣ እኔ ሳላስበው ከፊት ስቆም ያሰማችው ጩኸት የሚሌን ምድር ቀወጠው። ደላላው በድንጋጤ "ምንድነሽ?" አላት። እራቢያ ግን ፈጣን ናት፤ "ወንድሜ ነው! ከእርሱ መለየት አልችልም!" ስትል በድፍረት መለሰች። ወደ እኔ መጥታ ከኋላዬ ተለጥፋ "አንተ ጨካኝ! ጥለኸኝ ልትሄድ?" ስትለኝ፣ ያች ቀበጥና ቆንጆ ልጅ በውስጤ ሌላ እሳት ለኮሰች።
እጇን ፊቴ ላይ ስታሳርፈው... ወንድነት በስሜት ማዕበል ተናወጠ። "ወንድ ልጅ ተበላ" ይሉሃል እንዲህ ነው። "ከአጠገቤ ከራቅክ አለቅህም" የሚለው ማስፈራሪያዋ፣ ፍቅርና ስጋት የቀላቀለ ጣፋጭ እስር ሆነብኝ።
ባጃጆቹ ያለ መብራት፣ እንደ ሌባ ቀስ እያሉ በከተማው ኮርቻ ላይ ሲንሸራተቱ፣ እኛ በዝምታ ተውጠን ነበር። ከከተማው ወጣ ብሎ በረሃው ሜዳ ላይ ሲያወርዱን፣ የሌሊቱ ብርድ እንደ ጩቤ ይወጋ ነበር። እራቢያ ግን የዛኔ ተቀየረች፤ ከእኔ ልትላቀቅ ያልፈለገች ይመስል አይን አይኔን እያየች ጥምጥም ትልብኝ ጀመር። መሳም እስኪቀራት ድረስ ደረቴ ላይ ተለጥፋ፣ በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የስደቱን መከራ አስረሳችኝ። እንዲህ አልኩ፦
"በረሃው በብርድ - ገላን ሲገርፈው፣
የራቢያ ትንፋሽ - መከራን አቀላው፤
በአንድ በኩል ጌታዬ - በአንድ በኩል ስሜት፣
ነፍሴ ተወጠረች - በፈተና ድርሰት።"
አቤት ያኔ የነበረው ግብግብ! ቤተሰቦቼ ትዝ ይሉኛል፤ ያቺ "አገባሻለሁ" ብዬ የተሰደድኩላት ልጅ ትዝ ትለኛለች። ነገር ግን እራቢያ "ምን እያሰብክ ነው?" ስትለኝ፣ ያቺን ቆንጆ ልጅ እያየሁ ሁሉንም እረሳለሁ። ስደት በራሱ ፈተና ሆኖ ሳለ፣ የ.(ኢሏሂን.) ትእዛዝ መተላለፍ ደግሞ ሌላ የነፍስ ስደት ሆነብኝ። "አዋቂ ነኝ" የምለው እኔ፣ በራቢያ እቅፍ ውስጥ ሆኜ አቅመ ቢስ ሆንኩ።
መኪናው (ሀይዙዚ) መጣ። ፍጥነቱ እንደ ንፋስ ነው፤ ድንበር ለመቁረጥ የሚደረግ እብድ ሩጫ። መኪናው በሜዳው ላይ ሲጋልብ፣ ሰው በሰው ላይ ይደራረባል፤ አቧራው ታፍኖን ድብልቅልቅ ብለናል። ያቺ አጅሬ እራቢያ ግን ይህንን አጋጣሚ ተመቻት። እኔን አጥብቃ ለመቅፍ ቀበጥነቷን ቀጠለች። በመኪናው ውስጥ ካሉት ሴቶች ሁሉ ውብ እሷ ነበረች። ሰው እንዳይጫናት፣ በእኔ ላይ ተለጥፋ በጩኸትና በድፍረት ቦታዋን ታስከብራለች።
በዚያ በአቧራ በታፈነ መኪና ውስጥ፣ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ድንበር ስንጋልብ... የሞት ጥላ ከላያችን፣ የራቢያ ሙቀት ከጎናችን ሆኖ የታሪክን ገጽ መጻፍ ቀጠልን........
የውኃ ልማት ፈተናና የልብ ስብራት
ሌሊቱ ነግቶ ጨለማው ለብርሃን ቦታውን ሲለቅ፣ "ውኃ ልማት" ወደሚባለው ቀዬ ደረስን። አፋሮቹ ብስኩትና ጁስ እያቀረቡ "የበረሃ መና" ይሸጣሉ። ያቺ ቆንጆ ልጅ እራቢያ፣ በቅልጥፍናዋ ቀድማ ገዝታ "እንብላ" ስትል አቀረበችልኝ። በዚያ ሜዳ ላይ ሆነን፣ መኪናው ውስጥ በለበስነው አቧራ ተቀብረን ሳለ፣ አፋሮቹ "ወንዝ አለና ታጠቡ" አሉ።
ወደ ወንዙ ወረድን። እራቢያ ልክ እንደ ወገን፣ እንደ እህት ሆና "ልብስህን አምጣ ልጠብልህ" አለችኝ። በዚያ የወንዝ ዳር ቆይታችን፣ ንግግሯ ልክ እንደ ወንዙ ፍሰት የለሰለሰ፣ ወሬዋ ከፎቹ ድምፅ ጋ ደግሞ እንደ ማር የጣፈጠ ነበር። እንዲህ አለችኝ፦ "ሳውዲ ስትገባ ቶሎ ማግባት ትፈልጋለህ?" እኔም "አዎ፣ የእናቴም ፍላጎት ነው" አልኳት። እሷ ግን በረዥሙ ተንፍሳ እንዲህ አለችኝ፦አልጠየኳትም እኮ "እኔ ቤተሰቦቼን ሳልለውጥ አላገባም፤ ግን... እንደ አንተ ያለ ዝምተኛ ካገኘሁ አላውቅም" ብላ በፈገግታ ተከለችብኝ።
ያኔ በውስጤ እንዲህ አልኩ፦
"ልብስን ማጠብ ለካስ - ለልብም ኖሯል፣
በንግግር ውበት - ነፍስ ትታለላለች፤
የወንዙ ጩኸትና - የራቢያ ወሬ፣
አስረሳኝ መሰለኝ - የነገውን ፍሬ።"
ነገር ግን... የሰለፊያ ወንድሞቼ ሆይ! ልብ በሉ። ስደት ገላን ብቻ ሳይሆን እምነትንም ይፈትናል። በዚያ መከራ ውስጥ ሆነህ፣ ለአላህ ብለህ የጀመርከው ጉዞ በስሜት አውሎ ንፋስ እንዳይጠለፍ መጠንቀቅ ትልቁ ጅሃድ ነው።
ልብሳችን ደርቆ ወደ አፋሮቹ ግቢ (ሀውሽ) ስንመለስ ግን፣ ያልጠበቅነው "የዱብዳ መብረቅ" ወረደ። ደላላዎቹ ተሰበሰቡ። የሥጋ ነጋዴዎቹ የሰውን ልጅ እንደ እቃ ሊከፋፈሉ ቆሙ። የኔና የእራቢያ ደላላ ተለየ። እሷን ሊወስዳት ሌላ አፋር መጣ። ያኔ ነበር ዓለም የጨለመችው።
እራቢያ "አልሄድም! እሱን ጥዬ አልሄድም!" ብላ በበረሃው ላይ ድምጿን አናወጠችው። ለካስ ያ ሁሉ መቀራረብ በልቧ ውስጥ ትልቅ ግንብ ሰርቶ ኖሯል። መኪናው ላይ "ውጪ!" ተብላ ስትታዘዝ፣ እምቢኝ አሻፈረኝ አለች። ደላላው አፋር ተቆጣ፤ "ምን ትመስላለች!" ብሎ በጥፊ ሊመታት እጁን ሲሰነዝር፣ ወንድነቴ አልቻለም። ወንድምነቴና ስሜቴ ተደባልቀው እጁን አጥብቄ ያዝኩት።
ግቢው ቀወጠው! አፋሩ "ለምን ይዘኸኛል?" ብሎ ጮኸ። እራቢያ ባለቀሰችበት፣ እኔ እጁን በያዝኩበትና ደላላው በዛተበት በዚያ ሰከንድ፣ የታሪካችን ክር ሊበጠስ ጫፍ ደረሰ።
"ደላላው ሲያደላ - ነፍስን ሊያገበያ፣
እራቢያ ጮኸች - ሆና መከፋፈያ፤
የእጅ ጥፊ ሲሰነዘር - እኔ መሀል ቆምኩኝ፣
የበረሃውን ቁጣ - ለብቻዬ ተጋፈጥኩኝ።"
የበረሃው ስንብትና የሦስት ቀን ስቃይ
ክፍል ⓺ ይቀጥላል....~
⤵️⤵️⤵️
