ar
Feedback
الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ

الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ

الذهاب إلى القناة على Telegram

​الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ ​እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
2 151
المشتركون
-224 ساعات
+367 أيام
+41730 أيام
أرشيف المشاركات
ቀጣይ ክፍል 7 ለይል ይለቀቃል ኢንሻአሏህ እዚህ የምታውቁትና የምትረዱት ነገር የተፃፈውን በሌላ እናተ በፈቀዳቺሁት ሀሳብ መልኩ ልትገነዘቡት አይደለም ይልቁንም እኛ አሁን በሀራም ግንኙነት ፍቅር ላይ ነን ወይስ በሀላሉ ብላቺሁ ራሳቺሁን ልትመለከቱ ነው ልትማሩበትም ጪምር ነው ጠይብ ያሳልፍኩትስ ግንኙነት እደት ነው ብላቺሁ ትክክለኛ ተውበትን ትክክለኛ መመለስን ልትመለሱ ዘንድ እጂ የተፃፈው ባለታሪኩ የሳለፈውን የሀራም ግንኙነቶችን እድትይዙና ስሜት እድትገቡ አይደለም አይ ያለ ሰው ከባለታሪኩ ጋራ ትረዳዱ ዘዳ በውስጥ ፃፉልኝ✅👍

ፈጥኖ የመለስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል ቁርአን ዉስጥ 124 ሱራ አለ ?

ፈጥኖ የመለስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል ቁርአን ዉስጥ 124 ሱራ አለ ?

🟠 አሁን ቀጥታ ስርጭት ቂራአት ~~ 📖 የቁርአን ተፍሲር   🎙 በኡስታዝ አቡ ሐኒፋ ሑሰይን ኢድሪስ ሰዒድ ሐፊዘሁሏህ ተ    ጀ       መ           ረ 👉 ሸር አድርጉት. ተቀላቀሉ አድም አድርጉ https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris?videochat=59dc0e0734fd48907f

+1
🎀አይዞሽ እራሴ  አንድቀን የቤት እመቤት ሆነሽ  ከቤትሽ ሁነሽ  እፎይ ትያለሽ ኢንሸአሏህ ትንሽ ብቻ صبر
🤍 ኢንሻ አሏህ! ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል! የትዕግሥት ፍሬዋ ጣፋጭ ነውና ትንሽ ትዕግሥት ብቻ አሁንም ታጠቂ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ሁሉ ድካም አልፎ በቤተሰብሽ መሀል በሰላም በድል እና በእፎይታ የምትቀመጪበት ቀን ይመጣል።
إن شاءلله

+1
🎀አይዞሽ እራሴ  አንድቀን የቤት እመቤት ሆነሽ  ከቤትሽ ሁነሽ  እፎይ ትያለሽ ኢንሸአሏህ ትንሽ ብቻ صبر
🤍 ኢንሻ አሏህ! ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል! የትዕግሥት ፍሬዋ ጣፋጭ ነውና ትንሽ ትዕግሥት ብቻ አሁንም ታጠቂ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ሁሉ ድካም አልፎ በቤተሰብሽ መሀል በሰላም በድል እና በእፎይታ የምትቀመጪበት ቀን ይመጣል።
إن شاءلله

ወርቅ እና ሴቶች ያላቸው ትስስር ለምነው🫂?! ✨ ወርቅ💎 ​ሴቶች ከወርቅ ጌጦች ጋር ያላቸው ፍቅር ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ከልባቸው ጋር የተሳሰረ ነው። ሴቶች ወርቅን የሚመርጡት አሏህ ችግርን
+1
ወርቅ እና ሴቶች ያላቸው ትስስር  ለምነው🫂?!
✨ ወርቅ💎 ​ሴቶች ከወርቅ ጌጦች ጋር ያላቸው ፍቅር ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር  ከልባቸው ጋር የተሳሰረ ነው። ሴቶች ወርቅን የሚመርጡት አሏህ ችግርን አያስነካን እና ዛሬ ለውበት የሚለብሱት ጌጥ  ነገ በችግር ጊዜ የሚደርስላቸው አስተማማኝ ሀብት ነው  🤝 በችግር ጊዜ የማይጥል ዋጋውን ጠብቆ የሚኖር የሀብት ማከማቻ ስለሆነ  እንወድሀለን ወርቃችን
ሰበር ዜና  ወርቅ ቀነሰ ብርያላቺሁ ግዙ
ዛሬ ላይ የወርቅ ዋጋ ማሽቆለቆሉ ደግሞ ትልቅ ዕድል ነው!

لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ እረ ጎበዝ ህዝቡን እዳለ ተክፊር ሊያደርጉት ነው ሄዱ እኮ አላህ ቀልብ ይስጣቸዉ ሀቂቃ ሲነግሩ አቸዉ ቅናት ይመስላቸዋል የሚያሳዝኑ
لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ እረ ጎበዝ ህዝቡን እዳለ ተክፊር ሊያደርጉት ነው ሄዱ እኮ አላህ ቀልብ ይስጣቸዉ ሀቂቃ ሲነግሩ አቸዉ ቅናት ይመስላቸዋል የሚያሳዝኑ ወላጆቻችሁ ካፊር መባላቸው

አዳምጡት ጀዛኩሙላሁ ኸይራ   በኡስታዝ አቡ ኢምራን ዑዙር ቢል ጀህል ክፍል 01)    በሊንኩ ገብታቹህ  በደንብ አዳምጡ     በተለይ   በአሏህ ያጋራ ሙሽሪክ ነው  ለምትሉ   ሰወችን ለማክፈር የምትሮጡ ስሙ መጀመሪያ  አዳምጡ ተማሩ✅👇 https://t.me/abu_abdil_hayyi_channel/3053

አዕምሮህ ከፈቀደና ካመነበት ማንኛውንም ከባድ ፈተና ማለፍና ስኬትን ማግኘት ትችላለህ ማለት ነው። የስኬት መሰረቱ የአካል ጥንካሬ ሳይሆን የውስጥ እምነት ነው። ሰውነታችን ወይም አካላዊ አቅማችን የሚ
አዕምሮህ ከፈቀደና ካመነበት ማንኛውንም ከባድ ፈተና ማለፍና ስኬትን ማግኘት ትችላለህ ማለት ነው። የስኬት መሰረቱ የአካል ጥንካሬ ሳይሆን  የውስጥ እምነት ነው። ሰውነታችን ወይም አካላዊ አቅማችን የሚገዛው ለአዕምሯችን ውሳኔ ነው። አዕምሮ "እችላለሁ" ብሎ ካመነ አካልም ያንን አቅም ያመነጫል።

               ክፍል ⓻ ይቀጥላል

🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺   #የታሪኩ_ርዕስ #በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"       #ክፍል_☞ #ስድስት _⓺ ✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ .................. #እራቢያ ................ #ባለቤቱ_የሌለው_ስደት" አፋሩ እራቢያን በጉልበት ሊወስዳት ሲሞክር፣ እኔ እጁን እንደያዝኩ በመካከላችን የቃላት ጦርነት ተፋፋመ። ደላላው በግርምት "ምንድነህ? ምንህ ናት?" ብሎ ሲጠይቅ፣ ያቺ ድፍረት የታደለች ልጅ በሰው ሁሉ ፊት "እወደዋለሁ! ከሱ መለዬት!"አልችልም፣ ብላ አውጃ እርፍ አለች። በዚያ በስደተኞች መዓት ፊት፣ በታዛቢዎችና በሥጋ ነጋዴዎች መሃል፣ እራቢያ ልክ እንደ ሕፃን ልጅ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ያቺ ቆንጆ ልጅ ለእኔ ብላ ስታለቅስ ስመለከት፣ የድንጋይ ልብ ቢኖረኝ እንኳ ሊቀልጥ ግድ ነበር። እንባዬ ከአይኔ ሞልቶ ፈሰሰ። በውስጤ እንዲህ አልኩ፦ ወይኔ የሙሐመድ ልጅ! በበረሃው ቃጠሎ አልተሸነፍክም ነበር፣ ዛሬ ግን በፍቅር ተንበረከክክ!" ዓይናውጣነቴና "የአዋቂ አጥፊ" ማንነቴ አሸነፈኝና፣ አላህ ባልፈቀደልኝ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ፣ በዚያ ሁሉ ሰው ፊት ጥምጥም አድርጌ እቅፍ አደረኳት። ስሜቱ ልክ እንደ እሳት ውርር አደረገኝ።የቀራሁት ቂሪዓት አውቃለሁ ያልኩት ግን ያላከት  ማንነቴ "ይህ ስህተት ነው" እያለ ቢወቅሰኝም፣ የሰውነት ስሜቴ ግን በእራቢያ እቅፍ ውስጥ ሰጥሞ ነበር። እንዲህ አልኩ፦ "ሕግና ስሜት - ልቤ ውስጥ ሲጋጩ፣ "ሐላልና ሐራም - ሆነው ሲፋተጉ፤ በበረሃው መሃል - እቅፍሽ ገደለኝ፣ የእምነት ዋልታዬን - ናጋው መሰለኝ። አፋሮቹና በዙሪያችን የነበሩት ስደተኞች ሁሉ በትዕይንቱ አዘኑ። ደላላዬ ጠርቶ እንዲህ አለኝ፦ እዚህ ሦስት ቀን ትቆያላችሁ፤ እሷ ወደ ደላላዋ ትሂድና በሦስተኛው ቀን ትመለሳለች። ለሱማሌ ደላላ ስለምናስረክባችሁ እዚሁ ትገናኛላችሁ። አለኝ ይህ ቃል ለእኔ የትንሣኤ ያህል ነበር። "እራቢዬ ሂጂ፣ እንገናኛለን" አልኳት። እሷም ስልኬን ተቀብላ፣ አይኗ እንባ እያረገዘ መኪና ላይ ወጥታ ከአይኔ ተሰወረች። እራቢያ ስትሄድ ግን፣ በረሃው በድንገት ባዶ ሆነብኝ። የሐዘን አገር ከበበኝ። ያቺ ኢትዮጵያ ውስጥ "አገባሻለሁ" ብዬ የቃል ኪዳን እስረኛ ያደረግኳት ልጅ ትዝታዋ በእራቢያ ምክኒያት ደብዝዞ ነበር፤ አሁን ግን በብቸኝነቱ ሰዓት መልሶ አገረሸብኝ። ያ ሦስት ቀን.. ለኔ እንደ ሦስት ክፍለ ዘመን ረዘመብኝ። ፀሐዩ ሲወጣና ሲገባ፣ እኔ የምጠብቀው እራቢያን ብቻ ነበር። በሦስተኛው ቀን በዚያ በረሃ ላይ ከ600 በላይ ስደተኞች ተጠራቀሙ። አቧራው፣ ግርግሩና የሰው መዓት በሞላበት በዚያ ሜዳ ላይ አይኔ የራቢያን ጠረን ፍለጋ ይባዝን ነበር። "ሦስት ቀን መከራ - ሦስት ቀን ሰቀቀን፣ የራቢያን ሽታ - ፍለጋ ስባዝን፤ ስድስት መቶ ነፍስ - ሜዳውን ቢሞላው፣ አይኔ ግን እሷን ነው - አሁንም ሚመኘው።" የንፅህናው ድባብና የፍላጎት ማዕበል በዚያ በስደተኞች መዓት መሃል፣ የናፍቆት ጥም የደረቀውን የራቢያን ልብ ፍለጋዋ እውን ሆነ። ጓደኞቿ በግርግር ውስጥ " የት ነው?" እያሉ ሲያጠያይቁ፣ እኔና እሷ በዓይን ተገናኘን። ያኔ... ዓለም በሰከንድ ውስጥ ቆመች። ራቢያ ልክ እንደ ንፋስ ተወርውራ መጥታ ደረቴ ላይ ስትለጠፍ፣ በሰውነቷ ሙቀትና በናፍቆት ድምጿ ውስጥ ተቀበርኩ። ነገር ግን.. ያ ማቀፍ ብቻ ሆኖ አላበቃም። የሰው ልጅ ፍላጎት ልክ እንደ ሰደድ እሳት ነው፤ አንዴ ከተለኮሰ ድንበር አያውቅም። እራቢያ "ናፍቀኸኛል" እያለች በተቆራረጠ ትንፋሽ ከንፈሬን ስትስመኝ፣ የነፍሴ ዋልታ ተናጋ። በዚያ ሁሉ ሰው ፊት፣ በበረሃው አቧራ መሃል፣ እኔ.. ያ ከቤተሰቦቹ ጋር በእምነቱ ምክንያት የተለየው፣ ያ ከሼኹ ፊት ቁጭ ብሎ "ቃለ አላህ ቃለ ረሱል" እያለ ቁርኣን የሚያነበንበው የሱና ወጣት፣ዛሬ የመጨረሻ ዘቀጥኩ በማትገባኝ ሴት እቅፍ ውስጥ ወደቅኩ። "በአንድ በኩል ቂርዓት - በአንድ በኩል ስሜት፣ መሃል ላይ ቆሜ - በፈተና ድርሰት፤ የከንፈርሽ ጣዕም - ቢመስልም ማሬ፣ ልቤ ግን ያለቅሳል - ስለ ኃጢአት ፍሬ። ወይኔ የሙሐመድ ልጅ! በዚያች ሰከንድ ውስጥ አይኔ እንባ ያዝላል። "ልሙት ወይስ ልዳን?" ብዬ የምጠይቅበት፣ የእምነቴን ድንበር የጣስኩበት መራራ ወቅት ነበር። ራቢያ በውበቷ ልክ እንደ ጽጌረዳ አበባ ብታብብም፣ ለእኔ ግን ያ አበባ ውስጥ ያለው እሾህ ነፍሴን ይወጋት ነበር። ከእርሷ በኩል የሚመነጨው የሙቀት ስሜት ገላዬን ቢያቀልጠውም፣ ውስጤ ግን በታላቅ ፀጸት ይቃጠላል። ውድ አንባቢያን ሆይ! እዚህ ጋር ልባችሁን ሰብሰብ አድርጉ። ይህንን የምነግራችሁ ስሜታችሁን ለመቀስቀስ ወይም "ጭምልቅናን" ለማውራት አይደለም። እኔ ራሴ "ዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ ምን አደረሰኝ?" ብዬ ራሴን የምታዘብበት የታሪኬ መራራ ገጽ ነው። ይህ ታሪክ የመጨረሻው ዓላማው ትልቅ ትምህርት መለገስ ነውና፣ በቅንነትና በትዕግሥት ተከተሉኝ። የልጅነት ንፅህናዬ፣ የቀራሁት ዕውቀቴና ያሳለፍኩት መንፈሳዊ ሕይወቴ፣ በበረሃው ፈተና ውስጥ እንዴት እንደተፈተኑ ስታዩ፣ የሰው ልጅ ደካማነትና የአላህ ጥበቃ አስፈላጊነት ይገባችኋል። ታሪኩን መጨረሻውን ሳታዩ አትፍረዱ፤ የዚህ ጉዞ ማቆሚያ ሌላ ታሪክ አለው። ያኔ... በዚያ በረሃ አቧራ መሃል፣ የራቢያ ከንፈሮች ከከንፈሮቼ ጋር ሲጋጠሙ፣ ነፍሴ በሁለት ተቃራኒ ዋልታዎች መሃል ትወዛወዝ ነበር። በአንድ በኩል የወጣትነት ስሜት እንደ ሰደድ እሳት ገላዬን ሲያቀልጠው፣ በሌላ በኩል ግን ያ የቀራሁት ዕውቀትና የተማርኩት ተውሂድ በሕሊናዬ ፊት ቆሞ ይሞግተኝ ነበር። በዚያች ሰከንድ ውስጥ ታላላቅ የጥንት ገድሎች በአእምሮዬ መጋረጃ ላይ ብልጭ አሉ። አዎን! ነቢዩሏህ ዩሱፍም (ዐለይሂ.አሰላም) እኮ ያኔ በቤተ መንግሥቱ ዝግ ጓዳ ውስጥ፣ ውቢቱ ዙሌይኻ "ሀይተ ለክ" (ና ወደ እኔ) ስትለው ወጣት ነበር። እርሱ ግን "መዓዘላህ" (አላህ ይጠብቀኝ) በማለት የንፅህናውን ካባ አጥብቆ ያዘ። "መርየምም (ዐለይሃ አሰላም) በብቸኝነት ጎዳናዋ ውስጥ ያ ያማረ ወንድ (መላኢካ) ሆኖ ሲመጣላት፣ አላህን በመጥራት ራሷን ጠበቀች። የነቢዩ ኢብራሂም (ዐለይሂ.አሰላም) ባለቤት ሣራም፣ ያ ግፈኛ ንጉሥ እጁን ሊዘረጋባት ሲል፣ በዱዓው ኃይል አላህ ከለላ ሆናት። እኔ ግን.. የነዚህን ጀግኖች ታሪክ የምደግመው፣ የሰለፎችን መንገድ የምከተል የምለው "የሙሐመድ ልጅ"፤ በዚያች ቅጽበት እንደነርሱ መሆንን ባለመቻል የሞት ሞትን ሞትኩኝ ። እነርሱ ለአላህ ብለው ስሜታቸውን ሲገቱ፣ እኔ ግን በራቢያ እቅፍ ውስጥ ሰጥሜ፣ የከንፈሯን ጥንብ ጣዕም ለመቅመስ ነፍሴን አረከስኩ። እንዲህ አልኩ፦ "ዩሱፍ በዝግ ጓዳ - አላህን ሲጣራ፣ እኔ ግን በሜዳ - ሰራሁት መከራ፤ መርየም የጸናችበት - ያ የእምነት ዋልታ፣ እኔ ዘንድ ዛሬ - ሆነብኝ ሽንፈታ። የጥንቱ ጀግንነት - ታሪኩ ሲወራ፣ የኔ ግን ተጻፈ - በውርደት መዝገብ ላይ በበረሃው አጥራ። ወይኔ ፀጸት! በዚያ ሁሉ ሰው ፊት እራቢያ ስትጥምብኝ፣ እኔም የስሜት እስረኛ ሆኜ ስንበረከክ፣ አይኔ እንባ ያዝላል። ውስጤ "አትበላሽ! አትጥፋ!" እያለ ቢጮኽም፣ የሰውነት ሙቀት ግን ሰጥሞኝ ነበር። ውድ አንባቢያን ሆይ! ይህንን የምነግራችሁ የውድቀቴን ጥልቀት እንድትረዱ ነው። ሰው ዕውቀት ቢኖረውም አላህ ካልጠበቀው በስተቀር ምን ያህል አቅመ ቢስ እንደሆነ እንድታዩት ነው። ይህ የታሪኬ "ጥቁር ነጥብ" ወደፊት ለሚመጣው ትልቅ ለውጥ መነሻ ነውና፣ በትዕግሥት ተከተሉኝ። የተራራው ግርማና የእራቢያ ቃል

አል መስአለቱ አ ል ዑ ዝ ር ቢል ጀህል  👇👇👇

Repost from N/a
🚨 ከታላቅ ቅናሽ ጋር! 🚨 🛍ማስተዋወቅ የሚፈልጉት ነገር አለ ? ⭕️ መልሶት አዎ ከሆነ ከእኛ ጋር በመስራት የፈለጉትን ማስታወቂያ አሪፍ በሆኑ ከ90 ቻናሎች በላይ በማስተዋወቅ ስኬታማ መሆን ይችላሉ :: 👇 ፈጥነው ያናግሩን 👐

አሁን ቀጥታ ስርጪት ቁረአን ተፍሲር   ተጀምሯል ግቡ 👇👇 https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris