Abu Hayder Aliy
Ir al canal en Telegram
نشرالكتاب والسنة وقول العلمآء بائذن الله الباري بأبي حيدر علي إبن سليمان إبن أحمد الولغاوي
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
570
Suscriptores
+1324 horas
+267 días
+6030 días
Archivo de publicaciones
ኢብራሒም_ኢብኑ_አድሀም ረሒመሁሏህ እንዲህ ብለዋል : -
«እረፍትን የፈለገ ፍጡራንን ከቀልቡ ያውጣ የዛኔ ያርፋል።»
📚 ۞【سيــر السلـف الصالــح【477】۞
Repost from ስለ ቀልባችን
👁🗨የኪታብ PDF
اِنْتَبِهْ أَنْتَ مُرَاقَبْ!!
🪶ኢንተቢህ_አንተ_ሙራቀብ
https://t.me/Sle_qelbachn1/1964
Repost from ስለ ቀልባችን
🎙ቀጥታ ስርጭት ተጀመረ!
● ወንጀል ላደከማት ነፍስ!
https://t.me/Sle_qelbachn1?livestream=1ae6e66a0eee342f69
Repost from ስለ ቀልባችን
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
መውሊድ - በፉክክር የተጀመረ በዓል ነው!
~
መውሊድ ቀደምት የኢስላም ትውልዶች ዘንድ የማይታወቅ መጤ ፈጠራ መሆኑን ራሳቸው የመውሊድ አክባሪ የሆኑ አካላት የመሰከሩትን አሳልፌያለሁ። እነዚሁ አካላት መውሊድ ከክርስቲያኖቹ ገና ተኮርጆ በፉክክር እንደሚከበር የተናገሩቱን ደግሞ እናያለን። ዘግይተው የመጡ አንዳንድ ሱፍዮች ግን “መውሊድ በሀይማኖታችን መረጃዎች መሰረት የተፈቀደ በመሆኑ ላይ ከተግባባን ከክርስቲያን ወይም ከሂንዱ እምነት ጋር ባጋጣሚ ተመሳስሎ ቢገኝ ችግር የለውም” ይላሉ። በሀይማኖታችን መሰረት ቢኖረውማ እነ ኢብኑ ሐጀር “የመውሊድ ተግባር መሰረቱ ቢድዐ ነው። በሶስቱ ክፍለ ዘመናት ከነበሩት መልካም ቀደምቶች ከአንድም አልተላለፈም” አይሉም ነበር።
እያከበሩ ያሉት ሌላ መልክ ያለው ገና ነው። ገና (chrismas) ማለት ልደት ማለት ነው። ልደት ማለት ደግሞ በዐረብኛው መውሊድ ማለት ነው። ስለዚህ የሚከበረው ማንነት እንጂ የተለየው የሚያከብሩት ገናን ነው።
የክርስቲያኖች ገና = የሱፍዮች መውሊድ!
የክርስቲያኖች መውሊድ = የሱፍዮች ገና!
እንዲያውም መውሊድን የሚያከብሩት ከክርስቲያኖች ጋር ለመፎካከር ብለው ነው። የፉክክር ዒባዳ ማለት ነው! ይህንን ሐቅ በኪታብ ሳይቀር ያሰፈሩት አሉ። መረጃ እጠቅሳለሁ፡-
1. አስ-ሰኻዊይ ምን እንደሚል ተመልከቱ፡- “ባለ መስቀሎቹ (ክርስቲያኖች) የነብያቸውን ልደት ትልቁ ዒዳቸው አድርገው የሚይዙ ከሆነ ሙስሊሞችም (ነብያቸውን) በማክበርና በማላቅ ይበልጥ የተገቡ ናቸው።” [አት-ቲብሩል መስቡክ፡ 14]
2. ከጀዘሪም ቃል በቃል ተላልፏል።
3. አቡል ዐባስ አል-አዘፊይ (መውሊድን ለምዕራቡ ዐረቢያ ያስተዋወቀ ነው)፡- በክርስቲያን በዓላት ላይ የሚሳተፉ ወጣቶችን ለመመለስ ሲል እንደጀመረው በግልፅ ተናግሯል።
4. ዐብዱላህ አልሀረሪይ (የአሕባሾቹ መሪ):- ንጉስ ሙዞፈር መውሊድን የጀመረው ክርስቲያኖች የመሲሕ ልደትን በዓል ሲያከብሩ ተመልክቶ ነው። በዚህም ሳቢያ ሰይዳችንን ሙሐመድን ﷺ ስላወጣልን አላህን ለማመስገን ሲል መውሊድን ጀመረ ይላል። [ኢዝሃሩል ዐቂደቲ ሱንኒያህ፡ 240]
ስለዚህ የመውሊድ ቢድዐን በፉክክር የተለከፉ ሰዎች የፈጠሩት መጤ ፈሊጥ ነው ማለት ነው። በዚህ መልኩ በሌሎች መመሳሰል ደግሞ የተወገዘ እንደሆነ ነብያችን ﷺ አጥብቀው አሳስበዋል።
* ማስረጃ አንድ፦
مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ
"አንድን ሕዝብ የተመሳሰለ (የተከተለ) ከእነርሱ ነው (እንደነርሱ ይቆጠራል)።" [አቡ ዳውድ ፡ 4031]
* ማስረጃ ሁለት፦
በሌላም ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لتتَّبعنَّ سَننَ من كانَ قبلَكم حذو القُذَّةِ بالقُذَّةِ حتَّى لو دخلوا جحرَ ضبٍّ لدخلتُموه. قالوا: اليَهودُ والنَّصارى؟ قالَ: فمَن
“በርግጥ ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለጎች ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የወከሎ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን በርግጥም ትገቡታላችሁ!” ሲሉ “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው (ትከተላላችሁ) የምትለን?” ብለው ቢጠይቁ “ታዲያ ማንን ነው?!” አሉ። [ቡኻሪይ፡ 7320]
የተናገሩት በትክክል ተፈፀመ። ለብዙ ጥፋቶች የሚያጋልጠው በዓል ከክርስቲያኖች ተኮርጆ በ"ፋጢሚያ" ሺዐዎች ተጠንስሶ፣ በሱፍዮች ተዛምቶ ብዙ ሙስሊም ሊዘፈቅበት በቅቷል።
የሚያሳፍረው “ክርስቲያኖቹ የነብያቸውን ልደት እያከበሩ የኛ ነብይ ከማን ያንሳሉ?” የሚሉት ነገር ነው። ሱብሓነላህ! ለመሆኑ ዒሳ የኢስላም ነብይ አይደሉም እንዴ?! ታዲያ ይሄ ምን የሚሉት አፀያፊ ሎጂክ ነው? ደግሞ ምንም ሳያፍሩ መውሊድን የሚቃወሙ ሙስሊሞችን “የነቢ ጠላቶች ናቸው!” እያሉ ከባድ ክስ ይከሳሉ። የነብዩን ﷺ መውሊድ አለማክበር እሳቸውን መጥላት ከሆነ እናንተም የክርስቲያኖቹን ገና (chrismasን) ባለማክበራችሁ የዒሳ ጠላቶች ናችሁ ማለት ነው። መውሊድን ማክበር ነብዩን ﷺ ማክበር ከሆነ የሌሎቹን ነብያት ልደቶች ስለማታከብሩ ለሌሎች ነብያት በሙሉ ክብር የሌላችሁ የነብያት ጠላቶች ናችሁ ማለት ነው። ከአንደበታችሁ በቀጥታ ባይወጣም አመክኗችሁ የሚሰጠው ይህንን ነው።
አንዳንዶች "ገናን የማናከብረው የዒሳን ልደት ስለማናውቅ ነው" ይላሉ። የነብያችንም ﷺ የውልደት በየትኛው የረቢዕ ቀን ላይ እንደሆነ የሚያሳይ ሶሒሕ ማስረጃ የለም። በ12ኛው ቀን ነው የሚለው የሰነድ መቆረጥ እንዳለበት ኢብኑ ከሢር ገልፀዋል። [አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 3/109]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ኢብኑ_ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
«ንግግርህ ኸይር ነገር ከሆነ እንጅ ላላመናገር ሞክር። ይህን ማድረግህ ኢማንህን ያጠነክርልሀል፣ ምላስህን ይጠብቅልሀል፣ ወንድሞችህ ዘንድም ክብር ነው።»
📚 ۞ شرح أربعين النووي【1/215】۞
https://t.me/abu_hayder_aliy
https://t.me/abu_hayder_aliy
Repost from N/a
⭕️ይህ መልዕክት ለሱና ቻናል ባለቤቶች ⭕️
➲ ቻናላችሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ በአዲስ መልክ ጀምረናል
🛑በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 📥
➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች
ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች
ላላቸው
⚡️ የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ
👉 @Quran_mylife1
✨ አዲስ ብስራት ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ! ✨
በኢስላማዊ እውቀት ህይወትዎን ማሳመር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ «ኢብኑ ዐብባስ» Online መድረሳ በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቅዎታል።
📚 የምንጀምረው ትምህርት፦
«ኹዝ ዐቂደተክ» (كتاب خذ عقيدتك من الكتاب والسنة)
🎙 ትምህርቱ የሚሰጠዉ :-
በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ"
📌 ለመመዝገብና በቂ መረጃዎችን ለማግኘት፦
🔰 ለወንዶች፦ @Yufa4
🔰 ለሴቶች፦ @bint_Adem15
🔰 @Riiche1
🔰 «እውቀትን መፈለግ በምእመናን ላይ ግዴታ ነው!»
የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ፤ ለወዳጅ ዘመድዎም ያጋሩት!
🛍️ «ቲጃራህ ኦንላይን የገበያ ማዕከል» በሰላም መጡ! 🛍️
(Tijarah Online Shopping Center)
ታማኝነትን ከጥራት ጋር አጣጥመን፣ የሚፈልጉትን ማንኛውንም ዕቃ ባሉበት ሆነው በተጣጣመ ዋጋ የሚያገኙበት ታማኝ የኦንላይን ገበያዎ!
✨ እኛ ዘንድ የሚገኙ እቃዎች እና አገልግሎቶች፦
👗 ዘመናዊ አልባሳት — ለሴቶች፣ ለወንዶች እና ለልጆች
📱 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች — ስልኮች፣ የቤት ውስጥ ኤሌክትሮኒክስ እና መለዋወጫዎች
🛋️ አረቢያን መጅሊሶች — ለቤትዎ ውበት እና ምቾት የሚሆኑ
🍽️ የወጥ ቤት ዕቃዎች — ዘመናዊ እና ጥራት ያላቸው የኩሽና እቃዎች
🛏️ ምቹ የቤት ዕቃዎች — ጥራት ያላቸው ብርድልብሶች፣ ኮምፎርተሮች እና ፍራሾች
🛒 የቤት አስቤዛ — ትኩስ እና ጥራት ያላቸው የምግብ እቃዎች
📖 ኢስላማዊ መጻሕፍት — ቅዱስ ቁርአን እና የተለያዩ ጠቃሚ ኪታቦች
📍 አድራሻችን፦ ኮምቦልቻ
🚚 ማስታወሻ፦ በወሎ ውስጥ በማንኛውም ቦታ ባሉበት ያሉበት ቦታ ድረስ በፍጥነት እናደርሳለን!
📞 ለማዘዝ እና ለበለጠ መረጃ፦
📱 ስልክ፦ 0912899894
💬 በቴሌግራም ለማዘዝ፦ @Abu_Meymuna_Al_Asseriy
👇 አሁኑኑ ግሩፓችንን ይቀላቀሉ፣ ለወዳጅ ዘመድዎም ያጋሩ!
🔗 የቴሌግራም ሊንክ፦ https://t.me/Tijarah_Online_shopping_center
«ቲጃራህ — የታማኝነት እና የጥራት መገለጫ!»
Repost from N/a
🔒ጥያቄ ❔
በሱረቱ አል-ከህፍ ውስጥ የተጠቀሰዉ
የአስሃቡል ከህፍ ታሪክ ብቻ ነው ?
⚡️የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ 👉 @Quran_mylife1
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (45)
ለኸጢቦች እና ለዱዓቶች
~
የደዕዋ እና የኹጥባ መድረክ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መድረክ ነው። የማህበረሰብን ንቃተ ህሊና ለመቀየር፣ ዲኑን ለማስተማር፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለማንቃት እጅግ የላቀ ቦታ ነው። ግን እንደሚገባ እየተጠቀምነው ነው ወይ? መድረኩ ነብያዊ አማና ነውና አማናውን እየተወጣን ነው ወይ? ለመድረኩ የሚመጥን አቅምና ዝግጅትስ አለን ወይ? ሐቅን ለመናገር፣ ማህበረሰብን ለመጠበቅ የሰዎችን ስሜትና ፍላጎታቸውን ተከትለን ነው የምንፈሰው ወይስ አላህን በማሰብ፣ ለሐቅ በመቆርቆር፣ ዘላቂ ጥቅምን በማስቀደም በጀግንነት እንጓዛለን? ኃላፊነትን ባለመወጣት ከመጠየቃችን በፊት ከራሳችን ጋር ሂሳብ እንስራ።
1. ወደ ህዝብ ከመቅረባችን በፊት በቂ ዝግጅት እናድርግ፣ አቅማችንን እናዳብር። ሳይዘጋጁ መቅረብ ታዳሚን መናቅ ነው። ቦታውንም ክብር ማሳጣት ነው።
2. መሰረታዊ የኢስላም ርእሶችን ቅድሚያ እንስጥ። አርካኑል ኢማን፣ አርካኑል ኢስላም፣ ተውሒድና ሺርክ፣ ሱናና ቢድዐ፣ ከባኢረ ዙኑብ፣ ስነ ምግባር፣ ኢስላማዊ ቤተሰብ፣ እንደ ኡማ ሊኖረን የሚገባ መተዛዘንና መደጋገፍ፣ ዘረኝነት፣ እንደ ጫትና ሲጋራ ያሉ ጎጂ ሱሶች፣ ወዘተ. የህዝብን ቁጣና ኩርፊያ ሳንፈራ ግን ደግሞ ባማረና በማያስበረግግ መልኩ ደጋግመን እናስተምር።
3. ርእስ መረጣ ላይ የሰዎችን ስሜትና ፍላጎት እየተከተልን አንፍሰስ። ትኩረታችን የሚጠቅማቸውን መስጠት ይሁን። ደዕዋ ሰው መለወጫ እንጂ መዝናኛ መድረክ አይደለም። የሰዎችን ስሜትና ፍላጎት እየተከተለ የሚፈስ አስተማሪ ፈሪና አስመሳይ እንጂ እውነተኛ ተቆርቋሪ አይደለም።
4. እንደ ዘመን በህዝብ ላይ የተጋረጡ አደጋዎች እና ወቅታዊ ክስተቶች ሲኖሩ አቅጣጫ መስጠት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ በቂ ንቃትና ዝግጅት ይፈልጋል። ንቃትና ዝግጅት ማለት እንግሊዝኛ መቀላቀል አይደለም። በሚዲያ የሰማነውን ዜና ማስተጋባትም አይደለም። የዳዒ ኃላፊነት እንደ ጋዜጠኛ ክስተቶችን ማንልበልና መተንተን አይደለም። መድረኮችን የፖለቲካ መደስኮሪያ እያደረጉ ማርከስ ንቃት አይደለም። ከዳዒ የሚጠበቀው ነገሮችን በኢስላም መነፅር በመመልከት ህዝብን ማረጋጋት፣ ሰዎችን ወደ አላህ መመለስ፣ በወቅታዊ ክስተቶች ከአቅማቸው በላይ በመግባት እንዳይዋጡ ማሳሰብ ነው።
እንዳጠቃላይ ለመድረኩ የሚመጥን ትኩረት እንስጥ፤ አቅም እናዳብር፤ ዝግጅት እናድርግ፤ ጀግንነትን እንላበስ፤ ሐቀኛ ተቆርቋሪነትን ሁሌም እናስብ። ሰላም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 30/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ነገ ሀሙስ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያስታውስ!!!!
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው፣ ያንን መልካም ስራ እንደሰራው ሰው አይነት ምንዳ (አጅር) አለው።"
