Abu Hayder Aliy
Ir al canal en Telegram
نشرالكتاب والسنة وقول العلمآء بائذن الله الباري بأبي حيدر علي إبن سليمان إبن أحمد الولغاوي
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
569
Suscriptores
+1224 horas
+187 días
+4930 días
Archivo de publicaciones
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
“ከነብዩ ﷺ ቤተሰቦች እና ከተከታዮቻቸው ውስጥ ‘መውሊድ ይፈቀዳል’ ያለ አንድ እንኳን እንደሌለ ከተገለፀልህ ከነሱ ውጭ ያሉትን አቋም ልታውቅ ከፈለግክ ከሁሉም ሙስሊሞች ዘንድ ቢድዐ በመሆኑ ላይ ኢጅማዕ እንዳለ አረጋግጠንልሃል እንላለን፡፡” [ገፅ፡ 1091]
8. መውሊድ ውስጥ ሺርክ ወይም ሌላ ጥፋቶች ከሌሉበትስ ይፈቀዳል?
ሸውካኒይ፡- “ ‘መውሊዱ ላይ ለምግብ መሰባሰብና ዚክር ብቻ ከሆነ ይፈቀዳል፣ አብረውት የሚያጅቡት ነገሮች ክልክል መሆናቸው ክልክልነቱን አያስይዝም’ የሚሉ ሰዎች ማመሀኛ ፉርሽነቱ ከዚህ ላይ ግልፅ ይሆንልሀል፡፡ ምክንያቱም እኛ እራስህ እንዳመንከው መውሊድ ቢድዐ ከመሆኑ ጋር በልምድ ከብዙ መጥፎ ነገሮች ጋር የተቆራኘና ለብዙ ጥፋቶች መዳረሻ ሆኗል እንላለንና፡፡ ደግሞም ከምግብና ከዚክር ውጭ ያሉ ነገሮችን የማያካትቱ መውሊዶችን ማግኘት ከቀይ ድኝ የበለጠ ፈታኝ ነው፡፡” [ገፅ፡ 2/1090 - 1091]
“የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ ጋር ሲነፃፀሩ ጥቂቶች ከመሆናቸው ጋር ለምግብና ለዚክር ብቻ በሚል መስፈርት ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡ ለብዙ ጥፋቶች መዳረሻ እንደሆነ ደግሞ ይሄው አሳውቀንሃል፡፡ ይህን ከግምት በማስገባት ላይ አንድም አይፃረርም፡፡ ዛሬ የሚከሰተው የዚህ አይነቱ (ጥፋቱ የበዛበት) መውሊድ ግን በወጥ ስምምነት የተከለከለ ነው፡፡” [ገፅ፡ 2/1098 - 1099]
“ወደ ጥፋት የሚያደርሱ መንገዶችን መዝጋትና ወደማይፈቀድ ነገር መንጠላጠያ ገመዶችን መቁረጥ ብዙሃን ምሁራን እርግጠኛ ከሆኑባቸው ወሳኝ ሸሪዐዊ መርሆዎች ውስጥ ነው፡፡ አንተ እራስህ እንጥፍጣፊ ሚዛናዊነት ቀርቶህ ከሆነ ይህንን ሐቅ አትክድም፡፡” [ገፅ፡ 2/1091]
9. መውሊድ የልዩነት መንስኤ ነውን?
ሸውካኒይ፡- “ደግሞም ይሄ መውሊድ ከተከሰተ በኋላ ውዝግቡ ተጧጡፏል፡፡ በዚህም ላይ የሚፃፉት ኪታቦች ከከልካዩም ከፈቃጁም በዝተዋል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091]
10. መውሊድ ውስጥ አስቀያሚ ጥፋቶች ከኖሩበትስ?
ሸውካኒይ፡- “ሀሳቡ ሲጨመቅ የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ አንፃር ሲታዩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለዚያውም እነሱም ቢሆኑ ምግብ ለማብላትና ለዚክር ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡ ለጥፋቶች መዳረሻ እንደሆነ ደግሞ በርግጥም አሳውቀንሃል፡፡ ከዚህ አንፃር ሲታይ አንድም የሚወዛገብ የለም፡፡ የዚህ አይነቱ ዛሬ እየተከሰተ ያለው መውሊድ በዑለማእ ስምምነት ክልክል ነው፡፡ ርእሱ የፈቃጆቹን ንግግሮች እያቀረቡ ዘለግ ባለ መልኩ መመለስ የሚጠይቅ ቢሆንም ለጊዜው እዚህ ላይ ይበቃናል፡፡” ከዚያም በሙታን ላይ የሚፈፀመውን ሺርክና የጣኦት አምልኮ ጠቅሰው በጥብቅ ከኮነኑ በኋላ “እኛ ማስጠንቀቅና ማድረስ እንጂ ሌላ አቅም የለንም፡፡ ይህንን ይሄው አድርገናል፡፡ አላህ ሆይ! ለዲንህ ተቆጣ! ከነዚህ ቀብር አምላኪ ሸይጧኖች ቆሻሻም አፅዳው፡፡ ከነዚህ የጠንካራውን እምነት ንፅህና ካጠለሹ ቆሻሻዎችም አሳርፈን፡፡” [ገፅ፡ 1095 - 1101]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 25/2012)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሸውካኒይ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት)
~
ሙሐመድ ብኑ ዐሊ አሽ-ሸውካኒይ በ1250 ሂ. የሞቱ ታላቅ የመናዊ ዓሊም ናቸው፡፡ በሰፊው የሚታወቁ ስለሆኑ እሳቸውን በማስተዋወቅ ረጅሙን ፅሑፌን ይበልጥ ማስረዘም አልሻም፡፡ ሸውካኒይ መውሊድ ላይ እጅግ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡ ዛሬ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው መውሊድ ተኮር ጥያቄዎች ውስጥ የተወሰኑትን በመምዘዝ በሸውካኒይ ንግግር ምላሽ እሰጣለሁ፡፡ ሙሉ ንግግራቸውን መመልከት የፈለገ ሰው “አልፈትሑ ረባኒይ ሚን ፈታዋ አልኢማሚ ሸውካኒይ” በተሰኘው የፈትዋ መድብላቸው ውስጥ ሁለተኛውን ጥራዝ ከገፅ 1087 - 1101 ድረስ መመልከት ይችላል፡፡ (ፅሑፉ ስለ ረዘመ ዐረብኛውን ማካተት አልቻልኩም፡፡)
1. መውሊድ የሸሪዐ መነሻ አለውን?
ሸውካኒይ፡- “እስካሁን ድረስ ከቁርኣንም፣ ከሱናም፣ ከኢጅማዕም፣ ከቂያስም (ንፅፅራዊ ምልከታም) መሰረት እንዳለው የሚያመላክት መረጃ አላገኘሁለትም፡፡” [ገፅ፡ 2/1087]
2. መውሊድን ሰለፎች ያውቁታል?
ሸውካኒይ፡- “እንዲያውም ከዘመናት ሁሉ ምርጡ በሆነው (የሶሐቦች) ዘመንም፣ ከነሱ ቀጥሎ በነበሩትም፣ ቀጥሎ በነበሩትም (ዘመን) እንዳልነበር ሙስሊሞች ወጥ አቋም ይዘዋል (ኢጅማዕ አድርገዋል፡፡)” [ገፅ፡ 2/1087]
3. ቢድዐ በመሆኑ ላይ ልዩነት አለ?
ሸውካኒይ፡- “ቢድዐ በመሆኑ ላይ ከሙስሊሞች አንድ እንኳን የተቃወመ የለም፡፡” [ገፅ፡ 2/1088] “ይሄ ነገር ቢድዐ በመሆኑ ላይ ከሁሉም ሙስሊሞች ኢጅማዕ እንዳለበት አረጋግጠንልሃል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091]
4. መውሊድን በሚደግፉ መሻይኾች ማስፈራራት ያዋጣል?
ሸውካኒይ፡- “በምርጡ ነብይ ﷺ የማያሻማ ምስክርነት ቢድዐ ሁሉ ጥመት እንደሆነ ተነግሮ ሳለ የመውሊድን ቢድዐ መሆን ካመነ በኋላ ይፈቀዳል የሚል ሰው የተናገረው ከንፁሁ ሸሪዐ ጋር የሚፃረር ንግግር ነው፡፡ ያለ አንድ ተጨባጭ እውቀታዊ መነሻ ቢድዐን ወደተለያዩ ክፍሎች ለከፈለ ሰው በጭፍን ከመከተል ያለፈ ነገርም የለውም፡፡ የትኛውንም አቋም ይቻላል የሚልን ሰው ይህንን ቢድዐ በተለየ የሚመለከት ማስረጃ ካቀረበ በኋላ እንጂ አንቀበለውም፡፡ … እንጂ ‘እከሌ እንዲህ አለ’፣ ‘እከሌ እንዲህ አይነት ኪታብ አዘጋጅቷል’ የሚል ባዶ ንግግር ፋይዳ የለውም፡፡ ሐቅ ከየትኛውም አካል ይበልጣልና፡፡” [ገፅ፡ 2/1088 - 1089]
“ከነሱ (ከፈቃጆቹ) ውስጥ ቢድዐነቱን አምኖ መጥፎ ነገር ካልተቆራኘው በሚል መስፈርት የፈቀደው አለ፡፡ ምንም ማስረጃ ግን አላመጣም፡፡” [ገፅ፡ 2/1094]
ኢብኑ ሐጀር እንዳደረገው የዓሹራን ፆም ማስረጃ ማድረግ፣ ወይም ሲዩጢ እንዳደረገው ከነብይነት በኋላ ለራሳቸው ዐቂቃ ማውጣታቸውን መመርኮዝ ቢድዐን የማፅናት ፍቅር እንዲህ አይነት ነገር ላይ እንደሚጥል ከሚያሳዩ አስገራሚ ነገሮች ውስጥ ነው፡፡ [ገፅ፡ 1095]
5. መውሊድ የብዙሃን ሙስሊሞች ድጋፍ ነበረውን?
ሸውካኒይ፡- “በሰዎች ንግግሮች ላይ የምንመረኮዝ ከሆንና የእንቶ ፈንቶ ጅራቶችን የምንጨብጥ ከሆንን መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ‘ይፈቀዳል’ ባዮቹ ከሙስሊሞች በአቋም ያፈነገጡ ናቸው፡፡ …” [ገፅ፡ 2/1087-1089]
“ሲጨመቅ የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ አንፃር ሲታዩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለዚያውም እነሱም ቢሆኑ ምግብ ለማብላትና ለዚክር ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡” [ገፅ፡ 1095 – 1099]
(አስተውሉ! ይህ እንግዲህ በሸውካኒ ዘመን ነው፡፡ የሞቱት በ1250 ሂ. ሲሆን ሁለት መቶ አመት ሊሞላቸው ጥቂት ነው የቀራቸው፡፡ ሱፊያ ደፋር ነውና የዛሬን የመውሊድ ጨፋሪዎች በመመልከት ሸውካኒን “ውሸታም ነው” እንዳይሉ እሰጋለሁ፡፡)
6. መውሊድ እንዴት ተስፋፋ?
ሸውካኒይ፡- “ግና ቢድዐን በማፅናትም ሆነ በማጥፋት ላይ ንጉሳን ተፅእኖ አላቸው፡፡ ይህንን ቢድዐ (በሱኒው ዓለም ውስጥ) የፈጠረው ያ ንጉስ (ሙዞፈር) ሲሆን ኢብኑ ዲሕያ ደግሞ ‘አተንዊር ፊ መውሊዲል በሺር ነዚር’ የተሰኘ ኪታብ በማዘጋጀት አግዞታል፡፡ ሰውየው በዘገባ እውቀት ላይ የጠለቀ ከመሆኑም ጋር በዚህ ኪታቡ ግን ግልፅ ማስረጃ አላቀረበም፡፡ ለዚህ ስራው - ኢብኑ ኸሊካን እንደጠቀሱት - አንድ ሺህ ዲናር በንጉሱ መሸለሙ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ የዱንያ ፍቅር ከዚህም በላይ ያደርሳል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091]
“የቢድዐ ስርጭት ከእሳት ስርጭት የፈጠነ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ መውሊድ፡፡ ምክንያቱም የመሃይማን ነፍሶች ጥግ የደረሰ መናፈቅን ይናፍቁታልና፡፡ በተለይ ደግሞ ከምሁራን፣ ከክቡራንና መሪዎች በርከት ያለ ሰው ከተካፈለበት በኋላ ይሄ ቢድዐ ወሳኝ ከሆኑ ሱናዎች ይመስላቸዋል፡፡ … እንደ መውሊድና አምሳያዎቹ ያሉ ለሐራም ነገሮች የሚያመቻቹ የጥፋት መዳረሻዎች መሃይሞች ፈጥነው እንደሚገቡባቸው አያጠራጥርም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ በዒልም፣ በክብርና በስልጣን ዝና ያለው ሰው መካፈል ሲታከልበት ሐራም ነገሮችን እንደ ፈጣሪ ትእዛዛት ሲፈፅሙ፣ በድንቁርናና በጥመት ሸለቆች ውስጥ ገብተው ሲዘባርቁ፣ “የተከበሩ እከሌ፣ እከሌ፣ እከሌ፣… ተገኝተዋል” እያሉ ከተቃውሞ ሲያመልጡ የባሰ ይሆናል፡፡
መሃይሙ ህዝብ ይቅርና አንዱ በዒልም ፍለጋ ላይ ገኖ የወጣ ሰው አንዳንድ የኢጅቲሃድ እውቀቶችን ለመማር ከፊቴ ተቀምጦ ነበር፡፡ በዚህ ወር ከተከናወኑ መውሊዶች ውስጥ በአንዱ አዳር ላይ እንደተካፈለ ሲነግረኝ ተቃወምኩት፡፡ አንገሸገሸኝ፡፡ በዚህን ጊዜ ‘ሰዪዲ እከሌ፣ እከሌ፣ እከሌ፣… ተካፍለዋልኮ’ አለኝ፡፡ በነዚህ ታዋቂ ሰዎች ፊት የነበረውን አፈፃፀም ስጠይቀው እንዲህ አለኝ፡-
‘እነዚያ ታዋቂ ሰዎች እየዘፈኑና እያዳመጡ መንዙማውን አንድ ዱርየ አነበበ፡፡ ከዚያም አንዱ ልክ ከእስር የተነሳ ይመስል አፈፍ ብሎ ተነስቶ “መርሐባ ያ ኑረ ዐይኒ፣ መርሐባ” (እንኳን መጣህ ያይኔ ብርሃን እንኳን መጣህ!) ሲል ታዳሚው በመላ ታዋቂዎቹን ጨምሮ ተከትለውት ቆሙ፡፡ እነሱ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ቆሞ ማጓራት ያዘ፡፡ አንዱ ታዳሚ ደክሞት ቢቀመጥ ከታዋቂዎቹ ውስጥ አንዱ ንዴቱ ከፊቱ ላይ እየታየ ‘ተነስ! ጨዋታኮ አይደለም!’ ብሎ ጮኸበት፡፡ ቃል በቃል! የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚያች ሰዓት ከነሱ ዘንድ እንደደረሱ ጭራሽ አይጠራጠሩም፡፡ ከዚያም ተጨባበጡ፡፡ ከመሀይማን ከፊሎቹ በእጆቻቸው ሽቶ በመያዝ በፍጥነት ቀቡ፣ ተቀቡ፡፡ ልክ የሳቸውን ﷺ መገኘት ለመጠቀም፡፡’
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! የዲን ክብር የት ገባ?! ይህም ከጠፋ አይናፋርነት፣ ግብረ ገብነት፣ ህሊና የት ገባ?” [ገፅ፡ 2/1089 - 91]
7. መውሊድን የነብዩ ﷺ ቤተሰቦች ይደግፉታል?
መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎች “ከኛ በላይ ነብዩን ﷺ የሚወድ ላሳር!” የሚሉ ናቸው፡፡ እውነት ለመናገር የነብዩ ﷺ ዘሮች ሙእሚኖች ከሆኑ ለነብዩ ﷺ ያላቸው ፍቅር ልዩ ነው፡፡ መውሊዱ የፍቅር መገለጫ ቢሆን ኖሮ ከማንም ቀድመው ባከበሩት ነበር፡፡ ግን ከነሱ የተገኘው መውሊድን ማክበር፣ ማስከበር፣ ለሱ ሽንጥን ገትሮ መሟገት ነውን?
ሸውካኒይ፡- “ከነብዩ ﷺ ንፁሕ ቤተሰብም ይሁን ከተከታዮቻቸው ይህ ነገር እንደሚፈቀድ የተናገረ አንድም ፊደል አላገኘንም፡፡ እንዲያውም ይህቺ ቢድዐ ከተከሰተች ጀምሮ ወደ ጥፋቶች ከሚያሻግሩ አስቀያሚ መዳረሻዎች አንዷ እንደሆነች ንግግሮቻቸው ከሞላ ጎደል ተስማምተዋል፡፡” [ገፅ፡ 1089]
Repost from N/a
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው ብዙ
የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን
ያገኛል ።
ጥያቄ 1
💎ተዉሂድ በስንት ይከፈላል?
ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም
❝አቡሁረይራ - ረዲዬሏሁ ዓንሁ
ከአላህ መልክተኛ ﷺ ሰምተው ያስተላለፉት ሐዲስ ፣-ሰኞ እና ሐሙስ ስራዎች ይቀረባሉ፤ ጾመኛ ሆኘ ስራየ (ከአላህ ዘንድ) እንዲቀረብልኝ እወዳለሁ፡፡❞
•
ኢብራሒም_ኢብኑ_አድሀም ረሒመሁሏህ እንዲህ ብለዋል : -
«እረፍትን የፈለገ ፍጡራንን ከቀልቡ ያውጣ የዛኔ ያርፋል።»
📚 ۞【سيــر السلـف الصالــح【477】۞
Repost from ስለ ቀልባችን
👁🗨የኪታብ PDF
اِنْتَبِهْ أَنْتَ مُرَاقَبْ!!
🪶ኢንተቢህ_አንተ_ሙራቀብ
https://t.me/Sle_qelbachn1/1964
Repost from ስለ ቀልባችን
🎙ቀጥታ ስርጭት ተጀመረ!
● ወንጀል ላደከማት ነፍስ!
https://t.me/Sle_qelbachn1?livestream=1ae6e66a0eee342f69
Repost from ስለ ቀልባችን
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
መውሊድ - በፉክክር የተጀመረ በዓል ነው!
~
መውሊድ ቀደምት የኢስላም ትውልዶች ዘንድ የማይታወቅ መጤ ፈጠራ መሆኑን ራሳቸው የመውሊድ አክባሪ የሆኑ አካላት የመሰከሩትን አሳልፌያለሁ። እነዚሁ አካላት መውሊድ ከክርስቲያኖቹ ገና ተኮርጆ በፉክክር እንደሚከበር የተናገሩቱን ደግሞ እናያለን። ዘግይተው የመጡ አንዳንድ ሱፍዮች ግን “መውሊድ በሀይማኖታችን መረጃዎች መሰረት የተፈቀደ በመሆኑ ላይ ከተግባባን ከክርስቲያን ወይም ከሂንዱ እምነት ጋር ባጋጣሚ ተመሳስሎ ቢገኝ ችግር የለውም” ይላሉ። በሀይማኖታችን መሰረት ቢኖረውማ እነ ኢብኑ ሐጀር “የመውሊድ ተግባር መሰረቱ ቢድዐ ነው። በሶስቱ ክፍለ ዘመናት ከነበሩት መልካም ቀደምቶች ከአንድም አልተላለፈም” አይሉም ነበር።
እያከበሩ ያሉት ሌላ መልክ ያለው ገና ነው። ገና (chrismas) ማለት ልደት ማለት ነው። ልደት ማለት ደግሞ በዐረብኛው መውሊድ ማለት ነው። ስለዚህ የሚከበረው ማንነት እንጂ የተለየው የሚያከብሩት ገናን ነው።
የክርስቲያኖች ገና = የሱፍዮች መውሊድ!
የክርስቲያኖች መውሊድ = የሱፍዮች ገና!
እንዲያውም መውሊድን የሚያከብሩት ከክርስቲያኖች ጋር ለመፎካከር ብለው ነው። የፉክክር ዒባዳ ማለት ነው! ይህንን ሐቅ በኪታብ ሳይቀር ያሰፈሩት አሉ። መረጃ እጠቅሳለሁ፡-
1. አስ-ሰኻዊይ ምን እንደሚል ተመልከቱ፡- “ባለ መስቀሎቹ (ክርስቲያኖች) የነብያቸውን ልደት ትልቁ ዒዳቸው አድርገው የሚይዙ ከሆነ ሙስሊሞችም (ነብያቸውን) በማክበርና በማላቅ ይበልጥ የተገቡ ናቸው።” [አት-ቲብሩል መስቡክ፡ 14]
2. ከጀዘሪም ቃል በቃል ተላልፏል።
3. አቡል ዐባስ አል-አዘፊይ (መውሊድን ለምዕራቡ ዐረቢያ ያስተዋወቀ ነው)፡- በክርስቲያን በዓላት ላይ የሚሳተፉ ወጣቶችን ለመመለስ ሲል እንደጀመረው በግልፅ ተናግሯል።
4. ዐብዱላህ አልሀረሪይ (የአሕባሾቹ መሪ):- ንጉስ ሙዞፈር መውሊድን የጀመረው ክርስቲያኖች የመሲሕ ልደትን በዓል ሲያከብሩ ተመልክቶ ነው። በዚህም ሳቢያ ሰይዳችንን ሙሐመድን ﷺ ስላወጣልን አላህን ለማመስገን ሲል መውሊድን ጀመረ ይላል። [ኢዝሃሩል ዐቂደቲ ሱንኒያህ፡ 240]
ስለዚህ የመውሊድ ቢድዐን በፉክክር የተለከፉ ሰዎች የፈጠሩት መጤ ፈሊጥ ነው ማለት ነው። በዚህ መልኩ በሌሎች መመሳሰል ደግሞ የተወገዘ እንደሆነ ነብያችን ﷺ አጥብቀው አሳስበዋል።
* ማስረጃ አንድ፦
مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ
"አንድን ሕዝብ የተመሳሰለ (የተከተለ) ከእነርሱ ነው (እንደነርሱ ይቆጠራል)።" [አቡ ዳውድ ፡ 4031]
* ማስረጃ ሁለት፦
በሌላም ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لتتَّبعنَّ سَننَ من كانَ قبلَكم حذو القُذَّةِ بالقُذَّةِ حتَّى لو دخلوا جحرَ ضبٍّ لدخلتُموه. قالوا: اليَهودُ والنَّصارى؟ قالَ: فمَن
“በርግጥ ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለጎች ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የወከሎ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን በርግጥም ትገቡታላችሁ!” ሲሉ “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው (ትከተላላችሁ) የምትለን?” ብለው ቢጠይቁ “ታዲያ ማንን ነው?!” አሉ። [ቡኻሪይ፡ 7320]
የተናገሩት በትክክል ተፈፀመ። ለብዙ ጥፋቶች የሚያጋልጠው በዓል ከክርስቲያኖች ተኮርጆ በ"ፋጢሚያ" ሺዐዎች ተጠንስሶ፣ በሱፍዮች ተዛምቶ ብዙ ሙስሊም ሊዘፈቅበት በቅቷል።
የሚያሳፍረው “ክርስቲያኖቹ የነብያቸውን ልደት እያከበሩ የኛ ነብይ ከማን ያንሳሉ?” የሚሉት ነገር ነው። ሱብሓነላህ! ለመሆኑ ዒሳ የኢስላም ነብይ አይደሉም እንዴ?! ታዲያ ይሄ ምን የሚሉት አፀያፊ ሎጂክ ነው? ደግሞ ምንም ሳያፍሩ መውሊድን የሚቃወሙ ሙስሊሞችን “የነቢ ጠላቶች ናቸው!” እያሉ ከባድ ክስ ይከሳሉ። የነብዩን ﷺ መውሊድ አለማክበር እሳቸውን መጥላት ከሆነ እናንተም የክርስቲያኖቹን ገና (chrismasን) ባለማክበራችሁ የዒሳ ጠላቶች ናችሁ ማለት ነው። መውሊድን ማክበር ነብዩን ﷺ ማክበር ከሆነ የሌሎቹን ነብያት ልደቶች ስለማታከብሩ ለሌሎች ነብያት በሙሉ ክብር የሌላችሁ የነብያት ጠላቶች ናችሁ ማለት ነው። ከአንደበታችሁ በቀጥታ ባይወጣም አመክኗችሁ የሚሰጠው ይህንን ነው።
አንዳንዶች "ገናን የማናከብረው የዒሳን ልደት ስለማናውቅ ነው" ይላሉ። የነብያችንም ﷺ የውልደት በየትኛው የረቢዕ ቀን ላይ እንደሆነ የሚያሳይ ሶሒሕ ማስረጃ የለም። በ12ኛው ቀን ነው የሚለው የሰነድ መቆረጥ እንዳለበት ኢብኑ ከሢር ገልፀዋል። [አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 3/109]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ኢብኑ_ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
«ንግግርህ ኸይር ነገር ከሆነ እንጅ ላላመናገር ሞክር። ይህን ማድረግህ ኢማንህን ያጠነክርልሀል፣ ምላስህን ይጠብቅልሀል፣ ወንድሞችህ ዘንድም ክብር ነው።»
📚 ۞ شرح أربعين النووي【1/215】۞
https://t.me/abu_hayder_aliy
https://t.me/abu_hayder_aliy
Repost from N/a
⭕️ይህ መልዕክት ለሱና ቻናል ባለቤቶች ⭕️
➲ ቻናላችሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ በአዲስ መልክ ጀምረናል
🛑በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 📥
➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች
ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች
ላላቸው
⚡️ የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ
👉 @Quran_mylife1
