HOP Ministry
Ir al canal en Telegram
HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
446
Suscriptores
+124 horas
+197 días
+6730 días
Archivo de publicaciones
446
#A_Glimpse_into_the_Life_of_Praying_Hyde
እስቲ ልጠይቃችሁ ቅጽል ስም ይኖረን ይሆን? ካለን፤ ምናልባት ስለ እኛ የሆነ ነገር ይናገር ይሆናል፡፡ ቅጽል ስሙ እውነተኛ ህይወቱን ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው “ጸሎተኛው ሃይድ” (Praying Hyde) የሰው ልጅ ካለበት ዘርፈ ብዙ ምድራዊ ጥያቄ የተነሳ ወይ ስጠኝ አልያም ግደለኝ በማለት ከአምላኩ ጋር በሚሟገትበት በዚህ ዓለም ላይ ቢኖርም የእርሱ የሙግት ርዕስ ግን ከጀማው ርዕስ ጋር ለየቅል ነበር፡፡
ሰፊውን የህይወት ዘመኑን በጨለማ ስላሉት በመማለድ ያሳለፈው የጸሎት ሐዋርያው “John Hyde” የዘወትር ጩኸት “ #እግዚአብሔር_ሆይ_ነፍሳትን_ስጠኝ_አለበለዚያ_ግደለኝ!!” የሚል ነበር፡፡ በህንድ በነበረው አገልግሎት ወቅት አያሌ ሌሊቶችን በእግዚአብሔር ፊት ማሳለፍ ልማዱ ከመሆኑ የተነሳ የሀገሬው ሰዎች “የማይተኛው ሰው” የሚል ስያሜ የሰጡት የኢሊኖይ ፕሪስባይቴሪያን አገልጋይ ልጅ ጆን ኔልሰን ሃይድ ይሄ ሸክም በልቡ ሊሞላ የቻለው ከአገልጋይ አባቱ እያየ ካደገው ወንጌልን በታማኝነት የመስበክ ትጋት፣ እንዲሁም በምስባክ ላይ ብቻ ሳይሆን በቤተሰቡ መሰዊያ ላይ እግዚአብሔር ወደ መከሩ ሰራተኞችን አብዝቶ እንዲልክ ከሚደረገው ምልጃ የተነሳ ነው፡፡
እውቁ የዌልስ አገልጋይ Seth Joshua በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ጽፎ ነበር፡- “ጸሎት ከተዘጋው እልፍኝ በስተጀርባ የሚደረግ ስውር ተግባር ነው፡፡ እጅግ የተካኑት ጉድጓድ ቆፋሪዎች ከእይታ ተሰውረው ወደ ጥልቁ ይወርዳሉ፡፡ በዚህ መስክ ላይ የተሰማሩ አያሌ ሰዎች ናቸው፤ ነገር ግን ራሳቸውን ሰውረውና አጥፍተው ከእግዚአብሔር ጋር የሚታገሉት ጥቂቶች ናቸው፡፡"
” ኢየሱስና እርሱ ብቻ!!" ማላጁ ሃይድ እጅግ ሀሴት የሚያደርግበት ነገር ቢኖር #ከኢየሱስ_ጋር_ለብቻው መሆን ነው፡፡ በዚህ ሰው ህይወት ውስጥ ካሉት በጣም አስደናቂ ባህሪያት አንዱ በዚህ ሁኔታ ተደብቆ ለረጅም ጊዜ መቆየት መቻሉ ነው፤ በተለምዶው እንጨት፣ ሳርና ገለባ ለሰው እይታ ቅርብ ሆነው በቀላሉ ሲገኙ፤ ዋጋቸው የከበረው ወርቅ፣ ብርና የከበሩ ድንጋዮች ግን በጥልቅ ውስጥ ስውር ከመሆናቸው የተነሳ በቀላሉ አይገኙም፡፡ እንደዚሁ ጆን ሃይድም ከእግዜር ስውር ሀብቶች መካከል አንዱ ነበር፡፡ የጸሎት ሐዋርያው ገና በለጋ ዕድሜው ነው ሚሲዮናዊ ሆኖ ወደ ህንድ ያቀናው፡፡
ይቀጥላል...
